የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ በወራሾች መካከል የውርስ ሀብት ክፍፍል ስምምነት ሉፈፀም የሚገባበትን ፍርማሉትን አስመልክቶ ግልጽ የህግ ድንጋጌ ባይኖርም የሚደረገው ስምምነት በተስማሚዎቹ መካከል መብትና ግዳታን የሚፈጥር ውል እንደመሆኑ መጠን የሚደረግ የክፍፍል ወይም የማዚወር ስምምነቶች ሁለ በጽሐፍ በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዜገብ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት ላደረግና በሚመለከታቸው ወራሾች የተፈረመበት ላሆን የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1079፣ 1719፣1677 እና የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1723(2)
No summary available.
መስከረም 27/2014 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ዘውዱ እረዲ 2ኛ. ወ/ሮ ጥሩወይ በላይ እረዲ 3ኛ. አቶ ጌታሁን ተረፈ እረዲ 4ኛ. ወ/ሮ እመቤት አማረ እረዲ ተጠሪ፡- ወ/ሮ የሹምነሽ ስዩም መዜገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
በዙህ መዜገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የውርስ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአሁን አመልካቾች በሰቆጣ ወረዲ ፍ/ቤት በአሁን ተጠሪ ላይ ጥቅምት 14/2011 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱም ጭብጥ ከአያታቸው ቄስ ረዲ ተክለሃይማኖት በውርስ የተላለፈላቸውን ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዜርዜር ውስጥ የተጠቀሰውን በ245.8 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ አንድ ህድሞ ክብ ቤት የአሁን ተጠሪ ከነበረባቸው የቤት ችግር በመነሳት እንዱኖሩበት ፈቅደዉላቸው በኋላም በቤቱ ላይ በ2007 ዓ.ም በወራሾች ስም ካርታ አስወጥተው ለመከፊፈል ተጠሪ እንዱለቁላቸው ሲጠይቋቸው ያለምንም መብትና ጥቅም አለቅም ብለው ይዘው የሚገኙ መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው እንዱለቁላቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
በዙሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት ተጠሪ ጥቅምት 23/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ የስረ ነገር ክርክር አቅርበዋል። መቃወሚያውም ሁለት ነው። የመጀመሪያው ቄስ ረዲ ተ/ሒይማት ከሞቱ በኋላ 1ኛ አመልካች፣ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት አመልካቾች ወላጆች እና ወላጅ እናቴ ወ/ሮ ውዳ ረዲን ጨምሮ በሰባት ወራሾች መካከል የውርስ ሀብት ክፍፍል ተደርጓል፤ በክፍፍለም ወላጅ እናቴ ቀድሞኑም ከአባቸው ቄስ ረዲ ጋር ክስ በቀረበበት ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበረ ሲሆን አባታቸውን ጦረው፣ ሲታመሙም አስታመው፤ ከሞቱ በኋላ ደግሞ አስፈላጊውን ሃይማኖታዊ ስርዓት ሁለ የፈፀሙላቸው መሆኑ ከግንዚቤ ገብቶ አሁን ክስ የቀረበበት ቤት ለእናቴ በክፍፍል እንዱደርስ እና ቀሪውን ንብረት ላልች ወራሾች እንዱካፈለት በአስማሚ ሽማግላዎች ፉት ስምምነት ፈፅመዋል፤ በስምምነቱ መሰረት ወላጅ እናቴ ክስ የቀረበበትን ቤት ለ25 ዓመታት ኖረውበት እርሳቸው ከሞቱ በኋላም በውርስ ተላልፍልኝ ለ7 ዓመታት ስጠቀምበት የነበረ ነው፤ በመሆኑም ክሱ በወራሾች መካከል በስምምነት ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው። ሁለተኛው ደግሞ የውርስ ሀብት ክፍፍል ከተደረገ ከሶስት ዓመት በኋላ ክስ/መቃወሚያ ላቀርብበት የማይችል በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል ነው። በአማራጭ የስረ ነገር ክርክር ደግሞ ክስ የቀረበበት ንብረት ከእናቴ በውርስ የተላለፈልኝ ሆኖ እያለ አመልካቾች በመመሳጠር ሆነ ብለው የተጠሪን የውርስ ሃብት አካተው ካርታ ያወጡበት በመሆኑ ልለቅ አይገባም የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም ክሱ የቀረበው በስምምነት ባለቀ ጉዲይ ላይ ነው? ወይስ አይደለም?
