ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋና የውጭ ሀገር ዜጋ ህጋዊ ጋብቻ ፈፅመው በትዲር አብረው መኖር የሚከለክላቸው ህግ እስከላለ ድረስ ጉዱፈቻ ለውጭ ሀገር ዜጋ ተከልክሎል በሚል ብቻ ከትዲራቸው በፉት የባል ወይም የሚስት ልጅ የሆነውን ላላኛው ተጋቢ በጉዱፈቻ ለመውሰድ የጉዱፈቻ ስምምነት እንዱፀድቅላቸው የሚያቀርቡትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የላለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 187
No summary available.
ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካቾች፡ …….1. ወ/ሮ አርሴማ ኤልያስ ጠበቃ አበበ ዘበነ - ቀርበዋል።
ይህ የጉዱፈቻ ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካቾች የሥር አመልካቾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዙህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካቾች የፋዳራል ከፍተኛ በመ.ቁ.274588 በ22/11/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዚዜ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ 1ኛ አመልካች እና 2ኛ አመልካች ባልና ሚስት ሲሆኑ፣ 1ኛ አመልካች ከ2ኛ አመልካች የማትወለደውን ህጻን ልጃቸውን ህጋዊ ባለቤታቸው ለሆነው ለ2ኛ አመልካች በጉዱፈቻ ለመስጠት ያደረጉትን ስምምነት እንዱጸድቅላቸዉ ዲኝነት ጠይቋል።
ከዙህ በኋላ ፍ/ቤቱም ጉዲዩን በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ አመልካች (ሚስት) ጉዱፈቻ ሰጪ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ስትሆን 2ኛ አመልካች (ባል) ጉዱፈቻ ተቀባይ የውጪ አገር ዛጋ መሆናቸዉ ከቀረበዉ አቤቱታ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፣ 1ኛ አመልካች ከ2ኛ አመልካች የማትወልዲትን ልጅ በጉዱፈቻ ዉል ስምምነት ለ2ኛ አመልካች ለመስጠት የተፈራረሙ ቢሆንም ጉዱፈቻ ለዉጭ አገር ዛጋ በአዋጅ ቁ.1070/2010 መሰረት የተከለከለ መሆኑ የቀረበዉን የጉዱፈቻ ውል ስምምነት ፍ/ቤቱ ውድቅ አድርጎታል በማለት ወስኗል።
አመልካቾች በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን በትዕዚዜ በመሰረዜ የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን አመልካቾች ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ ጉዱፈቻ ሰጪ ኢትዮጵያዊ የሆኑና ጉዱፈቻ ተቀባይ የደች ዛግነት ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ጋብቻቸውን በመፈፀም ሕጋዊ ባልና ሚስት ሆነን ኢትዮጵያ ውስጥ ልጅ ወልደው እየኖርን ያለን በመሆኑ፤
ጉዱፈቻ ተሰጪ ሕጻንም ከእናቷ ጋርና ከእንጀራ አባቷ ጋር እየኖረች በስሙም እየተጠራች አብረው የሚኖሩ በመሆኑ፤ ጉዱፈቻዉም አባትነትን እንጂ እናትነትን በተመለከተ ወላጅ እናቷን የማይነካ በመሆኑ፤ ጉዱፈቻዉ ከዉጭ ዛጋዉ ከተወለደዉ ወንድሟ ጋር እኩል በማድረግ በጉዱፈቻ ተደራጊዋ ህጻን አእምሮ ሉፈጠር የሚችለውን አለታዊ ተፅዕኖ ለማስቀረት ለህጻኗ ጥቅም የታሰበ ሆኖ ሳለ፣ የሥር ፍ/ቤቶች በዙህ ጉዲይ የጉዱፈቻ ዉል ስምምነቱን በልዩ ሁኔታ በማየት ከተለያዩ ሕጎችና አዋጆች አንጻር እንዱሁም ከአዋጅ ቁጥር 1070/2010 ዓላማና መንፈስ አንጻር በመረዲት መወሰን ሲገባቸዉ፣ የሥር ፍ/ቤቶች የጉዱፈቻ ዉለን በመከልከል የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሻርልን፣ አመልካቾች ያደረግነዉ የጉዱፈቻ ዉል ስምምነት እንዱጸድቅልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣በዙህ ጉዲይ ጉዱፈቻ ሰጪ እና ጉዱፈቻ ተቀባይ ባልና ሚስት መሆናቸው ከመረጋገጡ አንፃር ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 1070/2010 የሚሸፈን መሆን አለመሆኑ አግባብነት፣ ለማጣራት ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት አዞል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት ይህን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በሥር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠዉ ጉዲይ ሲታይ 1ኛ አመልካች ኢትዮጵያዊት ስትሆን፣ 2ኛ አመልካች የደች የዉጭ አገር ዛጋ ሲሆን፣ ግራ ቀኛቸዉ ሕጋዊ ጋብቻ ፈጽመዉ አንድ ልጅ ወልደዉ አብረዉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት መሆናቸው፤ እንዱሁም ሕጻን አቪያ ቫንድራ ቬድ 1ኛ አመልካች የተወለደችና ከ2ኛ አመልካች ያልተወለደች ልጅ ከግራ ቀኙና ከጋራ ልጃቸዉ ጋር በአንድ ቤት እየኖረች እና አሁንም በ2ኛ አመልካች ስም የምትጠራ መሆንዋን መዜገቡ ያሳያል። አመልካቾች በትዲር አብረዉ እየኖር ያለ በመሆናቸው፣ 1ኛ አመልካች ከ2ኛ አመልካች ጋር ያልወለደትን ልጅ 2ኛ አመልካች የልጅቷ እንጃራ አባት በመሆኑ፣ በጋራ ከወለደትና ካላቸዉ ልጅ ጋር ይህችን ልጅ እኩል ለማሳደግ ሲባል 1ኛ አመልካች የልጅቷ እናትነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ 2ኛ አመልካች በጉዱፈቻ ስምምነት መሰረት የልጅቷ የጉዱፈቻ አባት ለመሆን፣ የጉዱፈቻ ስምምነት ፈርመዉ፣ ይህም ስምምነት በፍ/ቤት እንዱጸድቅላቸዉ ዲኝነት መጠየቃቸዉን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል።
ይህ ከሆነ በዙህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ የፋዳራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አግባብነት ያላቸዉ ድንጋጌዎች ናቸዉ ወይስ ይህን የተሻሻለዉን የቤተሰብ ሕግ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 1070/2010 ነዉ? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ መሆኑን ተገንዜበናል።
እንደሚታወቀዉ የፋዳራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 በምዕራፍ አሥር ከአንቀጽ 180—196 ድንጋጌዎች ሥር ስለጉዱፈቻ የሚመለከቱ መሆናቸውን ማየት ይቻላል።
በአንድ ሰውና በአንድ ልጅ መካከል በሚደረግ ስምምነት የጉዱፈቻ ዜምድና ሉፈጠር እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 180 ሥር ተመልክቶ እናገኛለን። ያገባ ሰዉ የሚያደርገዉን የጉዱፈቻ ስምምነት በተመለከተ በዙህ ሕግ አንቀጽ 187 ሥር በተደነገገዉ አግባብ መሆን እንዲለበት ተመልክቷል። በዙህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት የጉዱፈቻ አድራጊዉ ያገባ በሚሆንበት ጊዛ፣ ባልና ሚስቱ በጋራ ልጁን የጉዱፈቻ ልጃቸዉ የሚያደርጉት ካልሆነ በስተቀር የጉዱፈቻ ስምምነት ለማድረግ እንደማይቻል የሚደነግግ ሲሆን፣ በንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት የጉዱፈቻዉ ልጅ፣ የጉዱፈቻዉ ባል ወይም ሚስት ልጅ በሆነ ጊዛ፣ በዙህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈጻሚነት እንደማይኖረዉ ይደነግጋል። ከዙህ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለዉ ባልና ሚስት በጋራ የጉዱፈቻ ስምምነት በማድረግ የላላ ሰዉ ልጅን በጉዱፈቻ ማሳደረግ እንደሚችለ፣ እንዱሁም በጋራ ያልወለደትን የባል ወይም የሚስት የሆነዉን ልጅ ባል ወይም ሚስት በጉዱፈቻ ስምምነት ማሳደግ እንደሚችለ ነዉ። የጉዱፈቻዉ ልጅ የባል ወይም የሚስት በሆነ ጊዛ ላላኛዉ ተጋቢ በጉዱፈቻ ስምምነት የአንደኛዉን ልጅ በጉዱፈቻ ስምምነት ማሳደግ እንደሚችል ያስገነዜባል። ይህ ድንጋጌ የባል ወይም የሚስት የዛግነት ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ያስቀመጠዉ ክልከላ የለም። ነገር ግን ባል ወይም ሚስት የኢትዮጵያ ዛጎች ብቻ መሆን አለባቸዉ፤ ከመካከላቸው አንዲቸዉ የውጭ አገር ዛጋ ላሆን አይችልም የሚያስብል ሁኔታ የለም።
ምክንያቱም ባል ወይም ሚስት ከሁለቱ አንዲቸው የውጭ ዛጋ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም በውጭ አገር ጋብቻቸውን በሕግ አግባብ ፈጽመው በኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አይችለም በማለት በሕግ የተጣለ ግልጽ ክልከላ የለም።
በልላ በኩል የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ ለማሻሻል አዋጅ ቁጥር 1070/2010 ወጥቶ ሥራ ላይ መዋለ ይታወቃል። በዙህ አዋጅ አንቀጽ 2 መሰረት የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 193 የተሻረ መሆኑን፣ የአዋጁ አንቀጽ 194 (3፣ መ) ተሰርዝ ነባሩ ፉደል ተራ (ሰ) ፉደል ተራ (መ) ሆኖ መሸጋሸጉን፣ እና የአዋጁ አንቀጽ 194 (4) መሰረዘን ይደነግጋል።
እነዙህ ድንጋጌዎች የሚመለከቱት በውጭ አገር ዛጋ የሚደረግ የጉዱፈቻ ጉዲይ መሆኑን ማየት ይቻላል። በዙህ መሰረት በአዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 193 ድንጋጌ የጉዱፈቻ አድራጊዉ የውጭ አገር ዛጋ በሚሆንበት ጊዛ የጉዱፈቻ ስምምነቱ ተቀባይነት ሉኖረው የሚችልበትን አግባብ የሚያመለክተው ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 1070/2010 አንቀጽ 2 (1) ድንጋጌ መሻሩን ያመለክታል።
እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 194 (3፣ መ) እና (4) ድንጋጌዎች የጉዱፈቻ አድራጊው የውጭ ዛጋ የሚመለከቱ በመሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 1070/2010 አንቀጽ 2 ድንጋጌ መሰረዚቸውን ማየት ይቻላል። በመሆኑም ከአዋጅ ቁጥር 1070/2010 ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ መገንዘብ እንደሚቻለዉ የጉዱፈቻ አድራጊዉ የውጭ አገር ዛጋ የጉዱፈቻ ስምምነት በማድረግ አንድ ኢትዮጵያዊ/ዊት ልጅን በጉዱፈቻ መዉሰድ እንደማይቻል ያሳያል።
በዙህ አግባብ አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ አመልካች እና ተጠሪ ባልና ሚስት ሆነዉ፣ 1ኛ አመልካች ኢትዮጵያዊት ዛጋ ስትሆን፣ 2ኛ አመልካች የደች አገር ዛጋ ሲሆን፣ 1ኛ አመልካች ከ2ኛ አመልካች ያልወለደችውን ልጅ፣ የእርሷ እናትነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ 2ኛ አመልካች የልጅቷ የጉዱፈቻ አባት እንዱሆን ለማድረግ፣ በትዲራቸው በጋራ ካገኙት ልጃቸው ጋር ይህችንም ልጅ ለማሳደግ በማሰብ 2ኛ አመልካች የጉዱፈቻ አባት እንዱሆን ለማስቻል፣ የጉዱፈቻ ስምምነት ፈርመዉ ፍ/ቤቱ እንዱያጸድቅላቸዉ ያቀረቡ መሆናቸዉን መዜገቡ ያሳያል። የጉዱፈቻ ልጅ የሆነችዉ የ1ኛ አመልካች ልጅ፣ አመልካቾች በትዲራቸው ውስጥ ከወለደት ልጃቸው ጋር እያሳደጓት ያለ እና ይህች ልጅ አሁንም በ2ኛ አመልካች ስም እየተጠራች በአመልካቾች ዘንድ የምትኖር መሆንዋ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። ከዙህም በላይ አመልካቾች የሚኖሩት በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ማየት ይቻላል። አመልካቾች ሕጋዊ ጋብቻ ፈጽመው በትዲር አብረዉ በመኖር ልጅ ማፍራት የሚከለችላቸው ሕግ እስከላለ ድረስ፣ ከትዲራቸዉ በፉት የባል ወይም የሚስት ልጅ የሆነዉን ላላኛዉ ተጋቢ በጉዱፈቻ ስምምነት መዉሰድ አይችልም የሚባልበት የህግ አግባብ የለም። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው አዋጅ ቁጥር 1070/2010 አንቀጽ 2 መሰረት የአዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 193፣ 194 (3፣ መ) እና (4) ድንጋጌዎች መሰረዚቸዉን እንጂ የአዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 187 ድንጋጌ መሰረዘን ወይም መሻሻለን የሚያመለክት አይደለም። በመሆኑም በዙህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ሉኖረዉ የሚገባዉ የአዋጅ ቁጥር 1070/2010 ሳይሆን የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አግባብነት ያላቸዉ ደንጋጌዎች ናቸዉ።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች የግራ ቀኛቸውን የባልና ሚስት ግንኙነት፣ አንድ ልጅ በትዲራቸው ወልደው ያላቸዉ መሆናቸዉን፣ 1ኛ አመልካች የጉዱፈቻ ተደራጊዋ ልጅ እናት መሆንዋ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አመልካቾች የጉዱፈቻ ተደራጊዋን ልጅ አሁንም አብረዉ እያሳደጓት እና በኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ መሆናቸውን ከግምት ዉስጥ ሳያስገቡ፣ በአዋጅ ቁጥር 1070/2010 መሰረት ጉዱፈቻ ለዉጭ አገር ዛጋ ተከልክሎል በማለት አመልካቾች የጉዱፈቻ ስምምነት እንዱጸድቅላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ መስጠታቸው ተገቢ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአመልካቾችን ግንኙነት ከግምት ዉስጥ ሳያስገቡ ጉዱፈቻ ለውጭ አገር ዛጋ ተክልክሎል በማለት ያሳለፈት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.127142 በ9/9/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዚዜ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.274588 በ22/11/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዚዜ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆናቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተዘጋውን መዜገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታው በተመለከተው አግባብ አመልካቾች የጉዱፈቻ ስምምነት እንዱጸድቅላቸዉ ያቀረቡትን አቤቱታ በመመርመር ተገቢ ነዉ ያለውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዙህ ውሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
አመልካቾች በዙህ ችልት በነበረው ክርክር የደረሰባቸውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዜገቡ ተዘግቷል፡ ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.