ንብረት ያረፈበት ቦታ ለልማት ሲፈልግ ወይም በመሬት ላይ የሚገኝ ንብረት የተወሰደበት ሰዉ እንደ አግባብነቱ ምትክ ቦታ እንዱሰጠዉ ወይም ከመሬት ላይ ለተነሳዉ ንብረት የማፈናቀያ ካሳ እንዱከፍለዉ የመጠየቅ መብት ያለዉ ሲሆን መንግስትም ይህን የማድረግ ግዳታና ንብረቱ የተወሰደበት ወይም ከቦታዉ እንዱነሳ የተደረገ ሰዉ የሚያቀርበዉ የካሳ ይገባኛል ጥያቄ ይህን ሁለ ከግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባ አቶ ጫላ ያኢ ፈሪ እና የንፊስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(8) እና ለህዝብ ጥቅም ሲባል የግል ንብረትን መዉሰድ የሚቻልበትን አግባብ የሚደነግግ አዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 7 እና 8
No summary available.
ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- አቶ ጫላ ያኢ ፈሪ - ቀርበዋል ተጠሪ- የንፊስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት- አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታዉን ለለቀቀ ባለይዞታ ሉከፈል የሚገባዉን ካሳ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በጀመረበት በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የከተማ ቦታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበት ክስ በውርስ ከተላለፈልኝ መሬት ውስጥ መጠኑ 98,463 ካ.ሜ የሚሆነውን የእርሻ መሬት ተጠሪው በ1997 ዓ.ም የወሰደ ሲሆን 35,000 ካ.ሜ የእርሻ፣ 64,460 ካ.ሜ ደግሞ የግጦሽ በሚል ከፊፍል ካሳ ብር 5,273,572.20 ቢከፈለኝም ካሳው በአግባቡ አልተሰላም። የማፈናቀያ ካሳ፣ ለተደረገው ቋሚ ማሻሻያ እና የጎርፍ መቀልበሻ እና መከላከያ፣ ቁጥቋጦ ያስነቀልኩበት እና ያስመነጠርኩበት የጉልበት ዋጋ እና በመሬቱ ላይ ለነበረው ባህርዛፍ ካሳ ያልተከፈለኝ በመሆኑ ቀሪ ብር 9,216,506.29 እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
ተጠሪ የተለያዩ የመጀመሪያ መቃወሚያዎችን በማስቀደም ለክሱ በሰጠው መልስ በኤጀንሲው በተሰራ ግምት እና በወቅቱ በነበረው የካሳ ስላት መሰረት ለአመልካች ካሳ የተከፈላቸው ሲሆን በዚህ ላይ ቅሬታ ካላቸዉ በ30 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ሲገባቸዉ አላቀረቡም። ለመንገድ እና ጋራጋንቲ ስራ ተወስዶል በሚል የተጠየቀዉም ካሳ የተከፈለበት ሲሆን የባህርዛፍ ግምቱን በሚመለከት ሉከፈላቸው አይገባም እንጂ ሉከፈላቸው ይገባል እንኳን ቢባል የመፈናቀያ ካሳ ነጠላው በ10 ተባዝቶ ሳይሆን መሬቱን እንዱለቁ ከመደረጉ በፉት በነበሩት አምስት ዓመታት ውስጥ ያገኙ የነበረው ዓመታዊ ገቢ በ10 ተባዝቶ ነው፤ በአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ተወስድ ለደን ተከላ የዋለ 27,226.09 ካ.ሜ መሬት ካሳን በሚመለከት የቀረበውን ጥያቄ ተጠሪን የማይመለከተው ሲሆን ቦታውም ለልማት ተነሺ በሚል ስም በተጠሪ ያልተጠና እና ተነሺነቱ እውቅና ያልተሰጠው በመሆኑ ጥያቄው የተጠሪን ጽ/ቤት አይመለከትም በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩ የቀረበለት የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ አመልካች የተሰራላቸውን ካሳ ተቀብለው ቦታውን ለልማት እንዱያስረክቡ ቢነገራቸውም ፍቃደኛ ስላልሆኑ ካሳው በዝግ ሂሳብ እንዱቀመጥ መደረጉን፤ አመልካች በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለመሬት ልማት እና ከተማ ማደስ ጽ/ቤቱ እና ለከንቲባ ጽ/ቤት ቢያቀርቡም በወቅቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ላለው የካሳ ጉዲዮች እና ምትክ ቦታ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንዲላቀረቡ፤ የከንቲባው ጽ/ቤት ጉዲዩ በድጋሚ ታይቶ ህጋዊ ውሳኔ እንዱሰጣቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ በዝግ ሂሳብ እንዱቀመጥ የተደረገው ብር 452,784.16 የሆነው የካሳ መጠን ተሻሽል ብር 5,273,572.00 እንዱከፈላቸው ተወስኖ በቀን 12/05/2009 ዓ.ም ክፍያውን መቀበላቸውን፤ የድንጋይ ካባ እና በአካባቢ ጥበቃ ተወስድብኛል የሚለትን መሬት በሚመለከት በአቤቱታው ውስጥ የተካተተ እና ከክፍያው በፉት የተቋጨ እንደሆነ አመልካች እንዲልካደ፤ ለይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ለመጀመሪያ ጊዜ አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 21/05/2009 ዓ.ም የተሰጣቸውን መልስ መሰረት በማድረግ እንደሆነ፤ እንዱሁም ጉዲዩ በአስተዲደራዊ ውሳኔ እንደተቋጨ በመግለጽ የከንቲባው ጽ/ቤት በፍትህ እና በርትዔ መፍትሓ ያበጀለትን ጉዲይ እንደገና መርምሮ መወሰን አግባብነት የለውም፤ አመልካች አሁንም ተጎድቻለው የሚለ ከሆነ በተጀመረው አኳኋን ቅሬታቸውን ለከንቲባው ጽ/ቤት ማቅረብ ይችላለ ሲል አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩበት በኋላ ጉባኤው አመልካች ካሳው በህጉ አግባብ ተሰልቶ አልቀረበም፣ የተከፈለኝ ካሳም በቂ አይደለም በሚል ያቀረቡትን ቅሬታ እና የተጠሪን መልስ በማስረጃ አጣርቶ ሳይመረምር ለአመልካች የተከፈለው ካሳ የሚጠቅመው እንጂ የሚጎዲው አይደለም ሲል የደረሰበት መደምደሚያ ስህተት በመሆኑ ጉዲዩን በማስረጃ አጣርቶ እንዱወስን መልሶ ልኮለታል።
በዚሁም መሰረት ጉባኤው የተመለሰለትን ጉዲይ ከመረመረ በኋላ በመመሪያ ቁጥር 19/2006 መሰረት በወቅቱ ከእርሻ ማሳው ላይ የተሰበሰበው ዓመታዊ ምርት በ10 ተባዝቶ እንዱከፈላቸው፤ የድንጋይ ካባ መሬት ካሳ ክፍያን በሚመለከት የመንገድች ባለስልጣን በተደጋጋሚ ጊዜ በፃፈው ደብዲቤ መሰረት ካሳ የተከፈላቸው በመሆኑ አሁን በድጋሚ ሉከፍላቸው አይገባም፤ እንዱሁም የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ወሰደ የተባለውን መሬት በሚመለከት ጽ/ቤቱ ይዞታውን ከመንግስት የወሰደ ስለመሆኑ በደብዲቤ ስለገለጸ ተጠሪ ሉጠየቅ አይገባም በማለት ወስኗል። አመልካች አሁንም በዚህ ባለመስማማት ለከተማ አስተዲደሩ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በበኩለ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የያዘውንና የካባ ድንጋይ መሬትን እንዱሁም ወጪና ኪሳራን በሚመለከት የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመሻር ለጋራጋንቲ ስራ ለካባ ድንጋይ የተወሰደዉን ተጠሪ የ10,097.54 ካ.ሜ. ካሳ በመመሪያ ቁጥር 19/2006 እና በ2009 ዓ.ም በወጣው የካሳ ክፍያ ስላት መሰረት ካሳው መከፈል ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር አመልካች እንዱከፍል፣ በአካባቢ ጥበቃ የተያዘዉን የአመልካች ይዞታ አስመልክቶ የይግባኝ ሰሚ ጉባኤዉ መርምሮ ዉሳኔ እንዱሰጥበት፤ ጉባኤው አመልካችን ባለመብት አድርጎ በሰጠው ውሳኔ ላይ ወለድ እና ወጪና ኪሳራን በሚመለከት አመልካች ዝርዝር እንዱያቀርቡ በማድረግ በማስረጃ ካጣራ በኋላ የመሰለውን ውሳኔ እንዱሰጥ መልሶ ልኮለታል። ተጠሪ በበኩለ በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት የሰበር አቤቱታውን ለከተማ አስተዲደሩ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የካባ ድንጋይ መሬቱን በሚመለከት ጉባኤው በማስረጃ አረጋግጦ የሰጠውን ውሳኔ ያለበቂ ምክንያት መሻሩ፤ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የያዘውን መሬት በሚመለከት የመሬት ልማት እና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ቦታው ለልማት ተነሺነት ያጠናውና እውቅና ያልሰጠው መሆኑ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በራሱ አጥሮ የሚያስጠብቀውና ከመንግስት የወሰደው ይዞታ መሆኑ በተረጋገጠበት ለአመልካች ካሳ ሉከፈለው ይገባል፤ ስላቱን በሚመለከት መመሪያውን ተመልከቶ ይወስን በማለት ጉዲዩን ለጉባኤው መመለሱ ተገቢነት የለውም በማለት የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ የጉባኤውን ውሳኔ አጽንቶታል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 11/02/2012 ዓ.ም በተፃፈ 07 ገጽ የሰበር አቤቱታ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሰበር ሰሚ ችልት እና በይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ተፈጽመዋል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙላቸው ጠይቀዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ ለመንገድ ስራ ገረጋንቲ ማውጫ የተወሰደው መሬቴ ጠቅላላ ስፊቱ 46,448.50 ካ.ሜ ሲሆን ተጠሪ በሪፕርቱ ላይ የተከፈለኝ ለ39,902.29 ካ.ሜ መሆኑን ቢገልጽም የ13,471.01 ካ.ሜ መሬት ካሳ አልተከፈለኝም፤ ተጠሪ ሙለ በሙለ ስለመክፈለም በማስረጃ ባላረጋገጠበት ለጠቅላላው መሬት እንደከፈለ ተቆጥሮ ጥያቄዬ ውድቅ መደረጉ፤ ይዞታው ላይ የንብረት ካሳ ተከፍልታል እንኳን ቢባል ጉባኤው የመፈናቀያ ካሳ እንዱከፈለኝ ሉወስንልኝ ሲገባ ያለፈውና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ እንዱከፈለኝ የወሰነልኝን ሰበር ሰሚ ችልቱ መሻሩ፤ በተጠሪ ምክንያት ለክርክሩ ለዲኝት የተከፈለውን ጨምሮ ከፍተኛ ወጪ አውጥቼ እያለ ወጪና ኪሳራ የየራሳችሁን ቻለ፤ አንዱሁም በተጠሪ ችግር ምክንያት ተገቢው ካሳ ሳይከፈለኝ በመቆየቱ ወለድ እንዱከፈለኝ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተወሰነልኝን ውሳኔ ሰበር ሰሚ ችልቱ መሻሩ መሰረታዊ ስህተት በመሆኑ ካሳው በመመሪያ ቁጥር 19/2006 አንቀጽ 10(16) እና በ2011 ዓ.ም ሲሰራበት በነበረው የካሳ ስላት ቀመር መሰረት ተሰልቶ መከፈል ከነበረበት ጥር 12 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ለአመልካች ሉከፈላቸው የሚገባው ካሳ ስላቱ መሰራት ያለበት በ2006 ዓ.ም በወጣው መመሪያ መሰረት ነው? ወይስ በ2009 ዓ.ም በወጣው መመሪያ መሰረት ነው?
የሚለው መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቧል። ተጠሪም መልስ እንዱሰጥበት ተደርጎ በቀን 25/01/2013 ዓ.ም ጽፍ በሰጠው መልስ አመልካች ካሳ ተከፍሎቸው ቦታውን ለልማት እንዱለቁ የተወሰነው በ1997 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱም የተሰራላቸውን የካሳ ገንዘብ ለመውሰድ ፍቃደኛ አልነበሩም፤ በዚህም የተነሳ ለተለያዩ አስተዲደር አካላት ቅሬታ አቅርበው የካሳው መጠን ተሻሽል ብር 5,273,572.02 ተከፍሎቸው በ2009 ዓ.ም ተቀብለዋል፤ ካሳው የተሰራውም በዚሁ በ2009 ዓ.ም በነበረው ዋጋ በመመሪያ ቁጥር 19/2006 ዓ.ም መሰረት ነው፤ አመልካች በ1997 ዓ.ም እንዱለቁ በተደረገው መሬት ላይ በ2009 ዓ.ም በነበረ ዋጋ ካሳው የተሰራላቸው አንሶ በ2011 ዓ.ም በነበረ ዋጋ ይሰራልኝ ማለታቸው ተገቢ አይደለም፤ በመሬቱም ላይ ለእርሻ ማሳ ቋሚ ማሻሻያ እና በመሬቱ ላይ ለነበሩ ባህርዛፍች ካሳ አልተከፈለኝም የሚል ክርክር ቢያቀርቡም በማስረጃ አላረጋገጡም፤ በ1999 ዓ.ም በተደረገው የመጨረሻ የቦታው ልኬትም የተስማሙ ሲሆን በጊዜው በመሬቱ ላይ ምንም አይነት ባህርዛፍ በስፍራው ላይ አልነበረም፤ ተጠሪም እነዚህ ንብረቶች የወሰደ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ለአመልካች ካሳ እንዱከፈላቸው መወሰኑ በራሱ ስህተት ነበረ፤ ለመንገድ ስራ ጋራጋንቲ ማምረቻ ተወሰደብኝ የሚለትን 46,448.50 ካ.ሜ በሚመለከት በአራት የተለያዩ ጊዜያት በጠቅላላው ብር 627,013.79 የተከፈላቸው ሲሆን ስለመከፈለም በማስረጃ አረጋግጠን ተገቢው ውሳኔ አርፍበታል፤
እንዱሁም የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ካሳ ሳይከፍለኝ 27,226.09 ካ.ሜ ቦታ ወስድብኛል ቢለም ቦታው ለልማት የሚፈለግ ስለመሆኑ ለተጠሪ ቀርቦ ያልተጠና በመሆኑና መሬቱ በአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ስር እያለ ተጠሪ ካሳ የሚከፍልበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመረዉም አመልካች ከጠየቃቸዉ የተለያዩ ክፍያዎች ዉስጥ ለልማት የተለቀቀዉ የእርሻ እና የግጦሽ ይዞታ 98,800 ካ/ሜትር መሆኑ ተረጋግጦ በወቅቱ ከእርሻ ማሳ ላይ የተሰበሰበዉ የዓመት ምርት በ10 ተባዝቶ ለአመልካች እንዱከፈል የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ወስኗል። በዚህ ላይ የቀረበ ክርክር የለም። ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ የክርክር ነጥብ ለጋራጋንቲ የካባ ድንጋይ፣ ለአካባቢ ጥበቃ እንዱሁም ወለድን አስመልክቶ የቀረበዉ ጥያቄ ዉድቅ መደረጉ ነዉ። ይህ ችልትም እነዚህን አስመልክቶ በየደረጃዉ የተሰጡትን ዉሳኔዎች አግባብነት እንደሚከተለዉ ተመልክቶታል።
ለጋራጋንቲ ስራ ለካባ ድንጋይ ተወሰደ የተባለዉን ይዞታ አስመልክቶ ይህ መሬት ከአመልካች የተወሰደ ስለመሆኑ ተጠሪ ክድ አይከራከርም። በዚህ ምክንያት ከአመልካች የተወሰደዉ የይዞታ ካ/ሜትር ስለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ተጠሪም ይህን ሳይክድ የሚከራከረዉ ካሳ ተከፍልታል በማለት ነዉ። አመልካች የሚከራከረዉ የተከፈለኝ የ 36,350 ካ/ሜትር ብቻ ነዉ በማለት ይከራከራል። ይግባኝ ሰሚ ጉባኤዉ በዚህ ረገድ የቀረበዉን የአመልካች ክርክር ዉድቅ ያደረገዉ አመልካች ከመንገድች ባለስልጣን በተፃፈላቸዉ የካሳ ክፍያ ደብዲቤ መሰረት ካሳ ስለመዉሰዲቸዉ ከማህደራቸዉ መረጋገጡን በመጥቀስ ነዉ። በልላ በኩል ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተጠሪ በዚህ ለጋራጋንቲ እና ለካባ ድንጋይ ሲባል ለተወሰደዉ መሬት ካሳ ከፍያለሁ በማለት የሚከራከር ቢሆንም በዚህ ምክንያት ለተረከበዉ መሬት ስፊት ልክ በመመሪያዉ እና በካሳ አከፊፈል ስላት መሰረት ካሳ ስለመክፈለ ተጠሪ አላስረዲም በሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ የቀሪዉን የ10097 ካ.ሜትር መሬት ካሳ ተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት የወሰነ ሲሆን፣ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ይህን የይግባኝ ሰሚዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሲለዉጥ የጠቀሰዉ ምክንያት አመልካች ካሳ የወሰደ ስለመሆኑ በይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ተረጋግጧል በማለት ነዉ።
