አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለሀብትነት በማወቅ የመመዝገብ ሥልጣን ያለው አካል ይዞታ በስጦታ የተገኘ መሆኑ ተረጋግጦ በባህር መዝገብ ተመዝግቦ የዚህ ይዞታና ቤት ባለቤት ስለመሆን በሚመለከተው አካል ፉት የተረጋገጠ እንዱሁም የባለይዞታው ህጋዊ ይዞታ አይደለም የሚል ወገን ቢመጣም መቃወሚያ እንዲይሆን የሚያደርግ ህጋዊ ሂደቱ ተጠብቆ በህግ ጥበቃ እየተደረገለት ያለ መብት በህግ አግባብ ለባለይዞታ የተላለፈ እና ይህንኑ ንብረት ህጋዊ ውክልናን በመያዝ ሲተዲድር የቆየ መሆኑ የሚያሳይ ሆኖ እያለ ይዞታው እንዱለቀቅና በውርስ ህግ አግባብ ሉጠየቅ ይገባል በሚል የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የላለው ፅጌ ቀለመወርቅ እና ወ/ሮ አረጋይ ከበደው
No summary available.
ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡- ወ/ሮ ፅጌ ቀለመወርቅ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አረጋይ ከበደው ይህ መዝገብ ከመ/ቁ/ 205748 ጋር ተጣምሮ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው የአሁን ተጠሪ ይዞታን እና የቤት ኪራይ ገቢን አስመልክቶ በአመልካች ላይ በፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 33893 በሆነው ከሣሽ፣ በመ/ቁ/ 33695 በሆነው ተከሣሽ በመሆን ተከራክረው ሁለቱ መዛግብት ተጣምረው ተመርምረው በተሰጠው የአሁን አመልካች የሚያከራክረውን ይዞታ እንዱለቁ እና የቤት ኪራይ ገንዘብም እንዱከፍለ በሚል የተሰጠው ውሣኔ በይግባኝም ሆነ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያልተለወጠ በመሆኑ በስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ የተፈፀመውን መሰረታዊ የህግ ስህተት በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲለ አመልካች አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላየው የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በአሁን ተጠሪ ቀርቦ በመ/ቁ/ 33893 በሆነው መዝገብ እንደቀረበው በሰበታ ከተማ አስተዲደር ቀበላ 03 ውስጥ በሚገኝ በስተሰሜን፣ በምዔራብ እና በምሥራቅ መንገድ እና በደቡብ የበርታ ሀሰን እና የወ/ሮ ድርቤ መኮንን ቤት የሚያዋስነውን የቦታ ስፊቱ 555 ካ.ሜ. የሆነ ላይ የሚገኝ በሟች ባለቤቴ በአቶ ቀለመወርቅ ብርሃኔ ስም በአስተዲደሩ ተመዝግቦ ያለ የመሬት ይዞታ እና ቤት ተሰርቶበት የሚገኘው የድሮ ይዞታ ስለሆነ በደርግ ስርዓት ከአቶ ሙባረክ ዱኖ፣ታምሩ አበበ እና አቶ በየነ ሸዋ ከሚባለት ላይ ሟች ባለቤቴ አቶ ቀለመወርቅ ብርሃኔ ጎን እና ጎን ያለ መሬት የቦታው ስፊት 2000 ካ.ሜ በመግዛት የያዘው እንደገበሬ የመንግሥት ግብር እየተገበረበት በእርሻ እየተጠቀመበት የቆየ ሲሆን እኔ ከዚህ ባለቤቴ ጋር በ1994 ዓ.