ቤት የተሰራበት ይዞታ ለባልና ሚስት በጋራ የተመራና ከአንደኛው ተጋቢ በሞት መለየት በኋላ በህይወት ባለው ላላኛው ተጋቢ የተሰራ መሆኑ ከተረጋገጠ በጋራ የተመሩት ቦታ የከተማ ይዞታ ሆኖ ቦታው የተሰጠው የመኖሪያ ቤት ለመሥራት በመሆኑ ቤቱ የመሬቱ አንድ አቋም ተደርጎ ስለሚቆጠር ቤቱን የሰራው ተጋቢ በቤቱ ላይ ያለው ባለሀብትነት መሬቱንም የሚጨምር ሆኖ እያለ፤ ባልና እና ሚስት አከራካሪው ቤት የተሰራበትን የከተማ ይዞታ አብረው ስለተመሩ ብቻ በአንደኛው ተጋቢ ጥረት የተፈራው ቤትና ሟቹ ያልነበረው መብት በውርስ ሉተላለፍ የሚችል ስላለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1131፣ 1132 እና 826(2)
No summary available.
የሰበር መዝገብ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ አስማረች ጀምበሬ የቀረበ ተጠሪ፡- አቶ አዔምሮ አወቀ የለም ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
አመልካች ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ታልፍ መምህር አወቀ ሽፈራው ከሞቱ ከ24 ዓመት በኋላ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት ማግኘቱ፤ ተጠሪ የሟች ልጅ ስላልሆነ ልጅነቱ በደም ምርመራ እንዱረጋገጥ የቀረበው የዲኝነት ጥያቄ መታለፈ፤ ተጠሪ የጠየቀው ዲኝነት ቤት መካፈል ወይንም የቤቱ ግምት እንዱሰጠው እንጂ ቦታው የጋራ ነው ባላለበት ሁኔታ ሟች በሞቱበት ጊዜ ቦታው ያልተሰጠ ሆኖ እያለ ቦታው የተጠሪ አባት በሕይወት እያለ የተገኘ ነው ቢባል እንኳን ቤት እና መሬቱን በመነጣጠል አከራካሪው ቤት ከሟች ሞት በኋላ በአመልካች ጥረት መፈራቱ በማስረጃ የተረጋገጠው ፍሬ ነገር በሥር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘ ቢሆንም ተጠሪ የግንባታ ወጪውን ተጋርቶ ቤቱን ግራ ቀኙ እኩል ይካፈለ በማለት የደረሰበት መደምደሚያ የፍትሐ ብሓር ሕጉ እና የሕገ መንግስቱን ድንጋጌ የሚቃረን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አመልካች የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መዝገቡ ለችልቱ ቀርቧል።
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በባህርዲር ዙሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆኖ አመልካች ከሳሽ ፣ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ በስር ክሳቸው አመልካች እና ወላጅ አባቴ መምህር አወቀ ሽፈራው በአካባቢው ባህል መሰረት ተጋብተው ሲኖሩ፣ ወላጅ አባቴ ባደረባቸው ህመም ምክንያት የካቲት 12 ቀን 1991 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሟች አባቴ እና አመልካች በጋራ በትዲር እያለ በባህርዲር ከተማ መገናኛ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው በአመልካች ስም ገንዘብ ሲቆጥቡ ቆይተው ፣ በባህር ዲር ከተማ ቀበላ 11 ውስጥ በማህበሩ ቦታ ተመርተው ህዲር 4 ቀን 1990 ዓ/ም የማህበር የቦታ ካርታ ተሰርቶላቸው ቦታውንም በአመልካች ስም ተረክበው፣ የካቲት 4 ቀን 1990 ዓ/ም ከቀድሞው የባህር ዲር ልዩ ዞን መስተዲደር ጋር አመልካች ውል ገብተው፣ ሟች እና አመልካች በተመሩት ስፊቱ 250 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ ግንቦት 1990 ዓ/ም በብልኬት ቤት ሰርተውበታል። አባቴ ከመሞቱ በፉት በካርኒ በ1997 ዓ/ም ለባህርዲር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በማህበሩ ስም የከተማ ቦታ ግብር ከፍል ይገኛል። ተጠሪ በአሁኑ ሰዓት ዔድሜዬ 22 ዓመት ሲሆን ወላጅ አባቴ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩበት ወቅት አካለመጠን ያልደርስኩ በመሆኑ እና ቤቱም በአመልካች መያዙን ያወቀኩት ጥቅምት ወር 2011 ዓ/ም በመሆኑ መብቱን ሳይጠይቅ መቆየቱን ገልፆ ፤ይህ ግምቱ 6,000,000.00(ስድስት ሚልዮን) የሆነው ቤት የግምቱ ግማሽ እንዱከፈለው ወይንም በሕጉ ላይ በተመለከተው የክፍፍል ሥርዓት ድርሻው እንዱሰጠው ጠይቋል።
