የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጦብኛል፤ በዉል ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ፣ እንዱወሰንልኝ በማለት የሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄ በተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 (1) (ሀ) እና (መ)፣ በድሬደዋ አስተዲደር ቻርተር በአዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33 (1) (ሀ) እና (መ) ሥር የሚወድቅ ጉዲይ መሆኑን የሚያመለክት ነገር ስለላለ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደርም ሆነ በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ዉስጥ ከሉዜ ዉል አፈጻጸም ጋር የተያያዘ ጉዲዮች መሰረት በማድረግ የሚቀርበዉን ክስ ሰምቶ ለመወሰን የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች እንጂ የአዱስ አበባም ሆነ የድሬዲዋ ከተማ የአስተዲደር ፍ/ቤቶች ይህን ጉዲይ ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸው ስላለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 (1)፣ 79 (1) ሐጂ መሀመድ እስማኤል እና የድሬዲዋ አስተዲደር ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ፣ አቶ ጌታቸዉ ረጋሳ ካባ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.4 (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በ #### #### የሰ/መ/ቁ 54697 መዝገብ ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጧል።) የሉዜ ዉል በሕግ በግልጽ የአስተዲደር ዉል ነዉ ተብል ያልተመለከተ እና የከተማ ቦታን በሉዜ ዉል በመያዜ የመጠቀም መብት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.3132 ድንጋጌ አንጻር ሲታይ በዙህ ድንጋጌ ሥር የተመለከቱትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ባለመሆኑ የአስተዲደር ዉልች ሥር የሚወድቅ ነዉ ልባል የሚችል ስላለመሆኑ
No summary available.
መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የሉዜ ዉልን መነሻ ያደረገ ክርክር የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ይህ ጉዲይ ለዙህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.17839 በ14/3/2014 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዚዜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሕግ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ከሲራክ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር በዕዲ ምክንያት ወርሶ በጨረታ የሸጠልኝ ካ.ሜ የሆነዉን በማዕድን ዉሃ ማምረቻ ፊብሪካ በስሜ እንዱመዘገብ በጠየቅኩኝ መሰረት በካርታ ቁጥር መል/ሉ/3095 በስሜ ተመዜግቦልኝ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የሉዜ ዉል ተዋዉለን ሥራዉን ለማስቀጠል የዉሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር በዜግጅት ላይ እያለሁኝ፤ 1ኛ ተከሳሽ ከተሰጠኝ ይዝታ ዉስጥ 8620 ካ.ሜ ቦታ ቀንሶ ለ2ኛ ተከሳሽ በሉዜ ዉል የሰጠዉ በመሆኑ፤ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ያደረኩኝ የሉዜ ዉል ሉሰረዜ የሚችልበት ምክንያት ስለላለ 1ኛ ተከሳሽ ከዉላችን ዉጭ ቀንሶ ለ2ኛ ተከሳሽ በካርታ ቁጥር መል/ሉ/5455 የሰጠዉ የ8620 ካ.ሜ ቦታ የይዝታ ማረጋገጫ እንዱሰረዜልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
1ኛ ተከሳሽ (የአሁን 1ኛ ተጠሪ) በዙህ ክስ ላይ ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ይህ ጉዲይ በቀጥታ ክስ በመደበኛ ፍ/ቤት የሚታይ ባለመሆኑ ክሱ ዉድቅ ነዉ በማለት ተከራክሯል። በፍሬ ነገር ክርክር 1ኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ቦታ ቀንሶ ለ2ኛ ተከሳሽ የሰጠዉ በተደረገዉ የሉዜ ዉል እና በሕግ መሰረት ከሳሽ በቦታዉ ላይ ምንም ሥራ ባለመስራቱ እና ላለመስራቱም ከአቅም በላይ ችግር የገጠመዉ ስለመሆኑ በሉዜ ዉለ በተመለከተዉ ጊዛ ያላሳወቀዉ በመሆኑና አምስት አመቱም የተጠናቀቀ በመሆኑ፣ ከዙህ በላይ ጊዛ ሉሰጠዉ የማይችል በመሆኑ ክሱ ዉድቅ እንዱደረግልን በማለት ተከራክሯል።
