ውል ያልፈጸመ ወገን ያልተፈጸመው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ውል ያልፈጸመው ወገን የደረሰውን የጉዲት ኪሣራ የሚከፈለው ተዋዋዮች በፍ/ሕ/ቁ. 1889 መሰረት አስቀድመው የወሰኑት ከሆነ በውለ የተመለከተውን መጠን ሲሆን ተዋዋዮች አስቀድመው ኪሣራውን ካልወሰኑ በክርክር ሂደት ፍርድ ቤት ኪሣራውን በማስረጃ አጣርቶ የሚወሰን ሲሆን ከውል ውጭ ኃላፉነት መሰረት ያደረገ ከሆነ የሚከፈለው ካሣ ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመዛዛኝ ወይም ተመጣጣኝ መሆን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1790 እና 1791 እንዱሁም 2090(1)
No summary available.
ቀን፡- ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ታደሰ ጉታ፡- ጠበቃ አበበ ጉታ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ። አመልካች ያቀረቡት ክስ ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር የመንገድ ሥራ ፔሮጀክት ለመስራት ውል ገብቼ በርካታ ማሽነሪዎችና ዔቃዎችን ወደግንባታ ቦታው ወስጃለሁ። ለግንባታው ለሚጠይቀው ከፍተኛ ገንዘብ ሲባል በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 03 የቤት ቁጥሩ 1036(ሐ) የሆነ ቤትን በማስያዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መጋዘን፣ ወርክሾፔና የላልች ሰዎችን ንብረት በማስያዝ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ገንዘብ በመበደር የግንባታ ፔሮጀክቶችን በመፈጸም ከፍተኛ የሆነ ብደርና ዔዲ ውስጥ ገብቻለሁ። 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ያለምንም ጥፊት የግንባታ ሥራ ውለን በመቋረጥ ለመረጧቸው ላልች የኮንስትራክሽን ድርጅቶች በንዐስ ግንባታ የሥራ ውል አስተላልፈዋል። ማሽነሪዎች፣ መኪናዎች እና ዔቃዎች ከሶማላ ክልል እንዲይወጡ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በሰጡት ሕገ-ወጥ የዔግድ ትዕዛዝ ከማገዲቸውም በተጨማሪ ንብረቶችን እያከራዩ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጠቀሙባቸው ነበር። 1ኛ ተጠሪ መፍትሓ እንዱሰጠኝ ብጠይቅም ምላሽ ሉሰጠኝ አልቻለም። ስለሆነም፡-
ከ1991 ዓ/ም እስከ 2006 ዓ/ም ማሽነሪዎችና መኪናዎች ባከራይ ላገኘው የምችለው ገቢ ስለተቋረጠ የኪራይ ገንዘብ ብር 127,938,480.00 እና ወለድ ብር 15,890,976.14 በድምሩ ብር 143,829,456.14 እንዱከፍለ፣
ማሽነሪዎችና መኪናዎች ከሕግ ውጭ በመያዛቸው ከባንክ የተበደርኩትን ገንዘብ መክፈል ባለመቻላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 03 የቤት ቁጥሩ 1036(ሐ) የሆነ ቤትን የሸጠው በመሆኑ የንብረቱ የአሁን የገበያ ዋጋ ብር 32,000,000.00 እንዱከፍለ፣
ማሽነሪዎችና መኪናዎች ከሕግ ውጭ በመያዛቸው ከባንክ የተበደርኩትን ገንዘብ መክፈል ባለመቻላ የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዱስ አበባ ከተማ የሚገኝ መጋዘን፣ ወርክሾፔና ቢሮ የሸጠ በመሆኑ የንብረቱ የአሁን የገበያ ዋጋ ብር 14,650,000.00 እንዱከፍለ፤
በሪቴንሽን የተያዘ ገንዘብ ብር 176,566.40 በድምሩ ብር 192,457,377.62 እንዱከፍለ እንዱወሰን የሚል ነው።
ተጠሪዎች ባቀረቡት መልስ አመልካች ውል ያደረጉት ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ሉከሰስ አይገባም። ጉዲዩ በፍርድ ያለቀ ነው። ክሱ በይርጋ የታገደ ነው። ውለ የተቋረጠው በአመልካች ጥፊት ነው። የተበደሩት ለፔሮጀክቱ አይደለም። ማሽነሪዎችና ዔቃዎች ከሕግ ውጭ አልተያዙም፣ የተያዙት አመልካች እንደ ውለ ያልፈጸመው መኖሩን እስኪረጋገጥና በፍርድ ቤት እግድ ነው። የተጠየቀው የጉዲት ካሳ የተጋነነ ነው፤ ለክሱ ኃላፉነት የለብንም ብለዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን በብይን ውደቅ በማድረግ 1ኛ ተጠሪ የተከሰሰው የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የበላይ አካልና ተቆጣጣሪ ከመሆኑም በላይ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የፈጸሙት ተግባር መፍትሓ እንዱሰጥ ሲጠየቅ ምላሽ ያልሰጠ በመሆኑ በሕግ ያለበትን ኃላፉነት አልተወጣም በመባለ ስለሆነ ክሱ በእርሱ ላይ መቅረቡ ተገቢ ነው። የአመልካች ንብረት የሆኑትን ማሽነሪዎች ተጠሪዎች በመያዝ አመልካች ጥቅም ያጡ በመሆኑ ቢያከራዩ ሉገኝ የሚችለው ገቢ ብር 96,447,600.00 እንዱሁም ሪቴንሽን ገንዘብ ብር 176,566.40 ተጠሪዎች ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል። ካሣ ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ ሆኖ የሚከፈል በመሆኑና አመልካች ማሽነሪዎች በተጠሪዎች ተይዘው ለቆዩበት ጊዜ የተቋረጠ ገቢ እንዱከፈላቸው ስለተወሰነ በባንክ የተሸጡ ንብረቶች ዋጋ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት ክስ ከደረሰባቸው ጉዲት በላይ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ባለመቀበል ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ማሽነሪዎች በተጠሪዎች መያዛቸው አከራይቼ አገኝ ከነበረው ገቢ በተጨማሪ ተደራራቢ በገንዘብ ሉተመን የሚችል እና ሉተመኑና ዋጋ ሉወጣላቸው የማይችል ተደራራቢ ጉዲቶች ደርሰዋል። ማሽነሪዎች በመያዛቸው ሰርቼ ብደሩን መክፍል እንዲልችል አድርገው ንብረቴ የተሸጠ በመሆኑ በባንክ የተሸጡትን ንብረቶች የገበያ ዋጋ ብር 46,650,000.00 ተጠሪዎች እንዱከፍለ ሉወሰን ይገባል የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ አመልካች በባንክ ዔዲ ንብረቴ ተሽጦ ጉዲት ደርሶብኛል በማለት የጠየቁት ዲኝነት ውድቅ መደረጉ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከፍ/ሕ/ቁ. 2091 አንጻር ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ አዟል። ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ ይዘትም ለክሱ ኃላፉነት የለብንም፣ በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተወሰነው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ አቅርበን በሂደት ላይ ይገኛል። አመልካች ከደረሰበት ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ ካሣ እንዱከፈለው ስለተወሰነ በሐራጅ ለዔዲው በባንክ የተሸጡ ንብረቶችን ዋጋ ልንከፍል አይገባም።
የሰበር አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘው ጭብጥ፣ በሥር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ያቀረቡት ክስ ከ1991 ዓ/ም እስከ 2006 ዓ/ም ማሽነሪዎችና መኪናዎች ባከራይ ላገኘው የምችለው ገቢ ስለተቋረጠ የኪራይ ገንዘብ ብር 127,938,480.00 እና ወለድ ብር 15,890,976.14 በድምሩ ብር 143,829,456.14፣ ማሽነሪዎችና መኪናዎች ከሕግ ውጭ በመያዛቸው ከባንክ የተበደርኩትን ገንዘብ መክፈል ባለመቻላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 03 የቤት ቁጥሩ 1036(ሐ) የሆነ ቤትን የሸጠው በመሆኑ የንብረቱ የአሁን የገበያ ዋጋ ብር 32,000,000.00፣ ማሽነሪዎችና መኪናዎች ከሕግ ውጭ በመያዛቸው ከባንክ የተበደርኩትን ገንዘብ መክፈል ባለመቻላ የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዱስ አበባ ከተማ የሚገኝ መጋዘን፣ ወርክሾፔና ቢሮ የሸጠ በመሆኑ የንብረቱ የአሁን የገበያ ዋጋ ብር 14,650,000.00፤ በሪቴንሽን የተያዘ ገንዘብ ብር 176,566.40 በድምሩ ብር 192,457,377.62 ተጠሪዎች እንዱከፍለ እንዱወሰን የሚል ነው።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ለክሱ ኃላፉነት የለብንም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር የውል ግንኙነት የነበራቸው ስለመሆኑ በክስ ማመልከቻ የጠቀሱ በመሆኑ የቀረበው ዲኝነት በውል ግንኙነት መሰረት የተያዘ ገንዘብ ክፍያ እንዱፈጸም እና የውል ጉዲት ኪሣራን የሚመለከት ነው። በልላ በኩል ከ1ኛ ተጠሪ ጋር አመልካች የውል ግንኙነት የላላቸው ሲሆን ክሱ በ1ኛ ተጠሪም ላይ የቀረበው አመልካች ውል የወሰደበትን ሥራ 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመሆን ለ3ኛ ወገን በማስተላለፍ ሂደት ላይ በመሳተፍና ለደረሰብኝ ጉዲት መፍትሓ እንዱሰጠኝ ስጠይቀው ካለበት ኃላፉነት አንጻር ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠት ጉዲት እንዱደርስበኝ አድርጓል በሚል ከውል ውጭ ኃላፉነት መሰረት ያደረገ ክስ ያቀረቡ በመሆኑ ክሱ ሁለት የክስ ምክንያቶች ተጣምሮ የቀረበበት መሆኑን ተገንዝበናል።
የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ተመልክቶ የአመልካች ንብረት የሆኑትን ማሽነሪዎች ተጠሪዎች በመያዝ አመልካች ጥቅም ያጡ በመሆኑ ቢያከራዩ ሉገኝ የሚችለው ገቢ ብር 96,447,600.00 እንዱሁም ሪቴንሽን ገንዘብ ብር 176,566.40 ተጠሪዎች ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል፤ ካሣ ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ ሆኖ የሚከፈል በመሆኑና አመልካች ማሽነሪዎች በተጠሪዎች ተይዘው ለቆዩበት ጊዜ የተቋረጠ ገቢ እንዱከፈላቸው ስለተወሰነ በባንክ የተሸጡ ንብረቶች ዋጋ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት ክስ ከደረሰባቸው ጉዲት በላይ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። ተጠሪዎች ለክሱ ኃላፉነት አለባቸው ወይስ የለባቸውም የሚለው ጉዲይ ተጠሪዎች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ያቀረቡት ይግባኝ መዝገብ ላይ ውሳኔ ላሰጥበት የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አመልካች ለዚህ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከማሽነሪዎች ሉገኝ ከሚችለው የተቋረጠ ገቢ በተጨማሪ በባንክ ዔዲ ለተሸጡ ንብረቶች የገበያ ዋጋም ተጠሪዎች ሉከፍለ ይገባል የሚል ነው። ውል ያልፈጸመ ወገን በፍ/ሕ/ቁ. 1790 እና 1791 እንደተመለከተው ያልተፈጸመው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ውል ያልፈጸመው ወገን የደረሰውን የጉዲት ኪሣራ መክፈል አለበት።
የሚከፈለው ኪሣራ ተዋዋዮች በፍ/ሕ/ቁ. 1889 መሰረት አስቀድመው የወሰኑት ከሆነ በውለ የተመለከተውን መጠን ሲሆን ተዋዋዮች አስቀድመው ኪሣራውን ካልወሰኑ በክርክር ሂደት ፍርድ ቤት ኪሣራውን በማስረጃ አጣርቶ የሚወሰንው ይሆናል። ከውል ውጭ ኃላፉነት መሰረት ያደረገ ሲሆን ካሣ በፍ/ሕ/ቁ. 2090(1) እንደተመለከተው ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመዛዛኝ ወይም ተመጣጣኝ መሆን እንዲለበት መርህ ተቀምጧል። ሕጎቹ የተለያዩ ቢሆኑም ልዩነቱ ካሣው የሚከፈልበት ግንኙነት መሰረት እንጂ ዓላማቸው ተመሳሳይ ነው፤ እርሱም ጉዲት የደረሰበትን ሰው መካስ ነው። ሕግ አውጪው ሕግ ሲያወጣ ጉዲት የደረሰበት ሰው ከጉዲቱ እንዱያተርፍ ታሳቢ አድርጓል ልባል አይችልም።
አመልካች ንብረቶቻቸው ከውል እና ከሕግ ውጭ በተጠሪዎች ተይዘዋል በሚል በንብረቶች ሉያገኙት ይችለት የነበረው ገቢ ታስቦ በሥር ፍርድ ቤት ተወስኗል። አመልካች በብድር ለወሰደት ገንዘብ ባለመክፈላቸው ንብረታቸው ተሽጦ ዔዲው መከፈለን በመጥቀስ ማሽነሪዎች በተጠሪዎች ባይያዙ ኖሮ ዔዲውን ሰርቼ በመክፈል ንብረቶችን ማስቀረት እችል ስለነበር ለጉዲቱ ተጠሪዎች ካሣ ሉከፍለ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ንብረታቸው በሐራጅ የተሸጠው ለወሰደት ዔዲ ክፍያ በመሆኑ እንደጉዲት የሚታይ ካለመሆኑም በላይ አመልካች ማሽነሪዎቹ በእጃቸው ቢቆዩ ከገቢው ቀንሰው ለዔዲው ክፍያ ሉያውለት የሚችለ በመሆኑና በሥር ፍርድ ቤት የ14 ዓመት ሙለ ገቢ የተወሰነላቸው በመሆኑ፤ ለተሸጠው ንብረት ዋጋ በተጨማሪነት ከታሰበላቸው ካሣ ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመዛዛኝና ተመጣጣኝ መሆን አለበት የሚለውን መርሕ የሚጥስ ትርፍ ክፍያ ስለሚሆን የሥር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 03 የቤት ቁጥሩ 1036(ሐ) የሆነ ቤትን የገበያ ዋጋው ብር 32,000,000.00 የሆነ እና በአዱስ አበባ ከተማ የሚገኝ መጋዘን፣ ወርክሾፔና ቢሮ የንብረቱ የአሁን የገበያ ዋጋ ብር 14,650,000.00 ተጠሪዎች ሉከፍለ አይገባም ሲል የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሐምል 30 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ/ም በባንክ ዔዲ ለተሸጡ ንብረቶች ዋጋ ተጠሪዎች የመክፈል ኃላፉነት የለባቸውም በሚል የሰጡት ውሳኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.