የባልና ሚስት የጋራ ሀብት በዓይነት እንዱከፊፈል ማድረግ ቅድሚያ ሉሰጠዉ የሚገባዉ የክፍፍል ሥርዓት መሆኑን እና በግራ ቀኝ ስምምነት ለአንደኛዉ ተጋቢ ንብረቱ እንዱሰጥ የማይደረግ ከሆነ ንብረቱ በሃራጅ እንዱሸጥ የሚደረገዉ ንብረቱን በዓይነት ማካፈል እንደማይቻል ሲረጋገጥ እና እያንዲንደ ተጋቢ ከጋራ ሀብቱ የተወሰነ ንብረት እንዱደርሰዉ ማድረግ ቅድሚያ ሉሰጠዉ የሚገባዉ የክፍፍል ሥርዓት ሲሆን በዚህ መልኩ እኩል ማከፊፈል የማይቻል እንደሆነ ልዩነቱን በገንዘብ እንዱካካስ በማድረግ ክፍፍለን መፈጸም የሚገባ ስለመሆኑ የአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀጽ 102 (1 እና 2)
No summary available.
ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- አቶ ስንታየሁ አባተ ተጠሪ- ወ/ሮ ታድፊለች ገላዬ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ የተሰጠ ፍርድ የሚፈጸምበትን ሁኔታ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረዉ በባህርዲር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። የጉዲዩም አመጣጥ በባህር ዲር ከተማ ግሽ አባይ ክ/ከተማ በ500 ካ/ሜትር ቦታ ለይ የሚገኘዉ ቤት የጋራ ነዉ በማለት ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 03-21833 ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት የድርሻቸው እንዱሰጣቸው ግራ ቀኝ ያቀረቡትን የአፈፃፀም አቤቱታ መነሻ ያደረገ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የመኖሪያ ቤቱ በአይነት መከፈል የማይችል መሆኑ በባለሞያ ተረጋግጧል በማለት በጨረታ ተሽጦ ገንዘቡን ግራ ቀኙ ይካፈለ በማለት ቤቱ በኃራጅ እንዱሸጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ ትዕዛዝ ቅር የተሰኙት አመልካች ቤቱ ያረፈው በ500 ካ.ሜ ይዞታ ላይ በመሆኑ ክፍለ ከተማው ካርታ ከተሰራለት ስመ-ንብረት ማዞር እንደሚቻል ያረጋገጠልን ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጊዜ ሰጥቶን ካርታ ካሰራን በኋላ እኩል እንዱከፈል ማድረግ ሲገባው ቤቱ በኃራጅ እንዱሸጥ ትዕዛዝ መስጠቱ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት ለባህር ዲር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኛቸውን ቢያቀርቡም ተቀባይት አላገኘም። አመልካች አሁንም በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ይህም አቤቱታ ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 18/06/2013 ዓ.ም በተፃፈ 03 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙላቸው የጠየቁ ሲሆን የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ የክርክሩ መነሻ የሆነው መኖሪያ ቤት በባህርዲር ከተማ ግሽ አባይ ክ/ከተማ ቀበላ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የክፍለ ከተማው ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽ አገልግልት ጽ/ቤት ካርታ ለመስጠት ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ እያለ የኃራጅ ሽያጪ ሂደት ቅደም ተከተል ሳይጠበቅ፣ ግምቱን እየተቃወምኩ፣ ካርታ ከተሰራለት ለሁለት መከፈል እንደሚችል