የፍትሐ ብሓር ክርክርን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ለማየት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ተከራካሪ ወገኖች በግልጽ ባልጠየቁት ጉዲይ ላይ ዲኝነት የሚሰጥ ስላለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 182(2) በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት በተደረገ ክርክር ላይ ያልተነሳ አዱስ ክርክር በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ደረጃ ሉነሳ የሚችል ስላለመሆኑ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329(1)
No summary available.
የሰበር መዝገብ ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ ዘቢደር ከበደ አማረ - አልቀረቡም ከተባለ በኋላ ጠበቃ መኩሪያ አለሙ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አወል ሼይቶ - ቀርቧል ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል
አመልካች የተጠሪ አባት አከራካሪውን መሬት ለሟች ባለቤት በ1991 ዓ/ም ኪራይ ሰጥቶ ህይወቱ ካለፈ ከ18 ዓመት በኋላ መሬቱን እንድትለቅ ተጠሪ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ያቀረበችው መቃወሚያ ያለበቂ ምክንያት ታልፍ ሟቹ የተጠሪ አባት ያልነበረውን የይዞታ መብት ተጠሪ እንዱወርስ መወሰኑ የህግ ድጋፍ የላለው ከመሆኑም በላይ አላግባብ መሬቱ የተገኘው በግዥ እና ሽያጭ ነው በማለት አመልካችን ከይዞታዋ ላይ በማፈናቀል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረበችው የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል በመባለ መዝገቡ ለችልት ቀርቦ ታይቷል።
ጉዲዩ የገጠር መሬት ይዞታ ወራሽነትን የሚመለከት ሆኖ ክሱ በቀረበበት የደል መና ወረዲ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ ሲሆኑ አመልካች ተከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ በደል መና ወረዲ ፍርድ ቤት መገኛው እና አዋሳኞቹ በክሱ ላይ የተገለፀው 16 ጥማድ የሆነ የአመልካች ባለቤት ከሟች አባቱ በኮንትራት ወስድ ሲያርስ የነበረውን መሬት ከሐምል ወር 2011 ዓ/ም ከባሎ ሞት በኋላ አመልካች ምንም መብት ሳይኖራት አርሶ እንዲይጠቀም በማድረግ ይዞታዬ ነው በማለት በኃይል የያዘችውን የሟች አባቴን ይዞታ ትልቀቅልኝ በማለት ሐምል 20 ቀን 2012 ዓ/ም የተፃፈ ክስ አቅርቧል። አመልካችም ለክሱ በሰጠችው ምላሽ ሟች የአመልካች አባት ለሟች ባለቤቷ ሐምል 19 ቀን 1991 ዓ/ም እና ህዲር 7 ቀን 1995 ዓ/ም በተፃፈ ውል አቅሙ ደከሞ ማረስ ስለማይችል የድካሙን ሰጥቶት መሬቱን እንዱወስድ ባደረጉት ስምምነት ሰጥቶት እንጅ በጉልበት አለመያዟን በመግለፅ ፣ በአጠቃላይ መሬቱ ከ18(አሥራ ስምንት ዓመት) በላይ በእጃቸው የቆየ በመሆኑ የቀረበባት ክስ ውደቅ ሆኖ መዝገቡ እንዱዘጋ ጠይቃለች።
ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ መዝገቡን እንደመረመረው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መሬት የተጠሪ አባት መሆኑ እና በአመልካች እጅ መኖሩ በማስረጃ የተረጋገጠ ሆኖ ሟች የተጠሪ ባል የሟች የተጠሪ አባት የቤተሰብ አባል ባለመሆኑ በሕጉ አግባብ መሬት በስጦታ የሚተላለፍለት ባለመሆኑ፤ የሟች አባቱ የመሬት ይዞታ በውርስ ለተጠሪ የሚተላለፍ በመሆኑ አመልካች ከሕግ ውጭ አላግባብ የያዘችውን ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ይዞታ እንደትለቅለት ወሰኗል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ባቀረቡት ይግባኝ ጉዲዩን ያየው የባላ ዞን ክፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ አከራካሪውን መሬት ሟች አባቱ ለሟች የአመልካች ባል በኮንትራት ሰጥቷል በማለት ያቀረበውን ክርክር በማስረጃ ያላስረዲ በመሆኑ የክርክሩ ይዞታ አስቀድሞ የሟች የተጠሪ አባት ቢሆንም ለረዥም ጊዜ ከእጁ ወጥቶ በአመልካች እና በባላበቷ እጅ ገብቶ ሲጠቀሙበት የቆዩ ስለሆነና በአመልካች በኩል የቀረበው የሰነድ ማስረጃ በአመልካች ባል እና በተጠሪ አባት መካከል የተደረገው ውል የስጦታ ወይንም የግዥ እና ሽያጭ እንደሆነ አያሳይም በማለት የወረዲ ፍርድ ቤቱ የደረሰበት መደምደሚያ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀባይነት ማግኘቱን ግልፆ፤ በኮንትራት ሳይሆን ባልታወቀ መንገድ ከ1990ዎቹ አንስተው አመልካች እና ባለቤቷ ሲጠቀሙበት የነበረውን መሬት ሉለቅ አይገባም በማለት አመልካች ያቀረበችው የይርጋ መቃወሚያው ታልፍ አከራካሪውን የመሬት ይዞታ እንድትለቅ መወሰኑ አግባብ ባለመሆኑ ተጠሪ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ወስኗል። አከራካሪውን መሬት ሟች የመልስ ሰጭ ባለቤት የያዘው በግዥ እና ሽያጭ ውል መሆኑ ታውቆ እያለ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው መባለን በመቃወሜ ተጠሪ ባቀረበው ይግባኝ ጉዲዩን ያየው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደቡብ ቋሚ ችልት፤ ክርክር የተነሳበት መሬት የገጠር መሬት ይዞታ መሰረቱ የሟች የተጠሪ አባት ሆኖ ሟች የተጠሪ አባት በ1995 ዓ/ም በ750.00(ሰባት መቶ ሃምሳ) ብር ተቀብል ለሟች የአመልካች ባለቤት ያስተላለፈ መሆኑን ከመዝገቡ ግልባጭ ማስተዋለን ገልፆ፤ የገጠር መሬት ግዥ እና ሽያጭ ውል በሕገ መንግስቱም ሆነ በገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጁ ሕገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ በዚህ አግባብ የተያዘ መሬትን ለማስለቀቅ የሚቀርበው ክስ በይርጋ የማይታገድ ሆኖ እያለ፤ የባላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው ማለቱ ስህተት ነው በማለት የደል መና ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔን አፅንቷል።
አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችልት ያቀረበችው የሰበር አቤቱታ በመሰረዙ ያቀረበችውን በፍርደ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ ፤
የተጠሪ አባት መጠቀም ያቆመውን አከራካሪውን መሬት አመልካች ለረዥም ዓመት ሲጠቀሙበት እንደነበረ በሥር ፍርድ ቤት በተረጋገጠበት ሁኔታ የሽያጭ ውል ባልቀረበበት አከራካሪው መሬት በ750.00(ሰባት መቶ ሃምሳ) ብር ተሸጧል ተብል ክሱ በይርጋ ቀሪ አይሆንም የመባለ አግባብነት መጣራት አለበት በማለቱ ተጠሪ በመልሱ፡- አመልካች አከራካሪው መሬት የሟቹ የተጠሪ አባት መሆኑን አምና ሟቹ ለቆልናል በማለት ያቀረበችው ውል ተቀባይነት የላለው በመሆኑ እና አመልካች ያቀረበችው የሽያጭ ውል ሟች የተጠሪ አባት ያልፈረሙት የሀሰት በመሆኑ ፤ እንዱሁም ያቀረበችው ክርክር ተአማኒነት ባለው ማሰረጃ የተደገፈ ባለመሆኑ በይዞታው ላይ የባለቤትነት መብት የላላት የእኩል አራሽ ሆና ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ አላግባብ የያዘችውን ይዞታ እንድትለቅ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ያቀረበችው ቅሬታ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቶ ወጪ እና ኪሳራ እንዱወሰንለት ጠይቋል። አመልካችም አከራካሪውን መሬት በግዥ እና ሽያጭ አግቻለሁ የሚል መከራካሪያ ባላነሳችበት እና በጭብጥነት ባልተያዘ ጉዲይ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሬት ሽያጭ ውል ተፈፅሟል ማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና ግራ ቀኙ በዚህ ችልት ያደረጉት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑ አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ አንፃር እንደሚከተለው ተመርምሯል። የፍትሐ ብሓር ክርክር የሚመራው የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ድንጋጌ ተከትል ነው። የፍትሐ ብሓር ክርክርን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ለማየት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ተከራካሪ ወገኖች በግልጽ ባልጠየቁት ጉዲይ ላይ ዲኝነት መስጠት የማይችል መሆኑን የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 182(2) ይደነግጋል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ያቀረበው ክስ አስቀድሞ በኮንትራት የአመልካች ባለቤት ይዞት የነበረው እና ከባለቤቷ ሞት በኋላ በጉልበት የያዘችውን የሟች