የእርቅ ሥምምነት በፍርድ ቤት ከጸደቀ እንደ ፍርድ ተቆጥሮ የሚፈጸም በመሆኑ በዚህ መሰረት የአፈጻጸም ክስን መሰረት በማድረግ ጉዲዩ በመደበኛ ክስ አግባብ ሳይሆን በአፈጻጸም ክርክር ሥርዓት ሉመራ የሚገባ ስለመሆኑ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277(2) እና የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ላቀረቡት የአፈጻጸም ክስ ባለዔዲ የሆነውን ወገን ፍርድን ፈጽሞ እንዱቀርብ ወይም የማይፈጸምበትን ሕጋዊ ምክንያት በቃል እንዱያስረዲ ማዘዝ ሲገባ እንደ መደበኛ ክስ በጽሁፍ መልስ እንዱሰጥበት የሚደረግ ስላለመሆኑ በፍርድ ቤት የጸደቀ ለአፈጻጸም የቀረበ ዔርቅ እንደ ፍርድ የሚቆጠር እንጂ እንደ ውል ታይቶ በውል ሕግ መሰረት በፍ/ሕ/ቁ. 1678፣ 1731፣ 1757 እና 1771 ድንጋጌዎች መሰረት የሚመራ ስላለመሆኑ በፍርድ ቤት በፀደቀ የእርቅ ስምምነት ንብረት ከማዛወር ጋር በተያያዘ ሉከፈል የሚገባ የተጨማሪ እሴት ታክስን በተመለከተ በእርቅ ሥምምነቱ ማን ሉከፍል እንደሚገባ ያልተመለከተ ከሆነ የታክስ ክፍያው በገዢ (በመጨረሻ ተጠቃሚው) ሉከፍል የሚገባ ስለሆነ ሥመ-ሀብቱ ሲዛወር ገዢ ሉከፍል ይገባል በሚል የሚሰጥ ውሳኔ ፍርደን ለማስፈጸምና ሥመ-ሀብቱን ለማዛወር መታለፍ ያለባቸውን ሂደቶች እልባት የሚሰጥ እንጂ ከፍርደ/ከዔርቅ ሥምምነቱ ውጭ የተሰጠ ትዕዛዝ ተደርጎ የማይወሰድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያው የሚመለከትው ለየትኛው ንብረት ነው፣ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ሉዛወር የሚችል ንብረት መኖር አለመኖሩን በመለየት አፈጻጸሙም የሚቀጥል ስለመሆኑ በተሰጠ ፍርድ ላይ ሥመ-ሀብት ዝውውር የሚደረገው ክፍያው ተጠናቆ ከመከፈል ጋር ያልተያያዘ ሆኖ የፍርድ ባለመብት ያልተፈጸመለት እንዱፈፀም የአፈጻጸም ክስ ባቀረበበት ሁኔታ በፍርድ ቤት ዲኝነቱን ማስፈጽም ሲገባ አቤቱታ ሲቀርብ የሚታይ ነው በሚል የሚሰጥ ውሳኔ አፈጻጸም ችልት ያለውን ተግባርና ኃላፉነት ያልተከተለ ስለመሆኑ ግዳታ ለመፈጸም ዋስትና እንዱቀርብ በዔርቅ በሥምምነት ላይ ባልተመለከተበት ሁኔታ በዔርቅ ሥምነት መሰረት ካልተፈጸመ የአፈጻጸም ክስ በማቅረብና ገንዘብ በባለዔዲው ካልተከፈለ ንብረት በማስከበር መብትን ማስፈጸም እንጂ ግዳታን ለመወጣት ቅድሚያ ዋስ እንዱቀርብ መጠየቅ ፍርድንና የሥነ-ሥርዓት ሕግን የተከተለ ስላለመሆኑ
No summary available.
ቀን፡- ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ መንግስቱ የሺጥላ - ጠበቃ ጓንጉል ተሻገር - ቀረቡ ተጠሪ፡- ቢ.ኤንድ ዋይ ፕልትሪ ፊርም ኃ/የተ/የግል ማሕበር- ጠበቃ ወይንዓለም ወ/ሰንበት - ቀረቡ መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው ክርከሩ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን አመልካች እና ተጠሪ በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተው ሐምል 18 ቀን 2010 ዓ/ም የእርቅ ሥምምነት ያደረጉ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የእርቅ ሥምምነቱን ሐምል 23 ቀን 2010 ዓ/ም ተቀብል አጽድቆታል። አመልካች ጥቅምት 05 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በእርቅ ሥምምነቱ መሰረት ተጠሪ ማስተላለፍ የሚገባውን ንብረት አላስተላለፈልኝም በማለት ሥመ-ሀብቱን ተጠሪ ተገድ እንዱፈጽም እና ግዳታውን ባለመወጣቱ ስለደረሰው ጉዲት በአዱስ ክስ የመጠየቅ መብት ይጠበቅልኝ ሲለ አመልክተዋል። ተጠሪ ባቀረበው የጽሁፍ መልስ በእጁ የሚገኙ ንብረቶች ለአመልካች እንዲስረከበና አመልካች እየተጠቀመባቸው እንደሚገኝ፣ በፍራንኮ ቫልታ ከታክስ ነጻ ወደ አገር የገቡትን ንብረቶች እ.ኤ.አ. በ05/12/2018 በተደረገ ሥምምነት ወደአመልካች ተዛውረዋል። አመልካች ለሚፈለገው ሰው ውክልና በመስጠት ሆነ የተጠሪ ሥራ አስኪያጅ በአካል በመገኘት ሥመ-ንብረት ለማዛወር ቢሞክሩም አመልካች ንብረቱ ሲዛወርለት የሚሰበስበውን የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደገዥ እንዱከፍል ሲጠየቅ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ዝውውሩ ሉፈጸም አልቻለም። በአፈጻጸም ማመልከቻ ወደፉት ክስ የማቅረብ መብቴ ይጠበቅልኝ በማለት ጥያቄ ማቅረብ አይችልም። ጥያቄው ተቀባይነት የለውም ብሎል።
በልላ በኩል ተጠሪ ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በዔርቅ ሥምምነቱ መሰረት አመልካች ለተጠሪ ብር 8,000,000.00 የመክፈል ኃላፉነት አለበት። ገንዘቡን በየወሩ ተከፊፍል የሚከፈል ሲሆን አመልካች ጊዜውን እያሳለፈ ሲከፍል ቆይቶ ከሐምል ወር 2011 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ አቋርጧል። ስለሆነም እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ሉከፈል የሚገባውን ብር 930,010.65 ተገድ እንዱከፍልና ቀሪውን በእርቅ ሥምምነቱ መሰረት እንዱከፍል በቂ መያዣና ዋስትና እንዱያቀርብ ጠይቋል። አመልካች ባቀረበው መልስ ተጠሪው መልስ እንዱያቀርብ በታዘዘበት ቀጠሮ በፍርድ ቤት ያልታዘዘና በሬጅስትራር ያላለፈ ክስ ይዞ ላቀርብ አይገባም። ንብረቶችን ለማዛወር ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው ክፍያ ያቋረጥነው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምረን ስለከፈልን ድጋሚ ልንከፍል አይገባም ሲል ተከራክሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ የተጠሪ ማመልከቻ በሬጅስትራር ተመርቶ የቀረበ ስለሆነ ሉመረመር የሚገባው ነው ካለ በኋላ የሂሳብ ባለሙያ መድቦ ካሰራ በኋላ በእርቅ ሥምምነቱ መሰረት አመልካች ያልከፈለውን ብር 930,010.65 ከ8% ወለድ ጋር እና እስከ ታህሳስ 2012 ዓ/ም ድረስ የዋጋ ግሽበት ያመጣውን ብር 128,173.96 ለተጠሪ በ30 ቀናት ውስጥ እንዱከፍለ አዟል። የተጨማሪ እሴት ታክስን በተመለከተ በእርቅ ሥምምነቱ ማን ሉከፍል እንደሚገባ ያልተመለከተ በመሆኑና ንብረቱ የሚዛወረው ለአመልካች ስለሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 ድንጋጌዎች መሰረት ከታክሱ መርሕ አኳያ ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ እንደመሆኑ መጠን የታክስ ክፍያው በገዢ (በመጨረሻ ተጠቃሚው) ሉከፍል የሚገባ ስለሆነ ሥመ-ሀብቱ ሲዛወር አመልካች ሉከፍል ይገባል። ተጠሪ ተገቢውን ትጋት በማድረግ ሥመ-ሀብቱን ወደአመልካች እንዱያዛውርና ስመሀብቱ ሲዛወር አመልካች ክፍያውን ያለማቋረጥ የሚከፍለ ስለመሆኑ ቅድሚያ ቀሪ ገንዘቡን የሚመጥን ዋስትና እንዱያቀርቡ አዟል። አመልካች ስመ-ሀብቱን ተጠሪ የሚያዛውር ስለመሆኑ ዋስትና ያቅርብልኝ ያለውን በተመለከተ አመልካች በእርቁ መሰረት ክፍያውን እስከከፈለ ድረስ ስመ-ሀብቱ ያልተዛወረ ከሆነ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ሲያቀርቡ ተገቢው ትዕዛዝ የሚሰጥበት ይሆናል። የሂሳብ ባለሙያውን ክፍያ አመልካች ይክፈለ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ባለመቀበል ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ለመልስ በተቀጠረበት ቀን ተጠሪ ክስ ማቅረቡ፣ በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን አለመሰጠቱ ሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም። የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ያስፈልጋል የተባለው ለአንድ መኪና ሲሆን ከዚህ ውጭ ግን ያልተላለፈ ንብረት አለ። የተጨማሪ እሴት ታክስ አመልካች ይክፈል መባለ የጸደቀውን ሥምምነት የሚያሻሽል ነው። ተጠሪ ሥመ-ሀብቱን ካላዛወረ ለሁለተኛ ጊዜ አቤቱታ ለማቅረብ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ይከለክለናል። አመልካች ግዳታውን ያልተወጣ በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 1757 መሰረት ግዳታችን እንድንፈጽም ልንገደድ አይገባም። ተጠሪ ሥመ-ሀብቱን ያላዛወረው በራሱ ፍላጎትና ዝውውሩን በማገደ ስለሆነና በእርቅ ሥምምነቱ የሚያዛውርበት ጊዜ ገደብ ስላለፈ ወዱያውኑ እንዱያዛውር ትዕዛዝ ላሰጥ ይገባል። ዋስትና ማቅረብ ያለበት አመልካች ሳይሆን ተጠሪ ላሆን ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ በእርቅ ሥምምነቱ መሰረት ተጠሪ ኃላፉነቱን መወጣቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ቀሪ ክፍያ እንዱከፍል መወሰኑ ከፍ/ሕ/ቁ. 1757 አኳያ ሕጋዊነቱን ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ያዘዘ ሲሆን የቀረበው መልስ ይዘትም ጉዲዩ አዱስ ክስ ሳይሆን በጸደቀው እርቅ መሰረት የሚፈጸም የአፈጻጸም ክርክር ነው።
ተጠሪም በዔርቅ ሥምምነት መሰረት የተገኘውን መብት ለማስከበር የአፈጻጸም ክስ ማቅረቡ ተገቢ ነው። ተጠሪ በሥምምነቱ ያለበትን ግዳታ ፈጽሟል፣ አመልካች ክፍያውን አቋርጠዋል። የንብረቶችን ሰነድ ከአመልካች ስናገኝ ውክልና ለጉዲይ አስፈጻሚው ሰጥተናል፣ ሥመ-ሀብት ለማዛወር የተጀመረው ሂደት የሽያጭ ውል ከተዘጋጀና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ውስጥ ሰነድ አረጋጋጭ ቢሮ ከደረሰ በኋላ ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ የተጠየቀ ሲሆን አመልካች ክፍያውን አልከፍልም በማለታቸው የንብረት ማስተላለፍ ሳይከናወን ቀርቷል። አነስተኛ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ከፍለው