በተዋዋይ ወገኖች መካከል በተደረገ ውል የአፓርትመንት ቤቶችን ገንብቶ ለማስረክብ እና ክፍያዎችም መፈጸም የሚገባቸዉ የግንባታ ዉልች፣ የእነዙህ ዉልች አካል እንዱሆኑ የተስማሙባቸዉ ዱዚይንና ስፔስፉኬሽን መሰረት መሆን እንዲለበት በተደረገ ስምምነት ቤቶች ተሰርተው ባለመጠናቀቃቸው ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ እንዱያስረክብ በሚል የሚሰጥ ውሳኔ፤ ተሰርቶ የተጠናቀቁ ወይም ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ሉኖሩ ስለሚችለ ከዉለ አንጻር የተሰሩ ሥራዎችንና ግንባታዉ የደረሰበት ደረጃ በባለሙያ ሳይጣራ፤ ምን ያህል ክፍያ መከፈል እንዲለበት ተጣርቶ ሳይገመትና ምንም ዓይነት ክርክር ሳይነሳበት፤ በግንባታ ዉል መሰረት ሙለ ክፍያዎች ሉከፈለኝ ይገባል በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የላለው መይ ሪል ስቴት ዳቨልፔመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና እነ አቶ ፊሲል ጌታቸዉ (24 ሰዎች) ስለዉልች በጠቅላላዉ የተመለከቱት የፍትሕ ብሓር ሕግ እንዱሁም የሕንጻ ሥራን የሚመለከቱ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.3019-3040 ድንጋጌዎች
No summary available.
ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የቤት ግንባታ ዉል ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዙህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.162150 መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የሥር ከሳሽ (የአሁን አመልካች) ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ ከተከሳሾች ጋር ቀድሞ በነበረን ክርክር በመካከላችን ባለ የግንባታ ውል መሰረት ያልተከፈልን ገንዘብ ካለ መጠየቅ እንደምችል መብቱ ተጠብቆልኝ የተወሰነ በመሆኑና በዙህ የግንባታ ውል መሰረትም መክፈል የሚገባቸውን የተለያየ መጠን ያላቸውን ቀሪ ክፍያዎች፤ ከላልች የህንፃው ተጠቃሚዎች ጋር በጋራ ለሚጠቀሙበት መሰረታዊ መጠቀሚያዎች ከሳሽ ያወጣውን ወጪ፤ የተ.እ.ታ ክፍያዎች ፤
በሰበር ችልት(በቀድሞው ክርክር) ተከሳሾች የህንፃዎቹን የባንክ መያዣ ኃላፉነት እንወስዲለን ያለ በመሆኑና ከሳሽ ህንጸውን ከብድር መያዣ ለማስለቀቅ የከፈለውን የባንክ የብድር ወለድ እኩል መጠን ያላቸውን የቦታ ሉዜ ክፍያዎችን ፤ተከሳሾች በድርሻቸው መክፈል ከነበረባቸው ጊዛ ጀምሮ ከሚታሰብ 9 % ወለድና በክሱ ምክንያት የወጣውን ወጪ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለኝ በማለት የሰውና ሰነድ ማስረጃን በማያያዜ ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን፤
ተከሳሾች በበኩላቸው ከሳሽ ክሱን ያቀረበው ከተከሳሾች ጋር ከ1998 ዓ.ም እስከ 2001 ዓ.ም ባደረገው ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ባላቸው የግንባታ ውልች መሰረት ሲሆን; በዙህ ውል መሰረት ተከሳሾች በአራት ዘር ለከሳሽ ክፍያ መፈፀም ያለባቸው ሲሆን 1ኛ እና 2ኛ ዘር ክፍያ የሚከፈለው ውለ ሲፈረምና ግንባታው ሲጀመር በመሆኑ ሁለም ተከሳሾች ከፍለውታል። 3ኛ ዘር ክፍያ የሚከፈለው የህንጻዎቹን ግንባታ አጠናቆ ሲያስረክብ ሲሆን 4ኛ ዘር ክፍያ ደግሞ ከሳሽ የህንፃ ክፍልቹን ስመ ሀብት በተከሳሾች ስም አዘዋውሮ የባለቤትነት ማስረጃ ሲሰጥ በመሆኑና ከሳሽም ይህን ግዳታውን በቅድሚያ ያልተወጣ በመሆኑ የመክፈያ ጊዛው አልደረሰም/አልበሰለም፤ ክፍያ እንዱፈፀምለት የሰጠው ማስጠንቀቂያ ባለመኖሩ ክስ የማቅረብ መብት የለውም ተብል መዜገቡ እንዱዘጋላቸው የመጀ/ደ/መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን; በአማራጭነት በፍሬ ጉዲይ ላይ ደግሞ ከሳሽ በውላችን የውለ አካል እንዱሆኑ በተስማማንበት ዱዚይንና ስፔስፉኬሽን(የፉኒሽንግ ማቴሪያልች፤የክፍልቹን ስፊትና የዋጋ ዜርዜር ያካተተ) መሰረት ግዳታውን በመወጣት ያላስረከበ በመሆኑ ወለድና ወጪ ሉጠይቅ ካለመቻለሙ በላይ ርክክብ ሲደረግ ለተገኙ ጉድለቶች ማለትም የኩሽና እቃዎች፤የመብራት አምፖልችና ባልኮኒ ማስገባት ሲኖርበት ያላስገባ መሆኑ፤ወለለና የሽንት ቤት እቃዎች ጥራት ባላቸው የጣልያን እቃዎች መሰራት ሲኖርባቸው ተመጣጣኝነት በልላቸውና የጥራት ደረጃቸውና ዋጋቸው ዜቅተኛ በሆኑ እቃዎች የተሰሩ ከመሆኑም በላይ ያልተሰራ ወለል መኖሩ፤ ባለሶስት መኝታ ማስረከብ ሲገባው ባለ ሁለት መኝታ ማስረከቡ(ፓርትሽን ያልተሰራለት)፤ጣሪያና ግድግዲው በልሰና ላይ ያለ ቀለም ያልተቀባ በር ያልተገጠመላቸው መሆኑ እና አጠቃላይ የአፓርትመንቱ ስፊት በመቀነሱ ለከሳሽ ቀሪ ክፍያ የሚፈፀመው እነዙህ የተገኙ ጉድለቶችን ሲያስተካክል አልያም ለማስተካከያ የሚያስፈልገው ወጪ ተቀናሽ ከተደረገ በኃላ የሚቀር ካለ የሚከፈል ነው።