አባቱ የሆነ በውርሰ ለእሱ ሉተላለፍ የሚገባውን የገጠር መሬት ይዞታ እንድትለቅለት ላቀረበው ክስ፤ አመልካች ሟች የአመልካች አባት ለሟች ባለቤቷ ሐምል 19 ቀን 1991 ዓ/ም እና ህዲር 7 ቀን 1995 ዓ/ም በተፃፈ ውል መሬቱን ለማረስ አቅመ ደካማ በመሆኑ የድካሙን ሰጥቶት መሬቱን እንዱወስድ ባደረጉት ስምምነት የሰጠው እንጅ በጉልበት አለመያዟን እና መሬቱም ከ18(አሥራ ስምንት ዓመት) በላይ በእጃቸው የቆየ በመሆኑ የቀረበባት ክስ ውደቅ ላሆን ይገባል የሚል መቃወሚያ አቅርባለች። ከቀረበው ክስም ሆነ ተጠሪ ከሰጠው መልስ መረዲት የሚቻለው ግራ ቀኙ በግልጽ ሕገ ወጥ የገጠር መሬት ግብይትን አስመልክቶ የጠየቁት ዲኝነት የላለ ሲሆን ፤በአመልካች በኩል የቀረበው የሰነድ ማስረጃ በአመልካች ባለቤት እና በተጠሪ አባት መካከል የተደረገው ውል የስጦታ ወይንም የግዥ እና ሽያጭ መሆኑን እንደማያሳይ የደል መና ወረዲ ፍርድ ቤት የደረሰበት የፍሬ ነገር መደምደሚያ በይግባኝ ሰሚው የባላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተቀባይነትን አግኝቷል። የገጠር መሬት ይዞታ ግዥ እና ሽያጭን አስመልክቶ ግልጽ ዲኝነት ተጠይቆ ፣ ክርክር ተደርጎ ፣ አከራካሪው ጭብጥ ተለይቶ በማስረጃ ተጣርቶ ተገቢ መደምደሚያ ላይ መደረስ ሲገባ፤ የድል መና ወረዲ ፍርድ ቤት አከራካሪው መሬት አመልካች እጅ የገባው በኮንትራት ውል ነው ወይስ በስጦታ? በማን ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ እና ግብር በማን ስም እንደሚከፈል የያዘውን ጭብጥ ለማጣራት ከተሰሙት ምስክሮች ውስጥ የአመልካች 1ኛ ምስክር አከራካሪውን መሬት ሟች የአመልካች ባለቤት 750.00(ሰባት መቶ ሃምሳ) ብር ሰጥቶ ከሟች የተጠሪ አባት በስጦታ ማግኘቱን የመሰከረ ሲሆን ፤ የወረዲ ፍርድ ቤቱ ግልጽ ዲኝነት ያልተጠየቀበትንና አከራካሪ ጭብጥ ያልሆነውን የመሬት ሽያጭ እና ግዥ ጥያቄ ወደጎን በመተው ሟች የአመልካች ባለቤት የሟች የተጠሪ አባት የቤተሰብ አባል ባለመሆኑ በስጦታ የገጠር መሬት ማግኘት አይችልም በማለት ወስኗል።
አከራካሪው መሬት የሟች የተጠሪ አባት የነበረ መሆኑ በአመልካችም ያልተካደ ሲሆን በማስረጃም ተረጋግጧል። አመልካች ያቀረበችው ይርጋ መቃወሚያ መታለፈን በመቃወም ባቀረበችው ይግባኝ የባላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች እና ባለቤቷ ባልታወቀ መንገድ ከ1990ዎቹ አንስቶ አከራካሪውን መሬት ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ አመልካች ያቀረበችው የይርጋ መቃወሚያ ታልፍ አመልካች አከራካሪውን መሬት እንድትለቅ መወሰኑ አግባብነት የለውም ማለቱ ከተጠየቀው ዲኝነት አንፃር ተገቢ ሆኖ እያለ ፤ አከራካሪውን መሬት ሟች የአመልካች ባለቤት የያዘው በግዥ እና ሽያጭ ውል መሆኑ ታውቆ እያለ በይርጋ ይታገዲል መባለን በመቃወም ተጠሪ ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ጉዲዩን ያየው የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደቡብ ምድብ ቋሚ ችልት ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ባየው የደል መና ወረዲ ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር በይግባኝ ደረጃ መነሳቱ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329(1) ድንጋጌን የሚፃረር ሆኖ እያለ ፤ተጠሪ የገጠር መሬት ይዞታ ግዥ እና ሽያጭን የሚመለከት ክርክር እና ማስረጃ ባላቀረበበት አንድ የአመልካች ምስክር የአመልካች ባለቤት 750.00(ሰባት መቶ ሃምሳ) ሰጥቶ ከሟች የተጠሪ አባት በስጦታ አከራካሪውን መሬት አግኝቷል የሚል ምስክርነት ሰጥቷል በማለት መወሰኑ እንዱሁም የሰበር አጣሪ ችልቱም ስህተቱን ማረም ሲገባው በሥር ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ወድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችልት በመዝገብ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደቡብ ምድብ ቋሚ ችልት በመዝገብ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የባላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 8 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ውጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
No topics extracted.