ከሁከት ይወገድልኝ ክስ ጋር በተያያዘ የፍርድ ቤት ክርክር የክስ ማቅረቢያ ጊዜ አስመልክቶ ለአስተዲደር አካል የመብት ጥያቄ ማቅረቢያ ጊዜ እና ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረቢያ ጊዜን ለይቶ ማየትና የቀረበ የመብት ጥያቄ በእርግጥም በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ለማጣራት ለመብቱ መጠየቅ መሰረት የሆነው ጉዲይ የተፈጠረበትን እና ለአስተዲደር አካል እና ለፍርድ ቤት የመብት ጥያቄው የቀረበበትን ጊዜ በአግባቡ ማየት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1149(2) እና የፋዳራል ቤቶች ኮርፕሬሽን የቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 02/2010 አንቀፅ 56(1(ሀ)) በፍትሐ ብሓር ክርክር ጉዲይ ወደ ክስ ሥረ ነገር ክርክር ሳይገባ ክሱን ያቀረበው አካል ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የለውም በሚል ምክንያት አቤቱታውን ውድቅ ለማድረግ ክስ ያቀረበው አካል በእርግጥም መብት እና ጥቅም የላለው ለመሆኑ እርግጠኛ መሆንና በዚህ አኳኋን አቋም ለመውሰድ የሚያስችል ግልፅ ማሳያ ከላለ በቀር ክሱን ያቀረበው አካል የሚኖረው መብት እና ጥቅም በሥረ ነገር ክርክር ወቅት በማስረጃ የሚረጋገጥና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 33 መሰረት አቤቱታው ውድቅ የሚደረግ ስላለመሆኑ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በቀረበበት ወቅት ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት በከሳሽ እጅ መኖሩ ካልተካደ ሁኔታው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ በቂ መብት የሚፈጥር በመሆኑ ከሳሽ በመጀመሪያው የክርክር ምዔራፍ ላይ መብት እና ጥቅም የለውም ልባል የማይችልና የቤቱ አያያዝ ህጋዊነት፣ በህግ ረገድ ስለሚኖረው ውጤት እና ተያያዥ ጉዲዮች በክርክር ሂደት ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የተሟላ ክርክር እና ማስረጃ ነጥሮ የሚወጣ ጉዲይ እንጂ ክስ ለማቅረብ ከሚኖር መብት እና ጥቅም ጋር የሚያያዝ ስላለመሆኑ የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ንብረቱን በተመለከተ በህግ ከተረጋገጡለት መብቶች ውስጥ አንደ በሀብቱ ላይ የተፈጠረው ህገ ወጥ ሁከት እንዱወገድለት የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያቀርብ ሰው ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች የሆኑትን ሁከት ተፈጠረበት የተባለውን ንብረት/ሀብት/ ባልተጭበረበረ መንገድ በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት መሆኑን እና በዚሁ ይዞታው ላይ በተከሰሰው አካል ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሁከት የተፈጠረበት መሆኑን ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ/1140፣ 1146 እና 1149
No summary available.
ጥቅምት 29/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ በላይ ማሞ ከጠበቃ አቶ ግሩም አየለ - ቀርበዋል ተጠሪ፡- የፋዳራል ቤቶች ኮርፕሬሽን ነ/ፈጅ አቶ ደምሰው ተፈራ - ቀርበዋል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የሁከት ይወገድልኝ ክስን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/258880 ላይ ጥር 05/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/281986 ላይ መጋቢት 29/2012 ዓ.ም የተሰጠውን ብይን የሚነቀፍበት ጉድለት የለበትም በማለት በአሁን አመልካች የቀረበለትን የይግባኝ አቤቱታ የሰረዘበት የመጨረሻ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለማስለወጥ ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱ ይዘትም በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን ቤት ወላጅ አባታቸው በህይወት እያለ ከ1978 ዓ.