በሚል ጭብጥ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ሰምቷል። በዙሁ መሰረት በተጠሪ በኩል የቀረቡት ምስክሮች የውርስ ክፍፍል ስምምነቱን መርተዋል የተባለት ሽማግላዎች መሆናቸውን፤
በሰጡት ቃልም የግራ ቀኙ አያት በሞቱ ጊዛ የግራ ቀኙን ወላጆች ጨምሮ በሰባት ወራሾች መካከል በስምምነት የውርስ ሀብት ክፍፍል ያደረጉ መሆኑን፤ በስምምነቱ መሰረትም አሁን ክስ የቀረበበትን ቤት ለአሁን ተጠሪ ወላጅ እናት እንዱደርስ እና የተቀረውን የውርስ ሀብት ላልች ወራሾች ለመካፈል ተስማምተው በዙሁ መሰረት ጉዲዩን በስምምነት የጨረሱ ስለመሆኑ ሲመሰክሩ በአመልካቾች በኩል የቀረቡት ምስክሮች ደግሞ ክፍፍል መደረጉን አናውቅም በማለት የተናገሩ ስለመሆኑ መዜግቦ በሰጠው ብይን “የክፍፍል ስምምነቱ በቃል የተደረገ ቢሆንም በግራ ቀኙ ወላጆች መካከል የውርስ ሀብት ክፍፍል ስምምነት የተደረገ ስለመሆኑ ተረጋግጧል፤ የውርስ ሀብት ክፍፍልን አስመልክቶ በህግ ተለይቶ የተቀመጠ ፍርማሉቲ የለም፤ ክሱም በስምምነት በተጠናቀቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው” በማለት ውድቅ አድርጓል።
ይህንኑ ብይን በይግባኝ የተመለከተው የዝኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ ስምምነቱ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተደረገ ሲሆን የፍ/ብ/ህ/ቁ/1567፣ 1568 እና 1723 በሚደነግገው መሰረት በፅሁፍ የቀረበ ስምምነት ባለመኖሩ ተቀባይነት የለውም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሮ በይርጋ መቃወሚያው ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ እንዱወስን፤ ክሱ በይርጋ የማይታገድ ከሆነ በክሱ ስረ ነገር ክርክር ላይ አከራክሮ የመሰለውን እንዱወስን በነጥብ መልሷል። የአሁን ተጠሪ በተራቸው ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ለውርስ ሀብት ክፍፍል ስምምነት በህግ ተለይቶ የተቀመጠ ልዩ ፍርማሉት የለም፤ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተጠቀሱት የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1567፣ 1568 እና 1723 የውል ጉዲይን እንጂ የውርስ ጉዲይን የሚመለከቱ ባለመሆናቸው ለጉዲዩ አግባብነት የላቸውም በማለት የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤት ብይን አፅንቷል። ይኸው ውሳኔ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ተቀባይነት አግኝቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ህዲር 30/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዙህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም አመልካቾች የሟቹ ወራሽ ስለመሆናችን የወራሽነት ማረጋገጫ በማውጣት እነ ቄስ ተረፈ እረዲ በሚል በ2007 ዓ.ም በስማቸው በማዝር ካርታ አሰርተው እስከ 2012 ዓ.