ጋብቻ የተፈፀመበትን ትክክለኛ ጊዜ በተመለከተ በጋብቻ በምስክር ወረቀት ላይ የተገለፀውና በጋብቻ ክብር መዝገብ ላይ የተመዘገበው የተለያየ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ውሳኔ ስለሚሰጥበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 28፣ 30(ሐ) እና
No summary available.
የሰበር መዝገብ ህዲር 27 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ እሸቴ አድኔ ጠበቃ ዋና ኢንስፓክተር ሐየልም አስረስ -- ቀርበዋል ተጠሪ፡- ወ/ሮ አስናቀች ለውጤ -- አልቀረቡም ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል
አመልካች የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ፍርድ እና ውሳኔ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድ እና ውሳኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለት በሰበር ለማሳረም ህዲር 18 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል በመባለ መዝገቡ ለችልት ቀርቧል።
ጉዲዩ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት በከ/መ/ በተሰጠ ውሳኔ መፍረሱን ተከትል የቀረበ የንብረት ክርክር ሲሆን ክሱ በቀረበበት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ። አመልካች በሥር ክሳቸው ከተጠሪ ጋር በትዲር በነበሩበት ወቅት በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 13 የቤት ቁጥሩ አ.138 የሆነ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት ድርሻቸውን ተጠሪ ለማካፈል ፈቃደኛ ባለመሆን እየኖሩበት እና ከሚኖሩበት ከፍል ውጪ ያለውን ተጨማሪ ክፍል ብቻቸውን አከራይተው እንደሚጠቀሙበት ገልፀው ድርሻቸው እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም ለክሱ በሰጡት ምላሽ በግራቀኙ መካከል በነበረው የባልና ሚስት ክርክር የጋብቻ ውለ ሀሰተኛ ነው በማለት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 3 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ቅር በመሰኘት ያቀረቡት ይግባኝ በመዝገብ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙ የጋብቻ ውል ሀሰተኛ ነው በማለት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮ ከጥር 18 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ጋብቻ መኖሩን አረጋግጦ ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም እንዱፈርስ የወሰነ ሲሆን የክፍፍል ጥያቄ የቀረበበት ቤት መንግስት አቅመ ደካማ ለሆኑ ሰዎች ባደረገው ድጎማ(እገዛ) በብር 8,000(ስምንት ሺ) በግራቀኙ መካከል ጋብቻ ከመደረጉ ሶስት ዓመት አስቀድሞ ከአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ የቤት ማስተላለፍ ጽ/ቤት ባደረጉት ውል የተላለፈላቸው በ60.5 ካ.ሜትር ላይ ያረፈ የጋራ መኖሪያ ቤት የጋራ ንብረት ባለመሆኑ የተጠሪ የግል ንብረት ተብል እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ያየው የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አከራካሪው ቤት በግራ ቀኙ መካከል ጋብቻ አለ ተብል በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተወሰነበት ጊዜ ውስጥ መፈራት/አለመፈራቱን በጭብጥነት ይዞ መዝገቡን እንደመረመረው የክፍፍል ጥያቄ የቀረበበት ቤት ሰኔ 6 ቀን 1993 ዓ/ም ለተጠሪ ከተሰጠ በኋላ የቤቱ ሽያጭ በውል ቁጥር ገ/ቤሽ/0250/1998 ከአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ቤት ማስተላለፍ ጽ/ቤት ጋር በተደረገው የቤት ማስተላላፍ ስምምነት ለተጠሪ ለመተላለፈ የሰነድ ማስረጃ መቅረቡን ገልፆ ፤ ይህ ጊዜ በግራቀኙ መካከል የጋብቻ ግንኘነት መኖሩን የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መኖሩን ካረጋገጠበት ጥር 18 ቀን 2001 ዓ/ም በፉት የተገኘ መሆኑን ከማስገንዘቡም በላይ የተጠሪ ምስክሮች በሰጡት ምስክርነት ቃል ካዛንቺስ አካባቢ ነዋሪ የነበሩት ሰዎች በልማት ምክንያት የነበረው ቤት ሲፍርስ አከራካሪውን ቤት በመንግስት ተሰርቶ ለተጠሪ ተሰጥቷቸው ሲኖሩ ቆይተው ከመንግስት ጋር በገቡት ውል በብር 8000ሺ የቤቱ ካርታ የተሰጣቸው መሆኑና በዚህ ጊዜ አመልካች ከተጠሪ ጋር አብረው የማይኖሩ መሆኑን ያስረደ ፤ ሲሆን የአመልካች ምስክሮች አከራካሪውን ቤት ከተጠሪ ጋር ማፍራታቸውን እና ተጠሪ ቤቱ በተረከቡበት ጊዜ ግራቀኙ አብረው መኖራቸውን እንደክርክራቸው ያላስረደ በመሆኑ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር ጋብቻ ከመመስረታቸው በፉት ያፈሩት በመሆኑ የግራቀኙ የጋራ ንብረት ልባል አይገባም በማለት ወስኗል። ይግባኝ ሰሚው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካች ከተጠሪ ጋር ከ1982 ዓ/ም ጀምሮ ህጋዊ የሆነ ጋብቻ የነበራቸው መሆኑን እና በዚህ ጊዜ ውስጥ የተፈራው ንብረትም የጋራ ነው በማለት ሲከራከሩ ፤ ተጠሪ በ1982 ዓ/ም የተመሰረተ ጋብቻ አለመኖሩ በፍርድ መረጋገጡንና ንብረቱንም ከጋብቻ በፉት እንዲገኙት መከራከራቸውን ገልፆ ፤ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙ ጋብቻ በ1982 ዓ/ም እንደተመሰረተ የቀረበውን ማስረጃ በተመለከተ ውለ የተዘጋጀው ጥር ወር 2001 ዓ/ም ቢሆንም ልጃቸው በጋብቻ ውስጥ እንደተወለደ ለማስመሰል ጋብቻው በ1982 ዓ/ም እንደተፈፀመ የተዘጋጀ እንጂ የግራቀኙ ጋብቻ በ2001 ዓ/ም መመስረቱን የወሰነ በመሆኑ ፣ የግራቀኙ ጋብቻ በ1982 ዓ/ም ተፈጽሟል የተባለው የምስክር ወረቀት ለመውሰድ ስለተፈለገ እንጅ ሕጋዊ ጋብቻ የመሰረቱት በ2001 ዓ/ም በመሆኑ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ከጋብቻ በፉት በተጠሪ የተፈራ የግል ንብረቷ ነው በማለት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔን አፅንቷል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም ሆኖ ይዘቱም፡በግራቀኙ መካከል ጥር 18 ቀን 2001 ዓ/ም የተመሰረተ ጋብቻ መኖሩ ተረጋግጦ ሰኔ 7 ቅን 2010 ዓ/ም እንዱፈርስ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት አመልካች በጋብቻ ወቅት በላኩት ገንዘብ የተገዛ የጋራ ንብረት 50% ድርሻቸውን ተጠሪ ሉያካፍለ ሲገባ የሥር ፍርድ ቤት ጋብቻ መኖሩን እያወቀ እና እየተረዲ ወደጎን በመተው በጋብቻ ውስጥ የተፈራን ንብረት የተጠሪ የግል ንብረት ነው በማለት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መወሰኑና እና ይግባኝ ሰሚው የሥር ፍርድ ቤትም ውሳኔውን ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ስህተቱ ታርሞ በጋብቻ ውስጥ የተፈራው ንብረት ድርሻቸው እንዱወስነላቸው ጠይቀዋል።
የአመልካችን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ አመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ የመሰረቱት ጥር 6 ቀን 1982 ዓ/ም ሲሆን በክብር መዝገብ ላይ የተመዘገበ ብሓራዊ ጋብቻ የፈፀሙት ጥር 18 ቀን 2001 ዓ/ም የጋብቻ የምስክር ወረቀት የሚያስረዲ በመሆኑ አከራካሪው ቤት በግራቀኙ ጋብቻ ውስጥ በነበሩበት ወቅት የተፈራ መሆን/አለመሆኑን ለማጣራት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ በሰጡት መልስ፡በግራቀኙ መካከል የተደረገው ጋብቻ ጥር 18 ቀን 2001 የተደረገ ሲሆን ጥር 6 ቀን 1982 ዓ/ም ተፈረመ ተብል ለክብር መዝገብ ሹም የቀረበው ሰነድ ወደኋላ ተደርጎ ከግራቀኙ የሚወለደውን ልጅ እስራኤል ሀገር ወስጄ ላስተምር አመልካች በማለታቸው መሆኑ በተጠሪ በኩል የቀረቡት ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት በአመልካች ባለመስተባበለ ፣አመልካች በአባወራነት በዔድር ፣ በማኀበራዊ እና በቤተሰብ አባልነት ቅጽ የማይታወቁ እና የጋብቻ ሰነደም የቤተሰብ ሕጉ ካስቀመጠው ዓላማ እና ግብ አንፃር ያልተዘጋጀ ትዲር መኖሩን የማያስረዲ በመሆኑ የግራቀኙ ጋብቻ የተመሰረተው ጥር 2001 ዓ/ም መሆኑን ተረጋግጦ የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ከጋብቻ በፉት የተፈራው የተጠሪ የግል ንብረት የጋራ ነው በማለት አመልካች የሚያቀርቡት ቅሬታ ተገቢ ባለመሆኑ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተብል ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ውሳኔ ፀንቶ ኪሳራ እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና ግራቀኙ በዚህ ችልት ያደረጉት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑ አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር እንደሚከተለው መርምሮታል። የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 94 መሰረት ጋብቻ መኖሩን ለማስረዲት የሚቀርበው ማስረጃ ጋብቻ በተፈፀመ ዔለት ወይንም ከዚያ በኋላ በሕጉ አግባብ ተዘጋጅቶ በሚሰጥ የምስክር ወረቀት መሆኑን ያመለክታል። አንቀጽ 28 እና ተከታዮቹ የጋብቻ ምዝገባን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ሲሆኑ በአንቀጽ 28(3) ድንጋጌ መሰረት ጋብቻ ከተፈፀመበት ቀን ጅምሮ ውጤት እንደሚኖረው ተመላክቷል። የጋብቻ መዝገብ ጋብቻ የተመዘገበበት እና የተፈፀመበትን ቀን እንደሚያመለክት አንቀጽ 30(ሐ) ይደነግጋል። በተያዘው ጉዲይ የግራቀኙ ክርክር የጋብቻ ፍቺን ውጤት የሆነ የንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ቤት ድርሻቸው እንዱወሰንላቸው ላቀረቡት ክሰ ተጠሪ ጋብቻው የተመሰረተው ጥር 18 ቀን 2001 ዓ.ም ሲሆን በጋብቻ ምስክር ወረቀቱ ላይ ጋብቻ በ1982 ዓ.ም እንደተደረገ መገለፁ ከቤተሰብ ሕጉ ዓላማ ውጭ የግራቀኙ የጋራ ልጅ በጋብቻ ውስጥ እንደተወለደ አድርጎ ወደ እስራኤል ሀገር ለማውጣት መሆኑ ተከራክረዋል። በአመልካች እና ተጠሪ መካከል ጋብቻ የተፈፀመው ጥር 18 ቀን 2001 ዓ/ም መሆኑ እና ጋብቻው ከጥር 18 ቀን 2001 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም ፀንቶ ቆይቶ ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም በፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ መፍረሱ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የፀና ውሳኔ ያለ ሲሆን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ሰኔ 6 ቀን 1993 ዓ/ም ለተጠሪ በልማት ተነሽነት ተሰጥቷቸው በ1998 ዓ.ም ከአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ቤት ማስተላለፍ ጽ/ቤት ጋር በተደረገው ስምምነት ያገኙ የግል ንብረታቸው መሆኑ ተረጋግጧል። ስለሆነም በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 57 መሰረት የተጠሪ የግል ንብረት የሆነውን ቤት ለመካፈል አመልካች ያቀረቡት ክስ ውድቅ መሆኑ በህጉ አግባብ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ባለመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
የፍደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና ውሳኔ እንዱሁም የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድ እና ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ውጪ እና ኪሳራ ግራቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ውሳኔ አግኝቶ ሰለተዘጋ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.