በውላችንና የውላችን አካል በሆኑ የዋጋ ዜርዜር መሰረት የሉዜና የተ.እ.ታ ክፍያ በቤቶቹ ጠቅላላ ዋጋ ላይ የሚካተት ነው ፤ከቤቱ ጠቅላላ ዋጋ አካል አይደለም ቢባል እንኳን መክፈል የሚገባን ለተ.እ.ታ ተመዜጋቢ ከሆነ በኃላ ያለውንና ለመንግስት የተከፈለውን የሉዜ መጠን ለባለቤቶቹ በማካፈል ነው።የጋራ መገልገያ ናቸው የተባለት ለቤቶቹ የግድ የሚያስፈልጉ በመሆናቸው የቤቱ አካል ሆነው በቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ላይ የሚካተት ነው; ባይሆንም ለመስራት ፍቃዲችንን ባለመጠየቁ ልንጠየቅ አይገባም።በከሳሽና በባንክ መካከል ላለው ግዳታ ተከሳሾች በወልም ይሁን በውሳኔ ለከሳሽ የባንክ ክፍያ ኃላፉነት የምንወስድበት አግባብ የለም በማለት የመከላከያ መልሳቸውን ሰጥተው የቃል ክርክርም አድረገዋል።
ፍ/ቤቱም ተከሳሾች ያቀረቡትን የመ/ደ/መቃወሚያን ባለመቀበል ብይን ከሰጠ በኃላ በውላቸው መሰረት ግንባታው መከናውኑንና አለመከናወኑን ከነዋጋቸው እንዱያጣራ ባለሙያ የመደበ ሲሆን ከሳሽ በባለሙያው ገለልተኝነት ላይ ያነሳውን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ የምርመራውን ውጤት የመዜገቡ አካል እንዱሆን አድርጎታል።ተከሳሾች ቤቶችን በፍርድ የተረከቡ መሆኑና ቀሪ ክፍያም ያለ መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም። ከሳሽ በውላቸው መሰረት ግንባታውን አካሄድ ያስረከበ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት የሰው ማስረጃና የባለሙያ ማስረጃ ያጠናከረ ሲሆን፡ የከሳሽ የሰው ምስክሮች ቤቶቹ ለነዋሪዎች ምቾት (በተሻለ ሁኔታ እንዱጠቀሙበት) ሲባልና በቤት ገዢዎቹም ተስማምተው ባለሶስት መኝታ ቤትን ወደ ባለሁለት መኝታ ቤት እንዱቀየር ተደርጎ በፀደቀ ዱዚይንና በስፔስፍኬሽኑ ከተገለፀው በተሻለ ሁኔታ የተሰሩ መሆናቸውን፤የቤቶቹ ወለል በኤም ዱ ኤፍ የተሰራ መሆኑንና የፔንት ሀውሶቹ ወለል በፏርኬ ያልተሰራ መሆኑን፤የኩሽና እቃዎች በተጨማሪ ዋጋ የሚሰሩ መሆናቸውን ሲመሰክሩ፣ የተከሳሾች የሰው ምስክሮች በበኩላቸው ቤቶቹን በፍ/ቤት ውሳኔ መሰረት ተከሳሾች ሲረከቡ ቤቶቹ ቀለም ያልተቀቡ፤የበር እጄታ የላለው፤ወለለ በጣልያን ፏርኬ መሰራት ሲኖርበት በጥራትና በዋጋ አነስተኛ ኤም ዱ ኤፍ የተሰራ ከመሆኑም በላይ ያልተሰራም መኖሩን፤ያለ ፍቃዲቸው ከባለ ሶስት መኝታ ወደ ባለሁለት መኝታ ዜቅ ማለቱ፤ የቤቱ ስፊትም የቀነሰ በመሆኑና የኩሽና እቃዎች ያልተገጠሙና ያልተሟለ በመሆናቸው በመካከላቸው ባለው የውል ድዚይንና ስፔስፉኬሽን መሰረት ተገንብቶ ያልተጠናቀቀ መሆኑንና ተጨማሪ የጋራ መገልገያዎችንም እንደሚያሰሩላቸው በከሳሽ እንደተነገራቸው መስማታቸውን መስክረዋል። የባለሙያ ሪፖርትም በውላቸው መሰረት ወለለ በጣልያን ፏርኬ መሰራት ሲኖርበት ተመሳሳይ ጥራት በላለውና በደረጃም ሆነ በዋጋ ዜቅተኛ በሆነ ኤም ዱ ኤፍ የተሰሩ ሲኖሩ የፔንት ሀውሶቹ ወለል ያልተሰራላቸው መሆኑን፤በር ያልተገጠመላቸው ያለና የተገጠመላቸውም በውላቸው ካለው የኦክ እንጨት ውጪና ዜቅተኛ ጥራት ያለው መሆኑን፤
ቀለምና ኮርኒስ ተሰርቶ ያልተጠናቀቀ ሲሆን የኤላክትሪክ ስራው ደግሞ በዱዚይኑና ስፔስፉኬሽኑ መሰረት ያልተሰራ መሆኑን ገልጧል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ውል፤የሰው የባለሙያ ማስረጃን በመመርመር የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፎል; 1.በከሳሽና ተከሳሽ መካከል በተደረገው የግንባታ ውል መሰረት ከሳሽ ክፍያ ለመጠየቅ በቅድሚያ ቤቶቹን በውላቸው መሰረት ገንብቶ ማስረከብ ያለበት ሲሆን ከውለ ውጪ የተፈጸመውን ጉድለት በራሱ ለማስተካከል አልያም ለማስተካከል የሚያስፈልገውን ወጪ የመተካት ኃላፉነት አለበት፤
ይሁንና ከሳሽ ከውላቸው ውጪም ቢሆን ግንባታውን አከናውኖና ተከሳሾችም የተረከቡትን በውላቸው ላይ ካለው ዋጋ ላይ ተቀናሽ ተደርጎ ሉያዜለት የሚገባ ሲሆን ከዙህ የሚቀረው ዋጋና ከሳሽ ሙለ ለሙለ ያልሰራቸው ስራዎች ዋጋ ተከሳሾች መክፈል ካለባቸው ቀሪ ክፍያ (3ኛ ዘር ክፍያ) ላይ ተቀናሽ ላሆን ይገባል። ተቀናሽም የሚደረገውም የወለል፣ የኮርኒስ፣ የበርና የኤላክትሪክ ስራዎች ዋጋን ብቻ እንጂ ላልች ከዙህ ውጪ ያለ በውለ መሰረት አልተሰሩም ተብለው የቀረቡትን ወጪዎች የማያካትት ነው ተብሎል።
ምክንያቱም ግራ ቀኙ ሉገደደ የሚችለት የውላቸው አካል እንደሆኑ በተስማሙባቸው ዱዚይንና ስፔስፉኬሽን እንጂ የውለ አካል ባልሆኑት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (የቤቱ ዋጋ የሉዜ ዋጋ እንደሚያካትት የሚገልጽ)፤ የመዜናኛና የኩሽና እቃዎች በተጨማሪ ዋጋ እንደሚሰሩ (price add ons) የሚገልጸው አይደለም፣ ቢፈረምም አይገደደበትም፤ ከሶስት መኝታ ወደ ሁለት መኝታ የተቀየረው በስምምነት በመሆኑና ዱዚይኑም በመፅደቁ የውለ አካል ነው;ይህም በሰው ማስረጃም የተደገፈ በመሆኑ የተከሳሾች አቤቱታ ውድቅ ነው።
የመጨረሻውን (4ኛውን) ዘር ክፍያ ከሳሽ ለመጠየቅ በውላቸው መሰረት የቤቱን ማስረከብና ስመ ሀብቱንም በተከሳሾች ስም የማዘዋወር ግዳታ ያለበትና ያልፈፀመ በመሆኑ ይህንን ግዳታውን ሲወጣ ክፍያውን እንዱከፍለት የመጠየቅ መብቱ ተጠብቆለታል።
2.በውላቸው ላይ የሉዜ ዋጋንና ተ.እ.ታ የመንግስት ግብርን (ተ.እ.ታ በወቅቱ አለመመዜገቡ ይህን ግዳታ ቀሪ የማያደርገው በመሆኑ) ከቤቱ ዋጋ በተጨማሪነት ለመክፈል በግልፅ ስለተስማሙ በስምምነታቸው መሰረት ሉከፍለ ይገባል።
4.በሰበር ክርክር ወቅት ተከሳሾች ከሳሽ ከባንክ ላለበት ብድር ከሳሽን ተክተን እንከፍላለን ያላለና እንዱከፍለም ያልተወሰነባቸው በመሆኑ፤ከሳሽ እነዙህንና ላልች ቤቶችን ማስያዣ በማድረግ ከባንክ ተበድሮ የከፈለውን ግዳታ ተከሳሾች እንዱተኩ የሚያስገድድ ህግ የላለ በመሆኑ የከሳሽን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ተከሳሾች ሉከፍለ አይገባም በማለት ውሳኔ አሳልፎል።
የሥር ከሳሽ እና ተከሳሽ በዙህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር ባሳለፈዉ ዉሳኔ፡ 1.ከውላቸው ውጪ ከደረጃ በታች ለተሰሩ ስራዎች ኃላፉነቱን ሉወስድ የሚገባው ከውል ውጪ የሰራው እንጂ የሥር ተከሳሾች እንዱከፍለ የማይገደደ ባለመሆኑ ከቀሪ ተከፊይ ሂሳብ ተቀናሽ መሆን አለበት በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በዙህ ረገድ ሽሮታል።
በተከራካሪ ወገኖች መካከል ያለው የግንባታ ውል (ያልተገነባ ቤት) ሲሆን በውለ ላይ የተጠቀሰው ዋጋ ለምን ምን ስራ እንደሆነ አከራካሪ በመሆኑ ፤በድርድር ወደ ስምምነት የወሰዶቸው የዋጋ ማቅረቢያና ላልች ተያያዥነት ያላቸው ሰነድች; በሪል ስቴት ኢንደስትሪው የተለመደ ቢዜነስ አሰራርና ላላም ተገቢ የሆነ ማስረጃ በመስማት ዋጋውም የኩሽና እቃዎችን ማካተትና አለማካተቱን የተዋዋዮቹ ሃሳብ ምን እንደነበር ሳይጣራ መወሰኑ አግባብ አይደለም።
የሉዜ ክፍያን ገዢዎች ለመንግስት መክፈል እንዲለባቸው በውላቸው በግልፅ የተስማሙት በመሆኑ፤ ለመንግስት ቢከፍለ ሕንጻው ላረፈበት ቦታ ለህንጻው ነዋሪዎች ተካፍል በመሆኑ፤
ገንቢውም ይህን የሉዜ ክፍያ ከከፈለ ውለን መሰረት አድርጎ እንዱተካለት መጠየቅ የሚችል በመሆኑ ይህ ገንቢው ለሉዜ ለመንግስት የከፈለው መጠንና ምን ያህል ቤቶች እንዲለ ሳይጣራ በውለ የተመለከተውን ገንዘብን ይክፈለ ማለቱ አግባብ አይደለም።
በተጨማሪም 4ኛውን ዘር ክፍያ እንዱከፍለ ሳይወሰን ተ.እ.ታ እንዱከፍለ መወሰኑ አግባብ አይደለም። ለከፈለትም ደረሰኝ ሉሰጣቸው ይገባል።
ለጋራ መገልገያዎች ከውል ውጪ መሰራቱ በመረጋገጡና ገንቢውም ከውለ ውጪ የመስራት ኃላፉነት ስለላለበትና ላልች ገዢዎችም ስለከፈለ የሥር ተከሳሾች ወጪውን መተካት ቢኖርባቸውም ሁለም ነዋሪዎች እኩል የሚጠቀሙባቸው እንደመሆኑ መጠን እኩል ክፍያ መጠየቅ ሲገባው በቤቶቹ ስፊት መጠየቁ አግባብ አይደለም።
በውላቸው መሰረት ግንባታው መከናወኑን /አለመከናወኑን ያጣራው ባለሙያ ላይ የሙያ ስነምግባር ግድፈት እንዲለበት በቃለ መሀላና በማንኛውም ማስረጃ ማስረዲት ቢቻልም የስር ፍ/ቤት ይህንን ማስረጃ ሰምቶ በገለልተኛነቱ ላይ ውሳኔ ማሳለፍ ሲገባው በማለፍ መወሰኑ አግባብ አይደለም ፤በሂሳብ ስላት ላይ የቀረበው ቅሬታም ከዙሁ ጋር የሚፈታ ነው።
4ኛውን ዘር ክፍያ ይ/ባይ ስመ ሀብቱን በተጠሪዎች ስም ሲያዘዋውር መሆኑ በውላቸው የተገለፀና በዙሁ መሰረት የሚፈፀም ቢሆንም ይ/ባይ በውል የተጣለበትን ግዳታ ከተወጣ አዱስ ክስ በማቅረብ አንዱጠይቅ ማድረጉ ለተጨማሪ ወጪና ጊዛ ብክነት የሚዲርግ በመሆኑ ግዳታውን እንደተወጣ ከተ.እ.ታ ጋር ሉከፍለት ይገባል።
ወጪና ኪሳራን በተመለከተ እንደገና እንዱወሰን ወደ ስር ፍ/ቤት በመመለሱ እንደገና የሚታይ በመሆኑ ቀሪ ሆኗል በማለት በእነዙህ ጉዲዮች የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማሻሻል እና በላልች ጉዲዮች ላይ የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማሻር ነዉ።