ም ጅምሮ ከአሁን ተጠሪ ተከራይተው በ1998 እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ ከአባታቸው ጋር በቤቱ ውስጥ ሲኖሩ የነበረ መሆኑን፤ ወላጅ አባታቸው ከሞቱ በኋላ አቶ ወሰን ማሞ ከተባለት ወንድማችው ጋር ወራሽነታቸውን አረጋግጠው የቤቱ የተከራይነት መብት እንዱተላለፍላቸው ለአሁን ተጠሪ ጥያቄ ሲያቀርቡ የተከራይነት ስሙ በሁለቱ ወራሾች አልያም በአንዲቸው ስም ላሆን እንደሚችል በተጠሪ የተገለፀላቸው በመሆኑ ውለ በወንድማቸው ስም እንዱደረግ ተስማምተው በዚሁ መሰረት የኪራይ ውለ ተፈፅሞ ሁለቱም በቤቱ ውስጥ ሲኖሩ የቆዩ መሆኑን፤ ወንድማቸው በልላ ክፍለ ከተማ ቤት የደረሳቸው በመሆኑ የተከራይነት ስሙ በስማቸው እንዱዞርላቸው ተጠሪን ሲጠይቁ ‛ቤቱን የተከራየው ሰው ግዳታውን አልተወጣም!“ በሚል ምክንያት ቤቱን ለቀው እንዱወጡ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ነው ተብል እንዱወገድላቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት የአሁን ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ የስረ ነገር ክርክር አቅርቧል። የመቃወሚያው ይዘትም ክስ የቀረበበት ጉዲይ በፍርድ ቤት ክርክር የሚደረግበት ሳይሆን በአስተዲደራዊ መፍተሓ እልባት የሚያገኝ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር የዲኝነት ሥልጣን የለውም፤ ጥያቄውም በፋዳራል ቤቶች ኮርፕሬሽን የቤቶች አስተዲደር በመመሪያ ቁጥር 02/2010 አንቀፅ 56(1(ሀ)) በሚያዘው መሰረት በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል፤ ከሳሹም ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት የላለው በመሆኑ ክስ ለማቅረብ አይችልም የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ በሰጠው ብይን የቀረበው ክስ በይዞታ ላይ የተፈጠረ ሁከት ይወገድልኝ የሚል በመሆኑ ከሳሽ በንብረቱ ላይ የይዞታ መብት ያለው መሆኑ ወይም የንብረቱ አያያዝ ህጋዊ መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1149 የሚፈቅድለት በመሆኑ ፍርድ ቤት የዲኝነት ስልጣን የለውም ልባል አይችልም፤ ሆኖም አመልካች ጥያቄውን ለተጠሪም ሆነ ለፍርድ ቤት ያቀረበው በመመሪያ ቁጥር 02/2010 አንቀፅ 56(1(ሀ)) ስር ከተመለከተው ሶስት ወር በኋላ በመሆኑ ጥያቄው በይርጋ ይታገዲል፤ የቤቱ የተከራይነት መብትም በአመልካች ወንድም ስም የነበረ ስለመሆኑ ተገልጿል፤
የቤቱ የተከራይነት መብት በአመልካች እና በወንድሙ አልያም በአንዲቸው ስም ላደረግ የሚችል ስለመሆኑ በተጠሪ በኩል ስለመገለፁ የተረጋገጠ ነገር ባለመኖሩ አመልካች ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት የለውም በማለት ክሱውን ውድቅ አድርጓል።
የአሁን አመልካች በዚሁ ውሳኔ ላይ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የይግባኝ አቤቱታውን በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ዘግቷል። የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ነው።
አመልካች ሚያዝያ 08/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ብይን እና ትዕዛዝ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ነሐሴ 03/2010 ዓ.ም ወራሽነታቸውን በማረጋገጥ መስከረም 07 እና 28 ቀን 2011 ዓ.ም ለክርክር መነሻ በሆነው ቤት በተከራይነት ለመቀጠል ለተጠሪ ጥያቄ አቅርበው እያለ የቀረበው አቤቱታ በይርጋ ይታገዲል በሚል ውድቅ የተደረገበት አግባብነት ከመመሪያ ቁጥር 02/2010 አንቀጽ 56(1(ሀ)) አንጻር ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከአመልካች የሰበር ቅሬታ፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንግዱህ ከክርክሩ አመጣጥ በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው የአመልካች የክስ አቤቱታ ውድቅ የተደረገው በሁለተ ምክንያት ነው። የመጀመሪያ ክስ የቀረበበት ጉዲይ ለተጠሪም ሆነ ለፍርድ ቤት በመመሪያ ቁጥር 02/2010 አንቀፅ 