ዉል በፀና አኳኋን ተደርጓል ልባል በሚችል አኳኋን በተዋዋዮች ፈቃድ እና ችልታ፣ የዉለ ጉዲይ የሚቻል፣ ሕጋዊና ሞራላዊ ከመሆን አኳያ እና በሕግ ከተደነገገዉ ፍርም አንጻር ጉድለት ሳይኖርበት ጉድለት አለበት በሚል ክርክር ሳይቀርብበትና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ዉል የሚያስፈርስ ምክንያት በላለበት፤ የዉል ግዳታ መፈጸሚያ ጊዜ በመዘግየቱ ምክንያት የደረሰ እነ አቶ ደልቦ ደንድሬ (2 ሰዎች) እና አቶ ደጀኔ ጌታነህ ካለ ተገቢዉን ኪሳራ እንዱጠየቅ ከሚቻል በስተቀር በዉለ የተመለከተዉን ጊዜ አለማክበር ዐይነተኛ የሆነ የዉል መጣስ ወይም ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ ተጥሷል የማይባልና ዉል የሚያስፈርስና የሚያሰርዝ ምክንያት ባለመሆኑ ውለ ሉፈጸም የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1711፣1808 ተዋዋይ ወገኖች የኪሣራ ክፍያ የተዋዋለት ለውለ አፈጻጸም መዘግየት ስለመሆኑ በግልጽ ካልተመለከተ በስተቀር ሉፈጸም የሚችል ውል ላይ ኪሣራ ለመጠየቅ የሚቻል ስላለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1890(2)
No summary available.
ቀን፡- የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
ጉዲዩ የዉል ማፍረሻ ምክንያቶችን የሚመለከት ነዉ። ተጠሪ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ በመሰረቱት ክስ በቀን 08/01/2012 ዓ/ም ከአመልካቾች ጋር በብር 830,000.00 በአዱስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 01 የቤት ቁጥር B127/22 የቤት ሽያጭ ዉል ፈጽመናል። በዉለ መሰረት ቃብድ ብር 20,000.00 ለአመልካቾች ከፍያለሁ። አመልካቾች እስከ ቀን 05/02/2012 ዓ/ም ድረስ በዉለ መሰረት ቀሪ ገንዘብ ተቀብለው ቤቱን ሉያስረክቡኝ ስምምነት ብናደርግም በተባለዉ ጊዜ አላስረከቡኝም። በመሆኑም በዉለ ምክንያት የከፈልኩት ቃብድ እና ቅጣቱን ብር 70,000.00 አመልካቾች እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መልስ ሁለት የሽያጭ ውል አስፈርሞናል። ውለ ሥልጣን ባለው አካል ፉት አልተደረገም።
ባንክ ገንዘቡን ስላልፈቀደልኝ ቀብደን መልሱልኝ ያለን ተጠሪ እንጂ እኛ ውለን አልፈጽምም አላልንም በማለት ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃ ሰምቶ ተጠሪ ገንዘቡን ይዞ ሲመጣ እስከ 05/02/2012 ዓ/ም ድረስ አመልካቾች ቤቱን የሚመለከቱ ሰነድች ሳያቀርቡ ቀርተው ከ06/02/2012 ዓ/ም በኋላ በማቅረባቸው እንደውለ ያልፈጸሙት አመልካቾች ናቸው በማለት በማስረዲታቸው በውለ በተቀመጠው ጊዜ ተገቢውን ኃላፉነት ያልተወጡት አመልካቾች በመሆናቸው ገንዘቡን ከመቀጫ ጋር ብር 70,000.00 ሉመልሱ ይገባል ሲል ወስኗል። አመልካቾች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን አከራክሮ ውሳኔውን አጽንቷል።
