ኑዛዜ በመንፈስ መጫን የተደረገና ከሟች የቀድሞ ጋብቻ የሚወለደ ልጆችን በዝምታ ከውርስ የመንቀል ውጤት አለው በሚል ኑዛዜ እንዱሰረዝ ለቀረበ አቤቱታ ተናዛዡ የኑዛዜ ተጠቃሚዎች እንዲያበላልጥ በህግ የተቀመጠ ክልከላ ሳይኖር ሟች የሰፊ መብት ለወራሾች መስጠታቸው ኑዛዜው በመንፈስ መጫን የተደረገ፣ የላልች ወራሾችን መብት የጎዲና ውርሱ ተጣርቶ የእያንዲንደ ወራሽ ድርሻው ሳይታወቅ በውጤቱ ወራሾችን ከውርስ የነቀለ በመሆኑ ፈራሽ ነው የሚባል ስላለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 868
No summary available.
የሰበር መዝገብ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካቾች፡-
ተጠሪዎች ሟች ያደረጉት ኑዛዜ እንዱፈርስ የጠየቁት የሥር ፍርድ ቤት እንዲለው በንብረቶቹ ላይ ጉዲት ይደርሳል በሚል ሳይሆን በመንፈስ መጫን የተደረገ ነው በሚል በመሆኑ ኑዛዜው የተደረገው በመንፈስ መጫን ነው ወይስ አይደለም ከሚለው መከራከሪያ አንፃር መታየት ሲገባው በተከራካሪዎች ያልተነሳን መከሪከሪያ ለውሳኔ መሰረት መደረጉ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ቁጥር 182(2) ድንጋጌን የሚጥስ መሆኑን ፣ ኑዛዜው በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ሆኖ በንብረቱ ላይ ጉዲት ሉደርስ ይችላል ከተባለም የኑዛዜው ተጠቃሚዎች ዋስትና እንዱጠሩ ማድረግ ሲገባ ኑዛዜው ፈራሽ መባለ ፣ ኑዛዜው የተደረገው በሰነድች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት በመሆኑ ሟች ኑዛዜውን ሲያደርጉ ከተጽኖ ነፃ እንደነበሩ የሚገመት ሆኖ ኑዛዜው በመንፈስ መጫን የተደረገ መሆኑ በማስረጃ መረጋገጥ ሲገባው ኑዛዜው በመንፈስ መጫን የተደረገ ነው በማለት ድምዲሜ ላይ መደረሱ ፣ ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው በኑዛዜው 200 ካ.ሜ የቤት መሥሪያ ቦታ ስላገኙ ከውርስ ያልተነቀለ ሲሆን ኑዛዜው ከሩብ በላይ ጉዲት ስላደረሰብን ከውርስ ነቅልናል በማለት ያቀረቡት ክርክር ሳይኖርና ውርሱ ተጣርቶ ከሩብ በላይ ጉዲት ያደረሰባቸው መሆኑ ሳይጣራ ከሩብ በላይ ጉዲት ያደረሰባቸው በመሆኑ ሉሻር ይገባዋል መባለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሸሮ ሟች አቶ ስዩም ለማ ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ ሉፃና ይገባል ተብል እንዱወሰን አመልካቾች ህዲር 8 ቀን 2014 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት መዝገቡ ለችልት ላቀርብ ችሎል።
ጉዲዩ ኑዛዜ እንዱሰረዝ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በቀረበበት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በከሳሽነት አመልካቾች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል። ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- ተጠሪዎች ከሟች አቶ ስዩም ለማ የቀድሞ ሚስት የሚወለደ ልጆች እና የሟች ወራሾች መሆናቸውን ገልፀው ሟች ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ/ም ባደረጉት ኑዛዜ በጉለላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 10 ቁጥሩ 590 የሆነውን ቤትና የቤት ቁሳቁስ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች እንዱጠቀሙበትና እነሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ተጠሪዎች እንዲይጠይቁ በማለት ያደረጉት ኑዛዜ በመንፈስ መጫን የተደረገ ፣ የተጠሪዎችን በውርስ ሀብቱ የመጠቀም መብታቸውን የጣሰ ለሕግ ተቃራኒ የሆነና በዝምታ ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው መሆኑን ፣ የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 2-33759 አ.