ይግባኝ ባይ ያቀረበዉ የይግባኝ ማመልከቻ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.327 (2) መሰረት ከሥር ፍ/ቤቶች የመዚግብት ግልባጭ ጋር ለፍ/ቤት ተያይዝ ባልቀረበለት፣ መዜገቡ ቀጠሮ የተሰጠው መሆኑን በግልጽ ለይግባኝ ባይ መነገሩ ባልተረጋገጠበት ወይም ይግባኝ ባይ ቀጠሮን ባላወቀበት ሁኔታ በቀጠሮ ቀን ባለመቅረቡ ቅሬታዉን መስማት አለመቻለንና ቅሬታዉን የማሰማት መብትም መታለፈን በመጥቀስ ይግባኙ አያስቀርብም በማለትና በመሰረዜ ፍርድ ቤት የሚያሳልፈዉ ትዕዚዜ የህግ ድጋፍ የላለዉ አቶ ታዬ ሰይፈ መኩሪያ እና የሟች ወ/ሮ ስርጉት ተፈራ ወራሾች (4 ሰዎች)
No summary available.
ሚያዙያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ ……..አቶ ታዬ ሰይፈ መኩሪያ ------ የቀረበ የለም።
ተጠሪዎች፡ …….1. ሟች ወ/ሮ ስርጉት ተፈራ ወራሾች ከ2ኛ--4ኛ ተጠሪዎች 2. አቶ የሺጥላ ሰይፈ መኩሪያ 3. ወ/ሮ አባይነሽ ሰይፈ መኩሪያ የቀረበ የለም 4. አቶ ዓለማየሁ ሰይፈ መኩሪያ ይህ መዜገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የዉርስ ሀብት ይጣራልኝ ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዙህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.194893 በ27/2/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ ሟች አባቴ አቶ ሰይፈ መኩሪያ በሕይወት እያለ ከሟች አባቱ አቶ መኩሪያ እምሩ በዉርስ የተላለፈለትን በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 06 ዉስጥ የሚገኘዉ የቤት ቁጥር 128 ስፊቱ 1300 ካ.ሜ ይዝታ ላይ ያረፈዉን የመኖሪያ ቤት ያለዉ ሲሆን፣ በተከሳሾች መካከል በነበረን ጥብቅ የሆነ ቤተሰባዊ ግንኙነት ምክንያት ሳይከፊፈል የቆየዉን 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሽ ከሕግ ዉጭ በድብቅ ተከፊፍለዉ ወደ ስማቸዉ በማዝራቸዉ የዉርስ ሀብቱ ተጣርቶ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተከሳሾች በዙህ ክስ ላይ ባቀረቡት መቃወሚያ ከሳሽ ያቀረበዉ ክስ በይርጋ የታገደ ስለሆነ ዉድቅ እንዱደረግልን በማለት ተከራክረዋል፤ በአማራጭ ክርክር አከራካሪዉን ቤት 1ኛ ተከሳሽ የሰሩት፣ ግብር የሚገብሩበትና ካርታ በስማቸዉ ተሰጥቷል፤ ስፊቱ 875 ካ.ሜ ይዝታ ደግሞ በሉዜ ሕግ መሰረት ለኢንቨርስትመንት ለ4ኛ ተከሳሽ ከሚመለከተዉ አካል የተሰጠዉ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍ/ቤቶች ከሳሽ ያቀረበዉ ክስ በይርጋ ታገዶል በማለት ዉድቅ ያደረገ ቢሆንም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
በ29/10/2007 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን እንደገና በማየት ከሳሽ ያቀረበዉ የዉርስ ይጣራልኝ ክስ በተመለከተ ተከሳሾች ያነሱት የይርጋ መቃወሚያ በግራ ቀኙ መካከል ባለዉ ቤተሰባዊ ግንኙነት በመከባበር ምክንያት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.1853 (1) መሰረት ተቋርጧል ወይስ አልተቋረጠም? የሚለዉ በማስረጃ ተጣርቶ ዉሳኔ እንዱሰጥበት በማለት በመለሰዉ መሰረት የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን የሰዉ ምስክሮች በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በነበራቸዉ ዜምድና እና መከባበር መሰረት ይርጋዉ የተቋረጠ ነዉ በማለት መቃወሚያዉን ዉድቅ በማድረግ ዉርሱ ተጣርቶ እንዱቀርብ ትዕዚዜ ሰጥቷል።