ይሕ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ውለን የተወው ተጠሪ ነው፤ ውለን ከተወ ቃብድ የመጠየቅ መብት የለውም። ክሱ ሲቀርብ እንደውለ ለመፈጸም ዝግጁና ፈቃደኛ መሆናችን ገልጸን ተከራክረናል። ሰነድ በሟሟላት ግዳታችን ተወጥተናል።
ዉሳኔው ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ ባንክ ለተጠሪ የቤት ግዥ ዋጋ ለመክፈል መተማመኛ በሰጠበትና አመልካቾች ተፈላጊውን ሰነድ አቅርበው እያለ ቃብድና መቀጫ እንዱከፍለ መወሰኑ አግባብነቱን ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ ቤቱን አመልካች ለተጠሪ መሸጣቸው የሚካድ ነገር የለውም።
ውለን በውልና ማስረጃ ለማድረግ ተስማምተን በተፈጠረው የቃል አለመግባባት የተነሳ ውለ ቀሪ ሆኗል። በተጠሪ በኩል የተደረገ የውል ጥሰት የለም። ውለ የፈረሰው በአመልካቾች አለመተማመን ነው። አመልካቾች ተፈላጊውን ሰነድ በጊዜው አላሟለም። እንደውለ እንዱፈጸም ያልጠየቅሁት ለአመልካቾች ትዲር ብዬ ነው፤ ውለን አመልካቾች ስላፈረሱ የቃብድ ገንዘቡንና መቀጫውን መጠየቄ ተገቢ ነው። ውሳኔው ሉጸና ይገባል በማለት ብለዋል። አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ማስቀረቢያ ጭብጥ መሰረት በማድረግ በግራ ቀኙ መካከል የተፈጸመ የቤት ሽያጭ ዉል እንዱፈርስ መወሰኑ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም ተጠሪ በአመልካቾች ላይ በመሰረቱት ክስ በቀን 08/01/2012 ዓ/ም ከአመልካቾች ጋር በብር 830,000.00 በአዱስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 01 የቤት ቁጥር B127/22 የቤት ሽያጭ ዉል ፈጽመናል። በዉለ መሰረት ቃብድ ብር 20,000.00 ለአመልካቾች ከፍያለሁ። አመልካቾች እስከ ቀን 05/02/2012 ዓ/ም ድረስ በዉለ መሰረት ቀሪ ገንዘብ ተቀብለው ቤቱን ሉያስረክቡኝ ስምምነት ብናደርግም በተባለዉ ጊዜ አላስረከቡኝም። በመሆኑም በዉለ ምክንያት የከፈልኩት ቃብድ እና ቅጣቱን ብር 70,000.00 አመልካቾች እንዱከፍለኝ የሚል ነው። አመልካቾች በበኩላቸው ባንክ ገንዘቡን ስላልፈቀደልኝ ቃብደን መልሱልኝ ያለን ተጠሪ እንጂ እኛ ውለን አልፈጽምም አላልንም በማለት ተከራከረዋል።
እንደሚታወቀዉ ተዋዋዮች የመዋዋል ነጻነታቸዉን ተጠቅመዉ ግዙፊዊም ሆነ ግዙፊዊ ያልሆኑ መብትና ጥቅሞቻቸዉን በተመለከተ በዉል ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ወይም ለማስተላለፍ በዉል በሚስማሙት አኳኋን መብትና ግዳታዎችን ለማቋቋም ይችላለ። በዚህ አግባብ ተዋዋዮች ሕግ የወሰናቸዉንና የከለከላቸዉን ነገሮች በማክበርና በመጠበቅ የመዋዋል ነጻነታቸዉን ተጠቅመዉ ዉል በማቋቋም የሚዋዋለበትን ጉዲይ እንደመሰላቸዉ ሉወስኑ እንደሚችለ ከፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1711 አጠቃላይ መርህ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ዉል በፀና አኳኋን ተደርጓል ልባል በሚችል አኳኋን በተዋዋዮች ፈቃድ እና ችልታ ላይ ፣የዉለ ጉዲይ የሚቻል፣ሕጋዊና ሞራላዊ ከመሆን አኳያ እና በሕግ ከተደነገገዉ ፍርም