የወራሽነት ምስክር ወረቀት የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ በፍ/ሕ/ቁ. 997 መሰረት ወራሹ በምስክር ወረቀቱ እንደተገለጸው ወራሽ እንደሆነ ግምት የሚወሰድ ቢሆንም በፍ/ሕ/ቁ. 946 እና ተከታዮቹ መሰረት ወርስ ተጣርቶ የወራሾች ማንነትና የወራሾች የዉርስ ሀብት ድርሻ ተለይቶ በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 996 መሰረት ተገልጾ የተሰጠ የወራሽነት ምስክር ወረቀት ባለመሆኑ በህግ የተገኘን መብት ለማረጋገጥ የሚሰጥ እንጂ የወራሽነት ማስረጃዉን በመጥቀስ ክርክር የማይቀርብበትና በእራሱ የተለየ መብት የሚሰጥ ስላለመሆኑ አንድ ድርጊት ወይም መብትና ግዳታ በተፈጠረበት ጊዜ የነበረዉ ህግ በልላ ህግ የተተካ ሆኖ ሲገኝ እና ክርክሩ ለፍርድ ቤት ወይም ለዲኝነት ሰጪ አካል የቀረበዉ አዱሱ ህግ በስራ ላይ ከዋለ በኋላ ሆኖ ከተገኘ ይህ መሰረታዊ ህግ (substantive law) ወደ ኋላ ተመልሶ እንዱሰራ ህግ አዉጪዉ እራሱ በልዩ ሁኔታ ካላመላከተ በስተቀር፣ፍርድ ቤቱ ክርክሩን መምራት እና ዉሳኔ መስጠት ያለበት በተሻረዉ ህግ መሰረት ሲሆን ክርክሩ አዱሱ ህግ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለፍርድ ቤት መቅረቡ ጉዲዩ በአዱሱ ህግ መሰረት እንዱመራ ምክንያት ላሆን የሚችል እነ አቶ ሰይፈ ላቀው (2 ሰዎች) እና አቶ አሸናፉ ተክለ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 51/1999 እንዱሁም የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 252/2009 በፍ/ሕ/ቁ. 826(1) እንደተመለከተው ዉርስ የሚከፈተዉ አዉራሹ በሞተበት ጊዜ እና ቦታ በመሆኑ ለውርስ ክርክር ወራሾቹ ሆነ ቀዲሚ ወራሾች እነማን ናቸው የሚለው ሉወሰን የሚገባው አውራሽ በሞተበት ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት እንጂ በክርክሩ ጊዜ አዱስ ሥራ ላይ በዋለው ሕግ መሰረት ስላለመሆኑ (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ መዝገቦች ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጧል።)
No summary available.
ቀን፡- ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ቴዎድሮስ ምሕረት አበባ እምቢአለ እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ከሳሾች፤ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል። ጉዲዩ የተጀመረው በቀይት ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካቾች በ09/07/2011 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት የሟች እናታችንና አባታችን ወራሾች መሆናችንን በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 17/5 መሰረት ወራሽነታችንን አሳውጀናል። ነገር ግን ተጠሪ ላላኛውን የስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ ወ/ሮ ዘነበች ላቀውን ጨምሮ ያለ ህግ አግባብ የወላጆቻችንን መሬት ከጥር ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ ቦታው ስርጥ ተብል በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን 4 ጥማድ መሬት፣ ልዩ ቦታው ግመል ተብል በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን ½ ጥማድ መሬት፣ ልዩ ቦታው ዲዱስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን ¼፣ ላልች 2 ቦታ የሚገኙ 1/8 ጥማድ መሬት፣ ልዩ ቦታው ዋደር ተብል በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን 1/8 ጥማድ መሬትና ልዩ ቦታው አፊሳሽ ተብል በሚጠራው አካባቢ ¼ ጥማድ መሬት የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ ለቀው እንዱያስረክቡን እንዱወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪን የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽም በ20/07/2011 ዓ/ም ባቀረቡት የመከላከያ መልስ ተጠሪ የሟች ሙለነሽ አስፊው ወራሽ በአዋጅ ቁጥር 133/98 ደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/7/ለ ተወስኖልኝ ቀድሞ በስራ ላይ በነበረው አዋጅ መሰረት የቀደምትነት መብት ስላለኝ ከተራ ቁጥር 1-3 በክሱ ላይ በተዘረዘሩት የሙለነሽ አስፊው ድርሻ ተላልፍልኝ፣ በስሜ ተመዝግቦ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቶኝ፣ በስሜ እየገበርሁ የያዝኩት ስለሆነ አመልካቾች ሉጠይቁኝ አይገባም። አመልካቾች የሟች ቤተሰቦቻቸው ልጆች ቢሆኑም በቀድሞው አዋጅ መሰረት የውርስ ቅደም ተከተልን መሰረት በማድረግ በተጠሪ ቀድመው የመውረስ መብት ወይም መካፈል የሚያስችል ስላልነበራቸው የውርስ መሬቱን አልጠየቁም። አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 57 በቀድሞው አዋጅ መሰረት የተገኙ መብቶች የሚጸኑ መሆናቸውን ይደነግጋል። በመሆኑም በውርስ ያገኘሁትን መሬት ላካፍል ወይም ላስረክብ አይገባም በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ አሁን በተያዘው ክርክር ያልተካተተች ስለሆነ ክርክሯን መመዝገቡ አስፈላጊ ሆኖ ስላልተገኘ ታልፎል።
የወረዲ ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ በአመልካቾች አቤቱታ ላይ የተጠቀሱትን መሬቶች ተጠሪዎች ለአመልካቾች ለቀው ሉያስረክቡ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን ምስክሮች አስቀርቦ ሰምቷል። ወላጆቻቸው መሞታቸውን ተረጋግጧል፤ አመልካቾች የሟቾች ወራሾች መሆናቸውን በፍ/ብ/መ/ በ15/07/2011 ዓ.ም በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 17/5 መሰረት አረጋግጠዋል፤ በተጨማሪም በቅደም ተከተል በፍ/ብ/መ/ በ06/07/2011 ዓ/ምና በፍ/ብ/መ/ በ22/12/2011 ዓ/ም በአማራ ክልላዊ መንግስት የመሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 17/5 መሰረት ያሳወጁ መሆናቸውን 2 የወራሽነት ማስረጃ ከመዝገቡ ተያይዟል። ተጠሪ ደግሞ በፍ/መ/ በ02/02/2009 ዓ/ም በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት አዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 16/5ና በደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/7/ለ መሰረት ያሳወጀውንና በ05/12/2010 ዓ/ም የወ/ሮ ሙለነሽ አስፊውን መሬት በወረዲው መሬት አስተዲደር በኩል ተላልፍለት በይዞታ መለያ ቁጥር Am/11/6/5/1450 ያወጣውን የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በማስረጃነት ያያያዘ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ በዚህ መዝገብ ተከራካሪ ስላልሆነ ማስረጃውን መመዝገቡ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም። የተጠሪ ምስክሮች ተጠሪ መሬቱን ሉይዝ የቻለው የሟቾች የቤተሰብ አባል በመሆኑ ወራሽነቱን አረጋግጦ መሆኑን አስረድተዋል።
የአመልካቾች ምስክሮች አመልካቾች የሟቾች ልጆች ከመሆናቸው ውጪ የተለየ ያስረደት ነገር የለም።
ክርክር ያስነሳው የሟቾች መሬት ተጠሪና የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ያወጡበት መሆኑን አመልካቾች ያልካደት ጉዲይ ነው። በተጨማሪም የወረዲው መሬት አስተዲደር በቁጥር ባ/ወ/ወ/7/ወ/አስ/አጠ/5451/30/28 በ11/08/2011 ዓ/ም በጻፈው ደብዲቤ ተጠሪ የሟች ሙለነሽ አስፊው የገጠር መሬት ይዞታ ወራሽ መሆኑን በቀያት ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት የፍ/ብ/መ/ አስወስኖ ይዞታዋ እንዱተላለፍለት አመልክቶ ተቃዋሚ ካለ እንዱቀርብ ማስታወቂያ ተለጥፍ ባለመቅረቡ በውርስ የገጠር መሬት ይዞታ የሚተላለፍበት ፍርማሉቲ ተሟልቶ ውርስ እንዱተላለፍለት ተወስኖ ተላልፍ ይገኛል። ተጠሪ አዱስ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በደ/መ/ቁ Am/11/6/5/1450 ተመዝግቦ እንዲገኘ በመግለጽ መሬት አስተዲደር ማስረጃ ልኳል። ፍርድ ቤቱ ከላይ ከተጠቀሱት ማስረጃዎች የሟቾች መሬት ህጉን በጠበቀ መልክ ለተጠሪና ለ2ኛ የስር ፍርድ ቤት ተከሳሽ ተላልፎል። ተጠሪና የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ያወጡበት መሆኑን ገልጸዋል። አመልካችች ተጠሪ መሬቱን ለቆ ያስረክበን ከማለት ውጪ በተጠሪ ስለቀረበው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የገለጹት ነገር የለም። የአማራ ክልል የመሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 35/2 የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የባለ ይዞታው በህግ የተጠበቀ ማስረጃ መሆኑንና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እያለ ዳኞች ላልች የሰነድም ሆነ የሰው ማስረጃዎችን ቅደሚያ ሰጥተው ሉቀበለና ሉመለከቱ እንደማይችለ ሲገልጽ በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 5 ስር ደግሞ ይህንን የሚቃረን ጠንካራ የጽሐፍና አብልጦ የሚያሳምን ምክንያት ካልቀረበ በስተቀር የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ ተዘጋጅቶ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ እንደሆነ ህጉ ደንግጎ ይገኛል። የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ ተዘጋጅቶ የተሰጠው ሰው መሬቱ የእሱ አይደለም የሚል ክርክር የሚያቀርብ ግለሰብ ጠንካራ የጽሐፍ ማስረጃና አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ አለበት። በመሆኑም በሰው ምስክር ብቻ ተጠሪ ማረጋገጫ ደብተር አውጥተው የያዙትን መሬት የሚለቁበት የህግ አግባብ ስለላለ ሉለቁ አይገባም በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
አመልካቾች በዚህ ፍርድ ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታቸውን ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተጠሪን አስመልክቶ የቀረበውን ይግባኝ የሰረዘው ሲሆን በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበው በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈጸመም በማለት ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካቾች የካቲት 18 ቀን 2012 ዓ/ም በጻፈት የሰበር አቤቱታ የአሁን ተጠሪ በቀድሞው አዋጅ መሰረት የመሰረተው መብት የለውም ምክንያቱም በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 996 መሰረት የወራሽነት ማስረጃ ብቻ በመያዝ በአውራሹ ንብረቶች ላይ መብት መመስረት አይችልም። መሬቶቹን በመዘርዘር በመሬት ይዞታው ላይ እኔ ነኝ ወራሽ በማለት ተከራክረናል። ተጠሪ በቀድሞው አዋጅ ቁጥር 133/1998 መሰረት መሬቱን አልተረከበውም፤ በእጁ አላደረገውም ስለዚህ በቀድሞው አዋጅ መሰረት የተመሰረተ መብት የለውም። ስለዚህ ውሳኔ መሰጠት የነበረበት በአዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት ነው። በመሆኑም አመልካቾች የሟች ልጆች ስለሆንን በአዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት ወራሾች ነን። ተጠሪ በመሬቱ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ያገኘው በ05/12/2010 ዓ/ም ሲሆን ይዞታውን የተረከበው በጥር ወር 2011 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት መሆኑን ነው። ተጠሪ የቤተሰብ አባል ነው እንኳን እንዲይባል ፍርድ ቤቱ የቤተሰብ አባል ነው በማለት ውሳኔ አልሰጠም፤ በቤተሰብ አባልነቱ መብት አልመሰረተም። በመሆኑም ተጠሪ በቀድሞው አዋጅ መሰረት ህጋዊ መብት የላለው ስለሆነ በስር ፍርድ ቤቶች መሰረታዊ የህግ ትርጉም ስህተት የተፈጸመበት ውሳኔ ነው።
መሬቱ የማን ይዞታ ነው ወይም የእኔ ይዞታ ነው የሚል ክርክር አልተነሳም፤ ፍርድ ቤቱም ይህንን ጉዲይ በጭብጥነት አልያዘውም፤ መሬቱ የሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አስፊው መሆኑን ተጠሪ ክድ አልተከራከረም፤ በመሆኑም ተከራካሪዎች የተማመኑበት ጉዲይ ነው። በልላ በኩል ደግሞ የክልለ መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 35/2/ እና /5/ ተፈጻሚነቱ ክርክር በተነሳበት የይዞታ መሬት ላይ ህጋዊ ባለይዞታ ማነው የሚመለከተውን ክርክር በተመለከተ ስለሆነ የስር ፍርድ ቤቱ ይህን ድንጋጌ መሰረት አድርጎ የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። በጭብጥነት ሉያዝና ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው የወራሽነት መብት ያለው ማነው የሚለው ጭብጥ ነው። ተጠሪ የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ ልጅ መሆኑ ተረጋግጦ ባለበት የሟች ሙለነሽ አስፊው ልጅ ነው በማለት የተሰጠው ማስረጃ የሀሰት በመሆኑ፣ ያገኘው የመሬት ማረጋገጫ ደብተር ያገኘው ሀሰተኛ ማስረጃ ላይ ተንተርሶ ነው፣ የአዋጁን አንቀጽ 34/5 የሚጥስ ነው፤ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ድንጋጌዎችን መንፈስና የክርክርን ሂደት የሚጻረር ስለሆነ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት የላለው ነው። ይዞታው በአጠቃላይ የሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አስፊውና የሟች አቶ ላቀው ሙለጌታ የጋራ የይዞታ መሬት ነው። በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአባታችን ድርሻ እኩል እንድንካፈል ተወስኗል። የሟች እናታችን ድርሻ መሬት ተጠሪ ለቀው ሉያስረክቡን ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ከግራ ቀኙ ክርክር የአሁን አመልካቾች የሟቾች ወራሽ መሆናቸው አከራካሪ ባልሆነበትና የአመልካቾች ክስ/አቤቱታ/ በይርጋ ይቋረጣል ባልተባለበት ሁኔታ የአመልካቾች የውርስ ሀብት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በስር ፍርድ ቤቶች የሰጠውን ውሳኔ አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ ብል ተጠሪ የመከላከያ መልሳቸውን ይዘው እንዱቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪ ባቀረቡት መልስ ክርክር በሚደረግበት ይዞታ ላይ መብት አቋቁሜበታለሁ፣ በመሬት አስተዲደር ተመዝግቧል። በስር ፍርድ ቤቶች በነበረን ክርክር መብት መቋቋሙ በማስረጃ ተረጋግጦ የሙለነሽ አስፊው ድርሻ አይገባችሁም የላቀው ሙለጌታን ድርሻ ተካፈለ ተብለው ተካፍለዋል። አመልካቾች ወራሽነቱ በሀሰት የተገኘ ነው ይሰረዝልን የሚል ክስ በወረዲው ፍርድ ቤት አቅርበው በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ታይቶ ወራሽነት አይሰረዝም ተብል ስለተወሰነ ራሱን አስችል ክርክር አቅርቦበት ውሳኔ ያገኘ ጉዲይ ስለሆነ በዚህ ችልት ክርክር ላቀርብበት አይገባም። የይዞታ ማረጋገጫ በይዞታው ላይ መብት የተቋቋመበት ስለመሆኑ በቂና ተአማኒ የሆነ ማስረጃ ነው። አመልካቾች አዱስ አዋጀ ሲወጣ ልጆች ነን በሚል መብት የተቋቋመበት ይዞታ ከተጠሪ ላይ ሉወስደ አይችለም። የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን በአግባቡ መዝኖ ውሳኔ ሰጥተዋል። አመልካቾች የሙለነሽ አስፊው ውርስ ይገባናል ሲለ ውድቅ መደረጉ አግባብ ነው በማለት ተከራክረዋል።
አመልካቾች መጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በሰጡት የመልስ መልስ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሰበር ሰሚ ችልቱ ቀደም ሲል በመዝገብ የሰጠውን ውሳኔ ወደጎን በመተው የሰጡት ውሳኔ ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ውሳኔ ነው። በአዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት አመልካቾች የሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አስፊው ልጆች ስለሆኑ በዚህ አዋጅ መሰረት የመውረስ መብት ያላቸው አመልካቾች ናቸው። ስለዚህ ተጠሪ ወራሽ ሳይሆን መውረሱ ተገቢነት የላለው ነው። የሟች ወ/ሮ ሙለነሽ አስፊው ብቸኛ ወራሾች አመልካቾች ብቻ ናቸው። ተጠሪ በቀድሞው አዋጅ መሰረት በወረዲው መሬት አስተዲደር ወራሽ መሆኑን አረጋግጦ አላስመዘገበም መሬቱን አልተረከበም በማለት የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ለውርስ ክርክሩ ተፈጻሚነት ያለው ሕግ የትኛው ነው የሚለውን በመያዝ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካቾች ክስ ያቀረቡት የውርስ መሬት ለመረከብ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው የቤተሰብ አባል በመሆኑ የውርስ መሬቱ ወራሽ መሆናቸውን እና አውራሻቸው በሞቱበት ጊዜ በሥራ ላይ በነበረው ሕግ መሰረት ቀዲሚ ወራሽ መሆናቸውን ገልጸው ተከራክረዋል። bx!T×ùà yFT/B/@R ?G bxMSt¾W xNqA (Title) xg¶t$ yWRS SR›T XNÁT XNdçn ZRZR yçn# dNïCN yÃz# yWRS ?G DNUg@ãC tdNGgW Yg¾l#ÝÝ Xnz!H Sl WRS ytdngg#TN DNUg@ãC xq‰rA SNmlkT bxND bk#L yWRS ?G -Q§§ m¶ dNïC yçn# -Q§§ y?G DNUg@ãC Ãl#T s!