በሽያጭ ውል ሻጭ ለተሸጠዉ ንብረት ዋጋዉን ከገዥ መጠየቅ የሚችለዉ እና ገዥም ንብረቱን የገዛበትን ዋጋ ለሻጭ ለመክፈል የሚገደደዉ ንብረቱን በዉለ በተመለከተዉ አግባብ ከተረከበ ወይም ያለበቂ ምክንያት ንብረቱን ለመረከብ ፍቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ ብቻ መሆኑን፣ ገዥዉ ንብረቱን ተረክቦ ወይም መረከብ ሲገባዉ ያለ በቂ እና ህጋዊ ምክንያት ሳይረከብ ቀርቶ የንብረቱን ዋጋ ለሻጭ ያልከፈለዉ እንደሆነ ሻጭ ገዥዉ ገንዘቡን ተገድ እንዱከፍል ወይም ዉለ እንዱሰረዝ ወይም/እና ካሳ እንዱከፈለዉ ዲኝነት መጠየቅ የሚችል መሆኑን እና ሻጭ ይህን ዲኝነት ለመጠየቅ ግን በበኩለ በዉለ መሰረት የሚጠበቅበትን ግዳታ የተወጣ መሆኑን ወይም ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ አንቀጽ 2274፣ 2279፣ 2303፣ 2329-2359 እና 2360
No summary available.
ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- ባህርዲር ዪኒቨርሲቲ-- ነ/ፈጅ ቀርበዋል ተጠሪ- አቶ ኤፍሬም ደሳለኝ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ውልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረውም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረበዉ ክስ አመልካች ባወጣው የጨረታ ማስታወቂያ መሰረት የተለያዩ እቀዎችን ለማቅረብ ጨረታውን አሸንፋ የተወሰኑ እቃዎችን አቅርቤ ክፍያ ተፈፅሞልኛል። ከዚህም በተጨማሪ ብዛቱ 1750 የሆነ መፅሓት አንደን በብር 562.00 ለመስራት ጨረታ አሸንፋ መፅሓቱን ካዘጋጀሁ በኋላ ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ለርክክብ በአመልካች ዩኒቨርሲቲ የተገኘሁ ሲሆን ርክክቡ ሳይፈፀም የአመልካች ተማሪዎች በኃይል እና በጉልበት መጽሓቶቹን ተከፊፍለዋል፤ የአመልካች የፀጥታ ሰራተኞች እና ፕሉሶች ድርጊቱን እንዱያስቆሙ ጥያቄ ባቀርብም ክልከላ ብናደርግ ላላ ችግር ይፈጠራል በማለት ድርጊቱን ሳያስቆሙ ቀርተዋል። አመልካችም የመፅሓቱን ክፍያ እንዱፈፅምልኝ ስጠይቅ የሂሳብ ወጪና ገቢ ባልተሰራበት ለመክፈል አንችልም የሚል ምላሽ የሰጠኝ በመሆኑ የመፅሓቶቹን ጠቅላላ ዋጋ ብር 983,500.00 ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
አመልካች በበኩለ በሰጠው መልስ ተጠሪ እቃዎቹን በ45 ቀናት ውስጥ የማስረከብ ግዳታ ያለበት ሲሆን ይህም ጊዜ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ.ም ነው፤ ሆኖም ግን ተጠሪ መጽሓቱን ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ ከማቅረቡም በላይ ጥራቱ በውለ ላይ በተገለፀው አግባብ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፤ መፅሓቱ እና ፍልደሩ የሚሰራው የተማሪዎችን ምርቃት ለማድመቅ ሲሆን ተጠሪ ግን አቅርቦት የፈፀመው ተማሪዎች ከተመረቁ እና ወደ ቤተሰቦቻቸው ከተበታተኑ በኋላ ነው፤ ከዚህም ባለፈ አመልካች መፅሓቱን ያልተረከበ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባዋል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ግራ ቀኙ ግንቦት 01 ቀን 2010 ዓ.