አንጻር ጉድለት ሳይኖርበት የተደረገ እንደሆነ ዉለን የሚያፈርስ ምክንያት ስለማይኖር ሉፈጸም ይገባል(የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1808 ይመለከቷል)። በተያዘዉ ጉዲይ ተጠሪ በቀጥታ ውለ እንዱፈርስ የሚል ዲኝነት ባያቀርቡ በውለ መሰረት ያልተፈጸመልኝ ስለሆነ ቃብድና መቀጫ አመልካቾች ይክፈለኝ የሚለው ዲኝነት ውለ እንዱፈርስና የውል መፍረስ ውጤት የሆነውን የከፈለትን ገንዘብ ለማስመለስ የቀረበ ክስ መሆኑን ያስገነዝባል። ተጠሪ ዉለ እንዱፈርስ የጠየቁት እነዚህ የዉለ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች (Essential Elements of Contract) ጉድለት አለበት የሚል ክርክር ያላቀረቡ በመሆኑ ከዚህ አኳያ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ዉል የሚያስፈርስ ምክንያት የለም።
ተጠሪ ዲኝነት ሲጠይቁ በግልጽ ውለ እንዱፈርስ በክስ ማመልከቻቸው ላይ ያላመላከቱ ቢሆንም የከፈለት ገንዘብ እንዱመልስ የሚለው ዲኝነት ውጤት የሚያገኘው ውለ ሲፈርስና ወደነበሩበት ሲመለሱ በመሆኑ አመልካቾች በዉለ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ የቤቱን ስመ ሀብት ለማዛወር አስፈላጊ የሆኑ ሰነድችንና ቤቱን ለተጠሪ ለማስረከብ የገቡትን ግዳታ አለመወጣታቸዉ የቤት ሽያጭ ዉለን ሉያስፈርስ የሚችል ምክንያት መሆን አለመሆኑ መመርመር አስፈላጊ ነው። በፍትሐ ብሓር ሕግ በቁጥር 1731/1 ስር እንደተደነገገዉ በሕግ አግባብ የተደረጉ ዉልች በቋቋሟቸዉ ሰዎች ላይ ሕግ ነዉ።በዚሁ የፍትሐ ብሓር ሕግ የዉል አለመፈጸም(non-performance of contract) ስለሚያስከትለዉ ዉጤት በሚደነግገዉ ክፍል በቁጥር 1771 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስር እንደተመለከተዉ ከተዋዋዮቹ አንደ የዉለን ግዳታ ያልፈጸመ እንደሆነ የዉል ግዳታዉን ለተወጣዉ ላላዉ ወገን እንደ ነገሩ ሁኔታ እንዱጠቀምበት ሕጉ ሦስት መፍትሓዎችን (Remedies) ይሰጠዋል። እነዚህም (1) ላላኛዉ ወገን ተገድ እንደ ዉለ እንዱፈጸምለት (forced enforcement/performance) እንዱጠይቅ፣ (2) በሕግ ወይም በዉል በአንድ ወገን ብቻ ዉል የሚያሰርዙ ምክንያቶች ተደርገዉ የሚቆጠሩ ምክንያቶችን መሰረት አድርጎ(unilateral cancellation of contract based on conditions under the contract and laws) ዉለ መሰረዙን እንዱገልጽ ወይም ዉለ በፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱሰረዝ (Cancellation of contract by the Court) መጠየቅ እና (3) የጉዲት ካሳ (Damages) መጠየቅ የሚለ ናቸዉ። በዚሁ ክፍል በቁጥር 1785/2 ስር እንደተደነገገዉ በዉለ ላይ ዐይነተኛ የሆነ ዉል መጣስ ተግባር (Fundamental Breach of Contract) ካልተፈጸመ በቀር ዳኞች ዉለ እንዱሰረዝ መወሰን እንደማይችለ በግልጽ ተመልክቷል።
