በግራ ቀኝ መካከል ላለ ክርክር አልባት ለመስጠት የእርቅ ስምምነት ተፈጽሞ በፍርድ ቤት በማጽደቅ በተሰጠ ዉሳኔ ሶስተኛ ወገንን በተመለከተ የተደረገ ክርክር ካለመኖሩም በተጨማሪ የተሰጠ ዉሳኔ በላለበት ፍርድ የመፈጸም ግዳታ የሚኖርበት የፍርድ ባለእዲዉ እንጂ ከጉዲዩ ጋር ግንኙነት የላለዉ ሦስተኛ ወገን ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 378 እና 392/1
No summary available.
ቀን፡- 03/02/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሮ አገሪቱ አስናቀ - ወኪል ፍዚያ አህመድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ሼህ ኡመር መሀመድ - አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በፍርድ ቤት የፀደቀ የዔርቅ ስምምነት አፈጻጸም የሚመለከት ነዉ።አመልካች ለደሴ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የፍርድ አፈጻጸም ማመልከቻ ግራ ቀኝ በመካከላቸዉ ለነበረዉ የከተማ ቦታ ወሰን ክርክር እልባት ለመስጠት በቀን 23/05/2011ዓ/ም የእርቅ ስምምነት ፈጽመዉ የዔርቅ ስምምነታቸዉም በስር ፍርድ ቤት በቀን 01/06/2011ዓ/ም ፀድቋል። በዚህ የእርቅ ስምምነት መሰረት አመልካች 5 ሜትር ወርድና 0.80 ሜትር ቁመት (4 ካሬ ሜትር) ስፊት ያለዉን ቦታ በመልቀቅ ተጠሪ በዚህ ቦታ ላይ በሰሩት የሰርቪስ ቤት ግድግዲ ላይ የጣራ ተዛነፍ ጋር በማያያዝ በራሳቸዉ ወጪ ግድግዲዉን በብልኬት በማድረግ የግንባታ ፈቃድ አዉጥታ መስራት እንድትችል ስምምነት ፈጽመዋል። በዚህ በፀደቀዉ የዔርቅ ስምምነት መሰረት የአመልካች ይዞታ 196 ካሬ ሜትር እንዱሆን የተጠሪ ደግሞ 139 ካሬ ሜትር ሆኖ ካርታ እንዱሰራልን በዉሳኔ በጸደቀዉ መሰረት የደሴ ከተማ አስተዲደር የመናፈሻ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፈቃድ ስለከለከለኝ የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጠኝ ይታዘዝልኝ በማለት ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም የደሴ ከተማ መናፈሻ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ማኔጅመንት የግንባታ ፈቃድ ጽ/ቤትን ጠይቆ የመሬታቸዉ ስፊት 196 ስለሆነና ስታንዲርደ የሚጠይቀዉን 200 ካሬ ሜትር የሚለዉን ስለማያሟላ የግንባታ ፈቃድ አልተሰጣቸዉም በማለት አስተያየት ሰጥቷል።ይህንን ተከትል ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 18/02/2012 ዓ/ም የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሥልጣን በተሰጠዉ አስተዲደር አካል የሚታይ እንጂ ፍርድ ቤት የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጥ ሉያዝ የሚችልበት የሕግ አግባብ ባለመኖሩ በፍርድ ቤት ታይቶ ሉወሰን የሚችል የክስ ምክንያት የለዉም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ አድርጓል። አመልካች ይግባኝ ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን በመ/ ላይ በቀን 25/02/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 ሰርዞባቸዋል። እንዱሁም አመልካች ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበዉ ችልቱ በመ/6 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 13/04/2013ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች እንዱፈጸምላቸዉ የጠየቁትን የእርቅ ስምምነት ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ ስለሆነ የእርቅ ስምምነቱን በማጽደቅ የተሰጠዉ ዉሳኔ ይሻርልኝ የሚል ክርክር አቅርበዉ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ተከራክረዉ ተቀባይነት አላገኙም። በፀደቀዉ የእርቅ ስምምነት ላይ አመልካች የግንባታ ፈቃድ እንዱያገኙ በዉሳኔዉ ላይ ሰፍሯል ወይስ አልሰፈረም የሚለዉ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚመለከተዉ የመንግስት አስተዲደር አካል ከ200 ካሬ ሜትር በታች በሆነ ቅይጥ ይዞታ ላይ የግንባታ ፈቃድ ለመስጠት እንደማይቻል ስለገለጸ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ተገቢ ነዉ በማለት አፅንቷል።
