በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር የቀረበለት ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች በዝርዝር ባቀረቡት ወይም በግልጽ ባመለከቱት ጉዲይ ላይ ተመስርቶ በህጉ አግባባ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህን ውሳኔ ሲሽርም ሆነ ሲያሻሽል ግን በህግና በማስረጃ የተደገፈ ምክንያት ላሰጥ፣ ግራ ቀኝ የጠየቁትን የይግባኝ የዲኝነት ጥያቄ፤ ክርክሩ የሚመራበት የሥነ ሥርዓት ህግ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የዲኝነት ስልጣን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ያረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ሉያደረግ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2) እና 348(1)
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ ሩቂያ መሀመድ - ጠበቃ ኸይሩ ሲርጋጋ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ አይሻ በያን 2ኛ. አቶ ሸምሱ መሀመድ አልቀረቡም መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 18/12/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የቡታጀራ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 24/06/2012 ዓ.ም፣ የደ/ብ/ብ/ህ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 15/12/2012 ዓ.ም እንዱሁም የደ/ብ/ብ/ህ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 24/10/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ጉዲዩ የጋብቻ ንብረትን የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በስር የቡታጀራ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች በ2ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። 1ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተዋል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው በስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች በቀን 18/01/2010 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ከሳሽና ተከሳሽ በጋብቻ በጋራ ያፈራነው በማለት አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰ ይዞታና በይዞታው ላይ 48 ቅጠል ቆርቆሮ ክዲን ውስጥ ለውስጥ 3 ክፍል መኖሪያ ቤት በግል ገንዘቤ በ2007 ዓ.ም አሰርቼ አብረን የኖርንበት ሲሆን ቤቱ የተሰራበት መሬት ከወላጅ እናቱ ከወ/ሮ አይሻ በያን ለጎጆ መውጫ የተሰጠ ቦታ ላይ የሰራሁት ስለሆነ የጋራ ንብረታችን ነው እኩል እንድካፈል ይወሰንልኝ በማለት ከላልች ንብረቶች ጋር ዝርዝር በማቅረብ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተከሳሽ በሰጡት መልስ ከሳሽ የጠቀሰችው ቦታና ቤት በተመለከተ ቦታውም ሆነ ቤቱ ከሳሽና ተከሳሽ በጋብቻ ወቅት ያፈራነው ሳይሆን በእናቴ ወ/ሮ አይሻ በያን ስም የሚገበርበት ቦታ ሲሆን ቤቱንም የሰራችው ኩዌት ሀገር የነበረችው ልጅዋ ወ/ሮ ሉትያ መሐመድ የተባለችው በላከችላት ገንዘብ ነው፤
በኪራይ ቤት ከምትቀመጡ እህትህ እስክትመጣ በማለት በግዜያዊነት እንድኖርበት የሰጠችኝ ቤት ነው እንጂ የጋብቻ የጋራ ንብረት አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