çN bl@§ bk#L dGä yàC WRS bn#²z@ wYM Ãln#²z@ y¸t§lFbTN mNgD bZRZR y¸ÃSqM-# Sl WRS NBrT xStÄdR X yWRS NBrT XNÁT lw‰ëC XNd¸kÍfL y¸zrZ„ L† y?G DNUg@ãC tdNGgW Yg¾l#ÝÝ bFT/B/@R ?g# WRS Sl¸kfTbT g!z@ SF‰ lw‰ëC l!t§lû Sl¸Cl# yàC mBT GÁ¬ãC X àCN lmWrS Sl¸ÃSfLG ClÖ¬ kF¼?¼q$. 826(841 ytdngg#T y?G DNUg@ãC -Q§§ yWRS ?G DNUg@ãC mçÂcW bGLA tmLKaLÝÝ WRS äTN msrT xDR¯ mBT GÁ¬ kxND sW wdl@§ sW y¸t§lFbT y?G h#n@¬ nWÝÝ yF¼?¼q$. 1 msrT sW ktwldbT qN xNSè XSkätbT qN DrS y?G mBT xlWÝÝ Slz!H bäT MKNÃT xND sW ÃlW mBT y¸Ìr_ Slçn btlY kNBrT UR ytÃÃzW QM y¥N çñ Yq§L y¸lW XNÄ!h#M bäT bXN_L_L y¸qrW mBT MN YçÂL l¸l#T Ãq&ãC M§> yMÂgßW kWRS ?G nWÝÝ bF¼?¼q$. 826¼2¼ msrT bàC äT MKNÃT y¸Ìr-# μLçn bStqR bWRS WS y¸gß# yàC ynb„ mBèC GÁ¬ãC lw‰ëC ln#²z@ ÆlSõ¬ãC Yt§lÍl#ÝÝ ynz!H mBèC GÁ¬ãC mt§lF yWRS mkfTN wYM mjmRN yGD Y§LÝÝ yàC WRS tkft yMNlW àC bäT s!lY b?YwT zmn# s!ñR bnbrW mBt$ t-Qä Ãf‰W NBrT Ælb@T b¥Èt$ làC GÁ¬M t-ÃqE y¸çN Ælmñ„ yxNÄ!T xgR ?G yàCN mBT GÁ¬ ll@lÖC sãC ¼w‰ëC¼ l¥St§lF Sl àC WRS xStÄdR Tk#rT s_è _b” ¥DrG mjm„N yMÂmlKTbT nWÝÝ yx!T×ùà ?G bz!H §Y ÃlWN xÌM SNmlkT xND sW yät xNdçn bätbT g!z@ ê mñ¶Ã |F‰ bçnbT ï¬ yàC WRS Ykf¬L b¥lT yFT/B/@R ?G q$R 826/1/ YdnGULÝÝ kz!H y?G DNUg@ yMNrÄW yx!T×ùà yWRS ?G Sl àC NBrT“ yWRS xStÄdR Tk#rT mS-T _b” ¥DrG y¸jMrW àc$ kätbT g!z@ jMé MNM xYnT yg!z@ KFtT úYtW mçn#N nWÝÝ àC HYwt$ ¥lû ktrUg-bT QAbT jMé yàC WRS Ykf¬LÝÝ yàC WRS y¸kfTbTN g!z@ b?G mwsn# GLA bçn DNUg@ ¥Sqm-# àCN y¸wRsW sW àC kät b“§ bSNT g!z@ bHYwT yñr nW y¸lWN Ãq& lmmlS bl@§ xnUgR yàC w‰ëC Xn¥N XNdçn# l¥rUg mRÄt$ nWÝÝ bFT/B/@R ?UCN àCN lmWrS àC s!äT bHYwT mñR xSf§g! mçn# bF¼?q$.830 tdNGÙLÝÝ yàC WRS y¸kftW àC bätbT QAbT bmçn# àC kät b“§ bWSN g!z@M ²ÓÄ yät sW àCN wRî XNdät Yö-‰LÝÝ Slz!H yàC WRS y¸kfTbTN g!z@ Tk#rT s_è የ?g# DNUg@ bGLI ¥mLkt$ yw‰>nT ClÖ¬ን X bl@lÖC g#Ä×C §Y ytdngg#TN y?G DNUg@ãC l¥SfoM YrÄLÝÝ yàC WRS mkfT y¸lW ANs húB àC bHYwT XÃl ynbrW yFT/B/@R mBT GÁ¬ ytÌr- yàC NBrT bF¼?¼q$.942 btdnggW m\rT XNd xND L† NBrT tö_é /estate/ ?G _b” ¥DrG mjm„N y¸ÃmlKT YHM yàC HYwT ያlfbT QAbT jMé y¸kÂwN mçn#N y¸ÃúY nWÝÝ ከአመልካቾች የክስ አቤቱታ እንደተረዲነው አውራሾቻቸው የሞቱት እንደ ቅደም ተከተላቸዉ አባታቸው አቶ ላቀው ሙለጌታ የካቲት 30 ቀን 1996 ዓ/ም ሲሆን ወላጅ እናታቸው ወ/ሮ ሙለነሽ አስፊው ደግሞ ነሀሴ 04 ቀን 2009 ዓ/ም ነው። አመልካቾች በሰበር አቤቱታቸው የአባታቸውን የውርስ ድርሻ መሬት ያገኙ መሆኑ እና ተጠሪ የያዙት የእናታቸውን የውርስ ደርሻ መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል።
ተጠሪም ከስር ጀምሮ የሚከራከሩት የሟች ሙለነሽ አስፊው የቤተሰብ አባልና ወራሽ መሆናቸውን በመግልጽ በአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 51/1999 አንቀጽ 11(7)(ለ) መሰረት ቀዲሚ ወራሽ ነኝ በማለት ነው። አመልካቾች ጉዲዩ በአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት ሉገዛ እንደሚገባ ጠቅሰው ተከራክረዋል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የዉርስ ጉዲይ የገጠር መሬትን የሚመለከት ሲሆን፣ የወራሽነት መብት የሚተላለፍላቸዉን ሰዎች ማንነት አስመልክቶ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ዉጭ (ይህ በልዩ ሁኔታ በገጠር መሬት አዋጅ የተመለከተ በመሆኑ) ያለት ላልች ከዉርስ ጋር በተያያዘ በፍትሐብሕር ህጉ ላይ የተመለከቱ ደንቦች እና መርሆዎች ከገጠር መሬት ወራሽነት ጋር በተያያዘም እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚነት እንዲላቸዉ የሚታወቅ ነዉ። ዉርስ የሚከፈትበትን ሁኔታ አስመልክቶ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 826(1) ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለዉ ዉርስ የሚከፈተዉ አዉራሹ በሞተበት ጊዜ እና ቦታ መሆኑን ነዉ። መብት የሚመነጨዉ ከህግ መሆኑም እሙን ነዉ። ስለሆነም አንድ ሰዉ የሟች ወራሽ መሆን ያለመሆኑ የሚረጋገጠዉ ሟች በሞተበት ጊዜ በስራ ላይ ያለዉን ህግ መሰረት በማድረግ ይሆናል። የወራሽነት ማረጋገጫ፣ ከስሙም መገንዘብ እንደሚቻለዉ፣ በህግ የተገኘን መብት ለማረጋገጥ የሚሰጥ እንጂ በእራሱ መብት የሚሰጥ አለመሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል።
ለዚህ ጉዲይም ሆነ በተለያዩ የሰበር ችልት ውሳኔዎች ለተነሳው ጭብጥ መሰረት የሆነው የትኛው ሕግ የተከራካሪ ወገኖችን መብት ለመወሰን መዋል አለበት የሚል ሆኖ እናገኘዋለን። በአጠቃላይ የውርስ ሕግን መሰረት በማድረግ የውርስ ጉዲይ እልባት ለመስጠት ቢሞከር ብያኔው መሰረት የሚያደርገው በሕግ የታወቀን ዝምድና/ግንኙነትን ነው። አመልካቾች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 996 መሰረት አድርገው መብት እንዲገኙ የተከራከሩ ሲሆን የተጠቀሰው የምስክር ወረቀት የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ የፍ/ሕ/ቁ.
997 ወራሹ በምስክር ወረቀቱ እንደተገለጸው ወራሽ እንደሆነ ግምት ይወሰዲል። ሆኖም በሕጉ ታሳቢ የተደረገው የምስክር ወረቀቱ ወራሽ መሆንን ከማረጋገጥ ባለፈ የወራሹን ድርሻ የሚያመለክት መሆኑን እንደሆነ ከቁጥር 996 ንባብ መረዲት የሚቻል ቢሆንም በአሰራር ደረጃ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ማረጋገጫ ዝምድናን መሰረት አድርጎ ወራሽ መሆንን ከማወቅ የዘለለ አይደለም። በፍ/ሕ/ቁ.946 እና ተከታዮቹ መሰረት ተጠሪን ባሳተፈ መልኩ ወርስ ተጣርቶ የወራሾች ማንነትና የወራሾች የዉርስ ሀብት ድርሻ ተለይቶ በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 996 መሰረት ተገልጾ የተሰጠ የወራሽነት ምስክር ወረቀት ባለመሆኑ አመልካቾች የወራሽነት ማስረጃዉን በመጥቀስ የሚያቀርቡት ክርክር የሚሰጣቸዉ የተለየ መብት የለም።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተነሳው ክርክር ለውርስ መብቱ መሰረት የሆነው ሕግና ጉዲዩ የተከሰተበትን ውርሱ የተከፈተበትን ጊዜ ከግምት በማስገባት አግባብበነት ያለውን ህግ መለየት ያስፈልጋል። አመልካቾች ጉዲዩ በአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ በአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 133/1998 መሰረት ቀዲሚ ወራሽ ነኝ በማለት ነው። በፍሬ ነገር ደረጃ ተጠሪ ወራሽ መሆናቸው እንደተረጋጋጠ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲላቸው በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። አመልካቾች የመብት ጥያቄ የሚያነሱት በአዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት በመሆኑ ጥያቄው የሚሆነው ይህ አዋጅ ከመወጣቱ በፉት የተከናወኑ ተግባራት እና የተገኘ መብት ላይ ተፈጻሚ ላሆን መቻለን የሚመለከት ነው። ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ጉዲይ ላይ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተለያየ አቋም የተያዘ በመሆኑ የተነሳውን የሕግ ጥያቄ በዝርዝር ማየት ያስፈልጋል።
