በትዲር ጊዜ በርከት ያለ ገንዘብ ወጪ ያደረገ ተጋቢ ይኸው ገንዘብ ለትዲር ጥቅም እንዲልዋለ ክርክር ሲቀርብበት ገንዘቡ በሙለ ለትዲር ጥቅም ስለመዋለ የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ማስተባበል የሚጠበቅበት ሲሆን ማስተባበል ካልቻለ የላላውን ተጋቢ ድርሻ ገንዘብ የሚከፍል ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 62(1)
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ ምስራቅ ሞገስ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ገብረጻዱቅ አባይ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 02/09/2013 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 28/11/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው።
ጉዲዩ የጋብቻ ንብረት ክፍፍልን የተመለከተ ሲሆን ከአሁን በፉት እስከዚህ ሰበር ችልት ደርሶ ችልቱ በመ/ በቀን 24/01/2013 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የተዘጋውን የመ/ አንቀሳቅሶ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አዱስ ከተማ ቅርንጫፍ በተጠሪ ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር የተቀመጠ ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ) በግራቀኙ አለመግባባት ተፈጥሯል ከተባለበት ግዜ አንስቶ ያለውን ሙለ የሂሳብ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሪፕርት በማስቀረብ ገንዘቡ ለትዲር ጥቅም መዋል አለመዋለን አጣርቶ የመሰለውን እንዱወስን በማለት በፍ/ብ/ሥ/ስ/ህ/ቁ 343(1) መሰረት ጉዲዩን ለስር ፍርድ ቤት መልሷል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የተመለሰለት የስር ፍርድ ቤት አለመግባባት የተፈጠረው መቼ ነው የሚለውን ለማጣራት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቷል። ከባንኩ የተላከውን መግለጫም ተመልክቷል።
በመጨረሻም በሰጠው ውሳኔ አመልካች አለመግባባቱ የተፈጠረው ከጥቅምት 2010 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን የገለጹ እና የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው ከሚያዚያ 16/2010 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል። አመልካች ከጥቅምት/2010 ዓ.ም በኋላ አለመግባባቱ መፈጠሩን ቢገልፁም በዚህ ጊዜ ስለመፈጠሩ በጉዲዩ ልክ አላስረዲችም። ከዚህ በተጨማሪም ከሳሽ ክስ የመሰረተችው ሚያዚያ 17/2010 ዓ.ም ነው። ስለዚህ አለመግባባቱ የተፈጠረው ክስ በተመሰረተበት ከሚያዚያ 17 ቀን 2010 ዓ.ም ነው። የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በጻፈው ደብዲቤም ከቀን 18/08/2010 ዓ.ም በኋላ የወጣ ገንዘብ የላለ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም ከቀን 18/08/2010 ዓ.ም በኋላ የወጣ ገንዘብ የላለ መሆኑ በመረጋገጡ በጋብቻ ወቅት እያለ በተለያየ ጊዜ ወጪ የተደረገው ጥሬ ገንዘብ ለትዲር ጥቅም ውሎል በማለት ፍርድ ቤቱ መደምደሚያ ላይ ደርሷል። የአዋሽ ባንክ በቀን 19/03/2011 ዓ.ም በጻፈው ደብዲቤም ከቀን 18/08/2010 ዓ.ም በኋላ የወጣ ገንዘብ የላለ መሆኑን ገልጾ ያለው ተቀማጭ ገንዘብ ብር 505.00 (አምስት መቶ አምስት) መሆኑን የገለጸ ሲሆን ይህም የጋራ ንብረት ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካች በቀን 02/02/2014 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ የስር ፍ/ቤት በአመልካች የቀረቡትን የሰው ምስክሮች ምስክርነት ሙለ ይዘትና በፍ/ቤት ትዕዛዝ ከአዋሽ ባንክ ከቀረበው የሰነድ ማስረጃ ጋር በማገናዘብ በጥልቀት መርምሮ ውሳኔ ያለመስጠቱ የማስረጃ ምዘና መርህን ያልተከተለ ነው።