ጣልቃ ገብ ወ/ሮ አይሻ በያን በበኩላቸው ወደ ክርክሩ ገብተው ከሳሽ ጠቅሳ ያቀረበችው ይዞታ ወሰን ከእኔ ንብረት ጋር የማይገናኝ ቢሆንም የእኔ ወሰን በሰሜን ካሳ ከምሲ በደቡብ መሐመድ ሀሰን፣ በምስራቅ ሼፍ ኡመር፣ በምዔራብ መንገድ ሲሆን የጋራ ንብረት ነው ብለው የሚከራከሩበት ቤት በራሴ ይዞታ ላይ የሚገኝ ከመሆኑ በስተቀር ከሳሽ እንደጠቀሰችው አይደለም፤ ልጄ ፈትያ መሐመድ ከውጭ ሀገር ሰርታ በላከችልኝ ገንዘብ የሰራሁት ቤት እንጂ የከሳሽና ተከሳሽ የጋራ ንብረት አይደለም፤ ተከሳሽ ልጄ በመሆኑ ከከሳሽ ጋር አብረው በአቶ አብደላ ሻፉ ኪራይ ቤት ውስጥ ሲኖሩ ቆይተው በጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው የሚገቡበት በማጣታቸው ቤት እስኪያገኙ ድረስ በጊዜያዊነት በግል ቤቴ ውስጥ እንዱቀመጡ ካደረኩ በኋላ ባለመግባባት ምክንያት ፍቺ ፈጽመው የግል ንብረት የሆነው የቆርቆሮ ቤት እንደ ግል ንብረታቸው በማድረግ የቀረበው ክርክር ተገቢነት የላለው በመሆኑ የክርክር መነሻ የሆነው ቦታና ቤት የጣ/ገብ የግል ንብረት ተብል እንዱወሰን በማለት ጠይቀዋል።
በጣ/ገብ አቤቱታ ላይ ከሳሽ በሰጡት መልስ የጣ/ገብ አቤቱታ መብቴን ለማጣበብ ከተከሳሽ ጋር በመመሳጠር የቀረበ አቤቱታ ነው ምክንያቱም ጣ/ገብ ጠቅሳ ያቀረበችው ቤትና ይዞታ ከሳውዱ አረቢያ ከ2003-2005 ዓ.ም ሰርቼ ከመጣሁ በኋላ በ2006 ዓ.ም ከተከሳሽ ጋር ትዲር መስርተን ስንኖር እንደ አካባቢው ባህል ለጎጆ መውጫ ይዞታው ተሰጥቶን ከአረብ አገር ሰርቼ ባመጣሁት ብር ለጎጆ መውጫ ተብል በተሰጠን ይዞታ ላይ ከወራቄ መሐመድ የቤት መስሪያውን እቃ በብድር በመውሰድ ያሰራነው መሆኑን ፍ/ቤት ማረጋገጥ ይችላል፤ በተጨማሪም የ05 ቀበላ አስተዲደር እኔና ባለቤቴ መስራታችንን ማረጋገጥ የሚችል መሆኑ ታውቆ በደብዲቤ በመጠየቅ እንዱረጋገጥ፤ ጣ/ገብ አመልካች ያለማንም አስገዲጅ ይዞታውን ከሰጠችኝ በኋላ ቤት መስራቴን እያወቀች ከተከሳሽ ጋር ባለመስማማታችን ትዲራችን ሲፈርስ ተከሳሽን ለመጥቀም ያቀረበችው አቤቱታ ነው፤ ጣ/ገብ ያቀረበችው የሰነድ ማስረጃ ሀሰተኛ ነው ምክንያቱም ሰነደ የተሰራው ባለቤቷ እንዲለ በማድረግ ሲሆን የጣ/ገብ ባለቤት በ2003 ዓ.ም እንደሞተ እንዱታወቅልኝ እና የጣ/ገብ አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግ በማለት አቅርበዋል። ተከሳሽም መልሱን በማጠናከር የጣ/ገብ አቤቱታ ላይ ተቃውሞ እንደላለው ገልጿል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ቃል በመስማት፣ ከአስተዲደሩ ማስረጃ በማስቀረብ እንዱሁም ከማዘጋጃ ቤት ባለሙያ ጋር ቤትና ቦታውን ተመልክቶ ውሳኔ ሰጥቷል።
በሰጠው ውሳኔ ለክርክር መነሻ የሆነው ይዞታ ከስር መሰረቱ የጣልቃ ገብ ስለመሆኑ በከሳሽም ያልተካደች ቢሆንም የከሳሽ ክርክር ለጎጆ መውጫ የተሰጠ ይዞታ መሆኑና ጣ/ገብ ሳትቃወም ቤቱ የተሰራና የተሰራበትም ወጪ በከሳሽ የተሸፈነ ነው የሚል ሲሆን ጣ/ገብ ደግሞ አረብ አገር የምትኖረው ልጄ በምትልከው ገንዘብ የተሰራ የግል ንብረት ነው የሚል ነው። የከሳሽ ምስክሮች ከጣ/ገብ ምስክሮች በተሻለ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ አከራካሪው ቤት በከሳሽ ገንዘብ የተሰራ መሆኑን ይዞታውም ከሳሽና ተከሳሽ ትዲር በመሰረቱበት ጊዜ ለጎጆ መውጫ የተሰጠ ስለመሆኑ ሚዛን የሚደፊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም በይዞታው ላይ የተሰራው የቆርቆሮ ክዲን ቤት የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ላሆን የሚችልበት የህግ አግባብ ስለመኖሩ በንብረት ህግ ቁጥር 1179 መሰረት የጋራ ነው። ከይዞታው መጠን ጋር ተያይዞ የክ/ከተማው ማዘጋጃ ቤት በላከው ምላሽ መሰረት የክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታ መጠን ትክክለኛ መረጃ ተገኝቶ ማረጋገጥ ያልተቻለ በመሆኑ ቦታውን በአካል ከማዘጋጃ ቤት ባለሙያ ጋር በመሄድ በመመልከት ቤቱ ያረፈበትን ጨምሮ 1000 (አንድ ሺህ) ካ.ሜ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሁለቱም ወገኖች የየበኩላቸውን ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
