በመሬት ሽያጭ ግዢ ውል የተገኘ ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ በስም ውጥቶለትና ቤት በመስራት ግብርም እየተገበረበት ያለ ቢሆንም የመሬት ሽያጭ የተከለከለ በመሆኑ ይዞታው የተገኘበት መንገድ ህገወጥ ልባል ሲገባ የይዞታው መተላለፉያ መንገድ ሳይመረመር እና ህጋዊነቱም ከህገ መንግሥት ስለመሬት ማስተላለፉያ መንገድች በህጋዊ መንገድ ለመተላለፈ ሳይረጋግጥ ውሳኔ የሚሰጥ ቢላድ አህመድ ከሉፊ እና አንበር አህመድ ኡመር የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 (3)
No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡- ቢላድ አህመድ ከሉፊ ተጠሪ፡- አንበር አህመድ ኡመር አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካችና በሰበር ያልተጠራ መሀመድ ሃሰን በተባለ ግለሰብ ላይ ይዞታን አስመልክቶ አቅርበውት የነበረው ክስ ተቀባይነት አግኝቶ የውሃ ቤርካ ያለበት ይዞታ እና 39.40 በ38.20 ካ.ሜ. ይዞታ የተጠሪ ነው ቀሪው ግን የአሁን አመልካች ነው ሲል የሰጠው ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲለ አቤቱታ በማቅረባቸው መነሻነት ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላየው የሶማላ ክልል የቆራሄ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ አቅርበውት የነበረው ክስ በአጭሩ፡- በቀብሪደሀር ከተማ ዐ3 ቀበላ የሚገኝ 550 ሺ የሚገመት እና 2257.50 ካ.ሜ. በሆነው ይዞታ የአሁን ተጠሪ 500ካ.ሜ. ላይ ቪላ ቤት ገንብቷል፣ ሆኖም ዝምድና ስላለን እንዱጠብቅልኝ አድርጌ ሽማግላ ገብቶ 5000. ድላር እንድትከፍል ተጠይቃ አልከፈልም ስላለኝ 2ኛ የስር ተከሣሽም ወንድሟ ስለሆነ እየረዲት ስለሆነ ከስሻለሁ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን ተጠሪ በሰጡት መልስ ይዞታው የእኔ ነው፣ ወንድሜ መሬቱ ላይ እንድትኖር ስላደረገ አይቻት ትቼ ዝም ብዬ ነበረ፣ መሬቱ ብዙ ነው፣ ያጠረሽውም አሁን ልቀቂ አልላትም የሚያከራክረውን መሬት ግን ከተንበር ሰርታ ዘግታለች እናት በመሆኗ አልጠየኳትም በሚል አቅርባለች። 2ኛ ተጠሪ ከክስ ውጭ ስለሆነ መልስ አላቀረበም።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሰምቶ አከራካሪው ይዞታ ባለበት ቦታ ሄድ የተመለከተ ሲሆን፣ ከይዞታው ላይ 38.20 በ39.40 ካ.ሜ. የሆነው ይዞታ የከሣሽ መሆኑን ግራ ቀኙ የተማመኑ መሆኑን፣ ውሃ ቤርካ የተገነባበት ስፊቱ 11.40 ሜትር መሆኑን፣ ላላው በግል የታጠረው ቤትም የተሰራበት 17.ሜ በ26.70 የይዞታ መጠን ላይ ነው ሲል በመግለጽ ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው 11.40 እና 17 X 26.70 የማን ነው የሚል ጭብጥ በመያዝ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ማድረጉን ማዘዙን፣ ቀጥልም ክርክሩ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በመሆኑ የሰው ምስክር የማያስፈልግ መሆኑን፣ የስር ከሣሽ ያቀረቡትን የይዞታ ማረጋገጫን የሚመለከተው አካል አረጋግጦ ለፍ/ቤቱ እንዱልክ ትዕዛዝ መስጠቱን እና ምላሽ መቅረቡን ክርክሩ ያሳያል።
በዚሁ መሰረት የአሁን ተጠሪ ያቀረበችው የይዞታ ማረጋገጫ ያልተመዘገበ መሆኑን የሚመለከተው አካል መግለጫ የሰጠ ስለሆነ፣ 5000 ድላር ተጠሪ ልትከፍል ተስማምታለች የተባለውን በተመለከተም በጽሁፍ የተደረገ ውል ያልቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የላለ መሆኑን፣ የሚያከራክረው 39.40 x 38.20 የሆነው ይዞታ የውሃ ቤርካ ያለበት ይዞታ የተጠሪ ነው፣ ላላው ግን የቢላድ አህመድ ነው በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በውሣኔው ቅር ተሰኝተው ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አስቀርቦ እና የግራ ቀኙን ምስክሮች አስቀርቦ ሰምቶ የሚያከራክረው ይዞታ የአሁን ተጠሪ መሆኑ በምስክር ተረጋግጧል፣ በመሆኑም በይዞታው ላይ የተሰራው ቤት በአሁኑ ዋጋ ተገምቶ ለአሁን አመልካች ትክፈል ሲል የስር ፍ/ቤት ውሣኔን አሻሽል ወስኗል። አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህን የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔን በመቃወም ሲሆን፣ የአቤቱታው ይዘት በአጭሩ፡- የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ያቀረበችው ማስረጃ ህገወጥ መሆኑም ሆነ ከሚመለከተው አካል ያልተሰጠ ሆኖ እያለ፣ ባለቤት መሆኗንም የሚያረጋግጥ ሳይሆን፣ ክርክሩንም እንደ ሁከት ክርክር በመቁጠር እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1168 መሰረት ለ15 ዓመት ያህል የተከፈለ የመሬት ግብር የተገበረበት ባልቀረበበት፣ ባለእጅ ይዞታ ናችሁ በማለት የሰጠው ውሣኔ ባልተጠየቀ ዲኝነት በመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 182/2/ ድንጋጌ አንፃር በሚቃረን መልኩ ባልተጠየቀ ዲኝነት አስቀድሞ በሰበር በመ/ቁ/ 30956 ከሰጠው ውሣኔ ጋር የሚቀረን ውሣኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔም መሬት አይሸጥም አይለወጥም የሚለውን የህገ መንግሥት ድንጋጌን የሚቃረን በመሆኑ፣ ይዞታው ላይ ግንባታ ሳከናውን ምንም ተቃውሞ ሳይቀርብ የተገነባ ሆኖ እያለ፣ ተጠሪም ከእኔ የተሻለ መብት እንደላላት በተረጋገጠበት፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተጨማሪ ምስክሮችን ሰምቶ አመልካች ከሟች እናቴ በውርስ መቀበላን አስረድተው እያለ ተጠሪ መሬትን በህገወጥ መንገድ ሽያጭ ማግኘቷን ያስረደትን ምስክሮች በመቀበል የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ስላልሆነ ስህተቱ ሉታረም ይገባል ሲለ ጠይቀዋል።
አቤቱታው በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች የመሬት ግዢና ሽያጭ መሰረት ዋጋ ተገምቶ ቤት የገነባችበት መሬት ግምት እንድትከፍል በማለት የሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 አኳያ ለመመርመር ሲባል ለሰበር እንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ መዝገቡ የቀረበ ሲሆን መጥሪያም ለተጠሪ ተልኮላቸው ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
ተጠሪ በጠበቃቸው አማካይነት መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በተፃፈ በሰጡት መልስ የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 40/3 መሬት የህዝብና የመንግሥት በመሆኑ አይሸጥም አይለወጥም የሚለው መርህ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል። ይሁንና በተያዘው ጉዲይ በስር ፍ/ቤት መሬት ይሸጣል ወይም ይለወጣል የሚል ጭብጥ ተይዞ የተደረገ ከርክር እንዱሁም በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠ ውሣኔ የለም። ከዚህ ባሻግር የሁከት ይወገድልኝ ክስ ቀርቦ የባለቤትነት ክስን መሰረት በማድረግ የተሰጠ ውሣኔም የለም። ተሰጥቶም ከሆነ ሥነ ሥርዓታዊ ክርክር በመሆኑ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ የሚቀርብ ክርክር አይደለም።
ተጠሪ ከ20 ዓመት በፉት ከአሁን ተጠሪ ወንድም መግዛታቸውን፣ ቤት ገንብተውበታል፣የባለቤትነት ካርታም አውጥተውበት ህጋዊ ሆነዋል፣ ካርታውም የተሰጣቸው በ1996 ዓ.ም. ነው፣ ካርታው ህገ ወጥ ነው ከማለት በቀር ያቀረቡት ተጨባጭ ማስረጃ ስለላለ የሚሰጥ ውሣኔ አይኖርም።