አመልካች በመልሳቸው ሟች አቶ አወቀ ሽፈራው የአመልካች ባለቤት መሆኑ እና በ1991 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ መሆኑን አምነው ፣ ተጠሪ የሟች ልጅ አለመሆኑን ፣ የሟች ልጅ ታምራት አወቀ መሆኑ በፍርድ መረጋገጡን፣ የሟች ልጅ ነው ቢባል እንኳን ሟች ከሞቱ ከ21 ዓመት በኋላ ያቀረበው ክስ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ፣ ሟች ከሞቱ በኋላ በጋራ ለማህበሩ የከፈለትን 5,000.00 (አምስት ሺ) ብር ግማሹን 2,500.00 (ሁለት ሺ አምስት መቶ) ብር እና የቤት ቁሳቁስ ግማሹን ለሟች ልጅ ታምራት አወቀ በሞግዚቱ አማካኝነት የተሰጠ በመሆኑ የቀረ የጋራ ንብረት አለመኖሩን፣ ክስ የቀረበበትን ቤት ሟች ከሞቱ አንድ ዓመት በኋላ በግል ገንዘባቸው በሀምላ ወር 1992 ዓ/ም የቤቱን መሰረት አውጥተው፣ ጥቅምት ወር 1993 ዓ/ም ግንባታ ጀምረው፣ ታህሳስ ወር 1993 ዓ/ም 40 ቆርቆሮ ገዝቶ በማልበስ፣ መጋቢት ወር 1993 ዓ/ም የላሜራ በር አስገጥሞ ገብቶበት በ1997 ዓ/ም የቤቱን ግድግዲ ሉሾ አድርጎ፣ ህዲር 18 ቀን 2000 ዓ/ም ካርታ አሰርተው መረከባቸውን ፣ ከ2005- 2008 ዓ/ም ባለው ጊዜ ከራሳቸው እና በብድር በተገኘ ገንዘብ አጥር አጥረው እና ተጨማሪ ክፍልች፣ የውሃ ታንከር እና ሻወር ሰርተው ግብሩም ሟች ከሞቱ ከስድት ዓመት በኋላ የተከፈለው በአመልካች ሰም ስለሆነ ሟች ያልሰራው እና ግብር ያልከፈለበት ቤት እና ቦታ በትዲር ውስጥ የተፈራ ነው ልባል ስለማይገባ ክሱ ውድቅ እንዱሆን ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም ሉጣሩ ይገባቸዋል ያላቸውን ጭብጦች በመለየት የግራ ቀኙን ምስክሮች ቃል ሰምቶ እና ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ይረዲው ዘንድ በሚመለከተው የመንግስት ተቋም እንዱጣራ አድርጎ መዝገቡን እንደመረመረው በአመልካች የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ወድቅ አድርጎ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት እና ቦታ የሟች እና የአመልካች መሆኑ በምስክሮች እና በሰነድ ማስረጃ ሰለተረጋገጠ አመልካች የሟች ድርሻ የሟች ሕጋዊ ወራሽ ለሆነው ተጠሪ ልታካፍል ይገባል በማለት በአብላጫ ድምፅ ወስኗል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም በይግባኝ ለማሳረም ለአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ተጠሪም ክርክሩን ያቀረበው በጠበቃ ሆኖ እያለ ይቻቻለ መባለን በመቃወም ይግባኝ አቅርቦ ፤ ፍርድ ቤቱም ሁለቱንም መዝገቦች በማጣመር እንደመረመረው ለክርከሩ መነሻ የሆነው ቤት የተሰራበት ቦታ በ1990 ዓ/ም ተመርተው ፔላኑ በ1991 ዓ/ም ተሰጥቶ ግንባታው ከሟች ሞት በኋላ የተሰራ መሆኑን የአመልካች ምስክሮች ያስረደ ሲሆን፤ የተጠሪ ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት እምነት የሚጣልበት ባለመሆኑ የተጠሪ አባት የጉልበትም ሆነ የገንዘብ አስተዋጽኦ ያደረገ መሆኑ ሳይረጋገጥ ለክርክሩ መነሻ የሆነ ቤት የሟች እና የአመልካች የጋራ ሀብት ነው በማለት የተሰጠው ውሳኔ ማስረጃን ያገናዘበ አይደለም በማለት የባህርዲር እና አከባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር፤ አከራካሪው ቤት በአመልካች ጉልበት እና ገንዘብ የተሰራ መሆኑ ስለተረጋገጠ የሟቹ አስተዋጽኦ የላለበትን ቤት ተጠሪ ሉካፈል አይገባም በማለት በአብላጫ ድምፅ ወስኗል። የልዩነት ሃሰቡም ለክርከሩ መነሻ የሆነው ቤት የተሰራው ሟች እና አመልካች በጋራ ተደራጅተው ባገኙት ቦታ ላይ መሆኑ ያላከራከረ በመሆኑ፤ ተጠሪ ቦታውን የመውረስ መብት ያለው በመሆኑ ቤቱን ለመስራት የወጣውን ወጪ በድርሻው እንዱተካ ማድረግ ሲገባ በቦታው ላይ ያለውን የውርስ ድርሻ ጠቅላላ አመልካች እንድትወርሰ መደረጉ አግባብ አይደለም የሚል ነው። ተጠሪው በውሳኔው ባለመስማማት ባቀረቡት አቤቱታ ጉዲዩን ያየው የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልትም፡- በስር ፍርድ ቤት የተሰሙት የተጠሪ ምስክሮች የክርክሩን ቦታ አመልካች እና ሟች በጋራ የተመሩት መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን አመልካችም በሰጠችው የምስክርነት ቃል ቦታው ለማህበሩ የተሰጠው በ1990 ዓ/ም አመልካች እና ሟች ባልና ሚስት በነበሩበት ጊዜ መሆኑን ያረጋገጠች ሆኖ መምህር አወቀ ሽፈራው የሞቱትም ቦታው ለማህበሩ ከተሰጠ በ1991 በኋላ ዓ/ም በመሆኑ፤ ቦታው ሟች እና አመልካች በባልና ሚስትነት እያለ የተሰጠ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር በመሆኑ ሟች በባድ ቦታው ላይ ያለው የባለ ይዞታነት መብት ወራሹ እና ልጁ ለሆነው ተጠሪ የሚተላለፍ ሆኖ እያለ አመልካች ቤቱን በግል ገንዘቧ ሰርታለች በማለት ተጠሪ በባድ ቦታው ላይ ያለውን መብት እንዱያገኝ ማድረግ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት ፤ ቦታው እና ቤቱ እኩል ለሁለት ተከፍል ግራቀኙ እኩል የሚካፈለት ሆኖ ለተጠሪ በሚደርሰው ቦታ ላይ ያረፈውን ቤት ለመስራት የዋለው የቤቱ ወጪ ግምት በባለሞያ ተጠንቶ ተጠሪ ለአመልካች እንዱተካ በማድረግ፤ ይህ ካልተቻለ አጠቃላይ በቦታው ላይ የተሰራውን ቤት ለመስራት የወጣው ወጪ በባለሞያ ተጠንቶ ፤
የወጪውን ግምት ግማሽ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍላት ተደርጎ ቤት እና ቦታውን እኩል እንዱካፈለ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለት አመልካች ያቀረቡትን በፍርደ መግቢያ ላይ የተገለፀውን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ፡- ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የተሰራበትን መሬት አመልካች የቤት ሥራ ማህበሩ የተረከበው እና አመልካችም በመሬቱ ላይ ቤት የሰራች መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚያስረዲ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔን በመሻር ቦታው ለሁለት ተከፍል ለተጠሪ በሚደርሰው ቦታ ላይ ያለውን ቤት ለመስራት የወጣ ወጪ በባለሙያ ተገምቶ ለአመልካች እንዱከፈል በሚል የወሰነበትን አግባብነት በሰበር መዝገብ ላይ ከተሰጠው ውሳኔ ጋር አገናዝቦ ለመመርመር ለሰበር ይቅረብ በማለቱ ተጠሪ ተከታዩን መልስ ሰጥቷል። ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የተሰራበትን ቦታ ሟች እና አመልካች በባልና ሚስትነት በማህበር ተደራጅተው በአመልካች ስም የተመሩት እንጂ አመልካች በስሟ ብቻዋን ያገኘቸው አለመሆኑ አመልካች እና ሟች ቦታውን ለመቀበል ከባህርዲር ከተማ ልዩ ዞን አስተዲደር ጋር የካቲት 4 ቀን 1990 ዓ/ም ውል የያዙ መሆኑን ቦታውን ለመቀበል ከባህዲር ልዩ ዞን መስተዲድር ጋር የተደረገ ውል፣ የማሕበሩ ካርታ ፣ የባህርዲር ከተማ አገልግልት ፅ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ፣ የቦታ ምርት ካርኒ እንዱሁም በሥር ፍርድ ቤት የተሰሙት የሰው ምስክር ያረጋገጡትን ማስረጃ መሰረት አድርጎ የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ሆኖ እያለ አመልካች ቦታውን በግሎ ከሟች ሞት በኋላ እንደተመራችው ሁኖ የቀረበው ቅሬታ እና የተያዘው ጭብጥ ተገቢነት የላለው መሆኑን፤ የስር የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልት አከራካሪውን ቤት አመልካች በግል ገንዘቧ ሰርታለች በማለት የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመቃወም በመዝገብ ላይ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ የሰበር አቤቱታ አቅርቦ በቀጠሮ ላይ መሆኑን ገልፆ ፤