ም ያደረጉት ውል ተጠሪ እቃውን በ45 ቀናት ውስጥ ያማያቀርብ ከሆነ እና ይህ ጊዜ ካለፈ የውለ ገንዘብ መጠን 10 ፏርሰንት እስከሚደርስ ድረስ በእያንዲንደ ቀን 0.1 ፏርሰንት እንደሚቀጣ፣ አመልካችም የእቃው መዘግየት ዔቃውን ለተፈለገው ዓላማ የማይደርሰው ከሆነ ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውለን ለማቋረጥ እንደሚችል የሚያመለክት ሲሆን አመልካች ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውለን አላቋረጠም፤ በዚህም ምክንያት መቀጮ ከመጠየቅ በስተቀር ውለን ማፍረስ አይችልም፤ የመፅሓቶቹን ጥራት በባለሞያ በማረጋገጥ የመረከብ ኃላፉነት ያለበት እራሱ አመልካች ነው፤ ነገር ግን ይህንን ሳያደርገ መፅሓቶቹ ተማሪዎች በጉልበት እንዱወስደት ያደረገ በመሆኑ ተጠሪ ግዳታውን አልተወጣም ለማለት አይቻልም በማለት ተጠሪ ከዚህ በፉት ሰርቶ ላስረከበው ባይንደር የተከፈለው ብር 498,750.00 የውል ግዳታ ከተገባበት ጠቅላላ ገንዘብ ብር 1,366,440.00 ተቀናሽ ተደርጎ የሚመጣውን ብር 867,690.00 ክሱ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም አቤቱታው ተሰርዞበታል።
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያላቸውን ስህቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙለት ጠይቋል። የአቤቱታው ይዘትም አጠር ባለ መልኩ በውል ስምምነታችን መሰረት የአከፊፈል ሁኔታን በሚመለከት ተጠሪ በጨረታው ስፓሲፉኬሽን ላይ በተገለፀው የጥራት መጠን ልክ ሲያቀርብ አመልካች ደግሞ እቃው በውለ ላይ በተጠቀሰው መጠን እና አይነት መቅረቡን በማረጋገጥ በሞደል 19 ገቢ እንዱሆኑ ካደረገ በኋላ ክፍያ እንደሚፈፅም ተስማምተን እያለ እቃዎቹን በዚህ አግባብ ባልተረከብንበት እንደተረከብን ተቆጥሮ ክፍያ ፈጽሙ መባለ፤ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በገባው የውል ግዳታ መሰረት በ45 ቀናት ውስጥ እቃውን ሳያቀርብ ተማሪዎች ተመርቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ከተመለሱ በኋላ ላስረክብ መጥቼ ተማሪዎች በጉልበት ወስደውብኛል ሲል ያቀረብነውን አቤቱታ ተቀብል የግራ ቀኙን ውል እና የህጉን ዓላማ ያለገናዘበ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነዉ።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ግራ ቀኙ ባደረጉት የውል ስምምነት መሰረት ተጠሪ መጽሓቶቹን ለአመልካች ማስረከቡ ባልተረጋገጠበት አመልካች ተረክቧል ተብል ዋጋውን እንዱከፍል የተወሰነበት አግባብ ግራ ቀኙ ካደረጉት ውል አንፃር ተጠሪ ባለበት መመርምር ያለበት መሆኑ ታምኖበት ለዚህ ሰበር የሰሚ ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጎ ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ መልሱ ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም መፅሓቶቹን በመኪና ጭኜ ወደ አመልካች ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ጉዲዩ ለሚመለከታቸው የተማሪዎች ህብረት አመራሮች ጋር ስደውል በፈተና ምክንያት ፀብ ተፈጥሮ ከግቢ ውጪ መሆናቸውን የገለፀልኝ እና የሳይንቲፉክ ዲይሬክተሩን እንዲነጋገር ከገለጹልኝ በኋላ በመካከል በግቢው ውስጥ የነበሩት የአመልካች ተመራቂ ተማሪዎች የመኪናውን ረዲት በመደብደብ መጽሓቱን የወሰደ ሲሆን