2ኛ ተከሳሽ (የአሁን 2ኛ ተጠሪ) በዙህ ክስ ላይ ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የከሳሽ የሉዜ ዉል በሉዜ አዋጁ፣ ደንብ እና መመሪያ መሰረት ተሰርዝ የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም ወደ መሬት ባንክ እንዱገባ ያደረገዉ በመሆኑ፤ ፍ/ቤቱ ይህን ጉዲይ ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን የለዉም። በፍሬ ነገር ክርክር ከሳሽ በተሰረዘና በላለ ዉል ክስ ማቅረብ አይችልም፤ ክሱ እኔን አይመለከተኝም፤ ከሳሽ መከራከር ካለበት ዉለን ካደረገዉና ከሰረዘዉ አካል ጋር እንጂ ከእኔ ጋር መሆን የለበትም፤ ለእኔ ካርታ የተሰጠኝ ሕጉን ተከትል በመሆኑ ሉሰረዜ የሚችልበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል።
ከዙህ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠዉ ትዕዚዜ ግራ ቀኙ በክርክር ላይ እያለ የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከሳሽ ለክሱ ምክንያት ያደረገዉ የይዝታ ማረጋገጫ ካርታ የመከና መሆኑን ስላረጋገጠ፣ ይህ ደግሞ የከሳሽን ክስ ቀሪ የሚያደርግ በመሆኑ፣ በክርክሩ ሂደት ለክሱ መነሻ የሆነዉ ነገር ተቋርጧል በማለት መዜገቡን ዘግቶታል።
ከሳሽ በዙህ ትዕዚዜ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከረ ባሳለፈዉ ዉሳኔ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ያደረኩኝ የሉዜ ዉል እያለ 1ኛ ተከሳሽ ከዉላችን ዉጭ በመሰረዜ እና በሉዜ ካገኘሁት ይዝታ ላይ ቀንሶ ለላላ ሰዉ መስጠቱ ሕጋዊ አይደለም የሚል በመሆኑ፣ የከሳሽ የዲኝነት ጥያቄ የሉዜ ዉል አፈጻጸምን የሚመለከት በመሆኑ፤
ይህ ጉዲይ በፍ/ቤት መታየቱ ተገቢ ቢሆንም ከከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት እና ከመደበኛ ፍ/ቤት መካከል በየትኛዉ ፍ/ቤት መታየት አለበት የሚለዉ ነጥብ ምላሽ የሚፈልግ ጉዲይ ነዉ።
በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33 (1) (ሀ) እና (መ) መሰረት የከተማ አስተዲደር ዉልችን በተመለከተ እና የከተማዉን መዋቅራዊ ፕላን አስመልክቶ በሚነሱ ክርክሮች ላይ አከራክሮ ለመወሰን የሥረ-ነገር ስልጣን ያለዉ መሆኑን ስለሚያስገነዜብ፤ የሉዜ ዉል ደግሞ ከሉዜ አዋጅ እና አዋጁን ተከትል ከወጡ ሕጎች እንዱሁም የፍ/ብ/ሕ/ቁ.3132 መሰረት የአስተዲደር ዉል መሆኑን ስለሚያመለክት፤ የሥር ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ተቀብል የማከራከር የሥረ-ነገር ስልጣን የድሬዲዋ ከተማ ፍ/ቤት ነዉ በማለት ወስኗል። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ25/5/2014 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ያደረግነዉ የሉዜ ዉል 1ኛ ተጠሪ ከሕግ ዉጭ በመሰረዜ ከይዝታዉ ቀንሶ ለ2ኛ ተጠሪ መስጠቱ ሕገወጥ ተግባር መሆኑን በመግለጽ ክስ ያቀረብኩኝ በመሆኑ፤ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በተመሳሳይ ጉዲይ በ
በ27/10/2010 ዓ.ም በሰጠዉ አስገዲጅ ዉሳኔ ከድሬዲዋ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/96 አንቀጽ 33 እና 3132 መሰረት የድሬዲዋ ከተማ ፍ/ቤቶች ከሉዜ ዉል ጋር ተያይዝ የሚቀርበዉን ዲኝነት አይተዉ ለመወሰን የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን እንደላላቸዉ እና ጉዲዩን ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች መሆናቸዉን የወሰነ ሆኖ ሳለ፣ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሻርልኝ፤ ጉዲዩ ወደሥር ፍ/ቤት ተመልሶ በፍሬ ነገር ክርክር ታይቶ ዉሳኔ እንዱሰጥልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ተቀብል የማከራከር የሥረ-ነገር ስልጣን የለዉም በሚል የወሰነበትን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 416/1996 እና
ላይ ከተሰጠዉ አስገዲጅ ዉሳኔ አንጻር ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዘዘዉ መሰረት 1ኛ ተጠሪ በ20/8/2014 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት ባጭሩ፡ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት የዲኝነት ስልጣን የለዉም፣ ጉዲዩን ለማየት የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስላልሆነ እንዱጸናልን በማለት በዜርዜር ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪ በ20/8/2014 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ በዙህ ጉዲይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የዉሳኔ ምክንያት በመለወጥ እና የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠዉ ምክንያት፣ ዉሳኔዉ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ እንዱጸናልኝ በማለት በዜርዜር ተከራክሯል። አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር በ8/9/2014 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ አመልካች ባቀረበዉ ክርክር 1ኛ ተጠሪ በሉዜ ዉል ያገኘሁትን ይዝታ ከሉዜ ዉለ ዉጭ በመቀነስ ለ2ኛ ተጠሪ በሉዜ ዉል የሰጠ በመሆኑ፣ የ1ኛ ተጠሪ ተግባር ከሕግ ዉጭ በመሆኑ በሉዜ ዉል ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ ለ2ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ ካርታ እንዱሰረዜልኝ የሚል ነዉ። ተጠሪዎች በበኩላቸዉ ደግሞ አመልካች በሉዜ ዉል የተሰጠዉን ይዝታ በዉለ በተመለከተዉ ጊዛ ዉስጥ ስላልሰራበት በሕግ አግባብ ይዝታዉ የተወሰደ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ይህ ጉዲይ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክር እያየ እያለ የአመልካች ካርታ መሰረዘ ስለተገለጸ ክስ የቀረበበት ምክንያት ቀሪ ሆኗል በማለት መዜገቡን የዘጋ ሲሆን፣ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ ክርክሩን በማየት ይህ ጉዲይ የሉዜ ዉል አፈጻጸምን የሚመለከት ስለሆነ ጉዲዩን ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት መሆኑን በማመልከት የፋዳራል ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላቸዉም በማለት መወሰኑን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል።
በመሆኑም በዙህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለበት የግራ ቀኙ ክርክር የሉዜ ዉል አፈጻጸምን የሚመለከት በመሆኑ ጉዲዩን ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት ነዉ ወይስ የፋዳራል ፍ/ቤቶች ናቸዉ? የሚለዉ ነጥብ ነዉ።
ከዙህ አንጻር የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በአመልካቾች በእነ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመሬት ልማት አስተዲደር ባለስልጣን ሁለት ሰዎች እና በተጠሪ ድንቅ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል የነበረዉን ክርክር በመመርመር በ
መስከራም 24 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ጉዲዩ የሉዜ ዉልን መሰረት አድርጎ ለአንድ ሰዉ የተሰጠ ቦታ ለላላ ሰዉ ሲሰጥ ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን ያለዉ አካል የትኛዉ ነዉ? የሚለዉን ጭብጥ በመያዜ፤ የሥር ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የቀረቡትን የአመልካቾችን መከራከሪያ ነጥቦችን በመመርመር ጉዲዩ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም በማለት መወሰኑን እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደግሞ ይህን የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማሻር ጉዲዩን የማየት ሥረ-ነገር ስልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ናቸዉ በማለት የወሰነዉን በመመርመር፣ ይህ ጉዲይ በፍ/ቤት የሚታይ ነዉ መባለ ተገቢ ቢሆንም ጉዲዩን የማየት የሥረ-ነገር ስልጣን ያላቸዉ ፍ/ቤቶች የትኞቹ ናቸዉ (የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ወይም የፋዳራል ፍ/ቤቶች)፤ የተጠሪ ክስ መሰረቱ የሉዜ ዉል ሆኖ ዉለ ተጥሷል በሚል ዲኝነት የጠየቁ በመሆኑ፤ የተጠሪ ጥያቄ የክፍለ ከተማ አስተዲደር ከሕግ ዉጭ በሉዜ የተወሰደ ቦታ ለመዉሰድ ካርታና የምስክር ወረቀት በመሰረዜ ሕገወጥ እርምጃ ፈጽሟል በማለት በሉዜ ዉል ያገኙት የንብረት መብታቸዉ (የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 (6) ይመልከቷል) በፍርድ እንዱጠበቅላቸዉ የሚጠይቅ በመሆኑ በፍ/ቤት ሉያስተናግድ የሚገባዉ እና ዉሳኔ የሚሰጥበት ጉዲይ በመሆኑ እና መታየት ያለበትም በአዱስ አበባ ከተማ ነክ ጉዲዮች ፍ/ቤቶች በመሆኑ፤ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዙህ ረገድ የደረሰበት ድምዲሜ ከአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 (1) (ሀ) እና (መ) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አንጻር ሕጋዊ ሆኖ አግኝተናል በማለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዉሳኔን በማጽናት መወሰኑን ማየት ይቻላል።