ም ግብር እየገበሩ በጋራ የያዘት እና ያልተከፊፈለ የውርስ ሀብት ስለመሆኑ የሰነድና የሰው ማስረጃ አቅርበው አሰምተው እያለ በአግባቡ ሳይታይ የወረዲው ፍ/ቤት በብይን መዜጋቱ ትክክል ነው በሚል መወሰናቸው አግባብ አይደለም፤ ተጠሪ ቤት ስለላላቸው ቤቱን እየጠበቁ እንዱኖሩበት የተደረገ እንጅ ከቤቱ ላይ መብት የላቸውም፤ ተደረገ የተባለው ስምምነትም በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተደረገ ሲሆን ስምምነቱን የሚገልፅ የቀረበ የሰነድ ማስረጃ የለም፤ ይህ በላለበት ወንድም እና የአባታቸውን ወገን አቅርበው ስምምነት ነበር በመባለ ብቻ ጉዲዩ በስምምነት ያለቀ ነው ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለ ምክንያት ተጠሪ የፅሁፍ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል። በዙሁ አግባብ ተጠሪ መጋቢት 22/2013 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። ፍሬ ቃለም አንድን ፍሬ ነገር ለማስረዲት ተለይቶ የተመለከተ ማስረጃ እንዱቀርብ ህጉ ካላስገደደ በቀር ፍሬ ነገሩን በማንኛውም የማስረጃ አይነት ማስረዲት የሚቻል ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/47551 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፤ የውርስ ሀብት ክፍፍል ስርዓትን አስመልክቶ በወራሾች መካከል በሚደረግ ስምምነት ብቻ ሉፈፀም የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1079 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስር ከመገለፁ ውጭ ክፍፍለ ሉፈፀም ስለሚገባበት የተለየ ፍርማሉቲ አልተመለከተም፤ የአያታችን የውርስ ሀብት ክፍፍል አስመልክቶ ወላጆቻችን በራሳቸው በመረጧቸው ሽማግላዎች ስምምነት ተደርጎበት ክስ የቀረበበት ንብረት ለወላጅ እናቴ ስለመድረሱ የወረዲው ፍርድ ቤት በማስረጃ አረጋግጦ ወስኗል፤
ስለ ውርስ ሀብት ክፍፍል በህግ ተለይቶ የተመለከተ ፍርማሉቲ በላለበት የዝኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸውን እና ስለ የማይንቀሳቀስ ሀብት ርስት ምዜገባ የተመለከቱትን የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1567 እና 1568 ድንጋጌዎችን ጠቅሶ የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔን መሻሩ አግባብ ባለመሆኑ የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ተረድተው በማረማቸው የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም፤ አመልካቾች ክስ ያቀረቡት የውርስ ሀብት ክፍፍለ ከተደረገ ሶስት ዓመት በኋላ በመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1106 መሰረት ከመነሻው በይርጋ የሚታገድ በመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው። አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በመስጠት ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ክስ በስምምነት ባለቀ ጉዲይ ላይ የቀረበ ነው በሚል በመወሰኑ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመኖሩ ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ ተመርምሯል።
እንግዱህ ከክርክሩ አመጣጥ መረዲት እንደሚቻለው የስር ፍርድ ቤቶች የተለያዩት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ በወራሾች መካከል የውርስ ሀብት ክፍፍል ስምምነት ሉፈፀም የሚገባበትን ፍርማሉትን አስመልክቶ ነው። በመሰረቱ የውርስ ንብረት ክፍፍል አሰራር በወራሾች መካከል በሚደረግ ስምምነት፣ በወራሾቹ መካከል ስምምነት ከላለ ደግሞ ከእነርሱ መካከል አንደ ተግቶ ያሰናዲውን የክፍያ ሐሳብ ለዳኞች አቅርቦ በማፀደቅ ሉከናወን እንደሚችል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1079 