በአመልካች በኩል ሶስት ምስክሮች ቀርበው ሁለቱ ምስክሮች የተጠሪ የቅርብ ጓደኞች በመሆናቸው ገለልተኛ ምስክርነት መስጠት ስላልቻለ እንጂ አመልካች ከተጠሪ ጋር ከሚያዚያ 2010 ዓ.ም በፉት በነበረን አለመግባባት ሽምግልና ሲቀመጡ የነበሩና በመካከላችን ያለውን አለመግባባት በቅርበት የሚያወቁ ሆነው እያለና ከ3ኛ ምስክር ምስክርነት እና ከተጠሪ ክርክር አኳያ ሲመዘን እምነት የማይጣልበት ስለሆነ የምስክሮቹ ቃል ሙለ ይዘት ተጨምቆ ሲታይ ቢያንስ 3ኛው ምስክር በመካከላችን ከጥር ወር የጥምቀት በአል አካባቢ ጀምሮ ከባንክ ቡክ መደበቅ ጋር በተያያዘ መግባባት እንዲልቻልን መመስከሩ ከተጠሪ ጋር የነበረን አለመግባባት ምክንያት በባንክ ካለው ገንዘብ ጋር ተያይዞ እንደሆነ የተረጋገጠ ከመሆኑም በተጨማሪ ያለመግባባቱ ተጠሪ እንደሚለው ከሚያዚያ 16/2010 ዓ.ም ጀምሮ ሳይሆን ከዚህ በፉት ቢያንስ ከጥር ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ እንደሆነ በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ተጠሪም አመልካች በስር ፍ/ቤት ባቀረብኩት የፍቺ አቤቱታ ላይ በሰጡት መልስ በተደጋጋሚ በመካከላችን ግጭት እንደነበርና በሽማግላ ስንፈታ መቆየታችንና መጋቢት 27/2010 ዓ.ም በድጋሚ ሽማግላ ጠርተን ለማስማማት መቀመጣቸውን መግለጹ የሚያሳየው በእርግጥም አለመግባባቱ ተጠሪ እንደሚለው ከሚያዚያ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ሳይሆን ከዚያ በፉት እንደሆነ አመልካችም አለመግባባቱን ቀድሜ በሽምግልና ለመፍታት ሳደርግ የነበረውን ጥረት የሚያረጋግጥ ሆኖ ሳለ የስር ፍ/ቤት የወሰነው ውሳኔ ክርክራችንና ማስረጃን መሰረት ያላደረገ ነው። ከጉዲዩ ልዩ ባህርይ አኳያ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 261(2) አግባብ በቅድሚያ ምስክርነቴን እንድሰጥ ቢደረግ ኖሮ አለመግባባቱ መች፣ በምን ምክንያት እንደሆነ፣ ችግሩን በሽምግልና ለመፍታት ያደረኩትን ጥረት እና በተጠሪ የተደረገው ወጪ ለትዲር ጥቅም እንዲልዋለ ማስረዲት ስችል ፍ/ቤቱ ጥያቄዬን አለመቀበለ ሳያንስ አለመግባባቱ ከሚያዚያ ወር 2010 ዓ.ም በፉት ጀምሮ እንደነበርና አለመግባባቱንም በሽምግልና ለመፍታት ያደረኩት ጥረት እንዲልነበር በማተት የሰጠው ውሳኔ የማስረጃ ምዘና መርህን ያልተከተለ ነው። ከአዋሽ ባንክ የቀረበውም ማስረጃ ባቀረብኳቸው የሰው ምስክሮች በተረጋገጠው እንኳ አለመግባባቱ ከተፈጠረበት ከጥር ወር 2010 ዓ.ም በኋላ ያለው እንቅስቃሴ ሲታይ ወጪ ብቻ እንጂ ገቢ የማያሳይ ከመሆኑ በተጨማሪ የካቲት 06/2010 ዓ.ም ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ወጪ አድርጎ በድጋሚ መጋቢት 20/2010 ዓ.ም ላይ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በአንድ ግዜ ወጪ ማድረጉ እንዱሁም በዚሁ መዝገብ ቀድሞ ከአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በቀረበው የባንክ ስቴትመንት ላይ በተመሳሳይ መጋቢት 20/2010 ዓ.ም 690,000.00 (ስድስት መቶ ዘጠና ሺህ) ብር ከሂሳቡ ላይ ወጪ መደረጉ ተደምሮ ሲታይ ካለን የኑሮ ወጪ አንጻር ሁለት ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ይህን ያህል ከፍተኛ ወጪ ሉያስወጣ የሚችልበት ሁኔታ በላለበት የስር ፍ/ቤት ለተጠሪ በማስረጃ ያልተደገፈ መከራከሪያ ክብደት በመስጠት የሰጠው ውሳኔ ማስረጃዎችን በሙለ ይዘት ያልመረመረው መሆኑን የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ የተጠሪን ገንዘብ የማሸሽ ተግባር ያረጋገጠ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። የስር ፍ/ቤት ከባንኩ በቀረበው የሰነድ ማስረጃ ላይ አስተያየት እንድሰጥ ሳያደርግና በጉዲዩ ላይ ምስክርነቴን እንድሰጥ ሳያደርግ ውሳኔ መስጠቱ ኢ-ህገመንግስታዊና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ ቢያንስ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ከሚያዚያ 17 ቀን 2010 ዓ.