የተጋቢዎች ስምምነት ሳይኖር የጋራ ንብረት የሆነ ቤት ላይ የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ስልጣን ባለው ሰነድች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት ባልተመዘገበበት ሁኔታ በውለ ላይ ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ የተደረገውን የሽያጭ ውል አውቆ መቃወሚያ ሉያቀርብ የሚችልበት አግባብ የላለ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁጥር 1723 እና 2878 በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 69 መሰረት ከባልና ሚስት ከጋራ ስምምነት ውጪ የተደረገ ውል ስለሚያስከትለው ውጤት በማንኛውም ሁኔታ ውለ ከተደረገበት ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ የውል ይፍረስልኝ ክስ መቅረብ አለበት የሚለው ደንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው ውለ ቢመዘገብ ወይም ባይመዘገብም እንኳን በልላ አግባብ ስለውለ መደረግ በሚያውቅ ተጋቢ ላይ ሲሆን የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው የውለ መደረግ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ
No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ አያልነህ ገ/ማርያም ጠ. መንግስተአብ ይልማ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ክብነሽ ጎሹ ጠ. ዲንኤል ብርዬ - ቀረቡ 2ኛ. ወ/ሮ ሮዲ ሁሴን - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስ የቀረበ ክስን መሰረት ያደረገ ሲሆን ጉዲዩ በተመጀረበት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች 1ኛ ተከሳሽ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
1ኛ ተጠሪ ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዲ 12 የሚገኝ ስፊቱ 700 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት ከአመልካች ጋር አብረን ስንኖር በጋራ ያፈራን ሲሆን በመካከላችን በተፈጠረ አለመግባባት በ2004 ዓ.ም ተለያይተናል። ይህ የጋራ ንብረት ተሽጦ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ እንድንከፊፈል በዚሁ ፍ/ቤት በመ/ ክስ መስርቼ ክርክር ላይ እያለን 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ሰኔ 5 ቀን 2003 ዓ.ም በተደረገ ያልጸደቀ የሽያጭ ውል በብር 400,000 ከ1ኛ ተጠሪ መግዛታቸውን በመግለፅ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብ በመሆን ህዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም ካቀረቡት አቤቱታ ቤቱ መሸጡን ያወቅኩ ስለሆነ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ 1ኛ ተጠሪ የሽያጭ ውለ ይፍረስልኝ የሚል ክሳቸውን ያቀረቡት ውለ ከተደረገ ከ3 ዓመት 11 ወር በኋላ ስለሆነ ክሱ በይርጋ ይታገዲል፤ ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በተደረገ የንብረት ክፍፍል ስምምነት 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ ያላቸው የባለቤትነት መብት ቀሪ ስለሆነ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም የላቸውም፤ በዚህ ስምምነት ቤቱ ለአመልካች የደረሰኝ እና ጉዲዩ በሽምግልና ያለቀ ስለሆነ ክሱ ተገቢነት የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል። በአማራጭ ባቀረቡት መልስ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ እንደ ባልና ሚስት አብረን ስንኖር የተጠቀሰውን ንብረት በጋራ ያፈራን ቢሆንም ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም የንብረት ክፍፍል አድርገን ግንኙነታችን በመቋረጡ እና በየግል የያዝነውን ንብረት ለ3ኛ ወገን ያስተላለፍኩ ስለሆነ የሽያጭ ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪ በኩላቸው አመልካች ካቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪነትም ግራ ቀኝ በመ/ ላይ ክርክር እያደረግን ስለሆነ እና በሁለቱ መዝገቦች ላይ የሚያዘው ጭብጥ ተመሳሳይ ስለሆነ ክሱ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244(2)(ሐ) መሰረት ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። በአማራጭ ባቀረቡት መከራከሪያ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ መስማማት ባለመቻላቸው ሰኔ 12 ቀን 2002 ባደረጉት የመለያየት ውል ቤቱን አመልካች እንዱወስደ ተስማምተዋል። በዚህ መነሻነት 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ሰኔ 5 ቀን 2003 ዓ.ም በብር 400,000 ገዝቼ ተጨማሪ ግንባታ ያከናወንኩበት ስለሆነ ወደ ነበረበት ሉመለስ አይችልም። ውለም በአዋዋይ ፉት ያልተፈፀመው አመልካች እና ተጠሪ በ1993 ዓ.ም ቤቱን ሲገዙ ባልፀደቀ ውል ስለሆነ ነው በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ በመቃወሚያው ላይ በሰጠው ብይን በመ/ 1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት እንዱካፈለ እንዱወስንላቸው ሲሆን በተያዘው ጉዲይ የተጠየቀው ዲኝነት የሽያጭ ውል ይፍረስልኝ የሚል የተለያየ ጭብጥ ስለሆነ በፍ/ሥ/ስ/ሕ/ቁጥር 244(2)(ሐ) መሰረት የቀረበው መቃወሚያ ተገቢነት የለውም።
ውለን ለማፍረስ የሚያስችል የክስ ምክንያት አለ ወይስ የለም የሚለውም በፍሬ ነገር ክርክር የሚጣራ ነው። 1ኛ ተጠሪ የውለን መኖር ያወኩት ህዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም ነው በማለት ያቀረቡትን መከራከሪያ አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ስላልተቃወሙ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ውለ እንዱፈርስ ዲኝነት እስከተጠየቀበት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ያለው ግዜ 6 ወር ያልሞላው በመሆኑ በተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 69(2) መሰረት ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት መቃወሚያውን አልፍታል። በፍሬ ጉዲይ ላይ በሰጠው ውሳኔ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም በስምምነት ክፍፍል ስለማድረጋቸው የቀረበው ውልና በዚህ ውል መሰረት ቤቱን በሽያጭ ስለማስተላለፈቸው አመልካች ያቀረቡት ውል በሀሰት የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑ በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በወ/መ/ ተረጋግጦ አመልካች በወንጀል ተቀጥቷል። ይህ ውሳኔም በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በይ/መ/ ጸንቷል። በመሆኑም በክፍፍል በተገኘ ንብረት ላይ የተደረገ ሽያጭ ነው በማለት የቀረበው መከራከሪያ ተቀባይት የለውም። 2ኛ ተጠሪ የመጀመሪያው ውል ያልጸደቀ መሆኑን ጠቅሰው የሚከራከሩ ቢሆንም የውለ መፅደቅ ክርክር ያልተነሳበት እና በነበረ ውል ግንኙነት የተገኘው መብት አሁን ላይ ክርክር የተነሳበትና ያልፀደ ስለሆነ እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ በውለ ፈቃዲቸውን ያልሰጡ እና በሀሰት የተዘጋጀ ሰነድን መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ስለሆነ ውለ ሉፈርስ ይገባል። 2ኛ ተጠሪ በቦታው ላይ ላደረጉት ተጨማሪ ግንባታ 1ኛ ተጠሪን ከሰው ከማስከፈል በስተቀር ወደ ነበርንበት ልንመለስ አይገባም በማለት የቀረበው መከራከሪያ ተገቢነት የለውም በማለት ወስኗል።
አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኛቸውን ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዟል።