የእነዚህ ድንጋጌዎች ዓላማ ተዋዋይ ወገኖች መሰረታዊ ያልሆኑ ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ዉል መሰረዝ እንዲይችለ ማድረግና ዳኞችም ዉለ እንዱሰረዝ ከመወሰናቸዉ በፉት ዉለ ባይሰረዝ ከፍ ያለ ችግር የሚያስከትል መሆኑን እንዱያመዛዝኑ ኃላፉነት በመጣል በሕግ አግባብ ለተደረጉ ዉልች ጥበቃ ማድረግና በተቻለ መጠን እንደዉለ እንዱፈጸም ማድረግ ነዉ።
በያዝነዉ ጉዲይ ተጠሪ የቤት ሽያጭ ዉለ እንዱፈርስ እየጠየቁ ያለት አመልካቾች በዉለ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ ግዳታቸዉን አልተወጡም በሚል ምክንያት በመሆኑ የዉል ግዳታ ከመወጣት ጋር በተያያዘ መጠየቅ የሚቻለዉ ዲኝነት ላላዉ ተዋዋይ ወገን ተገድ ዉለን እንዱፈጽም ወይም ዉለ እንዱሰረዝ ወይም/እና ላላዉ ወገን ግዳታዉን ባለመወጣቱ ምክንያት ለደረሰበት ጉዲት ካሳ መጠየቅ እንጂ ዉለ እንዱፈርሰ መጠየቅ አይደለም።አመልካቾች በዉለ ላይ የቤቱን ስመ ሀብት ለማዞር አስፈላጊ የሆኑትን ሰነድችና ቤቱን ለተጠሪ በውለ በተወሰነው ጊዜ አለመስጠታቸዉ የቤት ሽያጭ ዉለን ሉያሰርዝ የሚችለዉ ዐይነተኛ የሆነ የዉል መጣስ ተግባር የሚያስከትል ነዉ ልባል የሚችል ሲሆን እና በዉለ የተመለከተዉ የአንድ ወር ጊዜ ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ ነዉ ልባል የሚችል ሲሆን ነዉ።በተያዘዉ ጉዲይ የዉለ ጉዲይ ቤት በሽያጭ ማስተላለፍ (መግዛት) በመሆኑ ዐይነተኛ የሆነ የዉል መጣስ ተከስቷል ልባል የሚችለዉ ወይም በዉለ የተመለከተዉ ጊዜ ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ ነዉ ልባል የሚችለዉ የአንድ ወር ጊዜ ካለፈ በኋላ የቤት ሽያጭ ዉለ እንዱፈጸም ማድረግ (አመልካች ሰነድቹን አሟልተዉ አቅርበዉ የቤቱን ስመ ሀብት ወደ ተጠሪ እንዱዞር ማድረጉ) ቤቱን ለመግዛት የተፈለገበትን ዓላማ እንዲይሳካ የሚያደርግ ሲሆን ብቻ ነዉ።ከዚህ አንጻር ተጠሪ አመልካቾች የቤቱን ስመ ሀብት በስሜ ለማዛወር የሚያስፈልጉትን ሰነድች ስላላስረከቡኝ ቤቱን ለመግዛት የፈለግሁበት ዓላማ ሳይሳካ ስለቀረ ከዚህ በኋላ እንደዉለ እንዱፈጸም ማድረግ ጥቅም የለዉም በማለት በማስረጃ በማስደገፍ በስር ፍርድ ቤት አልተከራከሩም። በዉለ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ አመልካቾች የዉል ግዳታቸዉን ያልተወጡ ስለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።ሆኖም በዚህ ምክንያት የዉል ግዳታ መፈጸሚያ ጊዜ በመዘግየቱ ምክንያት በተጠሪ ላይ የደረሰ ጉዲት ካለ ተጠሪ ተገቢዉን ኪሳራ እንዱጠይቁ መብት ሉሰጣቸዉ ከሚችል በስተቀር በዉለ የተመለከተዉን ጊዜ አለማክበር ዐይነተኛ የሆነ የዉል መጣስ ወይም ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ ተጥሷል የሚባል ባለመሆኑ ዉለ እንዱሰረዝ የሚያደርግ ምክንያት አይደለም።