ይህ በእንዱህ እንዲለ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በአመልካች በድሬዲዋ አስተዲደር የመሬት ልማትና ማንጅመንት ቢሮ እና በተጠሪዎች በእነ አቶ ደጉ ወ/ሚካኤል ሁለት ሰዎች መካከል በነበረዉ ክርክር በ
ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በሰጠዉ አስገዲጅ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ አመልካች በሉዜ ዉል መሰረት የተሰጠኝን ይዝታ በተመለከተ የሉዜ ዉልን በማቋረጥ ካርታዉን በማምከን፣ ለ2ኛ ተጠሪ ይዝታዉን በሉዜ ዉል በመስጠት ካርታ የሰጠ በመሆኑ፤ የ1ኛ ተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ የሉዜ ዉል እንዱጸናልኝ እና ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የተደረገዉ የሉዜ ዉል እንዱሰረዜ የሚጠይቅ መሆኑን የሚያስገነዜብ በመሆኑ፤ የድሬዲዋ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33 መሰረት የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቶችን ስልጣን የሚያመለክት ቢሆንም ከዙህ የአዋጁ ደንጋጌ እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.3132 አንጻር ሲታይ 1ኛ ተጠሪ የእኔ የሉዜ ዉል እንዱጸናልኝ እና ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የተደረገዉ የሉዜ ዉል እንዱሰረዜልኝ በማለት ያቀረበዉ የዲኝነት ጥያቄ የአስተዲደር ፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ሥር የሚወድቅ ሆኖ አልተገኘም፤ የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቶች ይህን ጉዲይ ሰምተዉ ለመወሰን የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን የላቸዉም በማለት የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር መወሰኑን ያመለክታል።
በመሆኑም ከፍ ሲል ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
በሰጠዉ ዉሳኔ የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጦብኛል በዉለ ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ በማለት የሚቀርበዉ የዲኝነት ጥያቄ በአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ሥር እንደሚወድቅ የሚል ሲሆን፣ በ
በሰጠዉ ዉሳኔ ደግሞ የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጦብኛል በዉለ ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ በማለት የሚቀርበዉ የዲኝነት ጥያቄ የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን የላቸዉም በማለት መወሰኑን ያሳያል። ምንም እንኳን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር እና የድሬዲዋ አስተዲደር ራሳቸዉን የቻለ ከተሞች ቢሆኑም ሁለቱም ከተሞች በቻርተር የሚተዲደሩና ተጠሪነታቸዉ ለፋዳራል መንግስት በመሆኑ፤ የአዱስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 (1) (ሀ) እና (መ) እና የድሬዲዋ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33 (1) (ሀ) እና (መ) ተመሳሳይ ይዘትና ዓላማ ያላቸዉ ድንጋጌዎች መሆናቸዉን ማየት ይቻላል። እነዙህ የአዱስ አበባ አስተዲደር እና የድሬዲዋ አስተዲደር ቻርተር ድንጋጌዎች ተመሳሳይ ይዘትና ዓላማ ያላቸዉ ሆኖ ሳለ፣ የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋረጦብኛል መብቴ እንዱከበርልኝ በማለት የሚቀርበዉን የዲኝነት ጥያቄ በተመለከተ በአዱስ አበባ አስተዲደር በከተማዉ አስተዲደር ፍ/ቤቶች እንደሚታይ፣ እና በድሬደዋ አስተዲደር ደግሞ በከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቶች እንደማይታይና የፋዳራል ፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ሥር እንደሚወድቅ መወሰኑን ያመለክታል። እነዙህ ሁለቱ የሰበር ዉሳኔዎች እርስ በእርሳቸዉ የሚቃረኑ በመሆናቸዉ እና ተከራካሪ ወገኖችን ላልተፈለገ ክርክር የሚዲርጉና ችልቱም ወጥና ተመሳሳይ የህግ ትርጉም እንዲይሰጥ እንቅፊት የሚሆኑ በመሆናቸዉ፣ እነዙህን ዉሳኔዎች አንድ ላይ አድርጎ አንድ ወጥ የሆነ የህግ ትርጉም እንዱኖር ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ህዲር 28 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ትዕዚዜ መሰረት በ