ከሳሽ በመ/ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ክርክር የተነሳበት ቤትና ይዞታ መጠኑ 2852.85 ካ.ሜ ሆኖ የስር ፍ/ቤት 1000 ካ/ሜ እኩል ይካፈለ ማለቱ ስህተት ነው በማለት አቅርበው ፍ/ቤቱም አከራካሪውን ይዞታ መጠን በተመለከተ ፍ/ቤቱ ቦታውን ተመልክቶ ከማዘጋጃ ቤትም በቀረበው ማስረጃ መጠኑ 2852.85 ካ.ሜ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ፍ/ቤቱ ለምን 1000 ካ/ሜ አድርጎ እንደወሰነ በግልጽ ያላብራራውና ከቀረበው ማስረጃም ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት የይዞታው መጠን 2852.85 ካ/ሜ ነው በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል። በልላ በኩል ጣ/ገብ በመ/ ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱም የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናት ወስኗል።
ጣ/ገብ በዚህ መልኩ ሁለት አይነት ውሳኔ መሰጠቱን በመቃወም እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታቸውን አቅርበው ፍ/ቤቱም በከፍተኛው ፍ/ቤት በመ/ በቀን 15/04/2011 ዓ.ም እና በመ/ በቀን 4/11/2010 ዓ.ም የተወሰኑትን ውሳኔዎች በመሻር መዝገቦቹ ተጣምረው ተጣርቶ እንዱወሰን ጉዲዩን ለከፍተኛው ፍ/ቤት መልሷል። በመለሰው መሰረት ከፍተኛው ፍ/ቤት አጣምሮ ተመልክቶ በመ/ በሰጠው ውሳኔ አከራካሪውን ቤት በተመለከተ የስር ከሳሽና ተከሳሽ ቤቱ በተሰራበት ግዜና ተሰርቶም ይኖሩበት በነበረ ግዜ ጣ/ገብ ያለመቃወሟ በመረጋገጡ በአከራካሪው ይዞታ ላይ የተሰራው መኖሪያ ቤት የባልና ሚስቱ የጋራ ሀብት ነው ተብል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ፀንቷል። ቤቱ ያረፈበትን ይዞታ በተመለከተ የገጠር ይዞታ የነበረው ወደከተማ እየተካለለ በመሆኑና አንድ እድሜው ለአቅመ አዲም የደረሰ ወጣት የገጠር ይዞታ ወደ ከተማ ሲከለል ሉያገኝ በሚችልበት አግባብ ለከሳሽና ተከሳሽ መውጫና መግቢያ ባገናዘበ መልኩ 400 (አራት መቶ) ካ/ሜ ብቻ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ላሆን ይገባል በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝና የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካች በቀን 18/12/2013 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ አከራካሪው መሬት አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ጋብቻ እንደፈጸምን የ2ኛ ተጠሪ ወላጆች ለጎጆ መውጫ ሰጥተውን እህል እየዘራን ስንጠቀምበት ረጅም ግዜ ቆይተን ልጅ ወልደን አብረን ኖረንበታል፤ 1ኛ ተጠሪ ከ5 ጥማድ በላይ መሬት አላት፤
ይሁንና ለጎጆ መውጫ ሰጥተውን አካባቢው እየተሻሻለ ሲመጣ 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተጠሪን አሳምና እኔን ለማፈናቀል ተመካክረው ጋብቻው እንዱፈርስ ተደርጎ አረብ አገር ሰርቼ ባገኘሁት ገንዘብ የሰራሁትን ቤት ክደው ተከራክረዋል። በስር ፍ/ቤት አከራካሪ የነበረው በተጠቀሰው አዋሳኝ ላይ ያለው ይዞታና ቤት በጋብቻ ግዜ የተፈራ መሆን አለመሆኑ እንጂ የአዋሳኝ የመጠን ጉዲይ አልነበረም። የይዞታው መጠን በስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ለጎጆ መውጫ ይዞታና በላዩ ላይ የሰራነውን ቤት ለሁለት እኩል እንድንካፈል በጠየኩት ዲኝነት መሰረት ማስረጃ አቅርቤ አረጋግጫለሁ። ተጠሪዎች የይዞታውን መጠን በተመለከተ ክርክር አላደረጉም። የከተማው ፍ/ቤት የመሬቱ መጠን 1000 ካ/ሜ ከእነ ቤቱ የጋራ ንብረት እንዱሆን የወሰነበት ተገቢ ባለመሆኑ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቤ ጉዲዩን የያዙት ዲኛም ከማዘጋጃ ባለሙያ ጋር በመሆን ግራ ቀኛችን በተገኘንበት የይዞታው መጠን 2852.85 ካ/ሜ መሆኑን በአካል አረጋግጦ የወሰነው ማስረጃን መሰረት አድርጎ ነው። ይዞታው ለጎጆ መውጫ ሲሰጠን መሬቱን ያለማና የከተማው ልማት በአካባቢው ባልተስፊፊበት ግዜ የገጠር መሬት ለጎጆ መውጫ ሲሰጥ እንደ አቅም በጥማድ ወይም በሶማ እና መሬቱ ያለበት አካባቢ ተጠቅሶ እንጂ ካ/ሜ አይታወቅም። የስር