ከዙህ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የዉርስ አጣሪ የሟችን የዉርስ ሀብት በማጣራት ሪፖርት እና ጉዲዩን በማጣራት አከራካሪዉ ቤት እና ይዝታ የሟች አቶ ሰይፈ መኩሪያ እና የወ/ሮ ስርጉት ተፈራ የጋራ ሀብት በመሆኑ፣ ግማሹ የ1ኛ ተከሳሽ (ወ/ሮ ስርጉት ተፈራ) እና ግማሹ ደግሞ ከሳሽን ጨምሮ ከ2ኛ--4ኛ ተከሳሾች 1/4ኛ ድርሻ አላቸዉ በማለት ሪፖርቱን በማጽደቅ ወስኗል።
ተከሳሾች በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር ባሳለፈዉ ዉሳኔ ከሳሽ ያቀረበዉ ክስ 1ኛ ተከሳሽ በተመለከተ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.1853 (1) መሰረት በይርጋ ቀሪ አልሆነም ተብል መወሰኑ ተገቢ ነዉ፤ ነገር ግን 2ኛ--4ኛ ተከሳሾችን በተመለከተ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.1853 (1) መሰረት ይርጋ የሚያቋርጥ ምክንያት መኖሩን ከሳሽ በማስረጃ ያላስረዲ በመሆኑ እነርሱን በተመለከተ የከሳሽ ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል፤ በከሳሽ እና በ1ኛ ተከሳሽ መካከል ያለዉን ክርክር ተጣርቶ ዉሳኔ እንዱሰጥበት በማለት የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በመሻሻል ለሥር ፍ/ቤት በመመለስ ወስኗል።
ከሳሽ በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የቀረበዉን ይግባኝ በትዕዚዜ በመሰረዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.337 መሰረት የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማሻር ነዉ።
የአሁን አመልካች ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታዬን አቅርቤ የፍ/ቤቱ ሬጅስትራር የሥር ፍ/ቤት መዜገብ እንዱመጣ ትዕዚዜ በመስጠት፣ ቅሬታዬ ለመስማት ለህዲር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ የሰጡኝ ሲሆን አመልካች በቀጠሮዉ ሲቀርብ መዜገቡ ለችልት ሳይቀርብ በመቅረቱ ችልት ጸሐፉ ሲጠይቅ መዜገቡ በ17/2/2013 ዓ.ም ለችልት እንደቀረበ እና በእኔ አለመቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ ለ27/2/2013 ዓ.ም ተሰጥቶ አሁንም አመልካች ባለመቅረቡ ይግባኙን የመስማት መብት ታልፍ መዜገቡ ተመርምሮ ይግባኙ አያስቀርብም ተብል መዜገቡ እንደተዘጋ መረዲት ተችሎል። ይህ ስህተት የተፈጠረዉ በሬጅስትራር ክፍል የተጨመረዉ ሰዉ ቀጠሮዉን እንዲዚባዉና ስህተቱ የፍ/ቤቱ መሆኑን መግለጫ ተሰጥቷል። በዙህ ረገድ በአመልካች ምክንያት የተፈጠረ ስህተት የለም። አመልካች ይህን በመጥቀስ ለፍ/ቤቱ አቤቱታ ያቀረብኩኝ ቢሆንም መዜገቡ ዉሳኔ ያገኘ በመሆኑ አቤቱታዉ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በመሆኑም የአመልካች ጥፊት ባልሆነ ምክንያት ቅሬታዬን የማሰማት መብቴ መታለፈ ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የማያስችልና የምስክሮችን ቃል መርምሮ መዜኖ ትክክለኛ ዉሳኔ የማግኘት መብቴን የሚያጣበብ ነዉ። የሥር ፍ/ቤት ከማስረጃ ምዜና አንጻር የምስክሮችን ቃል ዘርዜሬ ባቀረብኩት ቅሬታ መሰረት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሥር መዜገብ ሳይቀርብና ሳይመረመር በደፈናዉ ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነዉ። አመልካች ያቀረብኳቸዉ ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል አመልካች ከሁለም ተጠሪዎች ጋር የመከባበርና የመፈቃቀር ግንኙነት እንዲላቸዉ አረጋግጠዉ እያለ የሥር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1853 (1) መሰረት ይርጋ የተቋረጠዉ ከ1ኛ ተጠሪ በተመለከተ እንጂ ከላልች ተጠሪዎች ጋር አይቋረጥም በማለት ያሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ዉሳኔ እንዱሻርልኝ፣ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ እንዱጻናልኝ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት በዜርዜር አመልክቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት ታህሳስ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ አመልካች ባቀረበዉ ቅሬታ ይግባኛቸዉን ሳያሰሙ የታለፈት በቀጠሮ መሳሳት ምክንያት መሆኑን፣ ስህተቱም በሬጅስትራር የተፈጸመ እንጂ በችልት አለመሆኑን አረጋግጠዉ ያቀረቡ ቢሆንም ሬጅስትራር ጥፊት ፈጽመዉ ከተገኘ በአስተዲደር ከሚያስጠይቅ በቀር እንደ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተቆጥሮ በሰበር የሚታይ ጉዲይ አይደለም። የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረቡትን የምስክሮች ቃል በመመርመር በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል ይርጋዉን የሚያቋርጥ ምክንያት መኖሩን እንጂ ከ2ኛ--4ኛ ተጠሪዎች በተመለከተ አልተመሰከረም በማለት ዉሳኔ የሰጠ በመሆኑ ጉዲዩ የምስክሮች ቃል የማስረጃ ምዘና ሆኖ ባለበት አቤቱታዉ ያስቀርባል መባል አልነበረበትም። በመሆኑም የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ጠቅላይ ፍቤት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ አቤቱታዉ ዉድቅ ሆኖ ዉሳኔዉ እንዱጻናልን ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዜርዜር ተከራክሯል። አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር ሚያዙያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዙህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለበት ፣የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች ካቀረበዉ የይግባኝ ማመልከቻ ጋር የሥር ፍ/ቤት መዜገብ ተያይዝ ባልቀረበበት፣ የፍ/ቤቱ ሬጅስትራር የሥር መዜገብ እንዱቀርብ የሰጠዉ ቀጠሮ ሳይደርስ፣ ለአመልካች ቀጠሮዉ ተነግሮት ባላወቀበት በቀጠሮ ባለመቅረቡ የመሰማት መብቱ ታልፎል በማለት የይግባኝ ቅሬታዉን በትዕዚዜ በመሰረዜ ያሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዜበናል።
በዙህ መሰረት አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.231500 ጥር 22 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም የተጻፈ የይግባኝ ማመልከቻ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም የመ.ቁ.194893 በመክፈት፣ የፍ/ቤቱ ሬጅስትራር በ26/12/2012 ዓ.ም በተጻፈዉ ደብዲቤ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመ.ቁ.87486 እና የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት የመ.ቁ.231500 የሆኑት መዚግብት በ7/3/2013 ዓ.ም ከሆነዉ ቀጠሮ በፉት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 3ኛ ፍትሕ ብሓር ችልት እንዱላክልን፣ በቀጠሮ ላይ ከሆነ የመዜገቡ ግልባጭ እንዱላክልን በማለት መጠየቁን ያመለክታል። ይሁን እንጂ ተፈላጊዎቹ የሥር ፍ/ቤቶች መዚግብት ወይም የመዚግብቱ ግልባጭ መቅረቡን የሚያመለክት ነገር የለም።
ከሥር መዜገብ ማየት እንደሚቻለዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ17/2/2013 ዓ.ም በሰጠዉ ትዕዚዜ መዜገቡን መርምሮ ቅሬታዉን ለመስማት ለ27/2/2013 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ያመለክታል።
