ምንም እንኳን የፍርድ መቃወሚያ የቀረበው አስቀድሞ የነበረ ክርክር በሚታወቅበት ሁኔታ ቢሆንም የፍርድ መቃወሚያ የቀረበበት ክርክር የውርስ ሀብትን መሰረት ያደረገ ከሆነ የውርስ ሀብቱ ክፍፍል ከተደረገ በኋላም ቢሆን የሚቻል ክርክር በመሆኑ የፍርድ መቃወሚያ እነ አቶ መስፍን እንደሬ (4 ሰዎች) እና እነ ወ/ሮ ብዙነሽ እሸቴ አመልካች አስቀድሞ ክርክሩን ያውቅ ነበር በሚል ውድቅ የማይደረግና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ድንጋጌ የውርስ ሀብት ክርክርን በተመለከተ ተፈፃሚነት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ስላለመሆኑ የፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 1080 (2 ሰዎች)
No summary available.
የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካቾች:- 1ኛ. አቶ መስፍን እንደሬ 2ኛ. አቶ ተፈራ እንድሬ ጠበቃ ማረን ወንዳ - ቀረቡ።
3ኛ. ወ/ሮ የሻረግ እንድሬ 4ኛ. አቶ እንዲል እንድሬ ተጠሪዎች፦ 1ኛ. ወ/ሮ ብዙነሽ እሸቴ - ተወካይ አይተነው እንድሬ - ቀረቡ።
2ኛ. አቶ ሙስጠፊ እንድሬ - ጠበቃ አገኘሁ አይናለም - ቀረቡ።
በዚህ መዝገብ እና በ
ያለ ተከራካሪ ወገኖች በአንድ ዘንግ የሚመደቡ ከመሆናቸው በላይ የቀረበው የህግ ክርክርና የነገረ ጭብጥም አንድ በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 11/1/ መሰረት ሁለቱም መዝገቦች በማጣመር ጉዲዩን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ፦ የውርስ ሀብት ክርክርን መሰረት ያደረገ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በሻሸመኔ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን 2ኛ ተጠሪ በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ፍርድ ቤቱ በ24/4/2009ዓ.ም የሰጠውን ትእዛዝ እና በ17/6/2009ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ በመቃወም የአሁን አመልካቾች ከላልች 2 አመልካቾች ጋር ባቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ የስር ከሳሽ በስር ተከሳሽ እናታችን ላይ ባቀረቡት ክስ ፍርድ ቤቱ ሲያከራክር ቆይቶ የክርክሩን ንብረት ከሳሽ እና ተከሳሽ ብቻ እንዱካፈለ የሰጠው ውሳኔ የሟች አባታችን የአቶ እንድሬ ወርቁን ንብረትም ጭምር በመሆኑ እኛም የአባታችን ወራሽ መሆናችንን ያረጋገጥን በመሆኑ ውሳኔው የኛን መብት የሚነካ ስለሆነ ይህ ውሳኔ ተሰርዞ ድርሻችንን ማግኘት እንድንችል ይወሰንልን በማለት በ21/6/2009ዓ.ም የተጻፈ አቤቱታ በማቅረባቸው ነው። በልላ በኩል ለ
አቤቱታ ምክንያት የሆነው የአሁን አመልካቾች ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ሲደረግባቸው አዱስ ክስ ለሻሸመኔ ወረዲ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም በመ/ በቀን 9/8/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት ክሳቸው ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ በመቃወም አመልካቾች አቤቱታ ቢያቀርቡም በምዔራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆነ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ነው። በሁለቱ በዚህ መዝገብ እና በ
ያለ ተከራካሪ ወገኖች በአንድ ዘንግ የሚመደቡ ከመሆናቸው በላይ የቀረበው የህግ ክርክርና የነገረ ጭብጥም አንድ በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.
11/1/ መሰረት ሁለቱም መዝገቦች በማጣመር ጉዲዩን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ፍርድ ቤቱም የመቃወም ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ካደረገ በኋላ በመጀመሪያው ክርክር ጊዜ ተከሳሽን ወክል ይከራከሩ የነበሩት ከፍርድ መቃወሚያ አቅራቢዎች መካከል አቶ አይተነው እንድሬ የተባለት ግለሰብ በመሆናቸው እና የአሁን ፍርድ መቃወሚያ አቅራቢዎች የስር ተከሳሽ ልጆች በመሆናቸው ክርክሩን አያውቁትም ነበር ለማለት የማያስችል በመሆኑ በወቅቱ በክርክሩ ገብተው ለመከራከር የማያስችል በቂ ምክንያት የነበረ ስለመሆኑ አላስረደም በማለት አትቶ የአሁን አመልካቾች ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል። በልላ በኩል ለ
አቤቱታ ምክንያት የሆነው የአሁን አመልካቾች ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ሲደረግባቸው አዱስ ክስ ለሻሸመኔ ወረዲ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም በመ/ በቀን 9/8/2009 ዓ.ም በዋለው ችልት ክሳቸው ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ በመቃወም አመልካቾች አቤቱታ ቢያቀርቡም በምዔራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆነ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ነው። ስለዚህ ሁለቱም መዝገቦች በማጣመር ጉዲዩን መርምረናል።
አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን ለዚህ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት በነዚህ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም፦ የመቃወም ተጠሪዎች ባደረጉት ክርክር እኛ ባልተከራከርንበት የተሰጠው ውሳኔ እኛ ከሟች አባታችን ማግኘት የሚገባን ድርሻችንም ጭምር ውሳኔ ያረፈበት እና የፍትሐ ብሄር ስነ-ስርዓት ህጉም በላለበት የተሰጠ ፍርድ መብቱ የሚነካበት ሰው ፍርድ ከመፈጸሙ በፉት የፍርድ መቃወሚያ ሉያቀርብ እንደሚችል ተደንግጎ እያለ ይህ ሁለ ታልፍ ያቀረብነውን የፍርድ መቃወም አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት ቅሬታው ተጠሪዎችን ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ የጽሁፍ መልስ እና የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል። የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የቀረበውን የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ከተደረገው ክርክር እና ማስረጃ አንጻር የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር ያለመኖሩን መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም የአመልካቾች ክርክር አሁን ክርክር የተነሳበት ንብረት እኛም የአባታችን ድርሻ ያለበት ስለሆነ እኛ የክርክሩ ተካፊይ ያልተደረግንበት ውሳኔ መብታችንን ስለሚነካ ተሰርዞ የድርሻችንን እንድንካፈል ይወሰንልን በማለት ያቀረብነው የመቃወሚያ ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ነው።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ላይ እንደተመለከተው ማንኛውም በፍርደ ተካፊይ ላሆን የሚገባው ሰው ተካፊይ ባልሆነበት ሁኔታ የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካ ከሆነ ፍርደ ከመፈጸሙ በፉት መቃወሚያውን ሉያቀርብ እንደሚገባ ተደንግጎ ይገኛል። ነገር ግን የሱን መብት የሚነካ ክርክር መኖሩን ያወቀ ማንኛውም ሰው ፍርድ መሰጠቱን ሳይጠብቅ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት ወደ ክርክሩ ልግባ በማለት ጠይቆ ገብቶ ተከራክሮ መብቱን ሉያስጠብቅ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 41 ላይ ደንግጎ ይገኛል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የአመልካቾች የስር የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ውድቅ የተደረገው አመልካቾች አስቀድመው ክርክሩን ያውቁት ስለነበር አሁን ፍርድ እስከሚያልቅ ድረስ ጠብቀው ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ ተገቢ አይደለም በማለት ነው። በእርግጥም አስቀድሞ መብቱን የሚነካ ክርክር መኖሩን ያወቀ አካል ክርክሩ አብቅቶ ውሳኔውን ከመስማቱ በፉት ወደ ክርክሩ ሉገባ እንደሚገባ ከላይ በተመለከተው የህግ ድንጋጌ ተመልክቷል። አመልካቾች የፍርድ መቃወሚያ ያቀረቡበት ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት በነበረው ክርክር ላይ ተከሳሽ የነበሩት የአመልካቾች እናትን ወክል ይከራከር የነበረው ከፍርድ መቃወሚያ አቅራቢዎች አንደ የሆነው የስር ተከሳሽ ልጅ እና የአሁን የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ አቅራቢዎች ወንድም መሆኑ በስር በግራ ቀኙ ከተደረገው ክርክር መረዲት ችለናል። ይህ ከሆነ ደግሞ የአሁን የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ አቅራቢዎች በስር ወንድማቸው እና እናታቸው መካከል የነበረውን ክርክር በተለየ ሁኔታ እንደማያውቁ ካላስረደ በስተቀር ክርክሩ መኖሩን አያውቁም ነበር ማለት አይቻልም። ስለሆነም ፍርድ ሲሰጥ ጠብቀው በመምጣት የተሰጠው ፍርድ ይነሳልኝ በማለት አቤቱታ ማቅረብ የፍት/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 ላይ የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ አላማ የሚያሳካ አይደለም። ይሁን እንጂ ይህ ድንጋጌ ለውርስ ሀብት ክርክርን በተመለከተ ተፈፃሚነት ያለው ነው ለማለት የሚቻል አይደለም። እንኳን የውርስ ሀብቱ ሳይከፊፈል ቀርቶ ከተከፊፈለ በኋላም በላለበት የውርስ ሀብቱ የተከፊፈለበት አካል በሚያቀርበው አቤቱታ ክፍፍለ ሉፈርስ እና እንደገና ክፍፍል ላደረግ እንደሚገባ በፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 1080 ላይ ተደንግጎ ይገኛል። ስለሆነም ምንም እንኳን አመልካቾች ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ አስቀድሞ የነበረውን ክርክር በሚያውቁበት ሁኔታ ቢሆንም የፍርድ መቃወሚያ የቀረበበት ክርክር የውርስ ሀብትን መሰረት ያደረገ ከሆነ የውርስ ሀብቱ ክፍፍል ከተደረገ በኋላም ቢሆን የሚቻል ክርክር በመሆኑ የአመልካቾች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ አመልካቾች አስቀድመው ክርክሩን ያውቁት ነበር በማለት ውድቅ በማድረግ የሻሸመኔ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን በትእዛዝ በማጽናት የምዔራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በሻሸመኔ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ በቀን 1/7/2009 ዓ.ም እና የምዔራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በቀን መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዝያ 8 ቀን 2009 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካቾች ባቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ መነሻነት ክርክር ባቀረቡበት የውርስ ሀብት ላይ አመልካቾች ድርሻ አላቸው? ወይስ የላቸውም? የሚለውን ጭብጥ በማስረጃ አጣርቶ ይወስን ዘንድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት ለስር የሻሸመኔ ወረዲ ፍርድ ቤት ይላክ ብለናል።
ግራ ቀኙ ለዚህ ክርክር ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ በየደረጃው ለሚገኙ የስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
ት ዔ ዛ ዝ የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ከ
ይያያዝ ብለናል።
No topics extracted.