አመልካች ታህሳስ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ ተጠሪዎች በቀደመው ክርክራችን የማጠናቀቂያ ክፍያ ጠይቀው ባለማስረዲታቸው ውድቅ ተደርጎና ህንጻው የቀረው እንደላለ ባመኑት መሰረት ባለበት እንድናስረክብ የተወሰነውንና በዙህ ውሳኔ ያጡትን መብት አሁን ካለብን እዲ ይቀነስ ማለታቸው ዲግመኛ ዲኝነት መጠየቃቸው በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 መሰረት ተቀባይነት የላለዉ ሆኖ ሳለ፤ የኩሽና እቃዎችና የሉዜ ክፍያ በውላችን ላይ በግልጽ ከቤቱ ዋጋ ውጪ እንደሆነ የተስማማነውን እና የውላችን አካል ያልሆኑትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድንና ተጨማሪ ክፍያን (price add ons) ከግምት በማስገባት በውላችን ላይ የግራ ቀኙን ሀሳብ ምን እንደነበር ሉተረጎምና መጠኑም ሉቀነስ ይገባል መባለ፤ የታክስ አዋጅ ቁ.285/86 አመልካች ለተ.እ.ታ መመዜገብ ያለበት ከሆነ ተመዘገበም አልተመዘገበም ታክስ አዋጁ ከወጣ ጊዛ ጀምሮ መከፈል ያለበት በመሆኑ፤ በውላችን ላይ ተመሳሳይነት ባላቸው እቃዎች ግንባታ ማካሄድ እየቻልን ይህ ከግምት ሳይገባ የተወሰነ በመሆኑ፤ በቀደመው ክርክር የባንክ እዲን ኃላፉነት እንወስዲለን ያለ በመሆኑ አመልካች ይህንን እዲ ባይከፍል ሉከፍለ እንደሚገደደ ከግምት ውስጥ ሳይገባ የተወሰነ በመሆኑ፣ የሥር ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልንና በጠየቅነዉ ዲኝነት መሰረት እንዱወሰንልን አመልክተዋል።
የሰበር አጣሪ ችልቱም፣ ጉዲዩን በማየት ፣በዙህ ጉዲይ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር በከፍ/ፍ/ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ያለ ማስረጃ የቀረበ ክስ ነው ተብል የተዘጋባቸውና እስከ ሰበር በፀናበት ሁኔታ አመልካች ተጠሪዎች ቀሪ ክፍያ እንዱከፍለ ባቀረቡት ክስ መዜገብ በፍርድ ያጡትን መብት በስር ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ያገኘበት አግባብነት ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.5 አንጻር ፤የስር ፍ/ቤቶች በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል ያለውን አስገዲጅ ውል በአግባቡ መተርጎማቸውና አለመተርጎማቸውን ከመሰረታዊ የውል ህግ መርህ አንጻር እና ቤቶቹ የሚሰሩባቸውን እቃ በአማራጭ የተዋዋለትን ውል በአግባቡ መተርጎማቸውና አለመተርጎማቸውን፣ ለማጣራት ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ትዕዚዜ ሰጥቷል።
ተጠሪዎች መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ በቀድሞው ለግንባታው የሚያስፈልገው ዋጋ የይከፈልን ክርክር ከሳሾች ተጠሪዎች የነበሩ ሲሆን ለአሁን ይግባኝ መሰረት የሆነው በውላችን መሰረት ለገነባሁት ግንባታ ክፍያ የይከፈልኝ ክርክር ከሳሽ አመልካች ነው። ቤቶቹን በፍርድ በተቀበልንበት ወቅት ለተረጋገጠ ጉድለት በውላችን መሰረት (በግንባታ ህጎች) ሃላፉነት ያለበት በመሆኑ ጉድለቱን እንዱያስተካክል መጠየቃችን ዲግመኛ ዲኝነት አይደለም፤ የአመልካች ክስ መሰረትም ውላችን እንጂ የቀድሞው ውሳኔ ባለመሆኑ ፣ማስረጃም ሉሆነው ስለማይችል ፣የቀድሞው ውሳኔ አመልካች ላልሰራው ስራ ክፍያ እንዱጠይቅ መብት ያልሰጠው በመሆኑና የእኛንም የመከላከል መብት የማይነካ በመሆኑ፤ በውላችን የኩሽና እቃዎች የአመልካች ግዳታ አለመሆኑን በግልጽ ያላስቀመጠ በመሆኑ ግልፅነት የጎደለው ነው ይሁን እንጂ የውለ አካል በሆኑ ሰነድችና በ9ኛ ተጠሪ ውል ጭምር ይህ ወጪ የቤቱ ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ እንደሚካተት የተስማማንበት በመሆኑ፤ price add ons የሚለው ራሱ በጠቅላላው ላይ የሚጨመር ይሁን ከሱ ውጪ ያለ ወጪ መሆኑን ግልጽ ባለመሆኑ፤ ቤቶቹም በውላችን መሰረት ተመሳሳይነት ባላቸው እቃዎች እንዲልተሰሩ በባለሙያ ተረጋግጦ ሳለ አመልካች በባለሙያው ላይ ቅሬታ አቅርቦ ተቀባይነት በማግኘቱ እንደገና እንዱታይ የተባለ በመሆኑ የመጨረሻ ውሳኔ ካለማግኘቱም በላይ የማስረጃ ክርክር በመሆኑ በሰበር ላቀርብ አይችልም፤ ውል በፈጸምንበት ወቅት አመልካች የተ.እ.ታ ተመዜጋቢ ያልነበረ በመሆኑ በውላችን ያልተካተተ ሲሆን ቀድሞ ለከፈልነው ዋጋና እንድንከፍል ላልተወሰነብን ዋጋ የምንከፍልበት አግባብ የለም፤በውላችን መሰረት የቤት መስሪያ ዋጋን እየከፈልን የአመልካችን ብቻ የሚመለከት እዲን የምንከፍልበት አግባብ የለም፤ እኛ የተረከብነው ቤት ማስያዣ ከፍል አስለቀኩ ያለው ዜርዜር ውስጥ ካለመኖሩም በላይ አላስረዲም በማለት በዜርዜር ተከራክሯል።