ም በፉት በተጠሪ ከአዋሽ ባንክ ወጪ የተደረገው 750,000.00 (ሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ) ብር ለትዲር ጥቅም አልዋለም ተብል የዚህን ገንዘብ ግማሹን ተጠሪ ለአመልካች እንዱያካፍል እንዱወሰንልኝ በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት በአመልካች እና በተጠሪ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ መሆኑን በመውሰድ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 25/06/2014 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ የስር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው ከ17/08/2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ከዚህ ግዜ በፉት በጋብቻ ውስጥ እያለ የወጣው ገንዘብ ለጋራ የትዲር ጥቅም ውሎል በማለት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው፤ ከፍተኛው ፍ/ቤትም ቀደም ሲል ሰበር ሰሚው ፍ/ቤት በመ/ ጭብጥ ይዞ በመለሰው መሰረት አለመግባባቱ የተፈጠረበትን ግዜ በምስክሮች አረጋግጦና አለመግባባቱ ከተፈጠረ አንስቶ ከባንክ ወጪ የተደረገ ገንዘብ አለመኖሩን ባንኩ በላከው ሰነድ ማስረጃ አጣርቶና መርምሮ ውሳኔውን ማጽናቱ አግባብ ነው። የስር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ መሆኑን የወሰደው ከዚያ በፉት በሰላም አብረን እንኖር እንደነበርና ክስ ከቀረበበት ግዜ ጀምሮ አለመግባባት የተፈጠረ ስለመሆኑ አመልካች በቆጠሯቸው ምስክሮች በመረጋገጡ እንዱሁም አለመግባባቱ ከመፈጠሩ በፉት ጋብቻችን ጸንቶ በቆየበት ጊዜ ወጪ የተደረገ ገንዘብ ለጋራ ጥቅም እንደዋለ የሚቆጠርና የህግ ግምት የሚወሰድበት በመሆኑ ነው። ስለሆነም የስር ፍ/ቤት አለመግባባት የተፈጠረበትን ጊዜ በመውሰድ ውሳኔ መስጠቱ አግባብ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱጸና በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም በመልስ መልሳቸው አቤቱታቸውን በማጠናከር አቅርበዋል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በመሰረቱ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 62(1) ስር በግልጽ እንደተመለከተው ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኙት ገቢ ሁለ የጋራ ሀብታቸው ይሆናል። ስለሆነም በጋብቻው ጊዜ ያገኙት ገቢና ያፈሩት ንብረት የጋራ መሆኑ አከራካሪ አይሆንም። ከዚህም ላላ በርከት ያለ ገንዘብ በትዲር ጊዜ በአንደኛው ተጋቢ መውጣቱ ሳይካድ እና ይኸው ገንዘብ ለትዲር ጥቅም አለመዋለ ክርክርና ማስረጃ በልላኛው ወገን ሲቀርብ ገንዘቡ በሙለ ለትዲር ጥቅም ውሎል የሚል ወገን የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ማስተባበል ይጠበቅበታል።
በተያዘው ጉዲይ እስከዚህ ሰበር ችልት የዘለቀው የጋብቻ የንብረት ክፍፍል ጥያቄን አስመልክቶ አስቀድሞ በዚህ ሰበር ችልት ታይቶ ፍቺና የንብረት ክፍፍል ከተጠየቀበት ጥቂት ቀናት አስቀድሞ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አዱስ ከተማ ቅርንጫፍ በተጠሪ ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር ተቀምጦ የነበረውና ወጪ የሆነው ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ) በግራቀኙ አለመግባባት ተፈጥሯል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ያለውን ሙለ የሂሳብ እንቅስቃሴ በማየት ገንዘቡ ለትዲር ጥቅም መዋል አለመዋለን ተጣርቶ ይወሰን ተብል ተመልሷል። አመልካች ባቀረቧቸው ምስክሮች በተለይ በ1ኛ ምስክሯ ከጥር ወር ጀምሮ በሂሳብ ደብተር የተነሳ (የሂሳብ ደብተር ስለደበቀባት) አለመግባባት መኖሩን፤