56(1(ሀ)) ስር በተመለከተው የሶስት ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል ነው። ሁለተኛው ደግሞ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የተከራይነት ስም በልላ ሰው ስም ያለ በመሆኑ አመልካች ቤቱን አስመልክቶ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት የለውም የሚል ነው። እነዚህ ሁለቱ ነጥቦች በሚከተለው መልኩ በተናጠል ታይተዋል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ በፋዳራል ቤቶች ኮርፕሬሽን የቤቶች አስተዲደር በመመሪያ ቁጥር 02/2010 አንቀፅ 56(1(ሀ)) ስር የተመለከተው የይርጋ ጊዜ በተከራይ መሞት ምክንያት የተከራይነት መብቱ ሉተላለፍልኝ ይገባል የሚል አካል ወራሽነቱን በፍርድ ቤት ካረጋገጠ በኋላ ጥያቄውን ለቤቱ አከራይ አስተዲደር አካል የሚያቀርብበትን ጊዜ የሚመለከት እንጂ በፍርድ ቤት የክሰ ማቅረቢያ ጊዜን የሚመለከት አይደለም። የፍርድ ቤት ክርክርን አስመልክቱ ከሁከት ክስ ጋር በተያያዘ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ የተመለከተው በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1149(2) ስር ነው። ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት ለአስተዲደር አካል የመብት ጥያቄ ማቅረቢያ ጊዜ እና ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረቢያ ጊዜን ቀላቀል ማየቱ ስህተት ነው። እናም የአመልካች ጥያቄ በእርግጥም በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ለማጣራት ለመብቱ መጠየቅ መሰረት የሆነው ጉዲይ የተፈጠረበትን እና ለአስተዲደር አካለ እና ለፍርድ ቤት የመብት ጥያቄው የቀረበበትን ጊዜ በአግባቡ ማየት ያስፈልጋል።
በፍርድ ቤት የቀረበውን ክስ በተመለከተ ለክሱ መሰረት የሆነው የሁከት ተግባር ተፈፅሟል የተባለው ህዲር 25/2012 እና ታህሳስ 06/2012 ዓ.ም ሲሆን የሁከት ይወገድልኝ ክስ የቀረበው ደግሞ ታህሳስ 13/2012 ዓ.ም መሆኑን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል። የሁከት ይወገድልኝ ክስን አስመልክቶ ለክስ ማቅረቢያ የተቀመጠው ጊዜ የሁከት ተግባሩ ከተፈጠረበት አልያም ንብረቱ በሁከት ምክንያት ከተወሰደብት ጊዜ አንስቶ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(2) ይደነግጋል።
ከዚህ አንፃር አመልካች በፍርድ ቤት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ያቀረቡት ‛የሁከት ተግባር ነው“ የተባለው ድርጊት በተፈፀመ በቀናት ልዩነት በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገድ አይደለም።
ሆኖም ለአስተዲደር አካለ የመብት ጥያቄ ማቅረቢያ ጊዜን አስመልክቶ የቀረበው ክርክር በጥንቃቄ ላታይ የሚገባው ጉዲይ ነው። ከዚህ ጉዲይ ጋር በተያያዘ አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ወራሽነቴን ያረጋገጥኩት ነሒሴ 03/2010 ዓ.ም ሲሆን የስም ዝውውር እንዱደረግልኝ ለተጠሪ ጥያቄ ያቀረብኩት መስከረም 07 እና 28 ቀን 2011 ዓ.ም በመሆኑ በመመሪያ የተመለከተው የሶስት ወር ጊዜ አላለፈም በሚል ነው። በእርግጥ አመልካች ነሒሴ 03/2010 ዓ.ም ወራሽነታቸውን በፍርድ ቤት አረጋግጠው የስም ዝውውር እንዱደረግላቸው መስከረም ወር 2011 ዓ.ም ለተጠሪ ጥያቄ ስለማቅረባቸው የስር ፍርድ ቤት መዝገብ በራሱ ያሳያል። በልላ በኩል አመልካች ባቀረቡት የክስ ዝርዝር ውስጥ የቤቱ ተከራይ የነበሩት ወላጅ አባታቸው በ1998 ዓ.ም እንደሞቱ አመልካች እና ወንድማቸው ወራሽነታቸውን በፍርድ ቤት አረጋግጠው ተመሳሳይ የተከራይነት ስም ዝውውር አቅርበው የነበረ መሆኑን፤ በወቅቱም የተከራይነት ስሙ በሁለቱ አልያም በአንዲቸው ላሆን እንደሚችል በተጠሪ በኩል በመገለፁ የተከራይነት ስሙ በአመልካች ወንድም ስም እንዱሆን የተደረገ ስለመሆኑ ተገልጿል። በክሱ ውስጥ በተገለፀው አኳኋን አመልካች ቀደም ብለው ወራሽነታቸውን አረጋግጠው ከሆነ ነሒሴ 03/2010 ዓ.