በመርሕ ደረጃ ሕጎች የሚኖራቸው ውጤት የወደፉት ነው። በኢፋድሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 22 የወንጀል ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ እንደማይሰራ ስለተደነገገ የወንጀል ጉዲዩችን በተመለከተ ወደ ኋላ ተፈጻሚ የሚሆን ሕግ ኢ-ሕገመንግስታዊ ይሆናል። የፍትሐብሕር ጉዲዩችን በተመለከተ ምንም እንኳ ከልካይ የሕገ መንግስት ድንጋጌ ባይኖርም ተቀባይነት ያለው የሕግ አስተምሮ ሕጎች ተፈጻሚ መሆን ያለባቸው ወደፉት ብቻ እንጂ አስቀድሞ የተገኙ መብቶችን መቀየር የለባቸውም የሚል ነው። ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም ከሚለዉ አጠቃላይ መርህ (the principle of non-retroactivity of laws) አንፃር ስንመለከተውም ሕግ በዜጎች መካከል ያለዉን ግንኙነት ለመቆጣጠር ሲባል በሕግ አዉጪዉ አካል የሚወጣ ነዉ። ህግ የሚወጣዉም ህጉ በስራ ላይ ባለበት ወቅት በዜጎች መካከል ያለዉን ወይም ወደ ፉት የሚፈጠረዉን ግንኙነት ለመቆጣጠር ወይም ለመዲኘት በመሆኑ ህጉ ከመዉጣቱ በፉት ወይም ከተሻረ በኋላ በተፈጠረ/በሚፈጠር ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም። ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለዉም መርህ ከዚሁ የመነጨ ሲሆን፣ መሰረተ ሃሳቡም አንድ ህግ ተፈፃሚ የሚሆነዉ ህጉ በስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለተፈጠረ መብትና ግዳታ ወይም ፍሬ ነገር ነዉ የሚል ነዉ። በልላ አገላለጽ አንድ ህግ ተፈፃሚ መሆን የሚጀምርበትን ጊዜ አስመልክቶ በህግ አዉጪዉ ከተደነገገዉ ቀን በፉት ለተፈጠሩት ክስተቶች ወይም መብትና ግዳታዎች ተፈፃሚነት አይኖረዉም የሚል ሃሳብ ያለዉ ነዉ። ይህ መርህ ከህግ የበላይነት መገለጫዎች ዉስጥ አንደ ነዉ። ስለሆነም አንድ መሰረታዊ ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ እንዱሰራ ህግ አዉጪዉ እራሱ በልዩ ሁኔታ ካላመላከተ በስተቀር፣ ፍርድ ቤት ወይም ላላ የዲኝነት ስልጣን የተሰጠዉ አካል ለያዘዉ ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉን መሰረታዊ ህግ (substantive law) ሲወስን መሰረት ሉያደርግ የሚገባዉ ወይም መሰረት እንዱያደርግ የሚጠበቅበት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ በተፈጠረበት ጊዜ በስራ ላይ የነበረዉ ህግ ላሆን ይገባል። ስለሆነም ድርጊቱ ወይም መብትና ግዳታ በተፈጠረበት ጊዜ የነበረዉ ህግ በልላ ህግ የተተካ ሆኖ ሲገኝ እና ክርክሩ ለፍርድ ቤት ወይም ለዲኝነት ሰጪ አካል የቀረበዉ አዱሱ ህግ በስራ ላይ ከዋለ በኋላ ሆኖ ከተገኘ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን መምራት እና ዉሳኔ መስጠት ያለበት በተሻረዉ ህግ መሰረት ይሆናል፤
ክርክሩ አዱሱ ህግ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለፍርድ ቤት መቅረቡ ጉዲዩ በአዱሱ ህግ መሰረት እንዱመራ ምክንያት ላሆን አይገባም። ይህን ማድረግ ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለዉን የህግ መርህ የሚጥስ ከመሆኑም በላይ የህግ የበላይነት እንዲይረጋገጥ ወይም እንዱሸረሸር ምክንያት ይሆናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልቱ በተያዘው ጭብጥ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል የተለያየ አቋምን የያዘ ትርጉም የሰጠ ሲሆን በሰበር መዝገብ እና ላልች መዛግብት ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ በሥራ ላይ በነበረው ሕግ እንጂ በክርክሩ ጊዜ አዱስ ሥራ ላይ በዋለው ሕግ አይደለም በማለት ትርጉም ሰጥቷል። በልላ በኩል ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ እና በላልች መዛግብት ላይ በሰጠው ትርጉም ለውርስ ክርክር ተፈጻሚነት ያለው ሟች በሞተበት እና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ የነበረው ህግ ሳይሆን ክርክሩ በቀረበ ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት ላሆን ይገባል በማለት ትርጉም መስጠቱ በአንድ ጭብጥ ላይ የተለያየ እና የሚቃረን ትርጉም በመሆኑ ወጥ የሆነ ትርጉም መስጠት አስፈላጊ ነው። ከላይ በፍርድ ሐተታው እንደተገለጸው ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጠው ትርጉም ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለው መርሕ እና በፍ/ሕ/ቁ. 826(1) አግባብ የተመለከተው ዉርስ የሚከፈተዉ አዉራሹ በሞተበት ጊዜ እና ቦታ መሆኑን የሚለውን ያላገናዘበ በመሆኑ ትርጉሙ ሉለወጥ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም የውርስ ክርክር ወራሾቹ ሆነ ቀዲሚ ወራሾች እነማን ናቸው የሚለው ሉወሰን የሚገባው አውራሽ በሞተበት ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት ላሆን ይገባል ብለናል።