አ የሆነውን ተሸከርካሪ የኑዛዜው ተጠቃሚ ማን እንደሆነ ያልተገለፀ በመሆኑና በኦሮሚያ ክልል አስጎሪ አካባቢ የሚገኘው 1600 ካ.ሜ ቦታ ለተጠሪዎች ሰጥቻለሁኝ የሚለው የኑዛዜው ክፍልም ሉፈፀም የሚችል ባለመሆኑ ሟች ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ ፈራሽ እንዱሆን ጠይቀዋል። አመልካቾችም ለክሱ በሰጡት መልስ፡ተጠሪዎች በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው ይዞታ ተሰጥቷቸው እያለ ተነቅለናል ማለታቸው ተገቢ አለመሆኑንና የድርሻ ማነስ ከሆነ በክፍፍል ጊዜ የሚታይ መሆኑን ፤ ማስታመምና መንከባከብ ኑዛዜ ለማድረግ የሚያነሳሱ ምክንያቶች እንጂ የመንፈስ መጫን መኖሩን የሚያሳዩ አለመሆናቸውንና ለሕግ ተቃራኒ አለመሆኑን ፣ ገደብ ያለበት ኑዛዜ ማድረግን ሕጉ ስለሚፈቅድ ኑዛዜው ተጠሪዎችን መብት ያሳጣ አለመሆኑንና የተሽከርካሪው ተጠቃሚም በኑዛዜው መገለፁን ፣ የባላበትነት መብትም መተላለፈንና ለአፈጻጸምም አስቸጋሪ ባለመሆኑ ኑዛዜው የሚፈርስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ተብል የተጠሪዎች ክስ ወድቅ እንዱሆን ጠይቀዋል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ኑዛዜው ሉፈርስ ይገባል ወይንስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ ይዞ መዝገቡ እንደመረመረው፡- ቤቱንም ሆነ ቁሳቁሱን አመልካቾች በሕይወት እስካለ ድረስ ይጠቀሙ የሚለው የኑዛዜው ክፍል ሲታይ ቁሳቁሱ በመገልገል የተነሳ ከአገልግልት ውጪ የሚሆንበት ሁኔታን ስለሚፈጠር ወራሾች በውርስ መብት እንዲይሰሩበት የመከልከል ውጤት ያለው ሲሆን የእርጅና እና የለውጥ ወጪም ለላላ አከራካሪ ሁኔታ የሚዲርግ ሆኖ ሟች የሰፊ መብት ለአመልካቾች መስጠታቸው በመንፈስ መጫን የተደረገ የላልች ወራሾችን መብት የሚጎዲ ሲሆን ፣ ተሽከርካሪውንም የኑዛዜው ተጠቃሚ እስከመቼ እንደሚጠቀም ስላልተገለፀ ወራሾችን በውጤቱ ከውርስ የነቀለ እና ይዞታውም በወራሾች የድርሻ መጠን ላይ መብታቸውን የሚጎዲ ሆኖ ስለተገኘ ኑዛዜው ሉፍርስ ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካቾች በውሳኔው ባለመስማማት ያቀረቡት ይግባኝ በከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረዙ በፍርደ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። አመልከቾች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ በሥር ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ ኑዛዜው የተደረገው በመንፈስ መጫን ነው የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቱ አመልካቾች በንብረቱ ሲጠቀሙ ቢጎዲ ለጥገና ቢያወጡ ለላላ ክርክር የሚጋብዝ ነው በሚል ኑዛዜው ይፍረስ ብል የመወሰኑን አግባብነት መጣራት አለበት በማለቱ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ፡- የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተጠሪዎች ኑዛዜው ፈራሽ የሚሆንበትን በርካታ ምክንያቶች በመጥቀስ ያቀረቡትን ክርክር