መድን ሰጪ ለኢንሹራንስ ገቢዉ /ለደንበኛዉ/ በከፈለዉ የገንዘብ መጠን ጉዲት እንዱደርስ ባደረጉት ሶስተኛ ወገኖች በከፈለዉ ገንዘብ መጠን ባለት መብቶችና ክሶች በደንበኛዉ ምትክ ሆኖ መጠየቅ የሚችል በመሆኑ መድን ሰጪው ለደንበኛው በከፈለዉ የገንዘብ መጠን ባለት መብቶች በደንበኛው እግር ተተክቶ ወይም በምትክነት ለጉዲቱ መንስኤ ነዉ የተባለዉን ተሽከርካሪ ከሶ ከመጠየቅ የሚያግደዉ ነገር ስለላለ በደንበኛው ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት መንስኤ ነዉ የተባለዉን ተሽከርካሪ ባለቤት ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጎ ካሳ ድርሻዉን መክፈል አለበት በሚል ለሚቀርብ ክርክር ፍ/ቤት ይህን ሶስተኛ ወገን ወደ ክርክሩ እንዱገባ ከማድረግ የሚከለክል ነገር የላለ ስለመሆኑ የንግድ ሕግ አንቀጽ 683 /1/ እና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.43 /1/
No summary available.
ሚያዚያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የሰበር ጉዲይ በተሽከርካሪ ላይ ለደረሰ ጉዲት በመድን ዉል መሰረት ካሳ ለማስከፈል የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ ክርክር ሲሆን፣ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.01-00223 በ29/06/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት የአሁን አመልካች የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች፣ የአሁን አመልካች ተከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን፣ ከሳሾች ባቀረቡት ክስ የከሳሾች ንብረት የሆነዉ የሰላዲ ቁጥር ኮድ 3-06060 አ.ማ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በ5/7/2006 ዓ.ም ከጎንደር ወደ መተማ እየሄደ እያለ ከሰላዲ ቁጥር ኮድ 3-17800 ኤፍ.ኤስ.አር ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ ሙለ ጉዲት ደርሶበታል፣ የጉዲቱ መንስኤዉ የሰላዲ ቁጥር ኮድ 3-17800 ተሽከርካሪ እንደሆነ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዲት ከተከሳሽ ጋር የብር 300,000 የመድን ዋስትና ገብተናል፣ የደረሰዉን አደጋ ለተከሳሽ አሳዉቀናል ነገር ግን በመድን ዉለ መሰረት ስላልከፈለን ይህን ገንዘብ እንዱከፈለን በጊዜ ባለመክፈለ የተቋረጠብን ጥቅም ብር 100,000 እንዱከፍለን፣ ለወደ ፉትም በየወሩ 12,000 እንዱከፈለን በማለት ከሷል።
ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ የከሳሾች ተሽከርካሪ በመንገድ ትራንስፕርት ባለስልጣን ከተፈቀደለት የመንገደኞች ቁጥር በላይ ጭኖ ሲጓዝ ጉዲት የደረሰበት ስለሆነ በመድን ዉለ መሰረት ካሳ ሉከፈላቸዉ አይገባም፣ አዲጋ ያደረሰዉን ተሽከርካሪ ሉጠይቁ ይገባል እንጂ ተከሳሽ መጠየቅ የለባቸዉም፣ በተሽከርካሪዉ ጉዲት ምክንያት ለሚደርስ የጥቅም ማጣት የመድን ዋስትና ያልሰጠን ስለሆነ ልንከፍል አይገባም፣ ይህ የሚታለፍ ከሆነ የተከሰስንበትን ገንዘብ መጠን የአደጋ መነሻ 5% ተቀናሽ ተደርጎ ሉከፈል ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ በከሳሾች እና በተከሳሽ መካከል በተደረገዉ የመድን ዉል መሰረት ተከሳሽ በከሳሾች የሰላዲ ቁጥር ኮድ 3-06060 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ሙለ ለሙለ ጉዲት በገባዉ ግዳታ መሰረት 5% ተቀንሶ ለብር 250,000.00 ኃላፉነት ያለበት ስለሆነ ለከሳሾች ይክፈል፤ ይህን ገንዘብ ፍርድ ከተሰጠ ጊዜ ጀምሮ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ከ9% ወለድ ይክፈል፤ ከሳሾች ካሳዉ ባለመከፈለ የተቋረጠብን ጥቅም ተከሳሽ እንዱከፍለን ያለትን በተመለከተ ተከሳሽ ኃላፉነት የለበትም፣ ተከሳሽ የመኪናዉን ቅሪት ይረከብ በማለት ወስኗል።