አመልካች ባቀረበዉ የመልስ መልስ አመልክች ለተ.እ.ታ የተመዘገበው ውል ከመግባቱ በፉት በ1997 ዓ.ም ነው፤በቤቶቹ ላይ በዕዲ ምክንያት ለሚመጣ ኃላፉነት እንወስዲለን በማለት የተስማሙ ስለሆነና ተረክበው ስመ ሀብቱም የዝረላቸው በመሆኑ ሉከፍለ ይገባል በማለት አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ አመልካች እና ተጠሪዎች መካከል የአፓርትመንት ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ የግንባታ ዉልች የእነዙህ ዉልች አካል እንዱሆኑ የተስማሙባቸዉ ዱዚይንና ስፔስፉኬሽን መኖራቸዉ ያላከራከረ ጉዲይ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ ዉል ተዋዋይ ወገኖች ወደዉና ፈቅደዉ በተስማሙበት አግባብ መፈጸም እንዲለበት፣ ዉለን የመፈጸም ግዳታ ያለበት ወገን በዉለ መሰረት ያልፈጸመ እንደሆነ ጉድለቱን የማስተካከል ካልሆነ ለጉድለቱ ላስከተለዉ ጉዲት ካሳ የመክፈል ኃላፉነት እንደሚኖርበት ስለዉልች በጠቅላላዉ የተመለከቱት የፍትሕ ብሓር ሕጉ ድንጋጌዎች ያስገነዜባለ። እንዱሁም የሕንጻ ሥራን የሚመለከቱ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.3019-3040 ድንጋጌዎች የሕንጻ ግንባታን በተመለከተ እንደአግባብነታቸዉ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል። ስለሆነም አመልካች የአፓርትመንት ቤቱን ገንብቶ ለተጠሪዎች ማስረክብ ያለበት እና ተጠሪዎችም ደግሞ ክፍያዎችን መፈጸም የሚገባቸዉ በግንባታ ዉልቹ የዉልቹ አካል እንዱሆኑ የተስማሙባቸዉ ዱዚይንና እስፔስፉኬሽን እንዱሁም ከፍ ሲል የተጠቀሱት አግባብነት ያላቸዉ ድንጋጌዎች መሰረት መሆን እንዲለበት ግልጽ ነዉ።
ይሁን እንጂ ከዙህ ቀደም የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች እና የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ሁኖ በነበራቸዉ ክርክር፣ ከሳሾች በጠየቁት ዲኝነት ተከሳሽ በግንባታ ዉለ መሰረት ግዳታዉን በመፈጸም ቤቱን እንዱያስረክባቸዉ፣ ርክክቡ በመዘግየቱ ምክንያት ለደረሰባቸዉ ጉዲት ካሳ እንዱከፈላቸዉ፣ እንዱሁም ግንባታቸዉን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገዉን ወጪ ተከሳሽ እንዱከፍላቸዉ የጠየቁ ሲሆን፤ ተከሳሽም ተገቢ ነዉ ያለዉን ክርክር ካቀረበ በኋላ፤ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢ ነዉ ያለትን ዉሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፤ ጉዲዩ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበ ሲሆን ችልቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በ
መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካች ለክርክር መነሻ የሆኑትን ቤቶች ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች እንዱያስረክብ፤ አመልካች ደግሞ ተጠሪዎች አልከፈለኝም የሚለዉን ክፍያ በሕግ አግባብ መጠየቅ እንደሚችል በመወሰን፣ ተጠሪዎች የቤቶቹ ርክክብ በመዘግየቱ የደረሰብን ካሳ እና ግንባታዉን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገዉን ወጪ አመልካች እንዱከፍለን በማለት የጠየቁት ዲኝነት ማለፈን መረዲት ይቻላል። ይህን ዉሳኔ ተከትል የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክስ ከተጠሪዎች ጋር ባደረግነዉ የግንባታ ዉልች መሰረት ያልከፈለትን ክፍያዎች እንዱከፍለኝ በማለት ዲኝነት መጠየቁን እና እስከዙህ ችልት በክርክር ላይ መሆናቸዉን መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም አሁን በግራ ቀኛቸዉ መካከል ላለዉ ክርክር እልባት ለመስጠት እና ተጠሪዎች ለአመልካች ሉከፍለት የሚገባቸዉ ክፍያዎች ምን እንደሆኑ ለመለየት የግንባታ ዉልቹን የዉለ አካል እንዱሆን የተስማሙበትን ዱዚይንና ስፔስፉኬሽን እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ከሰጠዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መሆን አለበት። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ለክርክር መነሻ የሆኑትን አፓርትመንት ቤቶችን ባለበት ሁኔታ እንዱያስረክባቸዉ እና አመልካች ደግሞ ተጠሪዎች ሉከፍለኝ ይገባል የሚላቸዉን ክፍያዎች መጠየቅ ይቻላል በማለት ያሳለፈዉ ዉሳኔ ይዘትና ዓላማ አሁን ከቀረበዉ ክርክር አንጻር ያለዉን አንድምታ ማየቱ ተገቢ ነዉ። የፋዳራለ ሰበር ሰሚ ችልት ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ መዜገብ ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች እንዱያስረክብ ተብል መወሰኑ፣ አመልካች ቤቶቹን በግንባታ ዉልቹና የዉልቹ አካል እንዱሆን በተስማሙበት ዱዚይንና ስፔስፉኬሽ መሰረት አጠናቅቋልና ተጠሪዎች እንዱረከቧቸዉ ማለት ነዉን? ተጠሪዎች ደግሞ በዉለ ላይ የተመለከተዉን ሙለ ክፍያዎችን ለአመልካች እንዱከፍለ መወሰኑን ያመለክታልን?