አመልካች የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡት ይህን የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ነው። የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ ለክርክሩ መነሻ የሆነው የቤት ሽያጭ ውል የተፈፀመው ሰኔ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ውለ እንዱፈርስ በፍ/ቤት ክስ ያቀረቡት ሐምል 17 ቀን 2007 ዓ.ም በመሆኑ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 69(2) መሰረት አንደኛው ተጋቢ ውለ መደረጉን ካወቀ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ክሱን ማቅረብ ያለበት እና በማንኛውም ሁኔታ ከ2 ዓመት በኋላ ውለ እንዱፈርስ መጠየቅ የማይችል ስለመሆኑ የተቀመጠውን ፍፁም ይርጋ ያለአግባብ በመተርጎም 1ኛ ተጠሪ ውለ መኖሩን ያወቁት ህዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም በመሆኑ የ6 ወር ጊዜው አላለፈም በማለት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። 1ኛ ተጠሪ ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም በተደረገው የንብረት ክፍፍል ስምምነት ላይ ያለውን ፊርማ በመካዲቸው ፍ/ቤቱ ፊርማው እንዱመረመር ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ መዝገቡ የተዘጋ ቢሆንም እንደገና እንዱንቀሳቀስ ሲደረግ ፊርማው በፍረንሲክ እንዱመረመር አለመደረጉ ወይም ትዔዛዙ ቀሪ ስለመደረጉና ቀሪ የተደረገበት ምክንያት ሳይገለፅ መታለፈ አግባብ አይደለም። ውለ እንዱፈርስ ሲወስንም ተዋዋዮች ወደ ነበሩበት እንዱመለሱ የሚያስችል ምክንያት አለ ወይስ የለም፤ በውለ መፍረስ አንደኛው ወገን የሚበለፅግ እና ላላው ወገን የሚጎዲ መሆኑን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ ሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚል ነው።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ አመልካች ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ላታይ የሚገባው ሚስት የንብረቱን መሸጥ ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ ነው? ወይስ ውለ ከተደረገበት ሰኔ 5 ቀን 2003 ዓ.ም?
ጀምሮ የሚለውን ከቤተሰብ ሕጉ ድንጋጌ አንፃር ለመመርምር ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች መልሳቸውን እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
2ኛ ተጠሪ መጥሪያው ደርሷቸው ስላልቀረቡ መልስ የማቅረብ መብታቸው የታለፈ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልሳቸውን አቅርበዋል። የመልሱ ይዘት ባጭሩ 2ኛ ተጠሪ እና አመልካች አባት እና ልጅ ሲሆኑ አመልካች ክፍፍል ያልተደረገበትን ሰነድ አልባ ቤት ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የንብረት ክፍፍል አድርጌበታለው በማለት በሀሰት ባዘጋጀው የክፍፍል ስምምነት መነሻነት የተደረገውን የመንደር የሽያጭ ውል መኖሩን ካወኩበት ሕዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በቤተሰብ ሕጉ አንቀፅ 69 መሰረት በ6 ወር ጊዜ ውስጥ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ዲኝነት የጠየኩ ስለሆነ የይርጋ መቃወሚያው መታለፈ ተገቢ ነው። ለሽያጭ ውለ መነሻ የሆነው የስምምነት ክፍፍል በሀሰት የተዘጋጀ መሆኑ ተረጋግጦ አመልካች በወንጀል የተቀጣ በመሆኑ በወንጀል ድርጊት መነሻ የተፈፀመን ከመነሻው የላለ ውልን ሉፈርስ አይገባም በማለት አመልካች ያቀረበው ቅሬታ ተገቢ አይደለም። የክፍፍል ውለ ላይ 1ኛ ተጠሪ ያልፈረምኩ እና የማላውቀው መሆኑ በፍረንሲክ ተረጋግጦ አመልካች በወንጀል የተቀጡ በመሆኑ ሰነደ በፍረንሲክ አልተመረመረም በማለት የሚያነሱት ክርክር ተገቢነት የለውም። ውለን አመልካች ንብረቱን ከ1ኛ ተጠሪ ለማሸሽ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር የፈፀሙት እና ያልተመዘገበ ሕገ ወጥ ውል በመሆኑ የደረሰባቸው ጉዲት የለም። በተጨማሪም ወደ ነበሩበት ላለመመለስ በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ዲኝነት የለም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች የተፃፈ የመልስ መልሳቸውን ያቀረቡ ሲሆን የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር፣ በስር ፍ/ቤት በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች እንዱሁም ለጉዲዩ አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም አመልካች በዋናነት የሚከራከሩት ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም በተደረገ የስምምነት ውል መሰረት ክርክር የተነሳበት ቤት የአመልካች ድርሻ እንዱሆን ተስማምተን፤
ቤቱን ለ2ኛ ተጠሪ ሰኔ 5 ቀን 2003 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ያስተላለፍኩ በመሆኑና እንዱሁም በ1ኛ ተጠሪ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ክስ የቀረበው ሐምል 17 ቀን 2007 ዓ.ም ስለሆነ በፋደራል የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 69(2) መሰረት ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የቀረበው መቃወሚያ መታለፈ ተገቢ አይደለም በማለት ነው። በአንፃሩ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ሰኔ 12 ቀነ 2002 ዓ.ም የንብረት ክፍፍል ስምምነት አለመፈራረማቸውን፤ አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ሰኔ 5 ቀን 2003 ዓ.ም የሽያጭ ውል ማድረጋቸውንም ያወቁትም ህዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑን፤ ከዚህም ጊዜ ጀምሮ የስድስት ወር ጊዜ ሳያልፈው ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ውለ እንዱፈርስ ክስ የመሰረትኩ እና የሽያጭ ውለም ያልተመዘገበ መሆኑ ተረጋግጦ ውለ እንዱፈርስ መወሰኑ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል።
የጋራ የሆነን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ለመለወጥ፣ ለማከራየት፣ በመያዣነት ለመስጠት ወይም በልላ በማንኛውም ሁኔታ ላልች ሰዎች በንብረቱ ላይ መብት እንዱያገኙ ለማድረግ የተጋቢዎቹ የጋራ ስምምነት እንደሚያስፈልግ፤ ከዚህ በተቃራኒ አንደኛው ተጋቢ የውል ግዳታ የገባ እንደሆነ ፍቃደን ያልሰጠው ተጋቢ ግዳታው መገባቱን ካወቀበት ግዜ ጀምሮ በ6 ወር ውሰጥ ወይም በማንኛውም ሁኔታ ግዳታው በተገባ በ2 ዓመት ውስጥ ግዳታው እንዱፈርስ ሉጠይቅ እንደሚችል በፋደራል የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 68(1) እና 69 ላይ ተመላክቷል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ እንደቻልነው አከራካሪ የሆነውን ቤት አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ እንደ ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ በ1993 ዓ.ም በጋራ የገዙት ሲሆን አመልካችም ይህ ንብረት ከመነሻውም የጋራ ንብረት አይደለም በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ የለም። አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ከተጠሪ ጋር የንብረት ክፍፍል ማድረጋቸውን በዚህም መነሻነት ቤቱ የአመልካች ድርሻ እንዱሆን ተስማምተው የሽያጭ ውለ ሰኔ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ከተደረገ በኋላ በ2007 ዓ.ም ውለ እንዱፈርስ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ነው። 1ኛ ተጠሪ የሽያጭ ውል መኖሩን ያወቁት ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ የጋራ ንብረት ክፍፍል ክስ በኮ/መ/ መስርተው ክርክር ላይ እያለ ሕዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም 2ኛ ተጠሪ የሽያጭ ውለን መሰረት አድርገው በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ካቀረቡት አቤቱታ መሆኑን ገልፀው የሚከራከሩ ሲሆን አመልካችም ሆነ 2ኛ ተጠሪ ይህን በመቃወም ያቀረቡት መከራከሪያ የለም።