አመልካች በቀን 21/02/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡አመልካችና ተጠሪ የፈጸምነዉ የዔርቅ ስምምነት የሥር የወረዲ ፍርድ ቤት ከመፅደቁም በተጨማሪ በየትኛዉም የበላይ ፍርድ ቤት አልተሻረም። በፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ እስካልተሻረ ድረስ ሉፈጸም እንደሚገባ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቷል። ማዘጋጃ ቤቱ ዉሳኔዉ ሉፈጸም የሚችል አይደለም ስላለ ብቻ የክልለ ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የአፈጻጸም ማመልከቻ ዉድቅ ማድረጋቸዉ ስህተት ነዉ። በጸደቀዉ የእርቅ ስምምነት መሰረት አመልካች ከተጠሪ ግንባታ ጋር በማጋጠም እንድሰራ ስምምነት የተደረገ በመሆኑ የግንባታ ፈቃድ እንዲገኝ ተደርጎ መፈጸም ይገባል። እንዱሁም የእርቅ ስምምነቱ ለሕግ ተቃራኒ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ተቀብል ማጽደቅ አልነበረበትም ከተባለም ፀድቆ የነበረዉን የግራ ቀኙ የዔርቅ ስምምነቱ ሉፈጸም የማይችል በመሆኑ በዉሳኔ እንዲልጸደቀ ተቆጥሮ ተሰርዞ ወደነበርንበት እንድንመለስ ክርክሩ እንዱቀጥል በማድረግ ለክርክሩ እልባት መስጠት ሲገባቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ እልባት በማያገኝበት መንገድ መዝጋቱ ሉታረም የሚገባዉ ስህተት ነዉ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ በስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍርድ ቤት የፀደቀዉንና የግራ ቀኙ ስምምነት ወይም ፍርድ የሚጣጣም መሆን አለመሆኑን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 378 እና ተከታዮቹ አንጻር ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 20/05/2013 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል።
የዔርቅ ስምምነቱ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አይደለም ተብል በፍርድ ቤት ፀድቆ ክርክሩ ተቋርጧል።ፍርድ ቤቱ እንደዉሳኔዉ እንዱፈጸም ለደሴ ከተማ አገ/ግ/ጽ/ቤት እና ለደሴ ከተማ አስተዲደር ለመናፈሻ ክፍለ ከተማ ደርሶ ለአመልካች 196ካ/ሜትር ለተጠሪ ደግሞ 139ካ/ሜትር በሆነ ይዞታችን መጠን ካርታ ተዘጋጅቶ ተሰጥቶን ዉሳኔዉ ተፈጽሟል።በዚህ አግባብ ከተፈጸመ በኋላ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታም ሆነ የዔርቅ ስምምነቱ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ ነዉ የሚባል ከሆነ ሉፈርስ ይገባል በማለት ያቀረቡትን ክርክር የሥር ፍርድ ቤቶች ዉድቅ በማድረጋቸዉ የተፈፀመ ስህተት የለም።
የግንባታ ፈቃድ የመስጠት ሥልጣን የአስተዲደር አካል እንጂ የፍርድ ቤት ስላልሆነ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል።አመልካችም በቀን 27/07/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል የያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በክልለ ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ እንዱፈጸምላቸዉ የጠየቁት ከተጠሪ ጋር ለነበራቸዉ የከተማ ቦታ ወሰን ክርክር እልባት ለመስጠት ከተጠሪ ጋር ያደረጉት የዔርቅ ስምምነት በፍርድ ቤት ለሞራልና ለሕግ ተቃራኒ አይደለም በሚል በፀደቀዉ መሰረት የደሴ ከተማ አስተዲደር የመናፈሻ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፈቃድ ስለከለከለኝ የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጠኝ ይታዘዝልኝ በሚል ነዉ። ተጠሪ በመካከላቸዉ ለነበረዉ ክርክር እልባት ለመስጠት የዔርቅ ስምምነት አድርገዉ የእርቅ ስምምነታቸዉም በፍርድ ቤት መጽደቁን ሳይክደ አመልካች የጠየቁት ዲኝነት የክስ ምክንያት ያለዉ ዲኝነት ጥያቄ አይደለም በማለት ተቃዉመዋል። የወረዲዉ ፍርድ ቤት የተጠሪን ክርክር ተቀብል የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሥልጣን በተሰጠዉ አስተዲደር አካል የሚታይ እንጂ ፍርድ ቤት የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጥ ሉያዝ የሚችልበት የሕግ አግባብ ባለመኖሩ በፍርድ ቤት ታይቶ ሉወሰን የሚችል የክስ ምክንያት የለዉም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ አድርጓል። በየደረጃዉ በክልለ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ ታይቶ በመጨረሻ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠ ዉሳኔ የእርቅ ስምምነቱ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ ነዉ ተብል የፀደቀ ቢሆንም የአመልካች ይዞታ ከ200 ካሬ ሜትር በታች ስለሆነ የመንግስት አስተዲደር አካል ከ200 ካሬ ሜትር በታች በሆነ ቅይጥ ይዞታ ላይ የግንባታ ፈቃድ ለመስጠት እንደማይቻል ስለገለጸ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ተገቢ ነዉ በማለት አፅንቷል። አመልካች አጥብቀዉ የሚከራከሩት በጸደቀዉ የዔርቅ ስምምነት መሰረት የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጠኝ አለመታዘዙ፤
ይህ የማይሆን ከሆነም የዔርቅ ስምምነቱ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ ነዉ ተብል ፈርሶ ወደነበርንበት እንድንመለስ አለመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ በሚል ነዉ።
በአንድ የፍርድ ዉሳኔ ባለመብት ስለሆንኩ በዉሳኔዉ መሰረት ይፈጸምልኝ በሚል ተከራካሪ ወገን የፍርድ አፈጻጸም ማመልከቻ ሲያቀርብ ፍርደን የሚያስፈጽመዉ ፍርድ ቤት በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ስለ ፍርድ አፈጻጸም በተደነገገዉ ሰባተኛ መጽሐፍ ስር ባለ ድንጋጌዎች መሰረት እንዱፈጸም የተጠየቀዉን ፍርድ መሰረት በማድረግ እና በዚህ መጽሐፍ ስር ባለ ድንጋጌዎች የተዘረጋዉን ሥርዓት ተከትል ማስፈጸም ይኖርበታል። በዚህ መሰረት ፍርደን የሚያስፈጽመዉ ፍርድ ቤት ፍርደን ለማስፈጸም በሚል የሚሰጠዉ ትእዛዝ ፍርደን ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑንና የተወሰነላቸዉ ሰዎች የተወሰነላቸዉን ነገር እንዱያገኙ ለማድረግ የሚችል ተስማሚ ትእዛዝ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 378 እና 392/1 ስር የተደነገገዉ ያስገነዝባል። አንድን ፍርድ የመፈጸም ግዳታ የሚኖርበት የፍርድ ባለእዲዉ እንጂ ከጉዲዩ ጋር ግንኙነት የለላለዉ ሦስተኛ ወገን እንዲልሆነ ልብ ማለት ይገባል። በዚህ አግባብ በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋዉን ሥርዓት ተከትል ፍርደን ተግባራዊ ማድረግ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ዉሳኔ ማስፈጸም ስለመቻላቸዉ ዋነኛ ማረጋገጫ ከመሆኑም በተጨማሪ ነጻነቱ የተጠበቀ እና የሕዝብ አመኔታ ያለዉ ፍርድ ቤት ለመኖሩ ማሳያ ሆኖ የሚያገለግል የዲኝነት ሥራ ተግባር ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባ ነዉ።