በመሰረቱ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉን ዉሳኔዎች በማረም ላይ የተገደበ ስለመሆኑ በተሻሻለዉ የአዱስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 42(2) ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። ከጭብጥ አያያዝ እንዱሁም ከመሰረታዊ የማስረጃ አቀራረብ እና የምዘና መርህ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ ስህተት ካልሆነ በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት ከፍሬ ነገር ጋር የተያያዙ ጉዲዮችን በተለይም ማስረጃን መዝነዉ ፍሬ ነገርን የማጣራት ስልጣን ባላቸዉ ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር በድጋሚ መመርመርን እና መመዘንን እንደማያካትት የሚታወቅ ሲሆን፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም በበርካታ መዛግብት ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት ነዉ።
በመሆኑም ማስረጃን መዝኖ ፍሬ ነገርን የማጣራት ስልጣን የተሰጠዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት በካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተሰጠዉን ዉሳኔ ይዘት መርምሮ ተጠሪ ከአመልካች በተወሰደዉ መሬት ልክ በካሳ አወሳሰን እና አሰላል መመሪያ መሰረት ካሳ ስለመክፈለ አልተረጋገጠም በሚል የደረሰበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ በድጋሚ በመመርመር የሰጠዉ ዉሳኔ ስልጣኑን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በአካባቢ ጥበቃ ተወሰደ የተባለዉን ይዞታ አስመልክቶ በአመልካች ለተጠየቀዉ ዲኝነት ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረዉ መሬቱ ለልማት ተነሺ በሚል ስም በመመሪያዉ መሰረት ያልተጠና እና ዔዉቅና ያልተሰጠዉ ከመሆኑም በላይ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት አጥሮ የሚያስጠብቀዉ ይዞታ ከመሆኑ ዉጪ ለልማት ያልተፈለገ በመሆኑ ተጠሪ ሃላፉነት የለበትም በማለት ነዉ። ይህን አስመልክቶ በአመልካች የቀረበዉን ዲኝነት ይግባኝ ሰሚ ጉባኤዉ ዉድቅ ያደረገዉ በልማት ምክንያት ተነሺ መሆን ያለመሆኑን አስመልክቶ የቀረበ ማስረጃ ካለመኖሩም በላይ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ይዞታዉን የወሰደዉ ከመንግስት ስለመሆኑ ተረጋግጧል በማለት ነዉ። ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይህን በጭብጥነት ይዞ የመረመረ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት የንፊስ ስልክ ላ/ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት፣ የክ/ከተማዉ መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት፣ የክ/ከተማዉ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት፣ የከተማ አስተዲደሩ መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ በተለያዩ ጊዜያት የተፃፃፈአቸዉን ደብዲቤዎች በዋቢነት በመጥቀስ እነዚህኑ ከጉባኤዉ ዉሳኔ እና ከግራ ቀኝ ክርክር አንፃር በማገናዘብ መጠኑ 27,226.09 ካ/ሜትር የሆነዉ የአመልካች ይዞታ በአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የተወሰደበት መሆኑን፣ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር መሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ አመልካች መሬቱ የተወሰደባቸዉ ካሳ ያልተከፈላቸዉ ከሆነ ተጣርቶ ካሳ እንዱከፈላቸዉ ለን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት እና ለክ/ከተማዉ የአካባቢ ጽ/ቤት በጽሐፍ ያሳወቀዉ መሆኑን ጠቅሶ ተጠሪ ካሳዉን የመክፈል ኃላፉነት አለበት በሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል። በአንፃሩ የከተማዉ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ይህን የይግባኝ ሰሚዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ የሻረዉ ይዞታዉ በመመሪያ መሰረት በልማት ተነሽነት ተይዞ ዔዉቅና ያልተሰጠዉ ከመሆኑም በላይ የአካባቢ ጥበቃ ከመንግስት ተሰጥቶት አጥሮ የያዘ መሆኑ መረጋገጡን በመጥቀስ ነዉ።
ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ይዞታ የአመልካች እንደነበረ፣ ካሳ ሳይከፈልበት በክ/ከተማዉ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ታጥሮ እንደተያዘ እንዱሁም ተጣርቶ ካሳ ሉከፈለዉ እንደሚገባም በሚመለከተዉ አካል እንደታመነበት ማስረጃን መዝኖ ፍሬ ነገርን የማጣራት ስልጣን በተሰጠዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ መሆኑን ሲሆን ጉባኤዉም ሆነ የከተማ አስተዲደሩ ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበዉን የዲኝነት ጥያቄ ላለመቀበል የጠቀሱት መሰረታዊ ምክንያት ቦታዉ በልማት ተነሺነት ተጠንቶ ዔዉቅና ያልተሰጠዉ መሆኑን ነዉ።
በመሰረቱ እንደላልች መሰረታዊ መብቶች ሁለ ለንብረት መብት ከፍተኛ ግምት የሰጠዉ የኢፋዱሪ ህገ መንግሰት በአንቀጽ 40 ላይ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ እንደሚከበርለት፣ በህግ መሰረት ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም፣ የላልች ሰዎችን መብት ሳይቃረን ንብረትን የማስተላለፍ መብቶችን ያጎናጸፈዉ ሲሆን የንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ ብቻ ለንብረቱ ባለቤት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል ንብረትን መዉሰድ እንደሚችል ይደነግጋል። የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ባለቤትነት መብት የመንግሰትና የህዝብ ብቻ ነዉ የሚለዉ ይህ ህገ መንግስት ማንም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ፣ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባዉ ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገዉ ቋሚ መሻሻል ሙለ መብት እንዲለዉ ይደነግጋል (አንቀጽ 40/3 እና 7 ይመለከቷል)። የሥነ ህግ ሳይንስ (jurisprudence) መብትና ግዳታዎች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች (two sides of one coin) መሆናቸዉን ይነግረናል፤
ይህም ማለት ግዳታ በላለበት መብት ገቢራዊ ላሆን ስለማይችል መብት ባለበት ሁለ ግዳታ ሉኖር ግድ ይላል። በመሆኑም መንግስት ከላይ ለተመለከቱት የንብረት መብቶች በህገ መንግስቱ ዔዉቅና ሲሰጥ መብቶችን ለማክበር እና ለማስከበር ጭምር ግዳታ በመግባት ስለመሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል።
ስለሆነም ከንብረት መብት ጋር በተያያዘ መንግስት ሁለት መሰረታዊ ግዳታዎች ያለት ሲሆን አንድም ዜጎች በንብረት መብቶች ተጠቃሚ እንዱሆኑ በህግ እና በተቋማት ጥበቃ ማድረግ ሲሆን ሁለትም የንብረት ባለቤትነት መብትን ሉጋፈ የሚችለትን ተግባራት ከመፈጸም የመታቀብ ግዳታ ነዉ።