ይደነግጋል። በእርግጥ ህጉ የውርስ ሀብት ክፍፍል በዙህ መልኩ ሉከናወን እንደሚችል ከመደንገጉ ውጭ በወራሾች መካከል የሚደረገው የክፍፍል ስምምነት ሉፈፀም ስለሚኖርበት ፍርማሉቲ በግልፅ አላስቀመጠም። እናም ስለክፍፍለ የተለየ ፍርም አለመቀመጡ የስምምነቱ ፍርም አፈፃፀም ለወራሾች የተተወ ነፃነት ነው ልባል ይችል ይሆናል። ሆኖም በዙህ መልኩ የሚደረገው ስምምነት በተስማሚዎቹ መካከል መብትና ግዳታን የሚፈጥር ውል እንደመሆኑ መጠን የስምምነቱ ፍርማሉቲ ስምምነት ከሚደረግበት ንብረት ዓይነት እና ባህሪ አኳያ መታየት ያለበት ጉዲይ ነው።
በዙሁ አግባብ በፍትሐብሕር ህጉ አምስተኛ መፀሒፍ ውስጥ ስለልዩ ውልች የተደነገገው ልዩ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ከውልም ሆነ ከውል ውጭ የሚመነጭ ማናቸውም ስምምነት በፍትሐብሕር ህጉ አራተኛ መፀሀፍ ውስጥ ስለውልች በጠቅላላው በተደነገገው መርህ መሰረት የሚመራ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1677 ድንጋጌ ይዘት ያሳያል። ስለውልች በጠቅላላው ከሚደነግገው የህጉ ክፍል ውስጥ ከተመለከቱት መሰረታዊ መርሆዎች ውስጥ አንደ በቁጥር 1719 ስር የውል ፍርማሉቲን አስመልክቶ የተቀመጠው መርህ ነው። በዙህ ድንጋጌ መሰረት በህግ በልዩ ሁኔታ የውል ፍርም ካልተመለከተ በቀር ተዋዋይ ወገኖች ስምምነታቸውን በተስማሙበት አኳኋን ሉፈፅሙ እንደሚችለ ተመልክቷል። የተዋዋይ ወገኖች የስምምነታቸውን ፍርማሉት የመወሰን ነፃነት ከሚገደብበት ልዩ ሁኔታ ወይም በስተቀር ውስጥ አንደ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ስምምነትን አስመልክቶ ስለመሆኑ በቁጥር 1723 ስር ተመልክቷል። በዙሁ አግባብ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስምልክቶ የሚደረግ የክፍፍል ወይም የማዚወር ስምምነቶች ሁለ በጽሐፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዜገብ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት መደረግ እንደሚገባው የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1723(2) ድንጋጌ ያስገነዜባል።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስምልክቶ የሚደረግ ስምምነት በዙህ አይነቱ ጥብቅ የአፈፃፀም ስርዓት መሰረት እንዱመራ የተፈለገበት የራሱ ህጋዊ እና አስተዲደራዊ ምክንያት እንዲለው መረዲት ይቻላል። ከህግ አኳያ ንብረቱ በተፈጥሮው ዘለቄታዊ ባህሪ ያለው በመሆኑ ምክንያት በእንደዙህ ዓይነት ንብረት ላይ የሚፈጠር ማናቸውም መብት የሶስተኛ ወገኖችን መብት እንዲይጎዲ ተገቢውን ቁጥጥር እና ጥንቃቄ ለማድረግ ነው ብል መውሰድ ይቻላል። ከአስተዲደር አንፃር ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም የማይንቀሳቀስ ንብረት በህግ አግባብ በተቋቋመ መንግስታዊ አስተዲደር ክፍል ዘንድ መመዜገብ ያለበት እና በንብረቱ ላይ የሚደረግ ማናቸውም የመብት መለዋወጥ መረጃዎች ሁለ በሰነድ መደራጀት ያለበት ስለመሆኑ ስለ የማይነቀሳቀስ ንብረት መዜገብ በሚደነግገው የፍትሐ ብሓር ህጉ አንቀፅ 10 ከቁጥር 1553 ጀምሮ በዜርዜር ተመልክቷል።