ከዚህም ላላ 1ኛ ተጠሪ የሽያጭ ውለ አለመመዝገቡን ጠቅሰው ክርክር አቅርበዋል። አመልካችም ሆነ 2ኛ ተጠሪ የሽያጭ ውለ መመዝገቡን ገልጸው ያቀረቡት መከራከሪያ የለም። ይልቁኑም 2ኛ ተጠሪ የሽያጭ ውለ ያልተመዘገበው አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ቤቱን በ1993 ዓ.ም የገዙት ባልተመዘገበ ውል በመሆኑ ከአመልካች ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውልም ያለመመዝገቡን ገልፀው ተከራክረዋል። ይህም የሽያጭ ውለ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተፈፀመ እንደመሆኑ የፍ/ሕ/ቁጥር 1723 በሚደነግገው አግባብ ስልጣን ባለው ሰነድች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት አለመመዝገቡን የሚያረጋግጥ ነው።
እንዱሁም በፍ/ሕ/ቁጥር 2878 መሰረት ውለ ለክርክሩ መሰረት የሆነው ቤት በሚገኝበት አከባቢ በሚገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት መመዝገቢያ የባህር መዝገብ ላይ አለመመዝገቡን ያሳያል። የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ ውልች ምዝገባ አላማም በተዋዋዮች መካከል ውለን የተመለከቱ አከራካሪ ሁኔታዎች ቢነሱ ጉዲዩን በቀላለ እልባት ለመስጠት ለማስቻል እንዱሁም በንብረቱ ሽያጭ ላይ መብት ጠያቂ ሶስተኛ ወገኖች ካለ ውለ ስለመደረጉ አውቀው ተገቢውን መፈጸም እንዱችለ ለማስቻል ነው።
አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ውለን መዋዋላቸው ባይካካደም ይሕ የሽያጭ ውል በፍ/ሕ/ቁጥር 1723 እና 2878 መሰረት ስልጣን ባለው አካል ያልተመዘገበ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ የተደረገውን የሽያጭ ውል አውቀው መቃወሚያ ሉያቀርቡበት የሚችለበት አግባብ የለም። በአንፃሩ 1ኛ ተጠሪ ይህ የሽያጭ ውል መኖሩን ያወቁት ህዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ እና ውለ እንዱፈርስ በፍ/ቤት ክስ የመሰረቱት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ተረጋግጧል። እንደሚታወቀው የይርጋ ድንጋጌዎች አላማ መብቱን የሚጎዲ ነገር መፈጸሙን እያወቀ በመብቱ ሳይሰራ የሚቆይን ከሳሽ ክስ የማቅረብ መብት መገደብ እንጂ መብቱ ስለመነካቱ የማያውቅ ወይም ማወቅ የሚችልበት እድል የላለውን ከሳሽ ክስ የማቅረብ መብት መገደብ አይደለም። የሽያጭ ውለ ባልተመዘገበበት እና በልላ ሁኔታ 1ኛ ተጠሪ ስለሽያጭ ውለ መደረግ አወኩ ካለበት ጊዜ በፉት ስለማወቃቸው በአመልካች የቀረበ ክርክር የላለ ከመሆኑም በላይ 1ኛ ተጠሪ ውለ አውቀዋል ወይም ማወቅ ነበረባቸው ተብል የሚገመተው ውለ የተመዘገበ ቢሆን ኖሮ ነበር። ይህ ባልሆነበት ውለ በተደረገበት በ2 ዓመት ውስጥ ክስ ማቅረብ ነበረባቸው የሚለው የአመልካች ክርክር የቤተሰብ ህጉን አንቀጽ 69 አላማ እና መንፈስ ያላገናዘበ ከመሆኑም በተጨማሪ ከተጋቢዎች አንደ የላላኛውን ፍቃድ ሳያገኝ ውል እየተዋዋለ የ2 ዓመት የይርጋ ጊዜ እስኪያልፍ ደብቆ በማቆየት በውለ ላይ ፍቃደኝነቱን ያልገለጸውን ተዋዋይ ወገን ውለ እንዱፈርስ የመጠየቅ መብቱን አላግባብ እንዱያጣ የሚያደርግ ነው። በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረጉ ውልች በሚመለከተው አካል እስካልተመዘገቡ ድረስ የውል ይፍረስልኝ ክስ ማቅረቢያ የ2 ዓመት የይርጋ ጊዜ መቆጠር መጀመር ያለበት በውለ ላይ ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ የውለን መደረግ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ላሆን ይገባል። ይህም ማለት በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 69 በማንኛውም ሁኔታ ውለ ከተደረገበት ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ የውል ይፍረስልኝ ክስ መቅረብ አለበት የሚለው ድንጋጌ ተፈጻሚ መሆን ያለበት እንዱፈርስ የሚጠየቀው ውል በሚመለከተው የመንግስት አካል