አመልካች በሚያከራክረው ይዞታ ላይ ሉገኙ የቻለት ተጠሪ ወደ ውጭ አገር በሄደበት ወቅት አመልካች እና ባለቤታቸው/ማለትም የአሁን ተጠሪ ወላጅ አባት ጋር በአደራ ለመጠበቅ ስምምነት ላይ ደርሰው መሆኑን፣ አመልካችም ሲጠብቁ ቆይተው የተጠሪ ወላጅ አባት ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ በኋላ የተጠሪን አስቀድሞ የነበረን ቤት በማፍረስ በተጠሪ ይዞታ ላይ ያለተጠሪ እውቅና እና ፈቃድ አዱስ ግንባታ ገንብተው ለቅቀው ንብረቱን እንደያስረክቡ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ነው።
በመሆኑም በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 መሰረት ንብረት ማፍራት የሚቻለው በህግ አግባብ ሲሆን በልላ ሰው ይዞታ ላይ ግንባታ ከገነቡ በኋላ ህጋዊ ነኝ ማለት ግን ቅንነት የጎደለው እና አለአግባብ ለመበልፀግ የሚደረግ ጥረት ነው፣ አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ መገንባታቸውን ያልካደ፣ ተጠሪም ንብረታቸውን በአደራ እንዱጠበቅላቸው አደራቸውን ከማስቀመጥ ባሻገር በይዞታው ላይ ግንባታ አመልካች እንዱገነቡ ፈቃዲቸውን ያልሰጡ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ በመሆኑ ሉፀና ይገባል ሲለ አቅርበዋል፣ አመልካችም የቀደመው የሰበር አቤቱታቸውን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቀርበው ከመዝገብ ተያይዞ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ልውውጥ በዚህ ተጠናቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በእጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ መልስ እና የመልስ መልስ ከስር ፍ/ቤት አጠቃላይ ክርክር እና ውሣኔ እንዱሁም በአጣሪው ከተያዘው ማስቀረቢያ ጭብጥ አንፃር ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከክርክሩ አጠቃላይ ሂደት መገንዘብ የቻልነው ቀርቦ የነበረው ክስ የአሁን አመልካች 500ካ.ሜ. ላይ ቪላ ቤት ገንብቷል፣ ሆኖም ዝምድና ስላለን እንዱጠብቅልኝ አድርጌ ሽማግላ ገብቶ 5000. ድላር እንድትከፍል ተጠይቃ አልከፍልም ስላለኝ 2ኛ የስር ተከሣሽም ወንድሟ ስለሆነ እየረዲት ነው በሚል ክስ ማቅረባቸውን፣ አመልካች በበኩላቸው ይዞታው የራሳቸው እንደሆነ መከራከራቸውን ነው።
በአጣሪው ከተያዘው ጭብጥ አንጻር የመሬት ሽያጭ ውለ ከህገመንግሥቱ አንቀጽ 40/3/ አንፃር ተመርምሮ በስር ፍ/ቤት የመወሰን አለመወሰኑን አግባብነት በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በጭብጥነት ተይዞ ሉመረመር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ.ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 ንዐስ /3/ ‛የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ ነው። መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዩጵያ ብሓሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው።“ በሚል ይደነግጋል።
ተጠሪ የሚያከራክረውን ይዞታ ከአመልካች ወንድም ከ20 ዓመት በፉት ገዝተው ቤት ሰርተው እየኖሩበትና ግብርም እየገበሩ የይዞታ ማረጋገጫም በስማቸው አውጥተው እየተጠቀሙ ያለ መሆኑን በማንሳት የሚከራከሩ ሲሆን አመልካች በበኩላቸው የሚያከራክረው ይዞታ ከእናታቸው በውርስ የተላለፈላቸው መሆኑን አንስተው የመሬት ሸያጭና ግዢ ውል ህገ ወጥ ነው በማለት ነው።