ወይስ ቤቶቹ በተሰሩት መጠን ማለትም በጥራትም ሆነ በመጠን ባለበት ደረጃ ለተጠሪዎች እንዱያስረክቡ እና ተጠሪዎች ደግሞ ተሰርቶ ለተረከቡት ሥራ ተገቢዉን ክፍያ እንዱፈጽሙ የሚያመለክት ነዉ? የሚለት ጥያቄዎች ተገቢዉን ምላሽ የሚሹ ጉዲዮች ናቸዉ።
በዙህ መሰረት ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም ያሳለፈዉ ዉሳኔ ይዘትና ዓላማ ሲታይ የአሁን አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች እንዱያስረክባቸዉ ሲል አመልካች የሰራቸዉን ሥራዎች ባለበት ሁኔታ እንዱያስረክብ ከሚያመለክት በስተቀር አመልካች ቤቶቹን በግንባታ ዉልቹና የዉልቹ አካል እንዱሆን በተስማሙበት ዱዚይንና ስፔስፉኬሽን መሰረት መጠናቀቁን በማስረጃ መረጋገጡን ገልጾ ርክክቡ የተፈጸመ መሆኑን ድምዲሜ ላይ ደርሶ ዉሳኔ ማሳለፈን የሚያመለክት አይደለም። ይህ ችልት አመልካች ቤቶቹን በዙህ አግባብ ሙለ ለሙለ ገንብቶ ያጠናቀቀና ለተጠሪዎችም ያስረከባቸዉ ስለሆነ በዉለ መሰረት ሉከፈለዉ የሚገባዉን ሙለ ክፍያዎችን ከተጠሪዎች መጠየቅ ይችላል የሚል አንድምታ የለዉም። አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች እንዱያስረክባቸዉ መባለ አመልካች ላልሰራቸዉ ሥራም ጭምር በግንባታ ዉልቹ መሰረት ሙለ ክፍያዎችን ከተጠሪዎች መጠየቅ ይችላልና አሁን ለቀረበዉ ክስ ምንም ዓይነት መከላከያና መከራከሪያ ሳያቀርቡ ላልተሰራም ሥራ ጭምር ሙለ ክፍያዎችን ለአመልካች ለመክፈል ይገደዲለ የሚል ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የዉሳኔዉ አዉድ አያመለክትም። አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች እንዱያስረክባቸዉ ማለት የቤቶቹ ግንባታ በደረሱበት ደረጃ የቀረ የግንባታ ሥራ ቢኖርም እንኳን አመልካች ቀሪዉን የግንባታ ሥራ መቀጠል ሳይጠበቅበት ቤቱን እንዱያስረክብ የሚያስችል ነዉ። ተጠሪዎች በዙህ ዉሳኔ ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ እንዱረከቡ መወሰኑና ርክክቡ ለዘገየበት የጠየቁት ካሳ እና ቤቶቹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገዉን ወጪ እንዱከፈላቸዉ ጠይቀዉ ተቀባይነት ማጣቱ፣ ተጠሪዎች ላልተሰራ ሥራ ሁለ በግንባታ ዉልቹ ላይ የተመለከተዉን ሙለ ክፍያ ለአመልካች እንዱከፍለ፤ አመልካችም የተሰራዉና ያልተሰራ ሥራ ሳይጣራና ሳይለይ ሙለ ክፍያዎችን ጠይቆ መቀበል ይቻላል ማለት አይደለም። አመልካች ይህ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ ተከትል ለተጠሪዎች ያስረከባቸዉ ቤቶች የተሰሩት ሥራዎች መጠን ከግንባታ ዉልቹና የዉልቹ አካል እንዱሆኑ በተስማሙባቸዉ ዱዛይንና ስፓስፉኬሽን መሰረት ምን ያህል ነዉ የሚለዉ በብቁና ገለልተኛ ባለሙያ ተለክቶ ተገምቶ ሲታወቅ፣ ተጠሪዎች ደግሞ የቀረበዉን ግምት መሰረት በማድረግ በዉላቸዉ መሰረት ቀሪ ክፍያ የሚከፍለ ይሆናል ማለት ነዉ። አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ማስረከብ ማለት ተሰርቶ የተጠናቀቁ ወይም ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ሉኖሩ ስለሚችለ ይህን ማለት የሚቻለዉ በባለሙያ በማስረጃ በማጣራት ነዉ። በመሆኑም አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች ሲያስረክባቸዉ ቤቶቹን በተመለከተ የተሰሩ ሥራዎችንና ግንባታዉ የደረሰበት ደረጃ በባለሙያ ሳይጣራና በተጠሪዎች በኩል ምንም ዓይነት ክርክር ሳይነሳበት በግንባታ ዉልቹ መሰረት ሙለ ክፍያዎች ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም።
በመቀጠል መታየት ያለበት ጉዲይ ግራ ቀኙ መካከል በተደረጉት የግንባታ ዉልች መሰረት ተጠሪዎች ለአመልካች ሉከፍለት የሚገባቸዉ ክፍያዎች ምንድን ናቸዉ? የሚለዉ ነዉ። በግራ ቀኛቸዉ መካከል ከተደረገዉ የግንባታ ዉል አንቀጽ 2 መረዲት እንደሚቻለዉ ተጠሪዎች ለአመልካች ክፍያዎችን የሚፈጽሙበት በአራት ዙር ሲሆን 1ኛዉ ዙርና 2ኛዉ ዙር ክፍያዎችን በተመለከተ ተጠሪዎች ለአመልካች የከፈለአቸዉ መሆናቸዉ ያላከራከረ ጉዲይ ሲሆን፣ አከራካሪ የሆነዉ 3ኛ ዙር እና 4ኛ ዙር ክፍያዎች መሆናቸዉን መረዲት ይቻላል። በግንባታ ዉለ መሰረት 3ኛዉ ዙር ክፍያ የሚከፈለዉ የቤቶቹ ግንባታ ተጠናቅቆ ርክክብ ሲፈጸም ሲሆን፣ 4ኛ ዙር ክፍያ ደግሞ የቤቶቹን ስመ ሀብት በተጠሪዎች ስም እንዱመዘገብ ሲደረግና የቤት ባለቤትነት ማስረጃ ሲሰጥ መሆኑን ያስገነዝባል።
በዚህ መሰረት 3ኛ ዙር ክፍያ የሚፈጸመዉ አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች ሲያስረክባቸዉ በመሆኑ፤
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች ያስረከባቸዉ በመሆኑ፤ 3ኛ ዙር ክፍያዎች መጠየቁ ተገቢ ነዉ። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች ያስረከባቸዉ በመሆኑ፣ የቤቶቹ ግንባታ ሥራ መጠን ምን ያህል ነዉ ለዚህ ለተሰራዉ ሥራ ደግሞ ከግንባታ ዉለ አንጻር ተጠሪዎች ለአመልካች መክፈል ያለባቸዉ ክፍያዎች ምን ያህል ነዉ የሚለት ነጥቦች በማስረጃ ነጥረዉ ተጣርቶ ዉሳኔ ሉስጥባቸዉ የሚገቡ ናቸዉ። በግንባታ ዉለ መሰረት ለአመልካች ሉከፈለዉ የሚገባዉ 3ኛ ዙር ክፍያ ለተሰራዉ ሥራ እስከሆነ ድረስ፤ የተሰራዉን ሥራ በብቁና ገለልተኛ ባለሙያ በማስገመት ከግንባታ ዉለ አንጻር ተጠሪዎች ለአመልካች 3ኛ ዙር ክፍያ ዉስጥ ምን ያህል መክፈል እንዲለባቸዉ አጣርቶ መወሰኑ ተገቢ ነዉ። አመልካች ላልሰራቸዉ ሥራዎች ተጠሪዎች ክፍያ የሚከፍለበት አግባብ የለም። አመልካች ቤቶቹን ለተጠሪዎች እስካስረከባቸዉ ድረስ ለተሰሩት ሥራዎች ከተጠሪዎች ክፍያዎች መቀበል መብት እያለዉ፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከደረጃና ከጥራት በታች ለተሰሩት ሥራዎች ተጠሪዎች ክፍያ ሉከፍለ አይገባም በማለት የሰጠዉ የዉሳኔ ክፍል ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ከዙህ አንጻር አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ተጠሪዎች ከዙህ ቀደም ላልተሰራ ሥራ ለማስጨረስ የሚያስፈልገዉ ወጪ እንዱከፈለን ብለዉ ዲኝነት ጠይቀዉ ዉድቅ የሆነባቸዉ ስለሆነ አሁን ይህን ክርክር ድጋሚ ማንሳት አይችለም ክርክራቸዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 መሰረት ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ ከዙህ ቀደም ግራ ቀኛቸዉ መካከል በነበረዉ ክርክር ተጠሪዎች ግንባታዉን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገዉን ወጪ አመልካች እንዱከፍላቸዉ ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ ጥያቄአቸዉ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች እንዱያስረከብ መወሰኑ የሚታወስ ነዉ።
አመልካች በዙህ ዉሳኔ መሰረት ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች ካስረከበ በኋላ ተጠሪዎች ቀሪ ክፍያዎችን እንዱከፍለት ባቀረበዉ ክስ ላይ ተጠሪዎች ለአመልካች ክፍያዎችን መፈጸም ያለበት ለተሰሩት ሥራዎች እንጂ ላልተሰሩት ሥራዎች መሆን የለበትም ብለዉ መከራከራቸዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 (1) መሰረት ከዙህ ቀደም ፍርድ ያረፈበት ጉዲይ ነዉና አሁን ማንሳት አይችለም የሚያስብል ስላልሆነ አመልካች በዙህ ረገድ ያነሳዉ መከራከሪያ ተቀባይነት የለዉም ብለናል። እንግዱህ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ አመልካች ቤቶቹን ባለበት ሁኔታ ለተጠሪዎች አስረከበ ማለት የግንባታ ሥራዎቹ የተጠናቀቁ እና ያልተጠናቀቁ ሉኖሩ ስለሚችለ፣ ይህን መለየት የሚቻለዉ ደግሞ በማስረጃ በባለሙያ በማጣራት መሆኑ ግልጽ ነዉ። በዙህ ረገድ የሥር ፍ/ቤት ባለሙያ ተመድቦ እንዱያጣራ ማድረጉ ተገቢ አካሄድ ነዉ። ነገር ግን የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰራዉን ሥራ ገምቶ እንዱያቀርብ የተመደበዉን ባለሙያ አሬት ኮንሰልተንት በተመለከተ አመልካች ከባለሙያዉ ገለልተኛነት ጋር በተያያዘ ያነሳዉ ክርክር በግራ ቀኙ ማስረጃ ነጥሮ ዉሳኔ ላሰጥበት ይገባል ያለዉን አስመልክቶ የቅሬታ ነጥብም ስላልሆነ ይህ ችልት ይህን የዉሳኔ ክፍል አልነካዉም።
ላላዉ ግራ ቀኛቸዉን ያከራከረዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን የሚመለከት ነዉ። የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 2 (13 (5))፣ 3 (1፣ ሀ)፣ 7 (1)፣ 16፣ 17፣ 18 መሰረት ታክስ የሚከፈልበት የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ የሚያከናዉን ሰዉ ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዜገብ እንዲለበት ያስገነዜባል። በዙህ አዋጅ አንቀጽ 22 (1) ሥር