በሆኑት መዚግብት ላይ የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጧብኛል መብቴ እንዱከበርልኝ በማለት የሚቀርበዉን የዲኝነት ጥያቄ በተመለከተ ከፍ/ቤቶች ስልጣን አንጻር ዉሳኔዎቹ መካከል ቅራኔ ወይም ግጭት መኖሩን ስለሚያመለክት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች ለሚሰየሙበት ችልት ቀርቦ እንዱታይ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዙዲንት እንዱቀርብ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 (1) መሰረት አዞል። በዙህ መሰረት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዙዲንት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 26 (2) መሰረት ጉዲዩ በሰባት ዳኞች እንዱታይ በ7/4/2015 ዓ.ም ትዕዚዜ ሰጥቶበታል። በዙህ አግባብ ይህ ጉዲይ ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት እንዱታይ ተደርጓል።
በዙህ መሰረት አመልካች ባቀረበዉ የዲኝነት ጥያቄ 1ኛ ተጠሪ የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ በመሰረዜ በዉለ ያገኘሁትን ይዝታ በመቀነስ ለ2ኛ ተጠሪ በሉዜ ዉል በመስጠት ካርታ የሰጠዉ በመሆኑ ይህ የ1ኛ ተጠሪ ድርጊት ከሕግ ዉጭ በመሆኑ ለ2ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ የይዝታ ማረጋገጫ ካርታ እንዱሰረዜልኝ በማለት መጠየቁን ያመለክታል። ስለሆነም አመልካች የሉዜ ዉልን ሉያሰርዜ ወይም ሉያቋርጥ የሚችል ምንም ዓይነት ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖር በሉዜ ዉለ ያገኘሁት ይዝታ ተቀንሶ ለ2ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ ይዝታ ከሕግ ዉጭ ስለሆነ በሉዜ ዉል ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ በማለት የጠየቀዉ ዲኝነት ከሉዜ ዉል አፈጻጸም ጋር የተያያዘ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
እንደሚታወቀዉ የከተማ ቦታን በሉዜ ስለመያዘ የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 2 (1) መሰረት ‹‹ሉዜ›› ማለት በጊዛ በተገደበ ዉል መሰረት የከተማ ቦታ የመጠቀም መብት የሚገኝበት የመሬት ይዝታ ሥሪት መሆኑን ይደነግጋል። እንዱሁም የዙህ አዋጅ አንቀጽ 16 (1) እንደሚያመለክተዉ የከተማ ቦታ በሉዜ እንዱይዜ የተፈቀደለት ሰዉ አግባብ ካለዉ አካል ጋር የሉዜ ዉል መፈራረም እንደሚኖርበት ያስገነዜባል። ከዙህ ድንጋጌ መረዲት እንደሚቻለዉ የሉዜ ዉል የከተማ ቦታን በሉዜ በመያዜ የመጠቀም መብትን የሚፈጠር ውል መሆኑን ነዉ። የከተማ ቦታን በሉዜ በመያዜ እንዱጠቀም የሉዜ ዉል ያደረገዉ ሰዉ በዉለ መሰረት ይዝታዉን የተጠቀመ እንደሆነ እስከዉለ ጊዛ ገደብ ድረስ በይዝታዉ የመጠቀም መብቱ የተረጋገጠለት መሆኑን ያመለክታል።
በልላ በኩል የመንግስት አስተዲደር መስሪያ ቤቶች በሕግ የተጣለባቸዉን ኃላፉነት ለመወጣት የአስተዲደር ዉልችን ለመዋዋል እንደሚችለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3131 ሥር ተመልክቷል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3132 ሥር እንደተመለከተዉ አንድ ዉል እንዲስተዲደር መሥሪያ ቤት ዉል ሆኖ የሚቆጠረዉ፡ ሀ) ሕግ ወይም ተዋዋዮቹ ግልጽ በሆነ ቃል የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ዉል ነዉ ያለት ሲሆን፤ ለ) ዉለ ከሕዜብ አገልግልት ሥራ ጋር የተያያዘና ለሥራዉም አፈጻጸም የተዋዋዩን የአስተዲደር መሥሪያ ቤቱን ሥራ ተካፊይነት ሳይቋረጥ የሚጠይቅ ሲሆን፤ ሐ) በዉለ ዉስጥ ለጠቅላላ ጥቅም አስቸኳይ በመሆናቸዉ ብቻና የግል ሰዎች በሚያደርጓቸዉ ዉልች ዉስጥ የማይገኙ አንድ ወይም ብዘ ዉለታዎች ያለበት ሲሆን ነዉ በማለት ይደነግጋል።
እንግዱህ የሉዜ ዉል በሕግ በግልጽ የአስተዲደር ዉል ነዉ ተብል ባልተመለከተበት እና የከተማ ቦታን በሉዜ ዉል በመያዜ የመጠቀም መብት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.3132 ድንጋጌ አንጻር ሲታይ በድንጋጌ ሥር የተመለከቱትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ባለመሆኑ የአስተዲደር ዉልች ሥር የሚወድቅ ነዉ ለማለት አይቻልም።