ም. ተጋብተን እዚህ መሬት ላይ የተለያዩ ቤቶች በመሥራት ላላውን ደግሞ በእርሻ እየተጠቀምንበት በመሆኑ አካባቢው በሰበታ ከተማ አስተዲደር ስር ሲታቀፍ ይህ መሬት በእጃችን ስለቀረ ካርታ እንዱሰጠን ጠይቀን እየጠበቅን ያለን መሆኑ የከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ በሚሰራበት ጊዜ የመሬት ይዞታችን መንገድ ወጥቶበት ለሁለት ቦታ ያካፈለው ሲሆን፣ ሁለቱም ጊቢ በውስጥ የሚገኙ በባለቤቴ ስም ተመዝግቦ የመብራት ሀይል ቆጣሪ ገብቶልን በሰበታ ከተማ አስተዲደር ቀበላ 03 የቤ/ቁ/ 2046 ተሰጥቶ 13 ክፍል ቤቶች በተለያዩ ጊዜ በላዩ ላይ ተሰርቶ ያለን በማከራየት እየተጠቀምንበት የነበረ ባለቤቴ በቀን 09/12/2008 በሞት ከዚህ ዓለም የተለየ ሲሆን እኔ የልጆች ሞግዚትነት እና ሚስትነቴን አሳውጄ ማስረጃ ተሰጥቶኛል።
አመልካች በህግ የተሰጣት አንዲችም መብት ሳይኖራት የባልና ሚስት ንብረት የሆነውን ከሟች ጋር በጋራ አፍርቼ ያለኝን አመልካች ቤቱ የእኔ ነው ብላ በጉልበት የያዘችው የቤቱንም ኪራይ ከልክላኛለች ስለሆነም አመልካች የሟች ባለቤቴ አቶ ቀለመወርቅ ብርሃኔ ንብረት እና አብረን ያፈራነውን እና የልጆቼ የውርስ ንብረት የሆነውን እንድትለቅ ወጪና ኪሣራም እንድትከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን ተጠሪ ተሻሽል ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ የሚያከራክረው ቤትና ይዞታ ከባለቤቴ ጋር ያፈራነውና የተጋባንበት ነው። እስካሁንም ድረስ በሟች ባለቤቴ ስም ግብር የምንገብርበት ሲሆን መብራት እና ውሃም በሟች ስም ገብቷል። ይዞታው ወደከተማ ሲካለል የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲወጣ ሁለት ቦታ የተካፈለ 600 ካ.ሜ. በአንድ በኩል ከ600 ካ.ሜ. በላይ የሚሆን ደግሞ በዚህ በኩል ያለውን ቤቶች ሰርተን እያከራየን እየተጠቀምንበት ያለ መሆኑን፣ ሟች ባለቤቴ እና የአሁን ተከሣሽ አባት በቀን 09/12/2008 ከሞተ በኋላ ወ/ሮ ጽጌ ቀለመወርቅ የእኔ ነው ብላ የመሬት ይዞታ እና እነዚህን ቤቶች የያዘችው ቢሆንም አንዲችም መብት እንኳን ሳይኖራት በሀሰት ምስክር በመመርኮዝ የእኔ ነው ብላ የተከራከረች ቢሆንም በደርግ ስርዓት ውስጥ ቀበላው ከመሬት ክፍፍል አልፍ የመሬት ስጦታ ውል ሉያረጋግጥ የማይችል መሆኑን፣ እሷ ለምስክርነት ያቀረበችው ደረሰኝ የውሸት እና ከዚህ ጉዲይ ጋር የማይገናኝ መሆኑን እኔ 20 ክፍል ቤቶች እያከራየሁ በወር .00 ታገኛለች ያለችውም ውሸት መሆኑን፣ ቤቶቹ ፈራርሰው ከጥቅም ውጭ ስለሆኑ የተወሰኑት ክፍልች ብቻ እየተከራዩ የሚገኙና ገቢ እና ትንንሽ ልጆች እና ከሟች ጋር አብረን ያፈራናቸው እየተጠቀሙባቸው በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይደረግልኝ ሲለ ተከራክረዋል።
አመልካችም/የስር ተከሣሽ/ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ፡- ወ/ሮ አረጋይ ከበደው እነዚህ ቤቶች ንብረት በባለቤታቸው በአቶ ቀለመወርቅ ብርሃኔ ስም አለ ትበል እንጂ ከአቶ ታምሩ አበበ ላይ በስጦታ ያገኘችው መሆኑን እና የከራቡ ሁርቡ ቀበላ የማህበራዊ ፍርድ ቤት በቀን 21/12/1982 ዓ.ም. የተሰጠ ውሣኔ በተከሣሽ ስም ግብር እንደምትገብርበት ቤትም እላዩ ላይ እንድትሰራበት እና ማንኛውንም ንብረት በላይ ላይ እንድታፈራበት የተወሰነላት መሆኑን የመንግሥት ግብር በስሟ እየገበረች ቤቶች እላዩ ላይ ሰርታ እየተጠቀመችበት መቆየቷን እሷ ውጪ ሀገር ለስራ ከመሄዶ በፉት የመሬት ይዞታ እና እላዩ ላይ የተሰሩት ቤቶች አባቷ አቶ ቀለመወርቅ ብርሃኔ በውክልና ቁጥር 2116/1/98 ነሐሴ 3/1998 ዓ.ም.
ሰጥታው እሱም በዚህ ውክልና በመመርኮዝ በራሷ ገንዘብ የተለያዩ ቤቶች በተጨማሪነት በመሬቱ ላይ ሰርቷል ይሁን እንጂ ይህ የመሬት ይዞታ እና እነዚህ ቤቶች በ1999 ዓ.ም. ውስጥ በሰበታ ከተማ ቀበላ 03 ውስጥ ታቀፈ ሲባል የሰበታ ከተማ አስተዲደር የውስጥ ለውስጥ መንገድ በሚያወጣበት ጊዜ የመሬት ይዞታዬን ሁለት ቦታ እንዱከፈል ሆኗል።
በዚህም ምክንያት ይህ ክርክር የተነሳበት መሬት ስፊቱ 555 ካ.ሜ. የሆነ በእኔ እጅ የቀረ ሲሆን በግምት ከ600 ካ.ሜ. በላይ የሚሆን መሬት ትልቅ ቤት እና 20 ክፍል ሰርቪስ ቤቶች የሆኑት አብረው የተቆረጡ ከሣሽ/የአሁን ተጠሪ/ በሟች አባታችን በማመካኘት ግማሹን በጉልበት የያዘችባት መሆኑን እና ይህ ቤት ንብረት እንደምትለው የአሁን ተጠሪዋ ሳይሆን የአሁን አመልካች መሆኑን እና በስሟ ያለ እና የቤት ቁጥር 3686 የሚል ተሰጥቶት የሚገኝ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዱሆንላት ጠይቃለች።
የአሁን አመልካች የተሻሻለ ክስ በ14/03/2011 ዓ.ም. በመ/ቁ/ 33893 ላይ ያቀረበች መሆኑን፣ ይዘቱም ለክርክር ምክንያት የሆነውን መሬት የስጦታ ውል በቀን 12/12/1982 ዓ.ም. ያገኘሁት በላዩ ላይ ቤት ሰርቼ ያለው ተጠሪ የእኔን ንብረት ለ24 ወራት ከህግ ውጭ ለሰዎች እያከራየች እየተጠቀመችበት በመሆኑ የቤቶቹ ግምት .00 /ሁለት መቶ ሀሣሳ ሺ/ እንድትለቅልኝ እና የ20 ሰርቪስ ቤቶችን ኪራይ ደግሞ የአንድ ወር .00/ አስራ ዘጠኝ ሺ ሁለት መቶ / እና 9 በመቶ ወለድ .00/ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ብር/ በአጠቃላይ .00/ አምስት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺ ሰባት መቶ አርባ አራት / ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ እና የጠበቃ አበል እንዱሁም ወጪና ኪሣራ እንድትከፍል ይወሰንልኝ በማለት አቅርባለች።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሰምቶ እና መዝገቡን አጣምሮ በሁለቱም መዛግብት ላይ የቀረበውን ክርክር በማጠቃለል ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን ምስክሮች አዲምጧል። የቀረበውን ክርክር ለማጣራት ለሚመለከተው አካል ትዕዛዝ መስጠቱን እና ምላሽ መምጣቱን ተመልክተናል።
የቀረቡት ምስክሮች የሰጡትን ቃል፣በግራ ቀኙ በቀረበው ክርክር የቀረቡ የሰነድ ማስረጃዎችና እና ፍ/ቤቱ ጠይቆ የቀረበለትን ማብራሪያ መመርመሩን እና በተጠሪ በኩል በመ/ቁ/ 33893 በሆነው መዝገብ ቀርቦ የነበረውን ክስ አስመልክቶ ከሣሽ/ተጠሪ የመክሰስ መብት የላትም በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 33/2 መሰረት ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ አመልካችም አቅርባው የነበረውን ክስ መኖሪያ ቤቱ ሟቹ እና ተጠሪዋ በጋብቻ ወቅት አብረው ያፈሩት ነው በሚል ውድቅ ያደረገ እና በአብላጫ ድምጽ የወሰነ መሆኑን የውሣኔው ግልባጭ ያሳያል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የአሁን ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኛቸውን ያቀረቡ እና በመ/ቁ/ 322203 በሆነው የተከፈተና የተመረመረ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አስቀርቦ እና ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ በመሻር የአሁን አመልካች ለክርክር መነሻ በሆነው የመኖሪያ ቤት ንብረት ባለቤት መሆኗ ስላልተረጋገጠ ሰበታ ከተማ ቀበላ 03 ውስጥ አዋሳኙ በሰሜን፣በምዔራብ እና በምሥራቅ መንገድ፣ በደቡብ በርታ ሃሰን ቤት እና ወ/ሮ ድርቤ መኮንን መካከል ተዋስኖ የሚገኝ በግምት 555 ካ.ሜ. ቦታ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው መኖሪያ ቤት የአሁን አመልካች ለአሁን ተጠሪ እንድትለቅ እና አመልካች ወላጅ አባቷን ለመውረስ የምታቀርበውን መብት የሚያግድ አይደለም ሲል ወስኗል።
የአሁን አመልካች የስር ፍ/ቤት ውሣኔን በመቃወም ይግባኝ ያለች ሲሆን ይግባኛቸው በመ/ቁ. 322114 ላይ ተመርምሮ ውድቅ መደረጉን፣ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ በመ/ቁ/ 333945 በሆነው አቅርበው ውድቅ ተደርጓል።
ከዚህ የምንረዲው አመልካች በአንድ በኩል ተጠሪ በልላ በኩል የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መዛግብቱን አጣምሮ ባየው ጉዲይ በየፉናቸው ይግባኝ ማለታቸውን እና በተለያየ መዝገብ መስተናገዲቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም በየፉናቸው አቤቱታ ማቅረባቸውን እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን ነው።
አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት ያላገኘ በመሆኑ ተሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሣኔ በመቃወም ሲሆን አመልካች መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
የአቤቱታው ይዘት በአጭሩ፡- የሚያከራክረው ይዞታ የተጠሪ ባለቤት የገዛው ነው በሚል ተጠሪ ትከራከር እንጂ በስር ፍ/ቤት የሽያጭ ውል ያላቀረበች መሆኑን፣ በማስረጃነት የተያያዘው አቶ ታምሩ አበበ ለአመልካች ስጦታ የሰጡበት ማስረጃ መሆኑን፣ አባቴ በይዞታው ላይ መብት የለውም እንጂ መብት ያለው ቢሆን እና በግዢ አግኝቶት ህጋዊ ለማድረግ የተፈለገ ቢሆን ኑሮ ስጦታው ለአባቴ እንጂ ለእኔ ላሰጥ አይገባም ነበር፣ የስጦታ ውለንም ሟች መፈፀም ነበረበት፣ አባቴ በይዞታው ላይ መብት ያለው ቢሆን ኑሮ ለምን በአባቴ ስም የስጦታ ውለ አልተፈፀመም፣ የስጦታ ውለ ባልተሻረበት ንብረቱ ያንቺ አይደለም ተብል ሉወሰን የሚገባው ባልሆነበት፣ አባቴና እናቴ ጋብቻ የፈፀሙት በ1994 ዓ.ም.
