የፍደራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን በሆኑ ጉዲዮች ላይ የክልል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች፣ በቅደም ተከተል የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን በዉክልና የማየት ስልጣን ያላቸው ሲሆን ሆኖም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትንም ሆነ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በሀገሪቱ በሙለ ወይም በከፉል ማደራጀት እንደሚቻል በተደነገገው መሰረት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ከተደራጀ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዉክልና የማየት ስልጣን የላለዉ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(2 እና 4)፣ አንቀጽ 78 (2) እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በተወሰኑ ክልልች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ ቁጥር 322/95 አንቀጽ 2 የፍትሐብሕር ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቅድሚያ እንዱያከናዉን ከሚጠበቁት ተግባራት ዉስጥ አንደ የቀረበው ክስ ህጋዊ ብቃት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን የማረጋገጥ ተግባር በመሆኑ ይህ ሲረጋግጥ መሰረት የሚደርገዉም በከሳሽ የቀረበዉን ክስ መሰረታዊ ይዘት እንዱሁም የተከራካሪ ወገኖችን ማንነት እና አድራሻ መሰረት በማድረግ ሲሆን፣ የቀረበዉ ብዙነህ ቢላ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ሲ.አር.ሲ.ሲ ጋምቤላ አቦቮ ፐኚድ መንገድ ስራ ፔሮጀክት ህጋዊ ብቃቱን ያሟላ መሆን ያለመሆኑን በመወሰን ረገድ ግምት ዉስጥ መግባት ካለባቸዉ ሁኔታዎች ዉስጥም አንደ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የስረ-ነገር ስልጣን ያለዉ መሆን ያለመሆኑ ስለሆነ በስልጣን ስር ሉወድቅ የሚችል ካልሆነ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 231 (1/ለ) እና አንቀጽ 9
No summary available.
ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- ብዙነህ ቢላ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ተጠሪ- ሲ.አር.ሲ.ሲ ጋምቤላ አቦቮ ፐኚድ መንገድ ስራ ፔሮጀክት **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረበው ክስ አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገው ውል ለአስፊልት ስራ የሚውል ጠጠር በጥራትና በብዛት በወር አስር ሺ ሜትር ኩብ በጠቅላላ መቶ ሀምሳ ሺ አምርቶ እንዱያቀርብ ግዳታ ቢገባም ያመረተው ግን ጥራቱን ያልጠበቀ አስራ አምስት ሺ ሜትር ኩብ ብቻ ነው፤ አመልካች በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ በሚፈለገው ጥራትና መጠን ጠጠሩን ባለማቅረቡ በአማካሪ ድርጅቱ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው ምርቱን እንደማሻሻል ስራውን አቋርጦ ሓዶል፤ በዚህም ምክንያት በተጠሪ ላይ የብር 5,700,21000.00 ኪሳራ የደረሰብኝ በመሆኑ አመልካች ይህንን ገንዘብ ለተጠሪ ይክፈል ተብል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቆ ተከራክሯል።
ተጠሪ በሰጠው መልስ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም፤ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ያለው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው የሚለ መቃወሚያዎችን ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይ ደግሞ በገባነው የውል ግዳታ መሰረት ማሽን እና ተሸከርካሪ ወደ ሳይት በማስገባት ስራ የጀመርን ሲሆን ያመረትነው ጠጠር የጥራት ችግር እንዲለበት አልተገለፀልንም፤ ስራውንም ያቆምነው በተጠሪ ጥፊት በመሆኑ ልንጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች ያቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገ ሲሆን ፍሬ ነገሩን በሚመለከት ደግሞ አመልካች በውለ ላይ የገባውን ግዳታ ያላከበረ በመሆኑ ውለ እንዱሰረዝ፣ አመልካች በተጠሪ ሳይት ላይ የተከለውን ክሬሸር እንዱያነሳ እና ስራ በመዘግየቱ ምክንያት በተጠሪ ላይ የደረሰው ኪሳራ በባለሞያ ተሰልቶ ኪሳራ ይክፈል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው አመልካች ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ የተከራከሩበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል አመልካች ተጠሪ በክሱ ላይ እንዱከፈለው