በልላ በኩል ከሉዜ ዉል አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ማለትም የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጧል በዉለ ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ፣ እንዱወሰንልኝ በማለት የሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41 (1) (ሀ) እና (መ)፣ በአዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33 (1) (ሀ) እና (መ) ሥር የሚወድቅ ጉዲይ መሆኑን የሚያመለክት ነገር የለም። እንዱሁም ከኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 (1)፣ 79 (1) እና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.4 ድንጋጌዎች የጣምራ ንባብ ይዘትና ዓላማ ሲታይ ሕግ በቀጥታ ወይም በግልጽ ለላላ በሕግ የዲኝነት ስልጣን ለተሰጠዉ አካል ካልሰጠ በቀር በፍርድ ሉወሰን የሚገባዉን ጉዲይ ሰምቶ ለመወሰን ስልጣን ያላቸዉ መደበኛ ፍ/ቤቶች በመሆናቸዉ፤ የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ስለተቋረጠ በዉለ ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ በማለት ከሉዜ ዉል አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የሚቀርበዉን ክስ ተቀብል ሰምቶ ለመወሰን የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች መሆናቸዉን ያስገነዜባል። በዙህ መሰረት የአዱስ አበባም ሆነ የድሬዲዋ ከተማ የአስተዲደር ፍ/ቤቶች ይህን ጉዲይ ለማየት የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን የላቸዉም። ከዙህ አንጻር ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
መስከረም 24 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ቀሪ ላደረግ የሚገባዉ እና በ
ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተፈጻሚነት ሉቀጥል የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደርም ሆነ በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ዉስጥ የሉዜ ዉል ከሕግ ዉጭ ተቋርጦብኛል በዉለ ያገኘሁት መብት እንዱከበርልኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ከሉዜ ዉል አፈጻጸም ጋር የሚያያዘትን ጉዲዮች መሰረት በማድረግ የሚቀርበዉን ክስ ሰምቶ ለመወሰን የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች ናቸዉ ብለናል።
በዙህ አግባብ አሁን የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከተዉ 1ኛ ተጠሪ የሉዜ ዉልን ለማቋረጥ ወይም ለመሰረዜ የሚያበቃ በቂ ምክንያት ሳይኖር በሉዜ ያገኘሁትን ይዝታ በመቀነስ ለ2ኛ ተጠሪ በሉዜ ዉል የሰጠና ካርታ እንዱሰጠዉ ያደረገዉ ከሕግ ዉጭ በመሆኑ ለ2ኛ ተጠሪ የተሰጠዉ ካርታ እንዱሰረዜልኝ በማለት ያቀረበዉን ክስ፣ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በሕግ አግባብ አጣርቶ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ መስጠት ሲገባዉ በክርክር ሂደት ላይ እያለ የአመልካች የይዝታ ማረጋገጫ ካርታ መሰረዘ ስለታወቀ አመልካች ክስ ያቀረበበት ጉዲይ የክስ ምክንያት ተቋርጧል በማለት መዜገቡን መዜጋቱ የህግ መሰረት የለዉም። እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ባቀረበዉ ክስ የጠቀሰዉን የዲኝነት ጥያቄ ለማየት፣ የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች መሆናቸዉን ተገንዜቦ የግራ ቀኙን ክርክር አጣርቶ መወሰን ሲገባዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት የዲኝነት ስልጣን የላቸዉም፣ ጉዲዩን ለማየት የሥረነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸዉ የከተማዉ አስተዲደር ፍ/ቤቶች ናቸዉ በማለት ያሳለፈዉ ዉሳኔ የህግ ድጋፍ የላለዉ ነዉ ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የግራ ቀኛቸዉን ክርክር በሕግ አግባብ መርምሮ መወሰን ሲገባቸዉ የአመልካችን የክስ አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ ያሳለፈት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.77574 በ6/7/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዚዜ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.17839 በ14/3/2014 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተዘጋዉን መዜገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ አግባብ የግራ ቀኙን ክርክር በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዙህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ የሰበር ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዜገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዜገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.