በዚህ ረገድ የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ አግባብ ነው ቢባል እንኳን ቦታው በምሪት የተገኘው ሟች በሕይወት እያለ በመሆኑ ተጠሪ የግንባታ ወጪውን ሸፍኖ በቤቱ ላይ እኩል ባለመብት እንዱሆን የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ መሆኑን፤ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሟች ልጅ አይደለም በሚል ክርከር ያቀረቡ ቢሆንም የሟች ልጅ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር በአመልካች ባለመስተባበለ እንዱሁም ይርጋን በተመለከተም ተጠሪ አካለመጠን ካደረሰ በኋላ የሟች አባቱ ንብረት በአመልካች መያዙን አውቆ ክስ እስከመሰረተበት ያለው ጊዜ ሲሰላ ያቀረበው ክስ በይርጋ የማይታገድ መሆኑ ተረጋግጦ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ በመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ሆኖ የስር የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም ዋናውን አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን የሥር ፍርድ ለቤት መሥራያ የተሰጠውን የከተማ ይዞታ እና በይዞታው ላይ የተሰራውን ቤት በመለያየት አመልካች በግል ጥረታቸው ያፈሩት ቤት ቤቱ ያለበትን ይዞታ አይጨምርም በማለት የሰጡት ውሳኔ ህጉን ያገናዘበ መሆን አለመሆኑ እንደሚከተለው ተመርመሯል። ተጠሪ አከራካሪውን ቤት ሟች እና አመልካች በጋራ ያፈሩት በመሆኑ የሟች ድርሻ በውርስ እንዱተላለፍለት ላቀረበው ክስ አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን በማስቀደም በፍሬ ነገር መልሳቸው አከራካሪውን ቤት ከሟች ሞት በኋላ በግል ጥረታቸው ያፈሩት በመሆኑን ተከራክረዋል። በአመልካች የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት በማስረጃ አጣርቶ የደረሰበት የፍሬ ነገር መደምደሚያን ችልቱ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘውም። አከራካሪው ቤት የተሰራበት ይዞታን አመልካች እና ሟች በጋራ የተመሩት መሆኑ እና ቤቱ ከሟች ሞት በኋላ አመልካች የሰሩት መሆኑ ማስረጃን የመመዘን እና የመመርመር ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ሲሆን፤ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት አመልካች በግል ገንዘቧ ሰርታለች በማለት የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመቃወም በመዝገብ ላይ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። አመልካች እና ሟች በጋራ የተመሩት ቦታ የከተማ ይዞታ ሆኖ ቦታው የተሰጠው የመኖሪያ ቤት ለመሥራት ነው። አመልካች እና ሟች በጋራ ቤት ለመሥራት ቦታውን ቢወስደም ፤ መምህር አወቀ ሽፈራው ስለሞቱ አመልካች በቦታው ላይ በገነቡት ቤት ላይ በሕገ መንግስቱ 40(7) ድንጋጌ መሰረት ሙለ መብት ያላቸው ሲሆን ይህ የባለሀብትነት መብትም የሚገደበው በህግ በተመለከተው አግባብ ብቻ መሆኑን የፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1204 ድንጋጌ ያመለክታል። አመልካች በቤቱ ላይ ያላቸው የባለሀብትነት መብት በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1131 ድንጋጌ መሰረት በይዞታውም ላይ የሚዘረጋ ሲሆን ፤ በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1132 ድንጋጌ ላይ እንደተመለከተው ቤቱ የመሬቱ አንድ አቋም ተደርጎ ስለሚቆጠር አመልካች በቤቱ ላይ ያላቸው ባለሀብትነት መሬቱንም የሚጨምር ሆኖ እያለ ፤ አመልካች እና ሟች አከራካሪው ቤት የተሰራበትን የከተማ ይዞታ አብረው ስለተመሩ ብቻ በአመልካች ጥረት የተፈራውን ቤት ሟቹ ያልነበረውን መብት ተጠሪ እንዱወርስ የተሰጠው ውሳኔ የፍትሐ ብሓር ሕጉን ቁጥር 826(2) የሚፃረር በመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በመዝገብ የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸዉን ይቻለ።’
በዚህ መዝገብ ላይ ተሰጥቶ የነበረው ዔግድ ተነስቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.