ም በድጋሚ ወራሽነት ማረጋገጥ የተፈለገበት እና የተቻለበት ምክንያትም ግልፅ አይደለም። ከዚህ አንፃር በስር ፍርድ ቤት የተደረገ ማጣራት ስለመኖሩም የቀረበው የመዝገብ ግልባጭ የሚያሳይ ነገር የለውም። እናም አመልካች ለተጠሪ ያቀረቡት የተከራይነት ስም ይዛወርልኝ ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን አለመሆኑ ላይ አቋም ከመያዙ በፉት ከቀረበው ክስ እና ክሱን ለማረጋገጥ በአስረጂነት ከቀረበው ማስረጃ ይዘት አኳያ አመልካች በትክክል ወራሽነታቸውን ያረጋገጡት ጊዜ በአግባቡ ሉጣራ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር ተገናዝቦ እልባት ሉሰጠው የሚገባው ጉዲይ ነው።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ የአመልካች ክስ ውድቅ የተደረገው ክስ ባቀረቡበት ቤት ላይ ከውልም ሆነ ከህግ የመነጨ መብት እና ጥቅም የላላቸው በመሆኑ ክስ ለማቅረብ መብት የላቸውም በሚል ነው። በእርግጥ የፍትሒ ብሓር ሥነ ሥረዓት ህጉ በሁለተኛው መፀሒፍ ስለ ጠቅላላ ደንቦች በሚደነግገው ምዔራፍ አንድ ቁጥር 33 ስር በአንድ የፍትሒ ብሓር ክርክር ማናቸውም ሰው ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ላይ ወይም ክሱ በተመሰረተበት ሀብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ክስ ማቅረብ የማይፈቀድለት መሆኑን፤ እንዱሁም ከተከሳሽ ላይ የሚጠይቀውን ጥቅም ወይም መብት በማረጋገጥ አቤቱታ ካላቀረበ በቀር በማናቸውም ሰው ላይ ክስ ሉያቀርብ የማይችል ስለመሆኑ ተደንግጓል።
የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ ዓላማ ለክርክር ምክንያት በሆነው ጉዲይ ላይ ትክክለኛ ጥቅም ያለውን ወገን(Real party in the interest) መለየት ነው። ክርክር በተነሳበት ጉዲይ ላይ ትክክለኛ ጥቅም ያለውን ወገን መለየት ያስፈለገው በሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች ስለመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ከተፃፈት የጥናት ፅሁፍች መገንዘብ ይቻላል። የመጀመሪያው ምክንያት በአንድ ሰው መብት/ጥቅም ላይ ላልች ሰዎች ክስ እንዲያቀርቡ መከላከል(to prevent suit by a person who wants to litigate someone else’s claim against the defendant) የሚል ነው። ሁለተኛው ደግሞ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ጉዲይ ላይ ያለው መብት/ጥቅም ለላላ ሰው ተላልፍ ከሆነ ተከሳሹ ወገን በአንድ ጉዲይ በሁለት የተለያዩ ሰዎች ላቀርብበት ከሚችለው ሁለት ክስ መከላከል(to prevent two suits against the defendants for a single wrong where the interest in the subject matter has been transferred) የሚል ነው።
እናም በአንድ የፍትሒ ብሓር ክርክር ጉዲይ ወደ ክሱ ሥረ ነገር ክርክር ሳይገባ ክሱን ያቀረበው አካል ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የለውም በሚል ምክንያት አቤቱታውን ውድቅ ለማድረግ ከላይ ከተመለከቱት መመዘኛዎች አንፃር ክስ ያቀረበው አካል በእርግጥም መብት እና ጥቅም የላለው ለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። በዚህ አኳኋን አቋም ለመውሰድ የሚያስችል ግልፅ ማሳያ ከላለ በቀር ክሱን ያቀረበው አካል የሚኖረው መብት እና ጥቅም በሥረ ነገር ክርክር ወቅት በማስረጃ የሚረጋገጥ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 33 መሰረት አቤቱታን ውድቅ ከማድረግ ሉቆጠቡ ይገባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ክስ ያቀረቡት የተከራይነት መብቱ በውርስ ሉተላለፍልኝ የሚገባውን እና እየኖርኩበት ያለሁትን ቤት ተጠሪ ሉያስለቅቀኝ እንቅስቃሴ የጀመረ በመሆኑ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ነው ተብል ሉወገድልኝ ይገባል በሚል ነው። የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ንብረቱን በተመለከተ በህግ ከተረጋገጡለት መብቶች ውስጥ አንደ በሀብቱ ላይ የተፈጠረው ህገ ወጥ ሁከት እንዱወገድለት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) ይደነግጋል።