በተያዘው ጉዲይ ወ/ሮ ሙለነሽ አስፊው ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩበት ወቅት በ2009 ዓ/ም በክልለ ስራ ላይ የነበረዉ አዋጅ ቁጥር 133/98 ነዉ። የመሸጋገሪያ ድንጋጌን አስመልክቶ በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 57 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ በላልች ህጎች የተቋቋሙ መብቶች እና ግዳታዎች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተጋጩ ድረስ ተፈፃሚነታቸዉ እንደሚቀጥል እንዱሁም አዋጁ ከመዉጣቱ በፉት በመታየት ላይ ያለ ጉዲዮች በተጀመሩበት አግባብ እልባት እንደሚያገኙ የሚደነግግ ቢሆንም፣ ከዉርስ ጋር በተያያዘ ለሚነሳ ክርክር ይህ አዋጅ ወደ ኋላ ተመልሶ እንደሚሰራ አያመላክትም። በአመልካች የተነሳው ጥያቄ ተጠሪ በቀድሞው አዋጅ መሰረት መሬቱን አልተረከበውም፤ በእጁ አላደረገውም ስለዚህ በቀድሞው አዋጅ የተመሰረተ መብት የለውም እንዱሁም ተጠሪ በመሬቱ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ያገኘው በ05/12/2010 ዓ/ም ሲሆን ይዞታውን የተረከበው በጥር ወር 2011 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት መሆኑን በተመለከተ የተነሳው ክርክር መሬቱን መረከብ በመሬት ላይ ለሚኖር መብት መሰረት ባለመሆኑና ተፈጻሚ የሚሆነውን ሕግ ለመወሰን ስለማይረዲ ይህ ክርክር ተቀባይነት የለውም። በልላ በኩል አመልካቾች ልጆች ስለሆንን ተጠሪ ደግሞ የቤተሰብ አባል ስላልሆነ በአዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት አመልካቾች ወራሾች ነን በሚል የሚቀርበው ክርክር ከላይ በዝርዝር እንደቀረበው ይህ የሚወሰነው አግባብ ባለው ሕግ እንጂ አንደ ተከራካሪ ወገን ለክርክሩ መሰረት ባደረገው ሕግ ባለመሆኑ አግባብነት የለውም።
ስለሆነም አመልካቾች ሟችን ለመዉረስ መብት ያላቸዉ መሆን ያለመሆኑ የሚወሰነዉ በአዋጅ ቁጥር 133/98 መሰረት ይሆናል። ተጠሪ የሟች ሙለነሽ አስፊው ልጅ ባይሆኑም የቤተሰብ አባል እና ወራሽ ስለመሆናቸው መረጋገጡን የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት በፍርድ ሀተታው አስፍሯል። ይህም ተጠሪ በአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 51/1999 አንቀጽ 11(7)(ለ) መሰረት ወራሽ መሆናቸውን የሚያሳይ ሲሆን አመልካቾች የሟች ልጆች ሲሆኑ ራሱን ለማስተዲደር የግል መሬት ያለው ወራሽ የሆነ ልጅ በደንብ ቁጥር 51/1999 አንቀጽ 11(7)(ሐ) መሰረት ወራሽ ነው፤ ነገር ግን በአወራረስ ቅድመተከተል ተጠሪ ቀዲሚ ወራሽ በመሆናቸው ተጠሪ በውርስ የያዘቱን መሬት ሉለቁ አይገባም ተብል በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁጥር 03-11116 ሕዲር 22 ቀን 2012 ዓ/ም፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ 5 ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ/ም እና የቀይት ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 05 ቀን 2011 ዓ/ም ተጠሪን አስመልክቶ የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ላይ ለውርስ ክርክር ተፈጻሚነት ያለው ሟች በሞተበት እና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ የነበረው ህግ ሳይሆን ክርክሩ በቀረበ ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት ላሆን ይገባል በማለት የሰጠው ትርጉም ተለውጧል።
የውርስ ክርክር ወራሾቹ ሆነ ቀዲሚ ወራሾች እነማን ናቸው የሚለው ሉወሰን የሚገባው አውራሽ በሞተበት ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት ላሆን ይገባል በማለት ትርጉም ተሰጥቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.