ከተማ ፍ/ቤትም በአዋሳኝ ከተጠቀሰው ቀንሶ 1000 ካ/ሜ ያለበት አግባብና ከፍተኛው ፍ/ቤት 400 ካ/ሜ በማለት የወሰኑበት አግባብ ተገቢነት የለውም። ከፍተኛው ፍ/ቤት የመስክ ምልከታ ሳያደርግ የመሬቱ መጠን 400 ካ/ሜ እንዱሆን ሲወስን መሰረት ያደረገው በከተማ ክልል ውስጥ ያለውን ሁኔታ እንጂ በገጠር ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አይደለም። በመሆኑም የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው ተብል ውድቅ እንዱደረግና በመ/ የወሰነው ውሳኔ እንዱጸና በማለት የቅሬታ ማመልከቻቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በአጣሪ ችልት ተመርምሮ በግራ ቀኙ መካከል ያለው ክርክር የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ሆኖ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍ/ቤት አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ 1000 ካ/ሜ ላይ ያረፈውን ቤትና ይዞታ እንዱከፊፈለ ውሳኔ ሲሰጥ ግራ ቀኙ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ሁለቱም መዝገቦች በተለያየ ችልት ሳይጣመሩ በመታየታቸው በሁለቱም መዝገቦች የተለያየ ውሳኔ ስለተሰጠባቸው ጉዲዩን የክልለ ሰበር አይቶ መዝገቦችን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 11 መሰረት አጣምሮ እንዱያይ ለከፍተኛው ፍ/ቤት በመመለስ ውሳኔ ሲሰጥ ጉዲዩ የተመለሰለት ፍ/ቤት ሁለቱን መዝገቦች አጣምሮ አይቶ ግራ ቀኙ 400 ካ/ሜ ይዞታ ላይ ያለውን ቤት እንዱከፊፈለ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን የይዞታው መጠን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤት በአካል በቦታው ድረስ በመሄድ ያረጋገጠው 1000 ካ/ሜ መሆኑን ድምዲሜ ላይ ደርሶ ባለበት ፍ/ቤቱ ይህን ሉያስለውጥ የሚችል ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ 400 ካ/ሜ ላይ ያለውን ይዞታ እንዱከፊፈለ መወሰኑ ትክክል መሆን አለመሆኑን ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪዎች በቀን 11/04/2014 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ በተገቢው መንገድ ተጣርቶ 400 ካ/ሜ የተወሰነ እንጂ አመልካች እንደምትለው ያለምንም ማስረጃ የተወሰነ ባለመሆኑ በውሳኔው የተፈጸመበት የህግ ስህተት የለም ተብል እንዱጸና በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም በመልስ መልሳቸው አቤቱታቸውን በማጠናከር አቅርበዋል።
ከፍ ሲል የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን ለሰበር ችልቱ የተያዘውን ጭብጥ መሰረት በማድረግ የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደሚታወቀው ክርክሩ የቤተሰብ /የፍትሐብሄር/ በመሆኑ ሉመራ የሚገባው በቤተሰብ ህጉ እና በፍትሐብሄር ሥነ ስርዓት ህጉ አግባብ ነው። ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2) ግልጽ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለው የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራከራዎቹ ወገኖች በዝርዝር ባቀረቡት ወይም በግልጽ ባመለከቱት ጉዲይ ላይ ተመስርቶ በህጉ አግባብ ውሳኔ ይሰጣል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህን ውሳኔ ለማሻሻልና ለመሻር እንዱችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) ስልጣን የተሰጠው ሲሆን ውሳኔውን ሲሽርም ሆነ ሲያሻሽል ግን በህግና በማስረጃ የተደገፈ ምክንያት ላሰጥ ይገባል።