በያዝነዉ ጉዲይ አመልካች በፍርድ አፈጻጸም ማመልከቻቸዉ ፍርድ ቤቱ እንዱያስፈጽምላቸዉ የጠየቁት ከተጠሪ ጋር የነበራቸዉን ክርክር ለመቋጨት ያደረጉትን የዔርቅ ስምምነትና የዔርቅ ስምምነቱን በማጽደቅ የተሰጠ ዉሳኔ ነዉ። የዔርቅ ስምምነቱም ሆነ የእርቅ ስምምነቱን በማጽደቅ የተሰጠዉ ዉሳኔ የሚመለከተዉ ግራ ቀኙን እንጂ አመልካች የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጠኝ ጠይቄ ስለከለከለኝ የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጠኝ ይታዘዝልኝ ያለትን የደሴ ከተማ አስተዲደር የመናፈሻ ክፍለ ከተማን የሚመለከት አይደለም። አመልካች ከደሴ ከተማ አስተዲደር መናፈሻ ክፍለ ከተማ ጋር ያደረጉት ክርክር ካለመኖሩም በተጨማሪ የደሴ ከተማ አስተዲደር የመናፈሻ ክፍለ ከተማ ለአመልካች የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጥ የተሰጠ ዉሳኔም የለም። የጸደቀዉ የዔርቅ ስምምነት ለአመልካች የግንባታ ፈቃድ ይሰጣቸዉ የሚል እንኳን ቢሆን የግንባታ ፈቃድ የመስጠት ሥልጣንና ተግባር የአስተዲደር አካልን የሚመለከት ሥራ እንጂ ተጠሪ የሚፈጽሙት አይደለም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ እንደ ፍርድ ባለእዲ ለአመልካች የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጡ ሉታዘዝ ስለማይችል ከዚህ አንጻር አመልካች እንዱፈጸምላቸዉ የጠየቁት የእርቅ ስምምነት በተጠሪ ሉፈጸም የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት የአመልካችን የፍርድ አፈጻጸም ማመልከቻ ዉድቅ ማድረግ ነበረባቸዉ።
ሲጠቃለል የወረዲዉ ፍርድ ቤት አመልካች ፍርድ ቤቱ እንዱያስፈጽምላቸዉ የጠየቁት ዲኝነት የፍርድ ባለእዲ በሆኑት ተጠሪ የሚፈጸም አይደለም በማለት ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ የፍርድ አፈጻጸም ክርክር እንደ መደበኛ ክስ በመቁጠር አመልካች የጠየቁት ዲኝነት በፍርድ ላታይ የሚችል (Justiciable matter) አይደለም የሚል ምክንያት ጠቅሶ የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉ ሉታረም የሚገባዉ ስህተት ነዉ።እንዱሁም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የአስተዲደር አካል ተከራካሪ ሆኖ ያቀረበዉ ክርክር በላለበት የአመልካች ይዞታ ስፊት ከ200 ካሬ ሜትር ያነሰ ስለሆነ የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጣቸዉ የጠየቁትን የሥር ፍርድ ቤት ዉድቅ ማድረጉ ተገቢ ነዉ ሲል የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ ማጽናቱ አመልካች በቀጣይ በአስተዲደር አካል ላይ ሉያነሱ የሚችለትን ክርክርና ፍትህ የማግኘት መብት የሚያጠብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። አመልካችም የግንባታ ፈቃድ አለአግባብ ተከልክያለሁ የሚለ ከሆነ አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት በሚመለከተዉ አካል ላይ ክስ በማቅረብ መጠየቅ ከሚችለ በስተቀር ከተጠሪ ጋር የፈጸሙትንና በፍርድ ቤት የፀደቀ የዔርቅ ስምምነት መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት የግንባታ ፈቃድ እንዱሰጣቸዉ እንዱያዝላቸዉ መጠየቃቸዉ ስለፍርድ አፈጻጸም የተዘረጋዉን ሥነ ሥርዓት የተከተለ አይደለም። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የደሴ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 18/02/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ፣የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 25/02/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ፣ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/6 ላይ በቀን 13/04/2013ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
አመልካችም በአስተዲደር አካል የግንባታ ፈቃድ አለአግባብ ተከልክያለሁ የሚለ ከሆነ አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት በሚመለከተዉ አስተዲደር አካል ላይ ክስ በማቅረብ መጠየቅ ይችላለ ብለናል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ወስነናል።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዔግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ሄ/መ
No topics extracted.