በዙህ መሰረት ፍ/ቤቱ በ27/2/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት አመልካች ባለመቅረቡ ቅሬታቸዉን መስማት ባለመቻለ ቅሬታዉን የማሰማት መብታቸዉ ታልፎል። በመቀጠል ፍ/ቤቱ የይግባኝ ቅሬታዉን በመመርመር ባሳለፈዉ ትዕዚዜ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በፍሬ ነገርም ሆነ በሕግ ረገድ ጉድለት ያልተገኘበት ስለሆነ ቅሬታዉን ባለመቀበል ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.337 መሰረት መዜጋቱን የትዕዚዘ ግልባጭ ያሳያል።
እንደሚታወቀዉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይግባኝ የሚባልበትን ትዕዚዜ፣ ብይን፣ ዉሳኔ ወይም ፍርድ ያሳለፈዉ እንደሆነ ይግባኝ ባይ ቅሬታዉን ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ማቅረብ የሚገባዉ የፍትሕ ብሓር ሥነሥርዓት ሕጉ በተዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በዙህ መሰረት የይግባኝ ማመልከቻ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.327 ሥር የተመለከቱትን ነገሮች አሟልቶ መቅረብ እንዲለበት ያመለክታል። በዙህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 327 (2) መሰረት ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ የሰጠዉ ፍ/ቤት የመዜገብና የፍርድ ግልባጭ ትክክል ግልባጭ ለመሆኑ ታትሞበትና ተፈርሞበት ከይግባኝ ማመልከቻ ጋር ተያይዝ ለይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት መቅረብ እንዲለበት ይደነግጋል። እንግዱህ በዙህ መልክ የይግባኝ ማመልከቻዉ በሕጉ የተመለከቱትን ነገሮች አሟልቶ የቀረበ እንደሆነ፣ የይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት ይግባኝ ባዩ ወይም ጠበቃዉ የሚያቀርቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ የመጀመሪያዉ ደረጃ ፍ/ቤት ፍርድ የሰጠበትን የመዜገብ ግልባጭ መርምሮ ፍርደ ጉድለት የላለበት መሆኑን ከተረዲዉ መልስ ሰጭዉን ሳይጠራ ይግባኙን ዘግቶ ይግባኝ ባዩን ማሰናበት እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.337 ተደንግጓል። በመሆኑም የይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት የይግባኝ ማመልከቻዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.327 መሰረት ተሟልቶ የሥር ፍ/ቤት መዜገብ ወይም የመዜገቡ ግልባጭ ጋር ተያይዝ ከቀረበለት በኋላና የይግባኝ ባዩን ቅሬታ በመስማት የይግባኝ ባይ ቅሬታን ከሥር ፍ/ቤት የመዜገብ ግልባጭ ጋር አገናዜቦ በመመርመር የሥር ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍሬ ነገርም ሆነ በሕግ ረገድ ጉድለት የላለበት መሆኑን የተገነዘበ እንደሆነ መልስ ሰጪዉን ማስቀረብ ሳያስፈግል የይግባኝ ማመልከቻዉን በመሰረዜ መዜገቡን ዘግቶ ይግባኝ ባዩን ማሰናበት እንደሚችል ያመለክታል። ስለሆነም የይግባኝ ሰሚዉ ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤት መዜገብ ወይም የመዜገቡ ግልባጭ ሳይቀርብለትና ለይግባኝ ባይ በግልጽ የተነገረዉን ቀጠሮ እያወቀ ካልቀረበ በስተቀር ይግባኝ ባዩን ስለቅሬታዉ ሳይሰማ ጉዲዩን መርምሮ የይግባኝ ማመልከቻዉን መሰረዜ የህግ ድጋፍ የላለዉ መሆኑን ያስገነዜባል።