ከዚህ አንፃር የተያዘውን ጉዲይ ስንመለከተው አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ጋብቻ ሲፈጽሙ ለጎጆ መውጫ የተሰጣቸውን ይዞታና በጋብቻ ጊዜ በገንዘባቸው ተሰራ የሚለትን ቤት አዋሳኝ እና መጠን ጠቅሰው ድርሻቸውን እኩል ለመካፈል ዲኝነት ጠይቀዋል። የስር ፍርድ ቤት የአመልካች ምስክሮች ከተጠሪ ምስክሮች በተሻለ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ አከራካሪው ቤት በአመልካች ገንዘብ የተሰራ መሆኑንና ይዞታውም ለጎጆ መውጫ የተሰጠ ስለመሆኑ ሚዛን በሚደፊ መልኩ ማስረዲታቸውን በማረጋገጥ በይዞታው ላይ የተሰራው የቆርቆሮ ክዲን ቤት የባልና ሚስት የጋራ ንብረት እንደሆነ፤
የይዞታው መጠን ግን የክ/ከተማው ማዘጋጃ ቤት በላከው ምላሽ ስለ ይዞታ መጠን በትክክል ማረጋገጥ ያልተቻለ በመሆኑ ቦታውን በአካል ከማዘጋጃ ቤት ባለሙያ ጋር በመመልከት ቤቱ ያረፈበትን ጨምሮ 1000 (አንድ ሺህ) ካ.ሜ የባልና ሚስት የጋራ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በበኩለ በመጨረሻ በሰጠው ውሳኔ የገጠር ይዞታ የነበረው ወደከተማ እየተካለለ በመሆኑ ጉዲዩ አንድ እድሜው ለአቅመ አዲም የደረሰ ወጣት የገጠር ይዞታ ወደ ከተማ ሲከለል ሉያገኝ በሚችልበት አግባብ ላታይ ይገባል በማለት አመልካችና 2ኛ ተጠሪ መውጫና መግቢያ ባገናዘበ መልኩ 400 (አራት መቶ) ካ/ሜ ብቻ የባልና ሚስት የጋራ ሆኖ ሉካፈለ ይገባል በማለት በማሻሻል ወስኗል።
ይሁንና የገጠር ይዞታ የነበረ መሬት ወደ ከተማ ሲካለል ባለይዞታዎች የሚኖራቸው መብት እና የሚደርሳቸው የይዞታ መጠን እንዱሁም ካሳ ራሱን ችል የሚታይ እና በልላ ህግ አግባብ የሚስተናገድ እንጂ አሁን በተያዘው የባልና ሚስት ንብረት ክርክር ውሳኔ የሚያገኝ ጉዲይ አይደለም። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ ተመልሶለት መዛግብቱን አጣምሮ እንዱወስን ሲደረግ ከግራ ቀኙ ክርክር እና ከማስረጃቸው በመውጣት በራሱ ልኬት 400 (አራት መቶ) ካ/ሜ ብቻ የባልና ሚስት የጋራ ንብረታቸው ሆኖ ሉካፈለ ይገባል በማለት መወሰኑ ከፍሲል በተጠቀሰው ህግ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት ያደረገ አይደለም።
በአጠቃላይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ግራቀኝ የጠየቁትን የይግባኝ የዲኝነት ጥያቄ ፤
ክርክሩ የሚመራበት የሥነ ሥርዓት ህግ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን የዲኝነት ስልጣን እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ያረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ውሳኔው ሉታረም ይገባል ብለናል። የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህን ሳያርሙ ማለፊቸው የሚነቀፍ ነው። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የቡታጀራ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 24/06/2012 ዓ.ም፣ የደ/ብ/ብ/ህ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 15/12/2012 ዓ.ም እንዱሁም የደ/ብ/ብ/ህ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 24/10/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
የቡታጅራ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ ሚያዚያ 24/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት የቆርቆሮ ክዲን ቤት እና ቤቱ ያረፈበትን ጨምሮ 1000 ካ.ሜ ቦታ የአመልካችና የ2ኛ ተጠሪ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት በመሆኑ በተሻሻለው የክልለ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 101 መሰረት እኩል እንዱካፈለ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የዔግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል። ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.