ተሽከርካሪ ከሚያደርሰው ግጭት የሚመነጭ ኃላፉነትን መድን ገቢው የመድን ሽፊን እንዱኖረው በማድረግ ኃላፉነት፤ በንብረት ላይ ለሚደርስ ኪሣራ የመድን ሰጭው የኃላፉነት መጠን ጣሪያው 100,000.00 ያልበለጠ እንደሆነ የተመለከተው በዋነኛነት የተጎጂውን ቁጥር ሳይሆን ጣሪያው የተወሰነው አደጋ በደረሰ ጊዜ እና የኃላፉነት ጣሪያው የደረሰን አደጋ የሚከተልና ጉዲት በንብረት ላይ በሚደርስ ጊዜ ጉዲት የደረሰባቸው የባለንብረቶች ቁጥር ግምት ውስጥ ሳይገባ በጠቅላላው አንድ ጊዜ ለተከሰተ አደጋ በንብረት ላይ ለሚደርስ ኪሣራ የተገለጸ ጣሪያ መሆኑና በአንድ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ በተከሰተ አደጋ በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዲት፤ አደጋው በብዙ ባለንብረቶች ላይ ወይም በአንድ ሰው ንብረት ላይ ያደረሰው ኪሣራ ከ100ሺ በላይ ከሆነ መድን ሰጭው የመሸፈን ኃላፉነት ያለበት እስከ ብር 100,000.00 ድረስ ብቻ ስለመሆኑ የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1) (ሐ)
No summary available.
የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተጠሪዎች-
ጉዲዩ የጉዲት ካሳን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት ደቡብ ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ እንዱሁም አመልካች ጣልቃ-ገብ በመሆን ተከራክረዋል። 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ ግንቦት 06/09/2010 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ንብረትነቱ የ2ኛ ተጠሪ የሆነው እና የሰላዲ ቁጥሩ አአ 3-A17891 የሆነ ኤፍ.ኤስ.አር ተሸከርካሪ ነሐሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ም ወደ ኋላ በመንሸራተት በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ ዉስጥ ያለኝን የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ እና የቁልፍ ስራ ድርጅቴን ጉዲት ያደረሰበት በመሆኑ ጉዲት ለደረሰበት ንብረቴ ብር 158,297.00 እንዱሁም ከነሐሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 17 ቀን 2009 ዓ.ም ሰርቼ አገኝ የነበረውን በቀን ብር 1000.00 በጉዲቱ ምክንያት ያጣሁ በመሆኑ የ25 ቀን ብር 25,000.00 እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
2ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጠዉ መልስ በተሽከርካሪዉ ምክንያት ጉዲቱ መድረሱን ሳይክድ የ1ኛ ተጠሪ የንግድ ፍቃድ የቁልፍ ስራ እና የአትክልትና ፍራፍሬ ችርቻሮ ንግድ ሲሆን የሸቀጣሸቀጥ ንግድ እንደሚሰሩ አስመስለው ክስ ማቅረብ አይችለም፤ የቀረበው የንብረት ግምት እና የቀን ገቢ የተጋነነ ነው፤ ጉዲት አድርሷል የተባለው ተሸከርካሪም የመድን ሽፊን ያለው በመሆኑ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ወደ ክርክሩ በመግባት መልስ እንዱሰጥ ይታዘዝልኝ በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ወደ ክርክሩ በመግባት ባቀረበዉ መልስ ከዚሁ ጉዲይ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ፍርድ ቤት በልላ መዝገብ ላላ ግለሰብ ክስ አቅርቦ በክርክር ላይ ያለ በመሆኑ መዝገቦቹ ይጣመሩልኝ፤ ጉዲት ደርሶባቸዋል የተባለት ንብረቶች እና ኮንቴይነሩን ለማሰራት ወጣ የተባለው ወጪ ግምት የተጋነነ በመሆኑ በገለልተኛ ገማች እንዱገመትልን ይደረግ የሚል መቃወሚያ አቅርቧል። በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጠው መልስ ደግሞ 1ኛ ተጠሪ የንግድ ፍቃድ ያወጡበት ዘርፍ እና ጉዲት ደርሶባቸዋል የተባለት ንብረቶች አይገናኙም፤ ፍቃድ ላላወጡባቸው ንብረቶች ካሳ እንዱከፈላቸው መጠየቃቸው እና ሙለ ለሙለ ውድመት ላልደረሰበት ኮንቴይነር ካሳ መጠየቅ ተገቢ አይደለም፤ ከሱቁ ውስጥ ጠፊ የተባለው ጥሬ ገንዘብም በስፍራው የነበረ ስለመሆኑ የሚታምን አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የ1ኛ ተጠሪ የስራ ዘርፍ ንግድ ስራ ስለመሆኑ በምስክርም ጭምር ተረጋግጧል፤ የንብረቱን ግምት በተመለከተ አስራ ሶስት ከሚሆኑ የእቃ አይነቶች ውጪ የላልቹን ግምት ማስገመት ያልተቻለ ሲሆን አመልካችም ለማስገመት ተገቢውን ጥረት አላደረገም፤ የተገመቱት ንብረቶች ዋጋም 1ኛ ተጠሪ ካቀረቡት ግምት ቢበልጥም አመልካች ገምተው ያቀረቡትን ግምት ተቀብለናል፤ ከሱቅ ጠፍቷል የተባለውን ጥሬ ገንዘብ በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ ስለመጥፊቱ ያስረዲች ሲሆን አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ደግሞ አላስተባበለም ካለ በኋላ የአመልካችን የኃላፉነት መጠን በሚመለከት አመልካች በዚሁ ተሸከርካሪ ምክንያት በተመሳሳይ ሰዓት ጉዲት ለደረሰበት ላላ ግለሰብ በልላ መዝገብ ተከስሼ ብር 100,000.00 እንድከፍል የተወሰነብኝ በመሆኑ በአንድ አደጋ ምክንያት ከብር 100,000.00 በላይ ካሳ ልከፍል አይገባም ቢልም አደጋው የደረሰው በተለያዩ ሰዎች ንብረት ላይ በመሆኑ ኃላፉነት አለበት፤ ስለሆነም አመልካች ብር 100,000.00 እንዱከፍል፣ ቀሪውን ብር 83,279.00 ደግሞ 2ኛ ተጠሪ ከጠበቃ አበል እና ለዲኝነት ከተከፈለ ወጪ ጋር እንዱከፍለ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው አመልካች ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የኃላፉነት መጠን 2ኛ ተጠሪ ክድ ባልተከራከረበት ግልጽ የሆነውን የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1)(ሐ) ‛ን“ ያለአግባብ በመተርጎም መድን የተገባለት ተሸርካሪ በአንድ ጊዜ በተለያዩ ግለሰቦች ንብረት ላይ ጉዲት ካደረሰ ለእያንዲንዲቸው ግለሰቦች እስከ ብር 100,000.00 ድረስ ካሳ መክፈል አለበት ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ አመልካች በአንድ ድርጊት በሁለት ግለሰቦች ንብረት ላይ ጉዲት ደርሶ እያለ አመልካች ለእያንዲንዲቸው ካሳ ሉከፍል ይገባል የመባለ አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(3)(ሐ) አንፃር መጣራት ያለበት መሆኑ ታምኖበት ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቧል።
በዚሁም መሰረት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት በሚል መጥሪያ ተልኮላቸው 1ኛ ተጠሪ መጥሪያ ተቀብለው መልስ ለመቀበል በተያዘው ቀጠሮ ባለመቅረባቸው መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፎል።
2ኛ ተጠሪ ግን መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ ተሸርካሪያችን ጉዲት በንብረታቸው ላይ ጉዲት ያደረሰባቸው 1ኛ ተጠሪ እና አቶ ከሪም ሁሴን የተባለት ግለሰቦች የየራሳቸው ንብረት ያላቸው በመሆኑ የአንዲቸው መብት ከአንዲቸው ጋር ሳይቀላቀል ለደረሰባቸው ጉዲት ካሳ ሉከፈላቸው ይገባል፤ የስር ፍርድ ቤቶችም በዚሁ አግባብ ካሳ እንዱያገኙ መወሰናቸው ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር በ2ኛ ተጠሪ መልስ ላይ የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ከተያዘው ጭብጥ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርነው ንብረትንቱ የ2ኛ ተጠሪ የሆነዉ የሰላዲ ቁጥር አ.አ. 3-17891 በአመልካች ድርጅት ላይ አድርሷል ለተባለዉ የንብረት ጉዲት ብር 183,297.00 ለመክፈል 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት አለበት በሚል ከተወሰነዉ ዉስጥ አመልካች የሦሥተኛ ወገን መድን ሰጪ እንደመሆኑ ብር 100,000.00 እንዱከፍል የተወሰነ ሲሆን፣ አመልካች ከስር ጀምሮ አጥብቆ የሚከራከረዉ በተመሳሳይ አደጋ ምክንያት በልላ ሦስተኛ ወገን ላይ በደረሰ ጉዲት በደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ክስ ቀርቦበት ብር 100,000.00 እንዱከፍል የተወሰነበት መሆኑን ጠቅሶ በአንድ አደጋ ምክንያት ከብር 100,000 በላይ መክፈል የለብኝም በማለት ነዉ። የስር የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ ያደረጉት በጉዲት ምክንያት የሦስተኛ ወገን መድን ሰጪ የሚከፍለዉን የክፍያ መጠን አስመልክቶ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1-ሐ) ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ የብር 100,000.00 የክፍያ ጣሪያ በአንድ ሰዉ ላይ ለሚደርስ ጉዲት መድን ሰጪዉ ከዚህ የገንዘብ መጠን በላይ ለመክፈል እንደማይገደድ የሚገልጽ እንጂ በአንድ ጉዲት በብዙ ሰዎች ላይ ጉዲት የደረሰ ቢሆንም የመድን ሰጪዉ የኃላፉነት ጣሪያ ከብር 100,000.00 ሉበልጥ አይገባም የሚል ይዘት የላለዉ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ።
በንግድ ሕግ አንቀጽ 685 እና ተከታዮቹ መሰረት መድን ገቢ እና መድን ሰጭ ስለ ኃላፉነት ኢንሹራስ ውል ስምምነት ማድረግ እንደሚችለ የተመለከተ ሲሆን ስለተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 ዓ/ም አንቀጽ 15(1) ደግሞ ተሽከርካሪ ከሚያደርሰው ግጭት የሚመነጭ ኃላፉነትን መድን ገቢው የመድን ሽፊን እንዱኖረው የማድረግ ኃላፉነት እንዲለበት ይደነግጋል። የመድን ሰጭው የኃላፉነት መጠን ጣሪያውም በሕግ ተዘርዝሯል። በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1)(ሐ) መሰረት በንብረት ላይ ለሚደርስ ኪሣራ የኃላፉነት ጣሪያው ከብር 100,000.00 ያልበለጠ እንደሆነ ተመልክቷል።
አሁን ያከራከረው ይህ ጣሪያ ተፈጻሚነቱ ንብረቱ ላይ ጉዲት በደረሰበት ለእያንዲንደ ሰው ነው ወይስ በጠቅላላ ሁለም ንብረት ላይ ጉዲት ለደረሰባቸው 3ኛ ወገኖች የሚለው ነው። የኃላፉነት መጠኑን የደነገገው የአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1) ለ3ኛ ወገን የተሽከርካሪ አደጋ (ሰረዝ የተጨመረ) ማለቱ የኃላፉነት ጣሪያው በዋነኛነት የተጎጂውን ቁጥር ሳይሆን ጣሪያው የተወሰነው አደጋ በደረሰ ጊዜ እና የኃላፉነት ጣሪያው የደረሰን አደጋ የሚከተል እንደሆነ ያሳያል። የአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1)(ሀ) እና (ለ) ላይ በሰው ላይ ለሚደርስ የአካል ጉዲት ወይም ሞት የኃላፉነት ጣሪያው በተጎጂው ሰው ቁጥር ልክ መሆኑ በሕጉ በግልጽ ተመላክቶ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1)(ሐ) መሰረት በንብረት ላይ ለሚደርስ ኪሣራ ግን የኃላፉነት ጣሪያው ከብር 100,000.00 ያልበለጠ ተብል መደንገጉ፤ ጉዲት በንብረት ላይ በሚደርስ ጊዜ ጉዲት የደረሰባቸው የባለንብረቶች ቁጥር ግምት ውስጥ ሳይገባ በጠቅላላው አንድ ጊዜ ለተከሰተ አደጋ በንብረት ላይ ለሚደርስ ኪሣራ የተገለጸ ጣሪያ መሆኑን መረዲት ይቻላል። ስለሆነም በአንድ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ በተከሰተ አደጋ በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዲት፤ አደጋው በብዙ ባለንብረቶች ላይ ወይም በአንድ ሰው ንብረት ላይ ያደረሰው ኪሣራ ከ100ሺ በላይ ከሆነ መድን ሰጭው የመሸፈን ኃላፉነት ያለበት እስከ ብር 100,000.00 ድረስ ብቻ መሆኑን የሕጉ አነጋገር ያስረዲል። ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም የሰ/መ/ ጨምሮ በላልች መዝገቦች ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ ለ2ኛ ተጠሪ ክስ መነሻ በሆነው አደጋ ምክንያት በልላ ሰዉ ላይም ጉዲት መድረሱን ተከትል በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ላይ ክስ ቀርቦበት ብር 100,000.00 አመልካች እንዱከፍል ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ የሰጠ ስለመሆኑ ተጠሪዎች ክደዉ አይከራከሩም። አመልካች በዚሁ አደጋ ምክንያት በልላ ሰዉ ላይ ለደረሰው ጉዲት ብር 100,000.00 ከ2ኛ ተጠሪ ክስ አስቀድሞ የከፈለ በመሆኑ በአንድ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ በተከሰተ አደጋ በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዲት ያለበትን ከፍተኛ የኃላፉነት ጣሪያ ስለከፈለ ድጋሜ ክፍያ ሉጠየቅ አይገባም። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች የንብረት ጉዲት ካሣውን ለ2ኛ ተጠሪ ሉከፈል ይገባል በማለት መወሰናቸው የአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1) (ሐ) የተመለከተውን ያላገናዘበ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።
አመልካች ብር 100,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት በደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 04 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ተሰጥቶ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/6 ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የጸናዉ ዉሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ብር 100,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም ተብል ተወስኗል።
2ኛ ተጠሪ ብር 83,279.00 (ሰማኒያ ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር) እንዱከፍል በስር ፍርድ ቤቶች ከተወሰነዉ በተጨማሪ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍል ተወስኗል።
የሰበር አጣሪ ችልት መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።