ስለሆነም መንግስት የሰዎችን የንብረት ባለቤትነት መብት ሉገድብ ከሚችል ወይም በመብታቸዉ እንዲይጠቀሙ ሉያደርግ ከሚችል አግባብ ካልሆነ ተግባር የመታቀብ ኃላፉነት ያለበት ሲሆን፣ ንብረቱን ወይም ንብረቱ የሚገኝበትን ቦታ ለጠቅላላዉ ህዝብ ጥቅም (general public interest) የሚፈልግ ከሆነም ንብረቱን ወይም ንብረቱ የሚገኝበትን ቦታ በእጁ ከማስገባቱ በፉት አስቀድሞ ለባለንብረቱ ካሳ የመክፈል ግዳታ አለበት የሚለዉ መርህ ከንብረት መብት መርሆዎች አንደ በመሆን በዓለማችን ዔዉቅና ያገኘ ስለመሆኑም የሚታወቅ ነዉ። መንግስት ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል ንብረትን ለመዉሰድ እንደሚችል በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(8) ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌም ይህንኑ መነሻ ያደረገ ሲሆን፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የግል ንብረትን መዉሰድ የሚቻልበትን አግባብ የሚደነግግ አዋጅ ቁጥር 455/97 ወጥቶ በስራ ላይ ይገኛል።
ይህ አዋጅ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና የንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 455/97 በመባል የሚታወቅ ነዉ። ይህ አዋጅ የሚመለከተዉ የአስተዲደር አካል ለህዝብ ጥቅም ሲባል በመንግስት አካላት፣ በግል ባለሀብቶች፣ በህብረት ስራ ማህበራት ወይም በላልች አካላት የተሻለ ልማት ሉካሄድበት ይገባል ብል ያመነበትን የገጠር ወይም የከተማ መሬት በቅድሚያ ካሳ እንዱከፈል በማድረግ የማስለቀቅ ስልጣን እንዲለዉ የሚያስገነዝብ ሲሆን (አንቀጽ 3/1/ ይመለከቷል) የማስለቀቂያ ሥርዓቱ እንዱሁም የካሳዉ መጠን እና ዓይነት ምን እንደሆነም በዝርዝር ይደነግጋል። ከዚህም የምንረዲዉ መንግስት የአንድ ሰዉ ንብረት ያረፈበትን ቦታ ለልማት ሲፈልግ ግለሰቡን ከመሬቱ ከማስለቀቁ በፉት አስቀድሞ ካሳ (እንደ ሁኔታዉ ምትክ ቦታ ወይም የማፈናቀያ ካሳ ላሆን ይችላል / የአዋጁ አንቀጽ 7 እና 8 ይመለከቷል) መክፈል ያለበት መሆኑን ነዉ። ይህም ለልማት ዓላማ መሬቱ ወይም በመሬቱ ላይ የሚገኘዉ ንብረቱ በመንግስት የተወሰደበት ሰዉ መንግስት እንደአግባብነቱ ምትክ ቦታ እንዱሰጠዉ ወይም ከመሬቱ ላይ ለተነሳዉ ንብረት የማፈናቀያ ካሳ እንዱከፍለዉ የመጠየቅ መብት ያለዉ ሲሆን መንግስትም ይህን የማድረግ ግዳታ ያለበት መሆኑን ነዉ። ይህ ካልሆነ በህገ መንግስቱ ለመሬትም ሆነ በመሬት ላይ ለሚፈራ ሀብት የተደረገ ጥበቃ ዋጋ ያጣል። ስለሆነም መንግስት ቦታዉን ለልማት በመፈለጉ ምክንያት ንብረቱ የተወሰደበት ወይም ከቦታዉ እንዱነሳ የተደረገ ሰዉ የሚያቀርበዉ የካሳ ይገባኛል ጥያቄ ይህን ሁለ ከግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ ምላሽ ሉያገኝ ይገባል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ፣ ከላይ እንደተገለጸዉ፣ አመልካች ባህር ዛፍ ነበረበት የሚለዉ ይዞታዉ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት እጅ ታጥሮ የሚገኝ ሲሆን ጽ/ቤቱ አጥሮ ሉይዝ የቻለዉም ከመንግስት ስለተላለፈለት መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች የጠየቀዉም ለዚሁ የማፈናቀያ ካሳ እንዱከፈለዉ ነዉ። ምንም እንኳ በህገ መንግስቱ መሰረት መሬት የህዝብና የመንግስት በመሆኑ መንግስት ለመሬቱ ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ባይኖርበትም አመልካች በመሬቱ ላይ ባለማዉ ባህርዛፍ ላይ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40(7) መሰረት የባለቤትነት መብት ያለዉ በመሆኑ እና መሬቱንም በቋሚነት የለቀቀ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 8(1) መሰረት የማፈናቀያ ካሳ ሉከፈለዉ የሚገባዉ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች ባህርዛፍ ነበረበት የሚለዉን ይዞታ እንዱለቅ ተደርጎ ባህርዛፈም የመንግስት አካል በሆነዉ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ተይዞ የሚገኝ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ቦታዉ በተነሽነት አለመመዝገቡ እና ዔዉቅና ያልተሰጠዉ መሆኑ መንግስት ለልማት ዓላማ ከግለሰቦች መሬት ሲወስድ አስቀድሞ ካሳ እንዱከፍል የሚጠበቅበትን ግዳታ እንዲይወጣ ምክንያት ላሆን አይችልም። ይህ እንዱሆን መፍቀድ ለዜጎች በህገ መንግስቱ ጥበቃ የተደረገለትን የንብረት ባለቤትነት መብት ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባ ይሆናል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አስፈፃሚ እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 36 መሰረት ለአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት ዉስጥ አንደ የተለያዩ ዔፅዋት የሚተከለበትን ቦታ እና የሚሰጡትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና፣ አካባቢያዊ ጠቀሜታ በማጥናት እንዱሆኑ ማድረግ፣ በከተማዉ መሪ ፔላን ለመናፈሻ፣ ለደን፣ ለወንዝ ዲርቻና ለላላ አረንጓዳ ልማት በተከለለ ቦታዎች ላይ የሚተከለትን ዔፅዋት የማማከር ተግባር ሲሆን፤ ለከተማዉም ሆነ ለክ/ከተማዉ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ (ጽ/ቤት) ከተሰጡት ስልጣን እና ተግባራት ዉስጥ አንደ ቦታን ማስለቀቅና አግባብ ባለዉ አካል በሚወሰነዉ መሰረት ምትክ ቦታ መስጠት፣ ካሳ እና ላልች ክፍያዎችን መፈጸም ስለመሆኑም ከአዋጁ አንቀጽ 21 (6 እና 9) እና አንቀጽ 38(23) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ከዚህም የአካባቢ ጥበቃ ለሚፈልጋቸዉ ቦታዎች እንዲስፈላጊነቱ ምትክ ቦታ በመስጠት ወይም ካሳ በመክፈል ባለይዞታዉን አስለቅቆ የሚያስረክበዉ ተጠሪ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም የክ/ከተማዉ በእጁ አድርጎ ለአረንጓዳ ልማት እየተጠቀመበት ለሚገኝ እና በአግባቡ ካሳ ያልተከፈለበት የአመልካች ይዞታ ካሳ የመክፈል ኃላፉነቱ የተጠሪ በመሆኑ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አመልካች በአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት እጅ ይገኛል ለተባለዉ ይዞታ ተጠሪ ኃላፉነት እንዲለበት ከድምዲሜ ላይ በመድረስ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤዉ በመመሪያዉ መሰረት አጣርቶ የካሳ ክፍያዉን አስልቶ እንዱወስን መመለሱ በአግባቡ ሆኖ እያለ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ ያላግባብ በመሻር የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል። በልላ በኩል ካሳዉ በመመሪያ ቁጥር 19/2006 መሰረት መሰላት እንዲለበት ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ አመልካች ለከተማዉ አስተዲደር ሰበር ሰሚ ችልት በቀጥታ/በመስቀለኛ አቤቱታ ያላቀረበ ሲሆን ይህን ሳያደርግ ካሳዉ በመመሪያ ቁጥር 19/2009 መሰረት ሉሰላ ይገባል በማለት ለዚህ ችልት የሚያቀርበዉ ቅሬታ ሥነ ሥርዓታዊ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበዉን አቤቱታ ይህ ችልት አልተቀበለዉም። በዚህ ሁለ ምክንያት ተከታዩ ተወስኗል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 09/12/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ተሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 09/07/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.