መሰረት ያደረገ መሆኑን ፣ ውሳኔው መሰረት ያደረገው የመንፈስ መጫንን ሆኖ የመንፈስ መጫን መኖሩ የሰፊ መብት ለአመልካቾች መሰጠቱ በኑዛዜው ሰነድ ተረጋግጦ እና ውጤቱም ከውርስ መንቀል መሆኑ ተጣርቶ መወሰኑ አግባብ መሆኑን ፣ ንብረቱን አመልካቾች እየተጠቀሙ በሄደ ቁጥር በተጠሪዎች የንብረት መብት ላይ የሚያደርሰው ጉዲት ለክርክር የሚጋብዝ በመሆኑ ውሳኔው በተከራካሪዎች ያልተነሳ ክርክርን መሰረት ያደረገ ነው የሚያስብል አለመሆኑን ፣ በኑዛዜው የተሸከርካሪው ተጠቃሚ ላላ ሰው ሆኖ እያለ አመልካቾች ከተሸከርካሪው አንፃር ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የላለው ሆኖ ክርክሩ ተቀባይነት አለው ቢባል እንኳን 200 ካ.ሜ ይዞታ የተባለው በየትኛውም አቅጣጫ መንገድ የላለው ፣ በኑዛዜው መሰረት ለመካፈል የከተማ አስተዲደሩ ፔላን የሚፈቅድ መሆኑ ባልተረጋገጠበት እና ባድ መሬት ከጠቅላላው የውርስ ንብረት አንፃር ከሩብ በታች ሆኖእያለ ኑዛዜው መፍረስ የለበትም መባለ አግባብ አለመሆኑንና ከወርስ መንቀል የተባለውም ከውርስ ሃብቱ ከሩብ በታች ድርሻ ደርሶናል የሚለውን መከራከሪያ የያዘ መሆኑንና በተጠሪዎች እጅ የገባ ንብረት አለመኖሩ በዝምታ ከውርስ መንቀል በመሆኑና ኑዛዜው በመንፈስ መጫን መደረጉ የተጠሪዎችን መብት የሚጎዲ በመሆኑ ኑዛዜው እንዱፈርስ የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት ያለው በመሆኑ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልከቾችም የሰበር ቅሬታቸውን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ለሰበር ቅሬታው ምክንያት የሆነው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑ መዝገቡ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አንፃር እንደሚከተለው ተመርምሯል። ኑዛዜ በነፃ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። የኑዛዜ ተጠቃሚ ወይንም ማንኛውም ሰው በተናዛዡ ላይ ባለው ከመጠን ያለፈ መንፈስ መጫን በመርህ ደረጃ ኑዛዜ ሉፈርስ እንዲማይችል የፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 868 የሚያመለክት ሲሆን ፤ በቁጥር 869 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት በሕጉ ውስጥ ለተዘረዘሩት ሰዎች የተደረገውን ኑዛዜ በህጉ የተመለከተው ሁኔታ ተሟልቶ ሲገኝ ዳኞች ሉቀንሱ ወይንም ሉሽሩ ይችላለ። ሟች በፉት ካደረገው ጋብቻ የተገኙ ልጆች ያለት እንደሆነ ለኋለኛው ባል ወይንም ሚስት ጥቅም የተደረገ ኑዛዜን ለመቀነስ ወይንም ለመሻር እንደሚችለ ፣ በዚህ አግባብ የተደረገን ኑዛዜ እንዱቀነስ ወይንም እንዱሻር መጠየቅ የሚችለት የሟች ተወላጆች መሆናቸውና በህጉ የተመለከተው ሁኔታ ተሟልቶ በተገኘ ጊዜ ኑዛዜ ለማፍረስ ወይንም ለመቀነስ ዳኞች ምክንያት ማስቀመጥ እንዲለባቸው ከቁጥር 872 , 874 እና 875 ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። ከወራሽነት የመንቀል አይነቶች በግልፅ ፣ በዝምታና በተዘዋዋሪ ላሆን እንደሚችል እንደዚሁም ከውርስ ሉነቀለ የሚችለ እና የማይችለ ሰዎች ፣ ከውርስ መንቀል የሚቻልበት የህግ አግባብ ከፍትሐ ብሓር ሕጉ 937 – 940 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ ሟች አቶ ስዩም ለማ ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ በመንፈስ መጫን የተደረገና ከሟቹ የቀድሞ ሚስት የሚወለደ ተጠሪዎችን በዝምታ ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል በማለት ተጠሪዎች ላቀረቡት ክስ አመልካቾችም በመልሳቸው ተጠሪዎች በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው ይዞታ ተሰጥቷቸው እያለ ተነቅለናል ማለታቸው ተገቢ አለመሆኑንና የድርሻ ማነስ ከውርስ አለመነቀል መሆኑንና ማስታመምና መንከባከብ ኑዛዜ ለማድረግ የሚያነሳሱ ምንክያቶች እንጂ የመንፈስ መጫን መኖሩን ስለማያሳይ ኑዛዜው የሚፈርስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል። ግራቀኙ ክርክራችንን ያስረዲልናል ያለትን የሰው ምስክር የቆጠሩ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎችንም አቅርበዋል። የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ኑዛዜው ሉፈርስ ይገባል ወይንስ አይገባም የሚለውን በጭብጥነት የያዘ ቢሆንም ተጠሪዎች ኑዛዜው በመንፈስ መጫን የተደረገ በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል በማለት ያቀረቡትን ክርክር አመልካች የመንፈስ መጫን የለም በማለት ክድ ተከራካሮ እያለ ኑዛዜው የተደረገው በመንፈስ መጫን መሆን አለመሆኑን እንዱሁም የውርስ ሀብቱ ተጣርቶ ተጠሪዎች ከውርስ መነቀል አለመነቀላቸውን ሳያጣራ ግራቀኙን ባላከራከረ ጉዲይ አመልካቾች የውርስ ሀብቱን በተገለገለ ቁጥር በእርጅና እና የለውጥ ወጪ ወደፉት ሉያከራክር ይችላል የሚል ምክንያንት ለኑዛዜው ማፍረሻነት መጠቀሙ ተገቢነት የለውም። ተናዛዡ የኑዛዜ ተጠቃሚዎች እንዲያበላልጥ በህግ የተቀመጠ ክልከላ ሳይኖር ሟች የሰፊ መብት ለአመልካቾች መስጠታቸው ኑዛዜው በመንፈስ መጫን የተደረገ የላልች ወራሾችን መብት የጎዲ ማለቱ እንዱሁም ውርሱ ተጣርቶ የእያንዲንደ ወራሽ ድርሻው ሳይታወቅ በውጤቱ ወራሾችን ከውርስ የነቀለ በመሆኑ ሉፍርስ ይገባል ማለቱም የህግ ድጋፍ ያለው አይደለም።
ሲጠቃለል ሟች አቶ ስዩም ለማ ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ በመንፈስ መጫን የተደረገ ተጠሪዎች ከውርስ የነቀለ መሆኑን አለመሆኑ ተጣርቶ ፤ በመንፈስ መጫን የተደረገና ተጠሪዎችን ከውርስ የነቀለ ከሆነ ውጤቱ ምን መሆን አለበት የሚለው በጭብጥነት ተይዞ ተገቢ በሆነ መንገድ ተጣርቶ ውሳኔ አለመስጠቱ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ቁጥር 246, 247 ,249 ,257 እና 264 ድንጋጌዎች የሚጥስ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ብይን እና የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ ፤ ውሳኔ እና ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተዘጋውን የመዝገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሀተታው ውስጥ በተገለፀው መሰረት ሟች አቶ ስዩም ለማ ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ በመንፈስ መጫን የተደረገ መሆን አለመሆኑ እንዱሁም ተጠሪዎችን ከውርስ መንቀል አለመንቀለ ፤ በመንፈስ መጫን የተደረገ ከሆነ ወይንም ተጠሪዎችን ከውርስ የነቀለ ከሆነ ውጤቱ ምን መሆን አለበት የሚለውንና ተያያዥ ጭብጦችን ተገቢ ነው በሚለው መንገድ አጣርቶ እንዱወስን መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ መዝገብ ላይ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት የተሰጠው ዔግድ ተነሰቷል።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
No topics extracted.