ማዛወር ሲችለ ለተጠሪ የሚገባውን ክፍያ ላለመክፈል ያዘገዩታል። የተጨማሪ እሴት ታክስ ገዥ ነው የሚከፍለው። ንብረቶቹ በሙለ በአመልካች እጅ ነው የሚገኙት፤ ውሳኔው ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል ብሎል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የአፈጻጸም ክርክሩ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን እና የጸደቀውን የእርቅ ሥምምነት መሰረት በማድረግ የተመራ ስለመሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች እና ተጠሪ በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተው ሐምል 18 ቀን 2010 ዓ/ም የእርቅ ሥምምነት ያደረጉ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የእርቅ ሥምምነቱን ሐምል 23 ቀን 2010 ዓ/ም ተቀብል አጽድቆታል። የእርቅ ሥምምነት በፍርድ ቤት ከጸደቀ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277(2) እንደተመለከተው እንደፍርድ ተቆጥሮ የሚፈጸም ነው።
አመልካች ጥቅምት 05 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በእርቅ ሥምምነቱ መሰረት ተጠሪ ማስተላለፍ የሚገባውን ንብረት አላስተላለፈልኝም በማለት ሥመ-ሀብቱን ተጠሪ ተገድ እንዱፈጽም ሆነ ተጠሪ በዔርቅ ሥምምነቱ መሰረት ገንዘብ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት የአፈጻጸም ክስን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ጉዲዩ በመደበኛ ክስ በሚመራበት አግባብ ሳይሆን በአፈጻጸም ክርክር ሥርዓት ሉመራ የሚገባው ነው። የሥር ፍርድ ቤት ግራቀኙ ላቀረቡት የአፈጻጸም ክስ ባለዔዲ የሆነውን ወገን ፍርድን ፈጽሞ እንዱቀርብ ወይም የማይፈጸምበትን ሕጋዊ ምክንያት በቃል እንዱያስረዲ ማዘዝ ሲገባው እንደመደበኛ ክስ በጽሁፍ መልስ እንዱሰጥበት ማድረጉ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም።
ለአፈጻጸም የቀረበው ዔርቅ የጸደቀ በመሆኑ እንደፍርድ የሚቆጠር እንጂ እንደውል የሚታይ ባለመሆኑ ጉዲዩን የፍ/ሕ/ቁ. 1678፣ 1731፣ 1757 እና 1771 መሰረት በማድረግ በውል ሕግ መምራቱም ስህተት ያለበት ነው። በዔርቅ ሥምምነቱ መሰረት አመልካች ገንዘብ የመክፈል እና ተጠሪ ንብረት የማስተላለፍ ግዳታ ያለባቸው በመሆኑ ሁለቱም ወገን የሚያስፈጽሙት መብት ሆነ የሚፈጽሙት ግዳታ ስላለባቸው ያልተፈጸመላቸውን በመለየት የአፈጻጸም ዲኝነት ሉያቀርቡ ይችላለ። አመልካች ቀድሞ የአፈጻጸም ክስ ማቅረቡ ተጠሪን በልላ መዝገብ የአፈጻጸም ክስ እንዱያቀርቡ የሚያደርግ አይደለም፤ ለአፈጻጸም መሰረት የሆነው ፍርድ አንድ በመሆኑ ሁለቱም በተመሳሳይ መዝገብ የአፈጻጸም ዲኝነት መጠየቃቸው ወጪና ጊዜ ቆጣቢ እንዱሁም ውጤታማ በሆነ አግባብ ክርክሩ እንዱመራ የሚያደርግና የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች ለማሳካት የሚረዲ በመሆኑ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ ነው። ስለሆነም አመልካች የተጠሪን የአፈጻጸም ክስ እንደ ተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በመቁጠር ሥነ-ሥርዓት ሕግን ሳይከተል የቀረበ ነው በሚል የሚያቀርቡት ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በዋናነት የሥነ-ሥርዓት ሕግ የተቀረጸው ሰዎች ግጭቶችን ሰላማዊ በሆኑ ሁኔታ እንዱፈቱ ለማስቻል (peaceful resolution of