እንደተመለከተወ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ሰዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ መስጠት እንደማይችል ይደነግጋል። በመሆኑም አንድ ሰዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብስቦ ለሚመለከተዉ ለግብር አስገቢ ባለስልጣን ለማስረከብ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዜጋቢ ሆኖ ለሚሰበስባዉ የተጨማሪ እሴታ ታክስ ደረሰኝ መስጠት ሲችል መሆኑን መረዲት ይቻላል። በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በዙህ ጉዲይ የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የተጨማሪ እሴት ታክስ በተመለከተ አመልካች ለተጨማሪ እሴት ታክስ መቼ እንደተመዘገበ ተለይቶ ከታወቀ በኋላ ተገቢ ዉሳኔ እንዱሰጥበት ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለሱ የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት የለዉም ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉን ያከራከራቸዉ ላላዉ ጉዲይ የሉዜ ክፍያ ጉዲይ ነዉ። የሉዜ ክፍያ ጉዲይ ሉስተናገድ የሚገባዉ የከተማ ቦታን በሉዜ ስለመያዜ የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 እንዱሁም አዋጁን ተፈጻሚ ለማድረግ በወጡት ደንብ መሰረት እንደሆነ ግልጽ ነዉ። እንደሚታወቀዉ የሉዝ ክፍያ የሚከፈለዉ ለሚመለከተዉ የመንግስት አስተዲደር አካል ነዉ። በመሆኑም ግራ ቀኙ በግንባታ ዉልቻቸዉ ላይ ያመለከቱት ነገር ቢኖርም በተጨባጭ ለመንግስት ሉከፍል የሚገባዉ የሉዝ ክፍያ ምን ያህል ነዉ የሚለዉ ጉዲይ በማስረጃ ነጥሮ ከታወቀ በኋላ ተጠሪዎች ሉከፍለት የሚገባቸዉ ነዉ።
ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሉዝ ክፍያን በተመለከተ በማስረጃ ተጣርቶ ከታወቀ በኋላ ተጠሪዎች በድርሻቸዉ እንዱከፍለት በማለት ያሳለፈዉ ዉሳኔ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም። በልላ በኩል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከቀረበዉ ማስረጃ አንጻር መርምሮ የኩሽና ዔቃዎችን፣ የጋራ መገልገያ ወጪ አስመልክቶ የሥር ፍ/ቤት እነዚህን ነገሮች አጣርቶ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 (1) መሰረት የመለሰዉ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት ስላልተገኘ፣ በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበዉ ቅሬታ ባለመቀበል፣ ዉሳኔዉን አጽንተነዋል።
በልላ በኩል 4ኛ ዙር ክፍያን በተመለከተ ተጠሪዎች በምን አግባብ ለአመልካች መክፈል እንደሚገባቸዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከዉላቸዉ አንጻር መርምሮ የደረሰበት ድምዲሜ እና ከዚህ ክፍያ ጋር በተያያዘ ተ.እ.ታ በተመለከተ ያሳለፈዉ ዉሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ጉዲይ ከፍ ሲል በተመለከተዉ አግባብ አይተዉ መወሰን ሲገባዉ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.179592 ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.162150 መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች የግንባታዉን ሥራ ሰርቶ እያለ ከደረጃና ከጥራት በታች ስለሆኑ ተጠሪዎች ክፍያዎችን ሉከፍለ አይገባቸዉም ያለዉ የዉሳኔ ክፍል ተሽሯል። አመልካች ቤቶቹን ባስረከበበት ወቅት የተሰሩት ሥራዎች ምን ያህል እንደሆኑ በባለሙያ በማስረጃ ከተጣራ በኋላ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ አግባብ ተጠሪዎች 3ኛ ዘር ክፍያ የመክፈል ኃላፉነት አለባቸዉ ብለናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን፣ የሉዜ ክፍያን፣ የጋራ መገልገያ ወጪን፣ የ4ኛ ዘር ክፍያን፣ የባንክ ብድር ወለድን፣ የኩሽና ዕቃዎችን፣ አፋት ኮንሰልታንት ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በተመለከተ ያስተላለፈዉ የዉሳኔ ክፍል አልተነካም ጸንቷል።
የዙህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
ግራ ቀኙ በዙህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ዉሳኔ ህዲር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ተነቧል።መዜገቡ ተዘግቷል።