በመሆኑ ንብረቱ በጋብቻ ውለ ላይ ሉቆጠር ይገባው ነበር፣ የወላጅ አባቴ ሀብት ከሆነ የራሱን ሀብት እንዳት ከእኔ ውክልና ወስድ ሉያስተዲድር ይችላል የሚለና ላልች ዝርዝር ነጥቦችን በማንሳት የሚያከራክረው ይዞታና ቤት የእኔ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ሉሻር የሚገባው ነው በማለት አቤቱታ አቅርባለች።
አቤቱታው በአጣሪ ችልቱ ተመርምሮ በሰ/መ/ቁ/ 204748 በሆነው ክርክር የተነሳበት ይዞታ ለአመልካች በስጦታ ተላለፈ የተባለው በ1982 ዓ.ም. ሆኖ በተጠሪ እና በሟች መካከል ጋብቻ የተፈፀመው በ1994 ዓ.ም. መሆኑና ስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ በተመለከተበት ሁኔታ ስር ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ የመወሰኑን አግባብ ለመመርመር በሚል ጭብጥ የተያዘ ሲሆን፣ በሰ/መ/ቁ/ 201741 በሆነው ደግሞ የአሁን አመልካች ይዞታውን በስጦታ አግኝታ ለአባቷ ውክልና ሰጥታ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤት ገንዘብ በመላክ የሰራችው እና ግብርም እየገበረችበት የነበረው ቤት ለአመልካች አይገባትም ተብል የተወሰነበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር እንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ ሁለቱም መዛግብት ለችልቱ የቀረበ ሲሆን መጥሪያም ለተጠሪ ተልኮላቸው ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
ተጠሪ በሰ/መ/ቁ/ 205748 በሆነው ላይ ያቀረቡት ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በተፃፈ ያቀረቡት መልስ በአጭሩ፡- አመልካች በስጦታ አገኘሁ ያለችውን በተመለከተ በራሷ በኩል ቀርበው የነበሩ የፍርድ ሸንጏ ፀሐፉ የነበሩት ግለሰብ በሰጡት ምስክርነት ስጦታ ተሰጠ በተባለ ጊዜ አመልካች ህፃን ልጅ የነበረችና የምትኖረውም በአዱስ አበባ ለገሃር አካባቢ ከእናቷ ጋር የነበረ መሆኑን ስጦታ ተደረገ በተባለበት ቦታም በጊዜው ያልነበረች እና ስጦታ አረጉ የተባለት አቶ ታምሩ አበበንም የማታውቅ መሆኑን፣ ይልቁንም ስጦታ ተባለ እንጂ አቶ ቀለመወርቅ ከኪሣቸው ገንዘብ የከፈለና ኩታ ገጠም የሆኑ ይዞታዎችን የገዙ መሆኑን፣ አመልካች ከውጭ አገር ገንዘብ እየላኩ ተሰራ ያለችው ሀሰት መሆኑን እና የትኛው ቤት ሲሰራ ገንዘብ እንደላከች በመግለጽ ያለመከራከሯን፣ ባለቤታቸው አስቀድሞ ገዝተውት ለእርሻ ሲጠቀሙበት የነበረውን ይዞታ በ1994 ዓ.ም. ተጠሪን ካገቡ በኋላ ቤቶች እየተሰሩበት ሲጠቀሙ የቆዩ የጋራ ንብረት እንጂ የግል ንብረት አለመሆኑን፣ በስር ፍ/ቤት መዝገቡ ተጣምሮ በአንድ ላይ ጭብጥ ተመስርቶበት የተከራከሩ መሆኑን በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ግን ስለተጠሪ እና የአመልካች አባት ጋብቻን በተመለከተ ያልተነሳውን እና ክርክር ያልተካሄደበትን በመያዝ ተጠሪን መልስ ማሰጠት ተገቢ አለመሆኑን፣ የይዞታው አመጣጥም አቶ ቀለመወርቅ ኩታ ገጠም የሆኑ የእርሻ ይዞታዎችን ከተለያዩ ሰዎች በ1982 ዓ.ም. ገዝተው ቤት እየሰሩ እያረሱ መልሰው እየሰሩ ሲጠቀሙበት የቆዩ እና ወደ ከተማ ሲካለል በመንገድ ምክንያት ለሁለት የተከፈለ እና አቶ ቀለመወርቅ በ2008 ዓ.