ተረጋግጦ እና ግራ ቀኛችን ተስማምተን በገበያ ዋጋ ለመሸጥ እድል ሳይሰጠን በኃራጅ ይሸጥ ተብል ትዕዛዝ መሰጠቱ መሰረታዊ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ አከራካሪው ይዞታና ቤት የግራ ቀኙ በሆነበትና በፍርደም ላይ ከተቻለ በአይነት እንዱካፈለ ተብል እያለ የስር ፍርድ ቤት በቀጥታ ወደ ጨረታ ሂደት የገባበት አግባብ መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ በቀን 20/07/2013 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው የሰበር ቅሬታ የቀረበበት ጉዲይ ከአንድ ዓመት በፉት በባህር ዲር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 03- 21833 ውሳኔ የተሰጠበትና ይዘቱም ቤቱ በጨረታ እንዱሸጥ የታዘዘበት ሲሆን አመልካች ይህንን ውሳኔ ሳያሽሩ ተጠሪ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት እንዱፈፀምላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የወረዲ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ መነሻ በማድረግ አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም፤ የስር ፍርድ ቤቶችም ቤቱ በኃራጅ እንዱሸጥ ትዕዛዝ የሰጡት በዓይነት መከፈል እንደማይችል አረጋግጠው ስለሆነ የሰጡት ትዕዛዝ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም መዝገቡን ለማስቀረብ የተያዘዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም የግራ ቀኝ የጋራ ንብረት የሆነዉ እና ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነዉ ቤት በባህር ዲር ከተማ በግሸን ክ/ከተማ በ500 ካ/ሜትር ላይ የሚገኝ ቤት ስለመሆኑ አላከራከረም። ይህ ቤትና ይዞታ ካርታ ከተሰራለት በኋላ በዓይነት መካፈል እንደሚቻል ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለ ሲሆን አፈፃፀሙን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የባህር ዲር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ቤቱ በሃራጅ ሉሸጥ ይገባል በሚል ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነዉን ትዕዛዝ የሰጠዉ ቀደም ሲል በጨረታ ይሸጥ በተባለዉ ላይ ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ መጽናቱንና ወደ ኃላ ተመልሶ ካርታ በቅድሚያ ካርታ ይሰራ የሚል ትዕዛዝ መስጠት የማይችል መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። በአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር 79/95 ከአንቀጽ 101-103 ባለት ድንጋጌዎቹ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት በዓይነት እንዱከፊፈል ማድረግ ቅድሚያ ሉሰጠዉ የሚገባዉ የክፍፍል ሥርዓት መሆኑን እና በግራ ቀኝ ስምምነት ለአንደኛዉ ተጋቢ ንብረቱ እንዱሰጥ የማይደረግ ከሆነ ንብረቱ በሃራጅ እንዱሸጥ የሚደረገዉ ንብረቱን በዓይነት ማካፈል እንደማይቻል ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ከድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበዉ ነዉ። እያንዲንደ ተጋቢ ከጋራ ሀብቱ የተወሰነ ንብረት እንዱደርሰዉ ማድረግ ቅድሚያ ሉሰጠዉ የሚገባዉ የክፍፍል ሥርዓት ሲሆን በዚህ መልኩ እኩል ማከፊፈል የማይቻል የሆነ እንደሆነ ልዩነቱ በገንዘብ እንዱካካስ በማድረግ ክፍፍለን መፈጸም እንደሚገባ በህጉ አንቀጽ 102 (1 እና 2) ላይ ከተመለከቱት ግልጽ ድንጋጌዎች የምንገነዘበዉ ነዉ። ህጉ የአከፊፈል ሥርዓቱ በዚህ ቅደም ተከተል እንዱከናወን ሲደነግግ መሰረት ያደረገዉ አንድም ንብረቱ በተቻለ መጠን ከተጋቢዎች እጅ እንዲይወጣ ጥበቃ ለማድረግ ሁለትም የክፍፍለን ፍትሐዊነት በማረጋገጥ ባልና ሚስት በጋራ ንብረቶቻቸዉ ላይ ያላቸዉን የእኩልነት መብት እዉን ለማድረግ እንደሆነ ይታመናል። በመሆኑም ከባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ጋር በተያያዘ የሚነሳን ክርክር በተመለከተ የሚሰጥ ዉሳኔም ይህን ሁለ ከግምት ዉስጥ ያስገባ ላሆን ይገባል።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት ለአፈፃፀሙ መነሻ የሆነዉን ቤትና ይዞታ በተመለከተ በዓይነት ማካፈል አይቻልም የተባለዉ ከክፍፍለ በፉት ካርታ ሉሰራበት ይገባል በሚል ምክንያት ነዉ።
ከዚህ ዉጪ ቤቱን ለሁለት እኩል ማካፈል እንደማይቻል ላላ የተለየ ምክንያት አልቀረበም። ክፍፍለ በዓይነት ከተደረገ በኋላ ግራ ቀኝ በየበኩላቸዉ በደረሳቸዉ የይዞታ መጠን ልክ ካርታ እንዲይሰጥ የሚያደርግ ህጋዊ ምክንያት የለም። ስለሆነም ካርታ የሚሰጥበትን ጊዜን መጠበቅ ሳያስፈልግ ይዞታዉን ከላዩ ላይ ካለዉ ንብረት ጋር በዓይነት ማካፈል ይቻላል። በመሆኑም ካርታ በይዞታዉ ላይ አለመሰራቱ ወይም ዘግይቶ የሚሰራለት መሆኑ ግራ ቀኝ የጋራቸዉ መሆኑ ተረጋግጦ ፍርድ ያረፈበት እና በ500 ካ/ሜትር ይዞታ ላይ ያረፈ ቤት ግራ ቀኝ በዓይነት ለሁለት እንዲይካፈለ ምክንያት ላሆን አይችልም።
ይህ ሆኖ እያለ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ቤቱ በሃራጅ እንዱሸጥ የሰጠዉ ትዕዛዝ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል የሚፈጸምበትን ሥርዓት እና ቅደም ተከተል አስመልክቶ በክልለ የቤተሰብ ህግ ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ላላዉ የተጠሪ ክርክር ቤቱ በሃራጅ እንዱሸጥ አስቀድሞ በወረዲዉ ፍርድ ቤት የተሰጠዉ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለፀና በድጋሚ የቀረበ ነዉ የሚል ነዉ። ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ትዔዛዙን በመቃወም የቀረበለትን ይግባኝ ዉድቅ ያደረገዉ ይህንኑ ምክንያት በመጥቀስ ስለመሆኑ መዝገቡ ያሳያል።
በመሰረቱ አፈፃፀም በፍርድ ቤት ወይም በህግ የዲኝነት ስልጣን በተሰጠዉ አካል የሚሰጥ ፍርድ ወደ ተግባር የሚቀየርበት ሥርዓት በመሆኑ ፍርድ እንዱያስፈጽም አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት እንደ ፍርደ፣ ማለትም በፍርደ ላይ በተመለከተዉ ላይ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ፣ የማስፈጸም ኃላፉነት አለበት። በፍርድ ቤት የሚሰጥ ዲኝነት ያላግባብ የተወሰደ ንብረት ወይም ሀብት እንዱመለስ ወይም ገንዘብ እንዱከፈል ላሆን ይችላል። በዚህ መልኩ በሚሰጥ ዉሳኔ የፍርድ ባለመብት ተጠቃሚ ላሆን የሚችለዉ በተሰጠ ፍርድ መሰረት የተፈጸመለት እንደሆነ ነዉ። እያንዲንደ ጉዲይ የሚፈጀዉ ጊዜ እንደ የጉዲዩ ዓይነትና ባህርይ ሉለያይ የሚችል ቢሆንም፣ ክስ ከቀረበበት ጀምሮ እስከ ዉሳኔ ድረስ ያለዉ ሂደት የተወሰነ ጊዜ መዉሰደ አይቀሬ ነዉ። በዚህም ሂደት የፍርድ ቤት ብልም የተከራካሪ ወገኖች ጊዜይባክናል፤ ወጪና ድካም ይኖራል። ስለሆነም ፍርድን እንደ ፍርደ ማስፈጸም ይህን