አመልካች ሉያስቆማቸው አልቻለም፤ ይህም የአመልካች ችግር ሲሆን መፅሓቱም ጥራት እንዲለው በማስረጃ ያረጋገጥኩ ሲሆን አመልካች ግን ይህንን የሚያስተባብል ማስረጃ አላቀረበም፤ የመፅሓቶቹን ብዛት እና ጥራት አረጋግጦ የመረከብ ግዳታ እያለበት ያልተረከበ በመሆኑ ጥፊቱ የራሱ ነው፤ የስር ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ ግንዛቤ በመውሰድ አመልካች ክፍያውን እንዱፈፅም ውሳኔ መስጠታቸው ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ለማስቀረብ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብበነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ተጠሪ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ በመካከላቸዉ በተደረገዉ የተማሪዎች የምረቃ መጽሓት አቅርቦት ዉል መሰረት አመልካች መክፈል የሚገባዉን የመጽሓቶቹን ዋጋ አለመክፈለን ሲሆን፣ አመልካች በበኩለ በመካከላቸዉ መጽሓት አቅርቦት ዉል መደረጉን ሳይክድ አጥብቆ የሚከራከረዉ ተጠሪ መጽሓቶቹን በዉለ ላይ በተመለከተዉ ጊዜ እና ሁኔታ መሰረት ያላስረከበ እና ርክክቡ ሳይደረግ አመልካች የመጽሓቶቹን ዋጋ ለመክፈል የማይገደድ መሆኑን ነዉ። ተጠሪም ቢሆን በዉለ በተመለከተዉ አግባብ የርክክብ ሥርዓት አለመፈጸሙን ሳይክድ አመልካች ክፍያዉን የመፈጸም ኃላፉነት ይኖርበታል በማለት የሚከራከረዉ መጽሓቶቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ከወሰደ በኋላ ተማሪዎች በጉልበት ቀምተዉ የተከፊፈለ መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በዉለ መሰረት ርክክብ አለመደረጉን ካረጋገጠ በኋላ አመልካች የመጽሓቶቹን ዋጋ የመክፈል ኃላፉነት እንዲለበት ከድምዲሜ ላይ የደረሰዉ መጽሓቶች ወደ ግቢ መግባታቸዉንና አመልካች የመጽሓቶቹን ጥራት አረጋግጦ የመረከብ እና ተማሪዎችን የመቆጣጠር ግዳታ እያለበት ይህን ባለማድረግ ተማሪዎች በጉልበት እንዱወስደት አድርጓል የሚል ምክንያት በመጥቀስ ነዉ።
የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ መሰረታዊ ጭብጥም የቀረበዉ ክስ ዉልን መሰረት ያደረገ እንጂ አመልካች ተማሪዎችን ባለመቆጣጠሩ ምክንያት የሚኖርበትን ኃላፉነት የሚመለከት ባልሆነበት እና አመልካች መጽሓቶቹን በዉለ አግባብ ባልተረከበበት ሁኔታ አመልካች የመጽሓቶቹን ዋጋ የመክፈል ኃላፉነት እንዲለበት የተሰጠ ዉሳኔ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ ነዉ።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር ጉዲይ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቀዲሚነት እንዱያከናዉን ከሚጠበቁበት ተግባራት ዉስጥ አንደ እና መሰረታዊዉ ለቀረበለት ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉ የህግ ክፍል የመለየት ተግባር (identification of applicable law) ነዉ። አስቀድሞ ይህን ማድረግ የቀረበዉ ክስ የክስ ምክንያት ያለዉ መሆን አለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን እና ላልች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ካለ አስቀድሞ በመለየት መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉ ሲሆን፣ ጉዲዩ ወደ ሙለ የክርክር ሂደት (full scale trial) የሚገባ ከሆነም በጉዲዩ ላይ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉን ጭብጥ ይዞ ክርክሩን በመምራት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን ድንጋጌ በአግባቡ ለይቶ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት ያስችላል። በአጠቃላይ አስቀድሞ በጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ክፍል መለየት ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከክርክር አመራር ሥርዓት ጋር በተያያዘ በሥ/ሥርዓት ህጉ የተመለከቱትን ደንቦች እና ድንጋጌዎች መሰረት ባደረገ መልኩ ክርክሩን ይመራ ዘንድ ያስችለዋል። የክርክር አመራርን አስመልክቶ በህጉ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ጉዲዩን መምራት፣ የክርክር አመራሩ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ እንዱሆን በማድረግ የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት መብት እንዱከበር በማድረግ ሥነ ሥርዓታዊ ፍትሕ እንዱረጋገጥ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ፤ ለጉዲዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ፣ ተቀባይነት እና አግባብነት ያለዉን ማስረጃ ለይቶ በማስቀረብ እና በመመርመር ወሳኝ የሆኑ ፍሬ ነገሮች ነጥሮ እንዱወጡ በማድረግ ብልም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ድንጋጌ ለይቶ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ እንዱሰጥ ያስችላል። በክስ አቤቱታ ላይ የሚገለጹ ነገሮችን አስመልክቶ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 222 ላይ ከሳሽ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮችን እንዱሁም ተከሳሽ ለክሱ ምክንያት በሆነዉ ነገር ላይ በኃላፉነት የሚጠየቅበትን ሁኔታ ከሳሽ በግልጽ በክሱ ማካተት እንዲለበት፤ እንዱሁም የሚጠየቀዉ ዲኝነት በግልጽ መመልከት እንዲለበት በአንቀጽ 224 በአስገዲጅ መልክ ከደነገገባቸዉ ምክንያቶች ዉስጥ አንደ ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ክፍል አስቀድሞ እንዱለይ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት፣ ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ፣ ተጠሪ ለክሱ መሰረት ያደረገዉ አመልካች በዉለ መሰረት የሚጠበቅበትን የመጽሓቶችን ገንዘብ የመክፈል ግዳታዉን አለመወጣቱን ነዉ። የተጠሪ ክስ ይህ ከሆነ አመልካች እንዱያቀርብ የሚጠበቅበት ክርክርም ተጠሪ በዉለ መሰረት እንዱያቀርብ የሚጠበቅበትን መጽሓት በዉለ ላይ በተመለከተዉ አግባብ ያቀረበ መሆን ያለመሆኑ ነዉ። አመልካች ያቀረበዉ ክርክርም ይህንኑ መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ መዝገቡ ያሳያል። ተጠሪ በክሱ የግቢዉ የጥበቃ አካላትና ፕሉሶች ባለመከላከላቸዉ ተማሪዎች መጽሓቱን በጉልበት ተከፊፍለዉ ወስደዋል በሚል የገለጸ ቢሆንም ከዚህ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች በሚፈጽሙት ጥፊት አመልካች ከዉል ዉጭ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ የጠቀሰዉ ነገር ባለመኖሩ አመልካች ይህን አስመልክቶ ክርክር እና ማስረጃ አቅርቦ አልተከራከረም፤ ይህን እንዱያቀርብም የተጠሪ የክስ ምክንያት አይፈቅድለትም። ይህ በሆነበት ሁኔታ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካች ዩኒቨርሲቲ በግቢዉ ዉስጥ ያለትን ነገሮች የመቆጣጠርና ተማሪዎች መጽሓቶቹን ሲወስደ የማስቆም ኃላፉነት አለበት በሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱ ከተጠሪ የክስ ምክንያት ዉጪ በመሆኑ አመልካች ክርክር እና ማስረጃ አቅርቦ ያልተከራከረበትን ፍሬ ነገር መሰረት ያደረገ እና በዚህም ምክንያት የአመልካችን የመሰማት መብት ከግምት ዉስጥ ያላስገባ መሰረታዊ የክርክር አመራር ግድፈት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል።
ይልቁንም ከግራ ቀኝ ክርክር አኳያ ተጣርቶ እልባት ሉሰጠዉ የሚገባዉ ጉዲይ ተጠሪ በዉለ መሰረት የሚጠበቅበትን ግዳታ መወጣት አለመወጣቱ ነዉ። እንደሚታወቀዉ ዉል ተዋዋይ ወገኖች ስለ እራሳቸዉ ጉዲይ በእራሳቸዉ ለመወሰን ያላቸዉን ነፃነት በመጠቀም የሚያደርጓቸዉ ስምምነቶችን የሚመለከት ሲሆን፣ በህግ የተመለከቱትን አስገዲጅ ድንጋጌዎችን የሚፃረር እስካልሆነ ድረስ ተዋዋዮች የሚያደርጓቸዉ ስምምነቶች የህግ ኃይል ተሰጥቶአቸዉ ግራ ቀኝን የሚያስገድደ ስለመሆኑ በዉል ህግ ተቀባይነት ያገኘ መርህ ሲሆን፣ በፍትሐብሕር ህጋችን አንቀጽ 1711 እና 1731 ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎችም ይህንኑ የሚያስገነዝቡ ናቸዉ። በዚህ መልኩ የህግ ደረጃ የተሰጠዉ ተግባር በመሆኑም አመሰራረቱ፣ አፈፃፀሙ እና ዉጤቱ የሚወሰነዉ ስለጉዲዩ በሚደነግገዉ ህግ ነዉ። በዚህም መሰረት በተለይም ስለዉል አፈፃፀም እና ዉጤቱ የሚደነግገዉ የአገራችን የፍትሐብሕር ህግ ተዋዋይ የተዋዋለበትን ግዳታ በዉለ መሰረት ለላላኛዉ ተዋዋይ የመፈጸም ኃላፉነት እንዲለበት፣ በዉለ መሰረት በበኩለ የሚጠበቅበትን ግዳታ የተወጣ ተዋዋይ ላላኛዉ ተዋዋይ በዉለ አግባብ ግዳታዉን ያልተወጣ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ ይህን ግዳታዉን በፍርድ ኃይል ተገድ እንዱፈጽም አሉያም ዉለ እንዱሰረዝ ወይም/እና ካሳ እንዱከፈለዉ ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ይችላል (የህጉ አንቀጽ 1757 እና 1771 ድንጋጌዎች ይመለከቷል)። ይህ እንደ አጠቃላይ ሆኖ ስለ የሽያጭ ዉል በተለይ የሚደነግጉትን የህጉን ድንጋጌዎች ስንመለከት ሻጭ በዉለ ዉስጥ የተመለከተዉን ነገር ለገዥዉ በዉለ በተመለከተዉ አግባብ የማስረከብ ኃላፉነት እንዲለበት፣ በዉል በልዩ ሁኔታ ካልተመለከተ በቀር የማስረከቢያ ቦታም ዉለ ሲደረግ በነበረ መስሪያ ቤት መሆን እንዲለበት፣ ገዥዉም የገዛዉን ንብረት የመረከብ እና ዋጋዉንም ለሻጭ የመክፈል ግዳታ እንዲለበት፣ በዚህ መልኩ ያልተፈጸመለት ተዋዋይ እንደነገሩ ሁኔታ ዉለን በማስገደድ በፍርድ ኃይል ለማስፈጸም ወይም ለማሰረዝ ወይም/እና ካሳ እንዱከፈለዉ ዲኝነት መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ በአንቀጽ 2274፣ 2279፣ 2303፣ 2329-2359 እና 2360 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለዉ ሻጭ ለተሸጠዉ ንብረት ዋጋዉን ከገዥ መጠየቅ የሚችለዉ እና ገዥም ንብረቱን የገዛበትን ዋጋ ለሻጭ ለመክፈል የሚገደደዉ ንብረቱን በዉለ በተመለከተዉ አግባብ ከተረከበ ወይም ያለበቂ ምክንያት ንብረቱን ለመረከብ ፍቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ ብቻ መሆኑን፣ ገዥዉ ንብረቱን ተረክቦ ወይም መረከብ ሲገባዉ ያለ በቂ እና ህጋዊ ምክንያት ሳይረከብ ቀርቶ የንብረቱን ዋጋ ለሻጭ ያልከፈለዉ እንደሆነ ሻጭ ገዥዉ ገንዘቡን ተገድ እንዱከፍል ወይም ዉለ እንዱሰረዝ ወይም/እና ካሳ እንዱከፈለዉ ዲኝነት መጠየቅ የሚችል መሆኑን እና ሻጭ ይህን ዲኝነት ለመጠየቅ ግን በበኩለ በዉለ መሰረት የሚጠበቅበትን ግዳታ የተወጣ መሆኑን ወይም ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ነዉ። ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት በግራ ቀኝ መካከል በተደረገዉ ስምምነት መሰረት አመልካች የመጽሓቶቹን ዋጋ ለተጠሪ ለመክፈል የሚገደደዉ ተጠሪ በጨረታዉ ስፓስፍኬሽን መሰረት ዉለ ላይ በተገለጸዉ ጥራት መሰረት ሲያቀርብ አመልካች የቀረቡት መጽሓቶች በዉለ መሰረት ሙለ በሙለ በዓይነትና በመጠን መቅረባቸዉን ቆጥሮ በማረጋገጥ በሞዳል 19 መጽሓቶቹን ገቢ ያደረገ እንደሆነ ስለመሆኑ በዉለ አንቀጽ 16.1 ላይ የተመለከተ መሆኑን አመልካች ጠቅሶ የሚከራከር ሲሆን፣ ተጠሪ ይህን የዉለን ይዘት ክድ አይከራከርም። ተጠሪ መጽሓቶቹን በዉለ ላይ በዚህ መልኩ በተመለከተዉ አግባብ ለአመልካች ያላስረከበ ስለመሆኑ ግራ ቀኝን ያላከራከረ ጉዲይ ሲሆን፣ መጽሓቶቹን ተጠሪ በመኪና ጭኖ በአመልካች ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ካስገባ በኋላ ተማሪዎች በጉልበት ወስደዉ መከፊፈላቸዉ ተረጋግጧል። ይህም የሚያሳየዉ ተጠሪ መጽሓቶቹን በብዛት እና በጥራት በዉለ በተመለከተዉ አግባብ ለአመልካች አለማስረከቡንና ርክክብም አለመፈጸሙን ነዉ። ይህ በመሆኑም ተጠሪ መጽሓቶቹን በዉለ መሰረት የማስረከብ ግዳታዉን ተወጥቷል ለማለት አይቻልም። ተጠሪ በዉለ መሰረት ግዳታዉን ካልተወጣ ደግሞ አመልካች ገንዘቡን በዉለ መሰረት ለመክፈል የሚገደድበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም።
ሲጠቃለልም ለዉለ ምክንያት የሆኑትን መጽሓቶች አመልካች በብዛት እና በጥራት በዉለ ላይ በተመለከተዉ አግባብ መቅረባቸዉን አረጋግጦ ርክክብ ባልተፈጸመበት ሁኔታ በዉለ መሰረት ገንዘቡን የመክፈል ኃላፉነት የለበትም። ተማሪዎቹ ለሚፈጽሙት ህገ ወጥ ተግባር የአመልካች ዩኒቨርሲቲ ከዉል ዉጪ ኃላፉነት የሚኖርበት ስለመሆኑ በተጠሪ የክስ ምክንያት ሆኖ ክርክር አልተደረገበትም።
በመሆኑም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጠሪን የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ ተማሪዎቹ ለሚፈጽሙት ህገ ወጥ ተግባር አመልካች የፍትሐብሕር ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ ለክስ ምክንያት ሆኖ ክርክር ባልቀረበበት ሁኔታ ይህን በመጥቀስ አመልካች ገንዘቡን ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ይህንኑ በማጽናት የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 01-49370 የካቲት 05 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.