በዚህ መልኩ ክስ የሚያቀርብ ሰው ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች ሁከት ተፈጠረበት የተባለውን ንብረት/ሀብት/ ባልተጭበረበረ መንገድ በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት መሆኑን እና በዚሁ ይዞታው ላይ በተከሰሰው አካል ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሁከት የተፈጠረበት መሆኑን ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ/1140፣ 1146 እና 1149 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መረዲት ይቻላል።
በዚህ መልኩ ለቀረበው ክስ ተጠሪ በሰጡት መልስ የተከራይነት ስሙ በአመልካች ስም የላለ በመሆኑ ልከሰስ የሚችልበት ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ ምክንያት የለም በማለት ሞግቷል። ከተጠሪ መከራከሪያ በግልፅ መረዲት የሚቻለው ስለ ቤቱ አያያዝ ህጋዊነት ከሚከራከሩ በቀር ቤቱ በአሁን አመልካች እጅ የሚገኝ መሆኑን እና ይህንኑ ቤት ለማስለቀቅ ሂደት መጀመሩን አልካደም።
የሁከት ይወገድልኝ ክስ በቀረበበት ወቅት ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት በአመልካች እጅ መኖሩ ካልተካደ ሁኔታው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ በቂ መብት የሚፈጥር በመሆኑ አመልካች በመጀመሪያው የክርክር ምዔራፍ ላይ መብት እና ጥቅም የላቸውም ሉባለ አይገባም። የቤቱ አያያዝ ህጋዊነት፣ በህግ ረገድ ስለሚኖረው ውጤት እና ተያያዥ ጉዲዮች በክርክር ሂደት ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የተሟላ ክርክር እና ማስረጃ ነጥሮ የሚወጣ ጉዲይ እንጂ ክስ ለማቅረብ ከሚኖር መብት እና ጥቅም ጋር የሚያያዝ አይደለም።
ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የተሟላ ክርክር እና ማስረጃን ሳይሰማ በክርክር ሂደት በማስረጃ ሉጣራ የሚገባን ነጥብ መዝዞ አመልካች ክርክር በተነሳበት ንብረት ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላቸው መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉም ሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይህንኑ አቋም መቀበለ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 33 እና የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1149 ድንጋጌዎችን መሰረታዊ ዓላማ ከግንዛቤ ያላስገባ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም እና አረዲድ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/258880 ላይ ጥር 05/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/281986 ላይ መጋቢት 29/2012 የተሰጠውን ብይን በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በብይን የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ፡- 2.1. ከቀረበው ክስ እና ማስረጃ አኳያ አመልካች ወራሽነታቸውን በፍርድ ቤት ያረጋገጡበት ትክክለኛ ጊዜ መቼ እንደሆነ፤ በክሱ ዝርዝር እንደተመለከተው አመልካች ወራሽነታቸውን ያረጋገጡት በ1998 ዓ.ም ወላጅ አባታቸው እንደሞቱ ከሆነ ነሒሴ 03/2010 ዓ.ም በድጋሚ ወራሽነት ማረጋጥ የተቻለበት ምክንያት እና ህጋዊ ውጤቱ ምን እንደሆነ በመለየት አመልካች በፋዳራል ቤቶች ኮርፕሬሽን የቤቶች አስተዲደር በመመሪያ ቁጥር 02/2010 አንቀፅ 56(1(ሀ)) ስር በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ጥያቄያቸውን ለአሁን ተጠሪ አላቀረቡም በማለት በቀረበው መቃወሚያ ላይ ተገቢውን ብይን እንዱሰጥ፤
2.2. የቀረበው መቃወሚያ በምክንያት የሚታለፍ ከሆነ በክሱ ሥረ ነገር ክርክር ላይ የግራ ቀኙን የተሟላ ክርክር እና ማስረጃን በመስማት የመሰለውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 341(1) መሰረት ጉዲዩ ይመለስለት።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.