disputes)፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበት ዘዳ እንዱኖርና ፍርድ ቤቶች ክርክርን ፍትሐዊ እና ወጭ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት እንዱችለ ነው። የአፈጻጸም ችልት ጉዲዩን መምራት ያለበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎችና ለአፈጻጸም መሰረት የሆነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ሲሆን ውጤቱም ሰዎች በፍርድ ያገኙትን መብት ማስፈጸም ነው። ይሕ ሳይሆን ፍርድ የማይፈጸም ከሆነ የሕግ የበላይነት መገለጫ የሆነውን ዋናውን የፍርድ ቤቶች ኃላፉነት አለመወጣት ይሆናል። ዜጎች በፍትሕ ሥርዓቱ የሚጠቀሙት መብታቸውን ለማስከበር ነው። የመብት ማስከበር መሰረቱ ደግሞ ፍርድን ከማናቸውም መሰናክል ነጻ በማድረግ ማስፈጸም ነው። ፍርድ ቤቶች በዚህ አግባብ ኃላፉነታቸውን ካልተወጡ ዜጎች በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ያገኙት ፍትሕ የማግኘት መብትን ማረጋገጥ እና ማስፈጸም አይቻልም። ውጤቱ ደግሞ መብት ካለመከበሩም በተጨማሪ ፍርድ ቤቶች ላይ እምነት (public trust) እንዲይኖር ያደርጋል። ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ሰብዓዊ መብቶችን ከማስከበር እና የሕግ የበላይነት እንዱኖር ያላቸውን የማይተካ ሚና የመወጣት ግዳታ ያለባቸው በመሆኑና አንደ መገለጫ የወሰኑትን ውሳኔ ማስፈጸም በመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠ መብት ሳይፈጸም ፍርደ ያለውጤት እንዲይቀር የማድረግ ኃላፉነት መኖሩን ያሳያል።
አመልካች በጸደቀው የዔርቅ ሥምምነት መሰረት በየወሩ መክፈል ያለባቸውን ግዳታ ማቋረጣቸውን በክርክሩ ሂደት ገልጸዋል፤ ለዚህ ምክንያት ያደረጉት ተጠሪ ግዳታውን እየተወጣ አይደለም በሚል የፍ/ሕ/ቁ. 1757ን በመጥቀስ ነው። ከላይ እንደተገለጸው የእርቅ ሥምምነታቸው በፍርድ ቤት ከጸደቀ በኋላ እንደፍርድ የሚቆጠር ስለሆነ አመልካች ያለባቸውን ግዳታ የመፈጸም እና በተጠሪ የተመለከተው ግዳታ ካልተፈጸመ አሁን እንዲደረጉት የአፈጻጸም ክስ በማቅረብ መብታቸውን ማስከበር እንጂ ገንዘቡን መክፈል ሉያቋርጡ አይችለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የበሰለውን ክፍያ እንዱከፍለና ቀሪውንም በዔርቅ ሥምምነቱ መሰረት አመልካች እንዱፈጽሙ ማዘዙ ፍርደንና ሕጉን የተከተለ ሆኖ አግኝተነዋል። የተጠሪ ግዳታ ንብረቶችን ማስተላለፍ ሲሆን አመልካች ንብረቶችን መረከባቸውን አልካደም፤ የሚከራከሩት ሥመ-ሀብት አልተዛወረልኝም በሚል ነው። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ተገቢውን ትጋት በማድረግ ያልተዛወረ ንብረቶችን ሥመ-ሀብቱን ወደአመልካች እንዱያዛውር ብይን መስጠቱ ተገቢ ነው። ንብረት ከመዛወር ጋር በተያያዘ ሉከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስን በተመለከተ በእርቅ ሥምምነቱ ማን ሉከፍል እንደሚገባ ያልተመለከተ በመሆኑና ንብረቱ የሚዛወረው ለአመልካች ስለሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 ድንጋጌዎች መሰረት ከታክሱ መርሕ አኳያ ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ እንደመሆኑ መጠን የታክስ ክፍያው በገዢ (በመጨረሻ ተጠቃሚው) ሉከፍል የሚገባ ስለሆነ ሥመ-ሀብቱ ሲዛወር አመልካች ሉከፍል ይገባል በሚል የደረሰበት መደምደሚያ ፍርደን ለማስፈጸምና ሥመ-ሀብቱን ለማዛወር መታለፍ ያለባቸውን ሂደቶች እልባት የሚሰጥ እንጂ ከፍርደ/ከዔርቅ ሥምምነቱ ውጭ የተሰጠ ትዕዛዝ ተደርጎ ሉወሰድ አይገባም። የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያው የሚመለከት ለየትኛው ንብረት ነው፣ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ሉዛወር የሚችል ንብረት መኖር አለመኖሩን በመለየት አፈጻጸሙም አለመቀጠለ ግን ሉታረም የሚገባው ነው።