ም. ሲሞቱ አመልካች በጉልበት የያዘችው እንጂ በስጦታ ያገኘችው አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤት ውሣኔ እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል። በሰ/መ/ቁ/ 201741 በሆነው ላይ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱ በቀዲሚው መዝገብ ያቀረቡትን ክርክር የሚያጠናክር እንጂ የተለየ ሆኖ ባለመገኘቱ መመዝገብ አላስፈለገም። አመልካችም የቀደመውን የሰበር አቤቱታቸውን በማያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ በሁለቱም መዛግብት በማቅረብ እና ከመዝገብ ተያይዞ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ልውውጥ በዚሁ ተጠናቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በእጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ መልስ እና የመልስ መልስ ከስር ፍ/ቤት አጠቃላይ ክርክር እና ውሣኔ እንዱሁም በአጣሪው በሁለቱም የሰበር መዛግብት ላይ ከተያዘው ማስቀረቢያ ጭብጥ አንፃር ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደመረመርነውም በሁለቱም ለሰበር የቀረቡ መዛግብት የክርክር መነሻቸው በስር ወረዲ ፍ/ቤት ተጣምረው የታዩ በሂደት ሁለት ቦታ የተከፈለ ሆኖ ነገር ግን በአንድ ንብረት ላይ የተደረገ ክርክር ሲሆን፣ በሰ/መ/ቁ/ 205738 በሆነው አመልካች የቤቶቹ ግምት .00/ሁለት መቶ ሀሣሳ ሺ/ እንድትለቅልኝ እና የ20 ሰርቪስ ቤቶችን ኪራይ ደግሞ የአንድ ወር ብር 192ዐዐ.ዐዐ/ አስራ ዘጠኝ ሺ ሁለት መቶ / እና 9 በመቶ ወለድ .ዐዐ/ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ብር/ በአጠቃላይ .ዐዐ/ አምስት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺ ሰባት መቶ አርባ አራት / ከወለድ ጋር ተጠሪ እንድትከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ክስ ያቀረበች መሆኑን፣ በሰ/መ/ቁ/ 2ዐ1741 በሆነው መዝገብ ደግሞ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት በሟች ባለቤቴ በአቶ ቀለመወርቅ ብርሃኔ ስም በአስተዲደሩ ተመዝግቦ ያለ የመሬት ይዞታ እና ቤት ተሰርቶበት የሚገኘው የድሮ ይዞታ ይዞታችን መንገድ ወጥቶበት ለሁለት ቦታ ያካፈለው ሲሆን፣ ሁለቱም ጊቢ በውስጥ የሚገኙ በባለቤቴ ስም ተመዝግቦ የመብራት ሀይል ቆጣሪ ገብቶልን በሰበታ ከተማ አስተዲደር ቀበላ 03 የቤ/ቁ/ 2046 ተሰጥቶ 13 ክፍል ቤቶች በተለያዩ ጊዜ በላዩ ላይ ተሰርቶ የምንጠቀምበትን አመልካች በጉልበት ይዛ እየተጠቀመች ስለሆነ እንድትለቅ ይወሰንልኝ የሚል ክስ አቅርባለች።
የስር ፍ/ቤትም ሁለቱንም መዛግብት አጣምሮ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የግራ ቀኙን ክስ ውድቅ ያደረገ በመሆኑ ግራ ቀኙ ይግባኝ የጠየቁ በመሆኑ የአመልካች ይግባኝ ውድቅ ተደርጏ እስከ ክልለ ሰበር የፀና ሲሆን፣ ተጠሪ ያቀረበችው ይግባኝ ግን ተቀባይነት አግኝቶ አመልካች ይዞታውንና ቤቱን እንድትለቅ የወራሽነት ድርሻ አለኝ የምትል ከሆነ መጠየቅ እንደምትችል በማመላከት የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሮ ተወስኗል። ይህ ውሣኔ በሰበር ያልተለወጠና የፀና መሆኑን የክርክሩ አመጣጥ ያሳየናል።
ከአጠቃላይ ክርክሩ እና ከማስቀረቢያ ነጥቡ አንፃር የስር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔን አግባብነት መመርመር ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው ይዞታና ቤት አመልካች ለእኔ በስጦታ የተሰጠኝ እና ለአባቴ ውክልና ሰጥቼ በገንዘቤ ያስገነባሁት እንጂ ተጠሪ እንደምትለው አይደለም በማለት የምትከራከር ሲሆን ይህን ለማረጋገጥ የቀረበውም አቶ ታምሩ አበበ የተባለ ግለሰብ ለአመልካች ይዞታውን በስጦታ የሰጧት መሆኑን እንደሆነ የስጦታ ውለም በማህበራዊ ፍ/ቤት የፀደቀ መሆኑን እና ለወላጅ አባቷም ውክልና የሰጠች ፣ ቤቶቹን ተጠሪ እያከራየች እየተጠቀመች በመሆኑ ኪራዩን እንድትከፍለኝ የሚል ነው።