ተጠሪ የቤት ሽያጭ ዉለ በፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱፈርስላቸዉ ባቀረቡት ክስ ላይ የጠቀሱት ምክንያት ዉለን ለማስፈረስ የሚያስችል ምክንያት አይደለም። በተጨማሪም በዉለ የተመለከተዉን ግዳታ አመልካቾች አለመፈጸማቸዉ ዐይነተኛ የሆነ የዉል መጣስ ወይም ቁርጠኛ የሆነ የዉል መፈጸሚያ ጊዜ ተጥሷል የሚያስብል አይደለም። ስለሆነም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ዉል የሚያስፈርስና የሚያሰርዝ ምክንያት የለም። አመልካቾች በዉለ መሰረት ስመ ሀብቱን ለማዛወር የሚያስፈልጉ ሰነድችን ለማስረከብና እንደዉለ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸዉን በማረጋገጥ እስከዚህ ሰበር ችልት ድረስ ተከራክረዋል። ስለሆነም ዉለን ሉያስፈርስ የሚችል የሕግ ድጋፍ ያለዉ ምክንያት በላለበት የስር ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉለ እንዱፈርስና ለቃብድ የተከፈለ ብር 20,000.00 እንዱመለስ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። ግራቀኙ መስከረም 08 ቀን 2012 ዓ/ም ያደረጉት የኮንድሚኒየም መኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ያደረጉ ስለመሆኑ የተማመኑ ሲሆን ውለ በቃብድ ላይ የተመሰረተ ውል ካለመሆኑም በላይ በውላቸው ላይ ብር 20,000.00 የተከፈለው ለቅድመ ክፍያ ስለመሆኑ በግልጽ የተመለከተ በመሆኑ ክፍያው ቃብድ ተደርጎ መወሰደም ውለን ያገናዘበ አይደለም። በልላ በኩል አመልካቾች የዉል ግዳታቸዉን በጊዜው ባለመፈጸማቸዉ ምክንያት ጉዲት ደርሶብኛል በማለት ተጠሪ መቀጫ እንዱከፈላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። በፍ/ሕ/ቁ. 1890(2) እንደተመለከተው ኪሣራውን የተዋዋለት ለውለ አፈጻጸም መዘግየት ስለመሆኑ በግልጽ ካልተመለከተ በስተቀር ሉፈጸም የሚችል ውል ላይ ኪሣራ ለመጠየቅ አይቻልም። የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካቾች የውል ግዳታቸውን አለመወጣታቸውን ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ቢሆንም ውለ ከላይ በተመለከተው አግባብ ሉያስፈርስ የሚችል ምክንያት ባለመኖሩ፣ ውለ ሉፈጸም የሚችል በመሆኑ እና ግራቀኙ ያደረጉት ውል ላይ መቀጫው በግልጽ ለመዘግየት እንደሚከፈል ያልተመለከተ በመሆኑ ተጠሪ መቀጫ እንዱከፈላቸው ያቀረቡትን ዲኝነት ተቀባይነት የለውም ብለናል። በአጠቃላይ የሥር ፍርድ ቤቶች ውለን በማፍረስ ለተጠሪ አስቀድመው የከፈለት ገንዘብ ብር 20,000.00 እና መቀጫ ብር 50,000.00አመልካቾች እንዱከፍለ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 09 ቀን 2012 ዓ/ም እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሕዲር 30 ቀን 2013ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን የቤት ሽያጭ ዉል ሉያስፈርስ የሚችል ምክንያት የለም። ስለሆነም አመልካቾች ቅድመ ክፍያና መቀጫ ሉከፍለ አይገባም ብለናል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጪ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠ እግድ ተነስቷል። ይጻፍ የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.