የሟች ወራሽ ላልሆነ ሰዉ የተሰጠ የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃ እንዱሰረዝ መብት ያለዉ ሰዉ ክስ ሲያቀርብ ተከሳሹ የወራሽነት መብት የላለዉ መሆኑን በክሱ የማሳየት እና ይህንኑ የማረጋገጥ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ህግ አንቀጽ 997-999 በፍትሐብሕር ህግ አንቀጽ 1000(1) ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ጊዜ የወራሽነት ማስረጃን ለማሰረዝ ወይም ህጋዊ መብት በላለዉ ሰዉ የተያዘ የዉርስ ንብረት እንዱለቀቅ የሚቀርብ ክስ የሚቀርብበትን ጊዜ የሚመለከት በመሆኑ ይህም በባህሪዉ ክስ እንዲይቀርብ የሚከለክል (limitation of actions) ስለመሆኑ አንድ ሰዉ የወራሽነት ማስረጃን በተወሰነ ጊዜ ዉስጥ ከፍርድ ቤት ካልወሰደ ወይም ወራሽነቱን ካላሳወጀ የመዉረስ መብት እንደሚያጣ (extinctive prescriptive) በህግ የተመለከተ ድንጋጌ ባለመኖሩ የተሰጠ ማስረጃ ሉሰረዝ ይገባል በሚል የሚቀርብ ዲኝነት ተቀባይነት የላለዉ ወ/ሮ ገነት ጉልላት እና ወ/ሮ ተቋመወርቅ በለጠ
No summary available.
ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እንዲሻዉ አዲነ ተሾመ ሽፈራዉ መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡ ወ/ሮ ገነት ጉልላት- ከጠበቃ ኤሉያስ ጥላሁን ጋር - ቀርበዋል ተጠሪ፡- ወ/ሮ ተቋመወርቅ በለጠ - ቀርበዋል መዝገቡ ተመርመሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ በፍርድ ቤት የተሰጠ የወራሽነት ማረጋገጫ የሚሰረዝበትን አግባብ የሚመለከት ሲሆን፣ ክርክሩ በተጀመረበት በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ባቀረቡት ማመልከቻ ተጠሪ አዉራሽ አያታቸዉ ወ/ሮ አዛለች አወቀ በ1981 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩበት ጊዜ ጀምሮ ወራሽነት ሳይጠይቁ ቆይተዉ ከ33 ዓመት በኋላ የወሰደት የወራሽነት ማስረጃ መዉሰዲቸዉ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰዉ የተሰጣቸዉ የወራሽነት ማረጋገጫ ዉሳኔ እንዱሰረዝ የጠየቁትን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ። ተጠሪ በበኩላቸዉ ተጠሪ በመ/ ላይ ወራሽነታቸዉን ባረጋገጡበት መዝገብ ላይ አመልካች መቃወሚያ አቅርበዉ ዉድቅ ተደርጎ ዉሳኔዉ የጸና መሆኑን እና ላልች የመጀመሪያ መቃወሚያዎች ናቸዉ የሚሎቸዉን ክርክሮች በመጥቀስ መልስ ሰጥተዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ የአያታቸዉ ወ/ሮ አዛለች አወቀን ሀብት ለመዉረስ ያቀረቡት የወራሽነት ጥያቄ በሦስት ዓመት ይርጋ የሚታገድ መሆኑን የፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000(1) እና በመ/ ላይ የተሰጠዉን የሰበር ዉሳኔ በዋቢነት በመጥቀስ አስቀድሞ ለተጠሪ ተሰጥቶ የነበረዉን የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃ በመሰረዝ ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበኩለ የወራሽነት የምስክር ወረቀት መዉሰድ በይርጋ የማይታገድ በመሆኑ ተጠሪ የወራሽነት የምሰክር ወረቀት የወሰደት መብታቸዉ በይርጋ ቀሪ ከሆነ በኋላ ነዉ በሚል የወራሽነት ማስረጃዉን በመሰረዝ የተሰጠ ዉሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሮ ወስኗል። የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የከተማዉ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ይህንኑ ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚሁ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ። አመልካች ጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ የሆነዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመዘርዘር ታርሞ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን፣ የሰበር አቤቱታቸዉ መሰረታዊ ይዘትም በአጭሩ ሟች አባታቸዉ በህይወት በነበሩበት ወቅት ያላረጋገጡትን የሟች ወ/ሮ አዛለች አወቀ ወራሽነት ተጠሪ በምትክ ወራሽነት ከ33 ዓመት በኋላ ያሰጡት የወራሽነት ማረጋገጫ ዉሳኔ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች የወራሽነት ማስረጃዉ ሉሰረዝ አይገባም በማለት የሰጡት ዉሳኔ የፍትሐብሕር ህጉን አንቀጽ 1000(1)፣ 1677(1)፣ 1845 እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን ዉሳኔ መሰረት ያላደረገ ነዉ የሚል ነዉ።
የሰበር አቤቱታዉ በአጣሪ ችልት ተመርምሮም፣ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡትን ዉሳኔ አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል ተብሎል። በዚህም መሰረት ተጠሪ ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የተሰጣቸዉ የወራሽነት ማስረጃ በይርጋ ምክንያት ሉሰረዝ እንደማይገባ ተጠቅሶ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም የሚለባቸዉን ምክንያቶች በመጥቀስ ጸንቶ እንዱወሰንላቸዉ ተከራክረዋል። አመልካች የሰበር አቤቱታቸዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካች በስር ለከተማዉ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዲኝነት ለተጠሪ ተሰጥቶ የነበረዉ የወራሽነት ማረጋገጫ እንዱሰረዝ ነዉ። የሟች ወራሽ ላልሆነ ሰዉ የተሰጠ የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃ እንዱሰረዝ መብት ያለዉ ሰዉ ክስ ማቅረብ እንደሚችል እና ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ማስረጃዉ የተሰጠዉ ሰዉ ወራሽ አለመሆኑ ከተረጋገጠ የሰጠዉን የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃ መሰረዝ እንደሚችል በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 997-999 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ የምንገነዘበዉ ነዉ። የአመልካች አቤቱታም በዚሁ መሰረት የቀረበ ስለመሆኑ ከማመልከቻዉ ይዘት መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዝ ክስ የሚያቀርብ ሰዉ ተከሳሹ የወራሽነት መብት የላለዉ መሆኑን በክሱ የማሳየት እና ይህንኑ የማረጋገጥ ኃላፉነት አለበት።
ተጠሪ አባታቸዉን ተክተዉ የሟች ወ/ሮ አዛለች አወቀ ህጋዊ ወራሽ ስለመሆናቸዉ አመልካች ክደዉ አይከራከሩም፤ ተጠሪ ሟችን የማይወርሱበት ላላ ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩም ጠቅሰዉ አይከራከሩም።
ከላይ እንደተገለጸዉ ለተጠሪ የተሰጠዉ የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዝ ዲኝነት ሲጠይቁ አመልካች የጠቀሱት ምክንያት የወራሽነት ማስረጃዉን አዉራሽ ከሞተ ከ33 ዓመት በኋላ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። ወይም በልላ አገላለጽ ለተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ የተሰጣቸዉ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000 ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነዉ የሚል ምክንያት ነዉ። ስለሆነም ተጠሪ አባታቸዉን ተክተዉ ሟችን እንዲይወርሱ የሚከለክል በህግ የተመለከተ የጊዜ ገደብ አለ ወይ? የሚል ነጥብ የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ ነዉ።