እንዱሁም በላልቹም ምስክሮች በሽምግልና መታየታቸውን አስረድተዋል።
በአንጻሩ ተጠሪ ገንዘቡ በባንክ እንደነበር እና በእርሳቸው መውጣቱን ክደው ያልተከራከሩ በመሆኑ ይኸው በርከት ያለ ገንዘብ በርግጥም ለትዲር ጥቅም መዋለን ክርክርና ማስረጃ በማቅረብ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። ይሁንና ተጠሪ አለመግባባቱ የተፈጠረው ፍርድ ቤት ክስ ሲቀርብ (ከሚያዚያ 16/2010 ዓ.ም ጀምሮ) ነው እንዱሁም አለመግባባቱ ከመፈጠሩ በፉት ጋብቻችን ጸንቶ በቆየበት ጊዜ ወጪ የተደረገ ገንዘብ ለጋራ ጥቅም እንደዋለ የሚቆጠርና የህግ ግምት የሚወሰድበት ነው በማለት ከመከራከራቸው በቀር የተጠቀሰው ገንዘብ ለትዲር ጥቅም መዋለን አላሳዩም።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው እንደተያዘው ጉዲይ አይነት በርከት ያለ ገንዘብ በትዲር ጊዜ በተጠሪ መውጣቱ ሳይካድ እና ይኸው ገንዘብ ለትዲር ጥቅም አለመዋለ ክርክርና ማስረጃ በአመልካች በኩል ሲቀርብ ገንዘቡ በሙለ ለትዲር ጥቅም ውሎል የሚለት ተጠሪ የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ማስተባበል ይጠበቅባቸዋል። በአንፃሩ አለመግባባቱ የተፈጠረው የፍቺ ክስ በቀረበበት ቀን ነው ከዚህ ቀን ቀደም ብል በጥቂት ቀናት ውስጥ ከባንክ የወጣው ገንዘብ ለትዲር ጥቅም እንደዋለ ይገመታል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የህጉን ትክክለኛ ይዘትና መንፈስ የተከተለ አይደለም።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤት ሙለ ክርክሩንና የቀረበውን ማስረጃ ከህጉ ጋር አገናዝቦ ሳይመረምር እንዱሁም በዚህ ሰበር ችልት ከተያዘው ጭብጥ በመሸሽ ተጠሪ በአጭር ጊዜ ከባንክ ያወጣው ገንዘብ ለትዲር ጥቅም ስለማዋለ ማስረጃ አቅርቦ የአመልካችን ክርክር ባላስተባበለበት ሁኔታ ባንኩ ከቀን 18/08/2010 ዓ.ም በኋላ የወጣ ገንዘብ የላለ መሆኑን አረጋግጧል እንዱሁም በጋብቻ ወቅት እያለ በተለያየ ጊዜ ወጪ የተደረገው ጥሬ ገንዘብ ለትዲር ጥቅም ውሎል በማለት የደረሰበት መደምደሚያ እና ያሳለፈው ውሳኔ የሚነቀፍ ነው። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይህን ሳያርም ማለፈ አላግባብ ነው ብለናል። ተከታዩንም ወስነናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 02/09/2013 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 28/11/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ፍቺና የንብረት ክፍፍል ከተጠየቀበት ጥቂት ጊዜ አስቀድሞ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አዱስ ከተማ ቅርንጫፍ በተጠሪ ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር ተቀምጦ የነበረውና ወጪ የሆነው ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ) የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት በመሆኑና ተጠሪም ገንዘቡ ለትዲር ጥቅም አለማዋለን በተመለከተ የቀረበባቸውን ክርክርና ማስረጃ ስላላስተባበለ የዚህን ገንዘብ ግማሽ .00 (ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ) ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል በማለት ወስነናል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የስር ፍርድ ቤት መዝገብ በመጣበት መልኩ ይመለስ።
No topics extracted.