ነገር ግን ተጠሪ ክስ ሲያቀርቡ ከላይ እንደተመለከትነው በይዞታቸው ላይ ተጠሪ ቤት ገንብተውበት ሽማግላ ገብቶ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኗ፣ በሽማግላ የተወሰነውንም 5000 ድላር ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለችም በሚል ሲሆን፣ ተጠሪ አንስተው የተከራከሩት ደግሞ ይዞታው የእኔ ነው፣ ወንድሜ መሬቱ ላይ እንድትኖር ስላደረገ አይቻት ትቼ ዝም ብዬ ነበረ፣ መሬቱ ብዙ ነው፣ ያጠረችውም አሁን ልቀቂ አልላትም የሚያከራክረውን መሬት ግን ከተንበር ሰርታ ዘግታለች እናት በመሆኗ አልጠየኳትም በሚል በመሆኑ በስር ፍ/ቤት ተደርጏ የነበረው ክርክር የሚያሳየው የመሬት ሽያጭና ግዢ ተነስቶ ክርክር አለመደረጉን ይልቁንም አመልካች አጥረው የያዙትን ይዞታ ልቀቂ ማለት እንደማይፈልጉና ልቀቂ የሚለት ላላ አጥረው ከተምበር ሰርተው የዘጉትን ቦታ መሆኑን ነው።
የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መስመር ለማስያዝ በማሰብ ከሚያከራክረው ይዞታ ድረስ በመሄድ እና የሚያከራክረውን ይዞታ በመለየት የሚመለከተውን አካል በመጠየቅ ከአጠቃላይ የግራ ቀኙ ይዞታ ለክርክሩ መሰረት መሆን የሚገባው ይዞታ 11.40 እና 17 X 26.70 የማን ነው የሚል ጭብጥ በመያዝ ግራ ቀኙን አከራክሮ የሚያከራክረው 39.40 x 38.20 የሆነው ይዞታ የውሃ ቤርካ ያለበት ይዞታ የተጠሪ ነው፣ ላላው ግን የቢላድ አህመድ ነው በማለት ወስኗል።
ከላይ የተጠቀሰው የህገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች አንፃር የሚያከራክረውን ይዞታ ተጠሪ አገኘሁት የሚለት በሽያጭ እንደሆነ ምንም እንኳን በስር ፍ/ቤት ክርክር የተደረገበት መሆኑን የሚያሳይ ነገር ባይኖርም በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ራሳቸው በሰጡት ምላሽ አረጋግጠዋል። በመሆኑም በድንጋጌው መሰረት የመሬት ሽያጭ በህገ መንግሥቱ የተከለከለ በመሆኑ ተጠሪ ይዞታውን ያገኙበት መንገድ ህገ ወጥ በመሆኑ ለተጠሪ ሉፀናላቸው የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት የለም።
ይልቁንም በስር ፍ/ቤት የሚያከራክረውን ይዞታ ከክርክሩ መለየት ባለመቻለ ችልቱ በአካል ተመልክቶ እና ግራ ቀኙ የሚተማማኑበት የቱ እንደሆነ የሚከራከሩበት የቱ ይዞታ እንደሆነ ተለይቶ በሚያከራክራቸው ይዞታ ላይ ተከራክረው ማስረጃም ቀርቦ በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጦ የተወሰነ ሲሆን፣ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግን በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ወደ ጏን በመተው የይዞታው መተላለፉያ መንገድን ሳይመረምር እና ህጋዊነቱንም ከህገ መንግሥቱ ስለመሬት ማስተላለፉያ መንገድች በህጋዊ መንገድ ስለመተላለፍ ሳያረጋግጥ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ በማሻሻል አመልካች የመሬቱን የአሁን ዋጋ ግምት እንዱከፍለ ሲል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም የስር ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ላይ የተፈፀመውን ስህተት ሳያርም ማለፈ ተገቢ አይደለም ብለን ተከታዩን ወስነናል።
የሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 05-01-122/13 ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 05-01-183/12 የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የሶማላ ክልል የቆራሄ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ msgo/m5/012 በቀን 19/06/2012 ዓ.ም.
በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
በዚህ መዝገብ የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት በቆራሄ ከፍተኛ ፍ/ቤት አፈፃፀም ችልት በመ/ቁ/ msgo/m/1/13 ላይ የተሰጠው እግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.