በእርግጥ የፍትሐብሕር ህጉ አንቀፅ 10 ስራ ላይ የሚውልበት ቀን በነጋሪት ጋዛጣ እስኪታወጅ ድረስ ተፈፃሚ እንደማይሆን በፍ/ብ/ህ/ቁር 3363(1) ስር ተመልክቷል። ይህ እስከሚሆን ድረስም በምትኩ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 3364 - 3367 ድረስ የተመለከቱት ልማዲዊ ደንቦች ተግባራዊ የሚደረጉ ስመሆኑ በቁጥር 3363(2) ስር ተመልክቷል። በጊዛ ሂደትም መሬትን እና ላልች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ምዜገባ እና አስተዲደር የሚመለከቱ የአስተዲደር መዋቅሮች በህግ እንዱቋቋሙ ተደርጎ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ ስምምነቶች ላይ አስተዲደራዊ ቁጥጥር እየተደረገበት ያለ ለመሆኑ በችልት ግንዚቤ ሉወሰድበት የሚችል ጉዲይ ነው። አግባብ ያላቸው የአስተዲደር አካላት በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተደረገን ስምምነት ተቀብለው ለመመዜገብ እና በስምምነቱ መሰረት በንብረቱ ላይ ተጓዲኝ መብት ለመፍጠር ስምምነቱ በህጉ በተመለከተው ልዩ ፍርም ተፈፅሞ ላቀርብላቸው ይገባል ማለት ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ ለክርክር ምክንያት የሆነው የማይንቀሳቀስ ንብረት ከ1ኛ አመልካች አባት እንዱሁም ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት እና ከተጠሪ አያት በተዋረድ የመጣ የውርስ ሀብት ስለመሆኑ ግራ ቀኙን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ይልቁም የሚከራከሩት ንብረቱን አስመልክቶ በወራሾች መካከል የተደረገ የክፍፍል ስምምነት ስለመኖሩ ላይ ነው። የተጠሪ መከራከሪያ ክስ የቀረበበት ቤት የአያታችን የውርስ ሀብት ቢሆንም የውርስ ሃብቱን አስመልክቶ በወራሾች መካከል በቃል ስምምነት ክፍፍል ተደርጎ ቤቱ ለእናቴ ደርሷቸው ከእናቴ የተላለፈልኝ ነው የሚል ነው።
አመልካቾች በበኩላቸው ስምምነት ስለመኖሩ ክደዋል። እንዱያውም በንብረቱ ላይ በወራሾች ስም በጋራ የባለሀብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አውጥተው ግብርም በስማቸው እየገበሩ የሚገኙ መሆኑን ገልፀው ይከራከራለ። እንግዱህ ተጠሪ የሚጠቅሱት ስምምነት የተደረገው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በመሆኑ ከላይ በተሰጠው የፍርድ ትችት መሰረት ስምምነቱ ቢያንስ በፅሁፍ የተዘጋጀ እና በሚመለከታቸው ወራሾች የተፈረመበት ላሆን ይግባል። በዙህ መልኩ የቀረበ ስምምነት በላለበት እና ስምምነት ስለመኖሩም ከላልች ባለመብቶች ጭምር መከራከሪያ ቀርቦ ባለበት በህግ ረገድ እውቅና የሚሰጠው እና ህጋዊ ውጤት የሚኖረው ስምምነት አለ ለማለት አይቻልም። ክስ የቀረበበትን ንብረት አስምልክቶ ቀድሞ የተደረገ እና ህጋዊ ውጤት የሚኖረው ስምምነት ከላለ ደግሞ በዙሁ ምክንያት የአመልካቾች ክስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚዘጋበት አግባብ የለም።
ጉዲዩ ይህ በሆነበት የወረዲው ፍርድ ቤት የአመልካቾችን ክስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መዜጋቱ እና የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ መቀበላቸው ስምምነት ተደርጎበታል የተባለውን የውርስ ሀብት ባህሪ እና ከዙያው አኳያ የተቀመጠውን ተጓዲኝ አስገዲጅ የህግ ፍርማሉትን መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/03-27166 ላይ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሓረሰብ አስተዲዲር ዝን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/01037 ላይ ጥር 29/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ትዕዚዜ
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.