የተመዘገበ ከሆነ ወይም ባይመዘገብ እንኳን በልላ አግባብ ስለውለ መደረግ በሚያውቅ ተጋቢ ላይ ላሆን ይገባል። በመሆኑም በተያዘው ጉዲይ በቤተሰብ ሕጉ አንቀፅ 69 ላይ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ መቆጠር መጀመር ያለበት 1ኛ ተጠሪ ውለ መደረጉን ካወቁበት ህዲር 23 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ መሆን ስለሚገባው እና 1ኛ ተጠሪም የሽያጭ ውለ መደረጉን ካወቁበት ጀምሮ ክስ እስከ መሰረቱበት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም 6 ወር ሳይሞላው ክስ የመሰረቱ በመሆኑ በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ በኩል የተነሳው የይርጋ መከራከሪያ መታለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም።
በመቀጠልም የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ስንመለከት አመልካች አከራካሪውን ቤት ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋራ ያፈሩት መሆኑን ሳይክደ ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም በተደረገ የክፍፍል ስምምነት የአመልካች ንብረት እንዱሆን 1ኛ ተጠሪ የተስማሙ በመሆኑ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ መወሰኑ አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ነገር ግን ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የንብረት ክፍፍል ተደርጎበታል በተባለው ሰነድ ላይ 1ኛ ተጠሪ አለመፈረማቸው እና አመልካች ሰነደን በሐሰት ያዘጋጁት መሆኑ ተረጋግጦ አመልካች በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በወ/መ/ በወንጀል የተቀጡ ሲሆን ይህ የጥፊተኝነት ውሳኔም በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በይ/መ/ በተሰጠ ውሳኔ ፀንቷል። ይህ የወንጀል ውሳኔ በፍትሐ ብሓር ጉዲዮች ላይ እንዲለ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ (Conclusive Evidence) በመሆኑ አመልካች በስር ፍ/ቤት ፊርማው በፍረንሲክ ሳይመረመር የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት የሚያነሱት መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም። በመሆኑም ሰኔ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ተደረገ የተባለው የንብረት ክፍፍል ስምምነት በሀሰት የተዘጋጀ በመሆኑ እንዱሁም በሽያጭ ውለ 1ኛ ተጠሪ ፍቃዲቸውን ያልሰጡ መሆኑ በመረጋገጡ የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈፀመ የሕግ ስህተት የለም።
አመልካች በይዞታው ላይ ከሽያጭ ውለ በኋላ በ2ኛ ተጠሪ ተጨማሪ ግንባታ መደረጉን በመግለፅ ተዋዋዮችን ወደ ነበርንበት መመለስ አይቻልም፤ ውለ እንዱፈርስ ሲወሰንም አንደኛው ወገን ያለአግባበብ የሚበለፀግ መሆን አለመሆኑ ከግምት ውስጥ ሳይገባ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም ይህ መከራከሪያ ላቀርብ የሚገባው በ2ኛ ተጠሪ በመሆኑ እና 2ኛ ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ስለማቅረባቸው ወይም በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በተደረገው ክርክር መጥሪያ የደረሳቸው ቢሆንም ቀርበው ይህን ገልፀው ያቀረቡት መከራከሪያ እና የመስቀለኛ የሰበር አቤቱታ ስለላለ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት ተከታዩን ወስነናል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ የካቲት 22 ቀን 2008 እና ሚያዝያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ብይንና ፍርድ እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይ/መ/ቁጥር 237723 ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.