የሥር ተከሳሽ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የቀረበዉን ይግባኝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ5/7/2008 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል። የአቤቱታዉም ይዘት በአጭሩ፡--የተጠሪዎች ሚኒባስ ተሽከርካሪ አደጋዉ ሲደርስ 7 ሰዎች ትርፍ ጭኖ ሲያጓጉዝ የነበረ በመሆኑ በመድን ዉልም ሆነ በትራንስፕርት ደንብ እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ከሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም አንጻር የጉዲት ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ሳይኖርብን እንድንከፍል መወሰኑ እና ጉዲት አድርሷል የተባለዉን ተሽከርካሪ ወደ ክርክሩ እንዱገባ ጠይቀን ሳይገባ ዉሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ይህን ጉዲይ በማየት ፣የተጠሪዎች መኪና አደጋ በደረሰበት ጊዜ ትርፍ ሰዉ መጫኑ ያልተካደ እስከሆነ ድረስ በመድን ፕሉሲዉ ተጠቃሚ ይሆናለ ወይስ አይሆኑም? ለጉዲቱ ኃላፉ ነዉ የተባለዉ ተሽከርካሪ ባለቤት ጣልቃ እንዱገባ የተጠየቀዉን ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ በታዘዘዉ መሰረት በ28/8/2008 ዓ.ም የተጻፈ አምስት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡--የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ የቀረበዉ ቅሬታ ዉድቅ ተደርጎልን የሥር ዉሳኔ እንዱጻናልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። አመልካች ቀጠሮ እያወቀ በመቅረቱ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉ ክርክር ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርመሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች እና ተጠሪዎች ለተጠሪዎች ንብረት ለሆነዉ ሚኒባስ ተሽካርካሪ በተመለከተ የኢንሹራንስ ዉል ፕሉሲ መዋዋላቸዉ ያላከራከረ ጉዲይ ሲሆን፣ አመልካች በዚህ ተሽከርካሪ ላይ ለሚደርሰዉ ሙለ ዉድመት ከብር 300,000 ዉስጥ 5% ተቀናሽ ተደርጎ ለተጠሪዎች ለመክፈል መስማማታቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ነዉ። እንዱሁም በግራ ቀኛቸዉ መካከል በተፈረመዉ የኢንሹራንስ ዉል ፕሉስ ክፍል 3 እንደተመለከተዉ ተጠሪዎች በተሽከርካሪ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ላይ ከተመለከተዉ የተሣፊሪ ቁጥር በላይ የተጫነ እንደሆነ ለሚደርሰዉ ጉዲት ኃላፉ እንደማይሆን ተደንግጓል። ነገር ግን በፕሉስዉ ክፍል 10 ተራ ቁጥር 1 /ሀ/ ሥር እንደተመለከተዉ ተሽከርካሪዉ ትርፍ ሰዉ በመጫኑ ኃላፉ የማይሆነዉ የተፈጠረዉ የግጭት ወይም በተሽከርካሪዉ ላይ ለደረሰዉ አደጋ መንስኤዉ ትርፍ ሰዉ በመጫኑ እንደሆነ ነዉ። ይህ የኢንሹራንስ ዉል ፕሉሲ ደግሞ በንግድ ሕጉ በተመለከተዉ እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1711 እና 1731 /1/ በሚደነግገዉ አግባብ በግራ ቀኛቸዉ መካከል ሕግ ነዉ። በመሆኑም የተጠሪዎች ተሽከርካሪ ትርፍ ሰዉ መጫኑ ለአደጋዉ መንስኤ የሆነ እንደሆነ አመልካች በዉለ መሰረት የጉዲት ካሳ ለመክፈል ከኃላፉነት ነጻ እንደሚሆን ያመለክታል። ነገር ግን በተጠሪዎች ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት መንስኤዉ ትርፍ ሰዉ ጭኖ መገኘቱ ያልሆነ እንደሆነ አመልካች በመድን ዉል ፕሉሲዉ መሰረት ከኃላፉነት ነጻ የሚሆንበት አግባብ የለም።
ከዚህ አንጻር በሥር ፍ/ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ሲታይ በተጠሪዎች ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት መንስኤዉ ትርፍ ሰዉ ጭኖ በመጓዙ ሳይሆን የሰላዲ ቁጥር ኮድ 3-17800 ኤፍ.ኤስ.አር ተሽከርካሪ የቀኝ መስመሩን ለቆ ጉዲት ያደረሰ መሆኑን ነዉ። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች በተጠሪዎች ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ምክንያት የሆነዉ ተሽከርካሪዉ ትርፍ ሰዉ በመጫኑ ሳይሆን በልላ ተሽከርካሪ ጥፊት እንደሆነ ስለተረጋገጠ የአሁን አመልካች በመድን ዉል ፕሉሲ መሰረት ለተጠሪዎች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጡት ዉሳኔዎች በሕጉ አግባብ የተሰጡ ናቸዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ለማለት አይቻልም።
በቀጣይነት መታየት ያለበት ጉዲይ አመልካች የጉዲት አድራሽ ተሽከርካሪ ባለቤት የሆነዉ ሰዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.43 መሰረት ወደ ክርክር እንዱገባለት ጠይቀዉ የመታለፈን አግባብነት ነዉ።
በእርግጥ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.43 /1/ እንደሚደነግገዉ ተከሳሽ ለተከሰሰበት ነገር የክርክሩ ተካፊይ ያልተደረገ ሰዉ ከእኔ ጋር ድርሻ ካሳዉን መክፈል አለበት የሚልበት ምክንያት ካለ ይኼንኑ አስተካክል ይህ ሶስተኛ ወገን ወደ ክሱ እንዱገባ ማመልካቸዉን ለፍ/ቤት ማቅረብ እንደሚችልና ፍ/ቤቱም ይህ ሶስተኛ ወገን ወደ ክርክሩ እንዱገባ የፈቀዲ እንደሆነ ክርክሩን እንዱያቀርብ ትዕዛዝ መስጠት እንደሚችል በንዐስ አንቀጽ 2 ሥር ተመልክቷል። በዚህ አግባብ አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች መድን ሰጪ ሲሆን በደንበኛዉ መኪና ላይ ለደረሰዉ ጉዲት የሰላዲ ቁጥር ኮድ 3-17800 የሆነ ተሽከርካሪ ባለቤት ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጎ ካሳ ድርሻዉን መክፈል አለበት የሚል ነዉ።
የሥር ፍ/ቤት ከላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ አግባብ ይህን ሶስተኛ ወገን ወደ ክርክሩ እንዱገባ ከማድረግ የሚከለክላዉ ነገር አልነበረም። ነገር ግን በዚህ ድንጋጌ አግባብ ለጉዲቱ ምክንያት ነዉ የተባለዉ ሶስተኛ ወገን ወደ ክርክሩ እንዱገባ አለመደረጉ አመልካች የሚያጣዉ መብት አለ ወይ? ከሚለዉ ነጥብ ጋር በማገናዘብ መታየት ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ሲታይ በንግድ ሕግ አንቀጽ 683 /1/ እንደሚደነግገዉ መድን ሰጪ ለኢንሹራንስ ገቢዉ /ለደንበኛዉ/ በከፈለዉ የገንዘብ መጠን ጉዲት እንዱደርስ ባደረጉት ሶስተኛ ወገኖች በከፈለዉ ገንዘብ መጠን ባለት መብቶችና ክሶች በደንበኛዉ ምትክ ሆኖ መጠየቅ እንደሚችል ይደነግጋል። ይህ ከሆነ የአሁን አመልካች ለተጠሪዎች በከፈለዉ የገንዘብ መጠን ባለት መብቶች በተጠሪዎች እግር ተተክቶ ወይም በምትክነት ለጉዲቱ መንስኤ ነዉ የተባለዉን ተሽከርካሪ ከሶ ከመጠየቅ የሚያግደዉ ነገር የለም። ስሉዚህ የሥር ፍ/ቤቶች በተጠሪዎች ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት መንስኤ ነዉ የተባለዉን ተሽከርካሪ ባለቤት ወደ ክርክሩ እንዱገባ አለማድረጋቸዉ የአመልካችን መብት የሚነካበት ሁኔታ ስለላለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚያስብል ስላልሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.01-20431 በ26/4/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.01-00223 በ29/6/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠዉ የአፈጻጸም እግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል።
ይጻፍ።
No topics extracted.