እነዚህን ፍሬ ነገሮች አስመልክቶም በስር ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክር የሚያከራክረውን ይዞታ አቶ ታምሩ አበበ የተባለ ግለሰብ ለአመልካች ስጦታ መስጠታቸውን የሚያረጋግጥ ሥልጣን ባለው አካል የፀደቀ የስጦታ ውል የቀረበ ስለመሆኑ፣ አመልካች ለአባቷ ንብረቱን እንዱያስተዲድርላት ውክልና የሰጠች መሆኑ፣ ሟችም የሚያከራክረው ይዞታ ላይ ቤቶችን መገንባቱን፣ ይዞታውም በአመልካች ስም በባህር መዝገብ ተ.ቁ. 3686 በሆነው ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን፣ እንዱሁም ተጠሪ ሟች አቶ ቀለመወርቅን ያገቡት የሚያከራክረው ይዞታና ቤት ተገዝቶ እና ቤቶቹም በላዩ ላይ ከተገነቡ በኋላ ስለመሆኑ ማስረጃን የማረጋገጥ ፍሬ ነገርን የመለየት ሥልጣን ባላቸው የስር ፍ/ቤቶች ተረጋግጧል።
አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለሀብትነት በማወቅ የመመዝገብ ሥልጣን ባለው አካል ይዞታን አመልካች ከአቶ ታምሩ አበበ በስጦታ ያገኘች መሆኑን አረጋግጦ በባህር መዝገብ መዝግቦ ያለ በመሆኑ አመልካች የዚህ ይዞታና ቤት ባለቤት መሆኗ በሚመለከተው አካል ፉት የተረጋገጠ መሆኑን እንዱሁም የእሷ አይደለም የሚል ወገን ቢመጣም መቃወሚያ እንዲሆን የሚያደርግ ህጋዊ ሂደቱ ተጠብቆ በህግ ጥበቃ እየተደረገለት ያለ መብት እንደሆነ ያሳያል። በመሆኑም ይህ ይዞታ በህግ አግባብ ለአመልካች የተላለፈ እና ሟች አባቷም ይህንኑ ንብረት ህጋዊ ውክልናን በመያዝ ሲያስተዲድርላት የቆየ መሆኑ የማያሳይ ሆኖ እያለ የስር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይዞታውን እንድትለቅና በውርስ መጠየቅ እንደምትችል በመግለጽ መወሰኑ የበላይ ፍ/ቤትም ይህን ስህተት ሳያርም ማለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ ሉሻር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል አመልካች የኪራይ ገንዘብ ይከፈለኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ ተከትል የቀረበውን መዝገብ አስመልክቶ አጣሪ ችልቱ የያዘው ጭብጥ ከላይ ውሣኔ ያገኙትን ቤቶች እና ይዞታን መሰረት አድርጏ በመሆኑ በጭብጥም ያልተያዘ አመልካችም ይህ የኪራይ ገንዘብ ይከፈለኝ በማለት ያቀረበችውን ክርክር አመልካች ራሷ የሰራችውን ቤት ተጠሪ እያከራየች የምትጠቀም ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት በማስረጃም ያልተረጋገጠ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ክሱን ውድቅ ማድረጉና በበላይ ፍ/ቤቶችም ውሣኔው ያለመለወጡ ተገቢ እንጂ የሚነቀፍና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ልባል የሚገባው አይደለም ብለን አቤቱታውን ውድቅ አድርገን ተከታዩን ወስነናል።
በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/.
322203 ህዲር 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 333945 ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 322114 በ15/7/2012 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ እና የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 33695 በ11/03/2012 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ ፀንቷል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በግራ ቀኙ የወጣ ወጪ ካለ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
በዚህ መዝገብ በዛሬው ቀን የተሰጠው ውሣኔ ግልባጭ በመ/ቁ/ 201741 በሆነው የሰበር መዝገብ ላይ ተገልብጦ እንዱያያዝ ታዟል።
No topics extracted.