በዙህ መሰረት አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያሳለፈዉ ፍርድ በመቃወም የይግባኝ ማመልከቻዉን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን የፍ/ቤቱ ሬጅስትራር የሥር ፍ/ቤቶች መዚግብት ወይም የመዚግብቱ ግልባጭ ከህዲር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ በፉት እንዱቀርብ የጠየቀ ሲሆን፣ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እነዙህ ተፈላጊዎቹ የሥር ፍ/ቤቶች መዚግብት ሳይቀርቡ፣ በፋጅስተራር በኩል ለአመልካች የተሰጠዉ ቀጠሮ ህዲር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ሳይደርስ፣ ችልቱ በጥቅምት ወር ዉስጥ ቀጠሮ መያዘ ለአመልካች በግልጽ የተነገረ መሆኑን የሚያመለክት ነገር ሳይኖር፣ መዜገቡ ለችልቱ በጥቅምት 17 እና 27 ቀን 2013 ዓ.ም ቀርቦለት አመልካች ባለመቅረቡ ቅሬታዉን መስማት አለመቻለን፣ ቅሬታዉን የመሰማት መብቱ በዙህ ምክንያት መታለፈን በመጥቀስ፣ የይግባኝ ማመልከቻዉን አያስቀርብም በማለት በመሰረዜ ትዕዚዜ መስጠቱን መዜገቡ ያሳያል። ከዙህ የሚንገነዘበዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበዉ የይግባኝ ማመልከቻ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.327 (2) መሰረት ከሥር ፍ/ቤቶች የመዚግብት ወይም የመዚግብቱ ግልባጭ ጋር ተያይዝ ባልቀረበለት፣ መዜገቡ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም ዉስጥ የተቀጠረ መሆኑን በግልጽ ለአመልካች መነገሩ ባልተረጋገጠበት፣ አመልካች ለህዲር 7 ቀን 2013 ዓ.ም እንዱቀርብ በሬጅስትራር በኩል ቀጠሮ ተሰጥቶት ከሄደ በኋላ ፍ/ቤቱ አመልካቹ ቀጠሮን ባላወቀበት ሁኔታ በቀጠሮ ባለመቅረቡ ቅሬታዉን መስማት አለመቻለንና ቅሬታዉን የማሰማት መብቱም መታለፈን በመጥቀስ ይግባኙን አያስቀርብም በማለት በመሰረዜ ያሳለፈዉ ትዕዚዜ ከፍ ሲል የተጠቀሱት የህግ ድንጋጌ የሚቃረን ጉዲይ ነዉ።
ሲጠቃለል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበዉን የይግባኝ ማመልከቻ በተመለከተ የሥር ፍ/ቤቶች መዚግብት ተያይዝ ባልቀረቡለት፣ ለአመልካችም የተነገረዉ ቀጠሮ ለህዲር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ሆኖ ሳለ፣ አመልካች በችልቱ የተያዘዉ ቀጠሮ በግልጽ ተነግሮት የሚያዉቅ መሆኑን የሚያመለክት ነገር በላለበት፣ አመልካቹ ወይም ጠበቃዉ ቅሬታዉን ባላሰማበትና የይግባኝ ቅሬታዉን ከሥር ፍ/ቤቶች መዚግብት ጋር ተገናዜቦ ባልተመረመረበት የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ የፍሬ ነገርም ሆነ የህግ ጉድለት የለዉም፣ የይግባኝ ማመልከቻዉ አያስቀርብም በማለት በመሰረዜ መዜገቡን ዘግቶ አመልካችን ማሰናበቱ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.194893 በ27/2/2013 ዓ.ም ያሳለፈዉ ትዕዚዜ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተዘጋዉን መዜገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ መሰረት የሥር ፍ/ቤቶች መዚግብት ወይም የመዚግብቱ ግልባጭ እንዱቀርብ በማድረግ አመልካች ያቀረበዉን ቅሬታ ለመስማት ለአመልካቹ በግልጽ የተነገረዉን ቀጠሮ በመስጠቱ፣ አመልካቹ ወይም ጠበቃዉ ስለይግባኝ ቅሬታዉ በመስማት፣ የይግባኝ ቅሬታዉን ከሥር ፍ/ቤቶች መዚግብት ጋር በመመርመር፣ የይግባኝ ማመልከቻዉ ያስቀርባል ወይም አያስቀርብም? በሚለዉ ጉዲይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ትዕዚዜ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዙህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤት ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዙህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዜገቡ ተዘግቷል።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.