ሁለ ሂደት በማለፍ የተሰጠ ፍርድ ፍሬ አልባ እንዲይሆን የማድረግ ዉጤት ሉያስከትል የሚችል ከመሆኑም በላይ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ፍርድ ተፈፃሚነቱ ተገማች እንዱሆን ያስችላል። የፍት/ብ/ሥነ ሥርዓት ህጋችን ሰባተኛ መጽሐፍ ከአንቀጽ 371 ጀምሮ ባለት ድንጋጌዎቹ የፍርድ አፈፃፀም የሚመራበትን ሥነ-ሥርዓት ይደነግጋል። የፍርድ አፈፃፀም የቀረበለት ፍርድ ቤትም በዚህ የመጽሐፈ ክፍል እንዱሁም ስለአፈፃፀም አስመልክቶ በልላ ህግ የተመለከተም ካለ በዚህ መልኩ የተዘረጋዉን ስርዓት በመከተል ድንጋጌዎቹን እንደየአግባብነታቸዉ ተግባራዊ በማድረግ አፈፃፀሙን በመምራት እንደ ፍርደ የማስፈጸም ግዳታ አለበት። የፍርድ አፈፃፀም ዓላማ ፍርድ ወደ ተግባር እንዱለወጥ ማድረግ በመሆኑ አፈፃፀሙን የያዘ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ክርክርን አስመልክቶ የተቀረጹትን የፍት/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉን ድንጋጌዎች መከተል ሳያስፈልገዉ ከአፈጻጸም ጋር ተያይዞ የተዘረጋዉን ሥርዓት መሰረት በማድረግ አፈፃፀሙን የመምራት ኃላፉነት አለበት። የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ ከአንቀጽ 394-403 ባለት ድንጋጌዎቹ ስለ አፈፃፀም ሥርዓት (Modes of Execution) የሚደነግግ ሲሆን፣ እነዚህም ድንጋጌዎች በፍርደ የተሰጠዉን ዲኝነት ዓይነት መሰረት በማድረግ የሚፈጸሙ ስለመሆናቸዉ ከየድንጋጌዎቹ ይዘት የምንገነዘበዉ ነዉ። በመሆኑም በተያዘዉ ጉዲይ ላይ ለአፈፃፀሙ ምክንያት የሆነዉ የባልና ሚስት ንብረትን አስመልክቶ የተሰጠ ዉሳኔ በመሆኑ በፍርደ መሰረት ተፈጽሟል ለማለት የሚቻለዉ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል አስመልክቶ በክልለ የቤተሰብ ህግ ላይ በተመለከተዉ አግባብ ቅደም ተከተለን ጠብቆ ክፍፍለ የተደረገ እንደሆነ ነዉ። አፈፃፀሙ ይህን ተከትል የተደረገ አለመሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ቀደም ሲል በጉዲዩ ላይ ይግባኝ መቅረቡ ፍርድ ቤቱ አፈፃፀሙ ፍርደን እና ህጉን የተከተለ መሆን ያለመሆኑን አይቶ በህጉ አግባብ አፈፃፀሙን መርቶ ፍርደን እንዲያስፈጽም ምክንያት አይሆንም። በመሆኑም ይህን አስመልክቶ ተጠሪ ያቀረበዉ ክርክር የክርክሩን መሰረታዊ ባህርይ ከግምት ዉስጥ ያላስገባ በመሆኑ ይህ ችልት አልተቀበለዉም።
በዚህ ሁለ ምክንያት ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የባህር ዲር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 09/03/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ብይን፣ የባህር ዲርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/5 በቀን 23/04/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ፍርድ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 09/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ ተሽረዋል።
የባህር ዲር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤትና ይዞታ ለግራ ቀኝ እኩል እንዱካፈለ በማድረግ እንዱያስፈጽም ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የሰበር አጣሪ ችልት በቀን 26/06/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.