የጠየቀውን ገንዘብ እንዱከፍለው፣ ተጠሪ ደግሞ አመልካች ያመረተው 10,000 ሜትር ኪዩብ ጠጠር እንዱረከብና ሂሳቡን እንዱከፍል ሲል ወስኗል። አመልካች በዚህም ውሳኔ ባለመስማማት የሰበር አቤቱታው ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 07/07/2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው 04 ገጽ የሰበር አቤቱታ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የስረ-ነገር ስልጣን እንደላለው ጠቅሼ ያቀረብኩት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ-መንግስት እና የፍደራል ፍርድ ቤቶችን አዋጅ መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ፣ እንዱሁም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ደረሰ የተባለውን ኪሳራ በሚመለከት በባለሞያ ተጣርቶ ይከፈል ያለውን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የባለሞያ አስተያየት ሳይሰማ ዲኝነት የተጠየቀበትን ገንዘብ እንድንከፍል መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ተጠሪ የጠየቀው ገንዘብ በባለሞያ ተጣርቶ ሳይቀርብ አመልካች እንዱከፍል የወሰነበትን አግባብ ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት በቀን 30/07/2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካች የሰበር አቤቱታውን በሁለት ወራት ውስጥ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያላቀረበ በመሆኑ አቤቱታው በይርጋ ይታገዲል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል። ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ደግሞ CRCC 21 ጋምቤላአቦቦ-ፐኝድ መንገድ ስራ ፔሮጀክት አዱስ አበባ ካለው CRCC 21 የተለየና የተጠሪ አድራሻ በጋምቤላ ክልል ስለሆነ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለው፤ አመልካች በውለ ላይ የተቀመጠውን ግዳታ ባለመወጣቱ በተጠሪ ላይ ለደረሰው ኪሳራ በውለ መሰረት እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ከሚባል በስተቀር የሚነቀፍ ባለመሆኑ ሉፀና ይገባዋል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም አመልካች የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ሰበር ሰሚዉ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት አያስቀርብም የሚል ትዕዛዝ መስጠቱ ከአመልካች አቤቱታ ጋር ተያይዞ ከቀረበዉ የትዔዛዙ ግልባጭ መገንዘብ ይቻላል። ይህ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአቤቱታዉ የማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ የቀረበ ነዉ በሚል አቤቱታዉን ዉድቅ እንዲደረገ በመጥቀስ ተጠሪ በዚህ ችልት የሚያቀርበዉ ክርክር የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ትክክለኛ ይዘት ያላገናዘበ በመሆኑ ይህ ችልት አልተቀበለዉም።
በመቀጠል መታየት ያለበት ነጥብ የጋምቤላ ክልል የአኙዋ ብሓረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህን ጉዲይ ተቀብል የማየት የስረ-ነገር ስልጣን ያለዉ መሆን ያለመሆኑ ነዉ። አመልካች ነዋሪነቱ አዱስ አበባ ከመሆኑም በላይ ተጠሪም በቻይና አገር የተቋቋመ ድንበር ተሻጋሪ የኮንስትራክሽን ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ነዉ። ይህ መሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5(2/ እና 4) መሰረት ጉዲዩን የማየት ስልጣኑን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ያደርገዋል።
የኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(2 እና 4) የክልል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች፣ በቅደም ተከተል፣ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን በዉክልና የማየት ስልጣን እንዲላቸዉ የሚደነግግ ሲሆን ይሄዉ ህገ መንግስት በአንቀጽ 78 (2) ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትንም ሆነ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶችን በሀገሪቱ በሙለ ወይም በከፉል ማደራጀት እንደሚችል ይደነግጋል።
በዚህም መሰረት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በተወሰኑ ክልልች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ ቁጥር 322/95 በተወሰኑ ክልልች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱደራጁ ለማድረግ የወጣ አዋጅ ሲሆን በዚህ አዋጅ መሰረት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተደራጀባቸዉ ክልልች ዉስጥ አንደ የጋምቤላ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 2 ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
ይህም የሚያሳየዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣንን የጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዉክልና የማየት ስልጣን የላለዉ መሆኑን ነዉ።
በልላ በኩል፣ ምንም እንኳ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣንን በዉክልና ለማየት ያለዉ ስልጣን ያልተነሳ ቢሆንም፣ ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነዉ ጉዲይ ከገንዘብ መጠን አንፃር ሲታይ ከብር 500,000.00 በላይ በመሆኑ ክርክሩ በተጀመረበት ወቅት በስራ ላይ በነበረዉ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 14 መሰረት ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣን በላይ በመሆኑ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በዉክልና ለማየት የሚያስችል ስልጣን የለዉም።
እንደሚታወቀዉ አንድ የፍትሐብሕር ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቅድሚያ እንዱያከናዉን ከሚጠበቁበት ተግባራት ዉስጥ አንደ የቀረበለት ክስ ህጋዊ ብቃት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን የማረጋገጥ ተግባር ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 231 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
ፍርድ ቤቱ ይህን ሲያረጋግጥ መሰረት የሚደርገዉም በከሳሽ የቀረበዉን ክስ መሰረታዊ ይዘት እንዱሁም የተከራካሪ ወገኖችን ማንነት እና አድራሻ መሰረት በማድረግ ሲሆን፣ የቀረበዉ ክስ ህጋዊ ብቃቱን ያሟላ መሆን ያለመሆኑን በመወሰን ረገድ ግምት ዉስጥ መግባት ካለባቸዉ ሁኔታዎች ዉስጥም አንደ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የስረ-ነገር ስልጣን ያለዉ መሆን ያለመሆኑ ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 231 (1/ለ) ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ያስገነዝባል። የህጉ አንቀጽ 9 ድንጋጌም ይህንኑ የሚስገነዝብ ነዉ። ፍርድ ቤቶች ክርክሮችን በዘፈቀደ ሳይሆን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ የተዘረጉትን ደንቦች እና መርሆችን መሰረት በማድረግ ላሆን እንደሚገባ መገንዘቡም ተገቢ ነዉ።
የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ ከተከራካሪ ወገኖች ማንነት አንፃር ጉዲዩ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቅ ሆኖ ዲኝነት ከተጠየቀበት የገንዘብ መጠን አንፃርም ሲታይ ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣን በላይ በመሆኑ ክርክሩን ተቀብል የማየት ስልጣኑ በማንኛዉም ሁኔታ በክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር ሉወድቅ የሚችልበት ሁኔታ የለም። በመሆኑም ከአኙዋክ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ይህን ባለማድረግ ክርክሩን ተቀብል ዉሳኔ መስጠቱም ሆነ በክልለ በየደረጃዉ ያለ ፍርድ ቤቶችም ይህን ማረም ሲገባቸዉ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ያለ ስልጣኑ የሰጠዉን ዉሳኔ መሰረት በማድረግ በዋናዉ ጉዲይ ላይ አከራክረዉ በየበኩላቸዉ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የአኙሃ ብሓረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 20/02/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት፣ የጋምቤላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ//2013 በቀን 02/04/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ዉሳኔ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ//2013 በቀን 22/06/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ ተሽረዋል።
የአኙሃ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ስልጣን የለዉም።
ተጠሪ መብቱን ለማስከበር ስልጣን ላለዉ ፍርድ ቤት የሚያቀርበዉን ክስ ይህ ዉሳኔ አይከለክልም።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የሰበር አጣሪ ችልት በቀን 09/07/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።