በመሰረቱ ከፍትሐብሕር ጉዲዮች ጋር በተያያዘ ሦስት የይርጋ ዓይነቶች ያለ ሲሆን፤
የመጀመሪያዉ በህግ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ ወይም ዲኝነት ተቀባይነት እንዲይኖረዉ የሚከለክል የይርጋ ዓይነት ወይም በእንግሉዝኛዉ ‛period of limitation“ በመባል የሚታወቅና በፍትሐብሕር ህጋችን አንቀጽ 1845 ላይ የተመለከተዉ ዓይነት ነዉ። ሁለተኛዉ ዓይነት ይርጋ አንድን ንብረት በህግ ለተወሰነ ጊዜ በመያዝ ወይም በመጠቀም በንብረቱ ላይ የባለቤትነት ወይም የባለይዞታነት መብት የሚገኝበትና በእንግሉዝኛዉ ‛acquisitive prescriptive“ በመባል የሚታወቅ ሆኖ በፍትሐብሕር ህጋችን አንቀጽ 1168 ላይ የተመለከተዉ ዓይነት ሲሆን፣ ሦስተኛዉ በህግ ለተወሰነ ጊዜ ንብረትን ይዞ ባለመገኘት ወይም በንብረቱ ባለመጠቀም ወይም በህግ በተሰጠ መብቱ ባለመጠቀም የባለቤትነት ወይም የባለይዞታነት ወይም በአንድ ነገር የመጠቀም መብትን የሚያሳጣና በእንግሉዝኛዉ ‛extinctive prescriptive“ በመባል የሚታወቅ ሆኖ በህጋችን አንቀጽ 1192 ላይ የተመለከተዉ ዓይነት ይርጋ ነዉ። ይህም በአጭሩ ሲቀመጥ የመጀመሪያዉ ይርጋ ዓይነት የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላ ክስ ማቅረብን የሚከለክል ሲሆን፣ በሁለተኛ እና ሦስተኛ ላይ የተመለከቱት ግን በህግ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላ መብትን የማግኘት ወይም የማጣት ዉጤትን የሚያስከትለ ናቸዉ።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት አመልካች የተጠሪ መብት በይርጋ ታግዶል በማለት የሚከራከሩት የወራሽነት ማስረጃዉን የወሰደት በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000(1) ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ መሆኑን ሲሆን፣ ይህ የይርጋ ደንብ የወራሽነት ማስረጃን ለማሰረዝ ወይም ህጋዊ መብት በላለዉ ሰዉ የተያዘ የዉርስ ንብረት እንዱለቀቅ የሚቀርብ ክስ የሚቀርብበትን ጊዜ የሚመለከት ነዉ። ይህም በባህሪዉ ክስ እንዲይቀርብ የሚከለክል (limitation of actions) ነዉ።
አመልካች በጠቀሷቸዉ መዛግብት ላይ ይህ ሰበር የሰጣቸዉ ዉሳኔዎችም ይህንኑ መሰረት ያደረጉ ናቸዉ። ይሁንና በአመልካች ላይ የቀረበ ክስ ባለመኖሩ አመልካች ይህን እንደመከራከሪያ ሉያነሱ የሚችለበት ህጋዊ ምክንያት የለም። በልላም በኩል አንድ ሰዉ የወራሽነት ማስረጃን በተወሰነ ጊዜ ዉስጥ ከፍርድ ቤት ካልወሰደ ወይም ወራሽነቱን ካላሳወጀ የመዉረስ መብት እንደሚያጣ (extinctive prescriptive) በህግ የተመለከተ ድንጋጌ የለም። በመሆኑም አመልካች ለተጠሪ የተሰጠ ማስረጃ ሉሰረዝ ይገባል ሲለ የጠየቁት ዲኝነት ተቀባይነት የላለዉ ሆኖ እያለ የስር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ህጉን አንቀጽ 1000(1) እንዱሁም በሰ/መ/ ላይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ ያለቦታዉ በመጥቀስ ማስረጃዉን በመሰረዝ የሰጠዉ ዉሳኔ በእርግጥም የህግ ስህተት በመሆኑ፣ የከተማዉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር የሰጡት ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም።
ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የማይነብብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.