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ክፍያውን ከፈጸሙ ሥመ-ሀብት እንዱዛወርላቸው አቤቱታ ማቅረብ ይችላለ ማለቱ በፍርደ ላይ ሥመ-ሀብት ዝውውሩ ክፍያው ተጠናቆ ከመከፈል ጋር ያልተያያዘ በመሆኑና አመልካች ያልተፈጸመላቸው እንዱፈጽም የአፈጻጸም ክስ ባቀረቡት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ዲኝነቱን ማስፈጽም ሲገባው አቤቱታ ሲያቀርብ የሚታይ ነው ማለቱ አፈጻጸም ችልት ያለውን ተግባርና ኃላፉነት ያልተከተለ ነው። በተጨማሪም በዔርቅ ሥምምነቱ አመልካች መክፈል ያለባቸውን ግዳታ በየወሩ የመክፈል ግዳታ ሲኖርባቸው ተጠሪ ደግሞ ሰነድችን በተቀበለ በ60 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የማስተላለፍ ግዳታ ያለበት በመሆኑ፤ ተጠሪ ያለበትን ግዳታ ለመፈጸም ዋስትና እንዱቀርብ በሥምምነቱ ባልተመለከተበት ሁኔታ ሥመ-ሀብቱን ለማዛወር በቅድሚያ አመልካች ዋስትና እንዱያቀርቡ መታዘዙ ከፍርድ ውጭ የተሰጠ ትዕዛዝ ነው። ተጠሪ በዔርቅ ሥምምነት መሰረት ካልተፈጸመለት አሁን እንዲደረገው የአፈጻጸም ክስ በማቅረብና ገንዘቡ በባለዔዲው ካልተከፈለ ንብረት በማስከበር መብትን ማስፈጸም እንጂ ግዳታውን ለመወጣት ቅድሚያ ዋስ እንዱቀርብለት መጠየቅ የማይችል በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ትዕዛዝ ፍርደንና የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ያልተከተለና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። በልላ በኩል አመልካች ስለሂሳብ ባለሙያ ወጪን በተመለከተ ላቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአመልካች የሚከፈለውን ክፍያ ለማስላት የሂሳብ ባለሙያ ተመድቦ የነበረ ሲሆን የባለሙያው ወጪ ክፍያ በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት ክፍያውን ያቋረጡት አመልካች በመሆናቸው ግዳታው የእርሳቸው መሆኑን በመገንዘብ ወጪውን አመልካች ይሸፍኑ ማለቱ ተገቢ ነው።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 29 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች በጸደቀው የእርቅ ሥምምነት መሰረት ያልከፈለትን ክፍያ ሆነ ወደፉት ሉከፈል የሚገባው ክፍያ እንዱከፍለ ሆነ ተጠሪ ሥመ-ሀብት እንዱያዛውር የተሰጠው ውሳኔ ክፍል ተገቢ ስለሆነ ጸንቷል።
አመልካች ዋስትና እንዱያቀርቡና ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ስለስመ-ሀብት ዝውውሩ አቤቱታ እንዱያቀርቡ የተሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ያለባቸውን ክፍያ እንዱከፍለ በማድረግ፣ ተጠሪ ወደአመልካች ስመ-ሀብታቸው የሚያዛውሯቸውን ንብረቶች በመለየት ንብረቶችን እንዱያስተላልፍ እንደፍርድ ሆኖ በሚፈጸመው በጸደቀው የእርቅ ሥምምነት መሰረት ተከታትል እንዱያስፈጽም ጉዲዩን መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም አዘናል።ይጻፍ አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ማ/አ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.