ፍርድ ቤት በክስ አቤቱታ ላይ የተገለፀው ነገር የማያስከስስ ሆኖ ሲያገኘው፤ እንዱሁም በክሱ ላይ የተገለፀው ጉዲይ ከፍርድ ቤቱ ሥልጣን ውጪ ሲሆን የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብል መወሰኑ ከሳሽ ክሱን አሻሽልና አስተካክል እንዲያቀርብ የማይከለክልና ክሱ ተቀባይነት የለውም መባለ ወይም መሰረዙ ከሳሽ ክሱን አሻሽል እና የጎደለውን አሟልቶ በዚያው ነገር እንደገና ክስ ከማቅረብ የሚያግደው ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 231(1)፣ 232(2) እና 231 በድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይቻለው በቀደመው ክርክር የተያዘው ጭብጥ እና የፍሬ ነገር ክርክር ተመሳሳይ መሆኑና የተከራካሪ ወገኖች አንድነት በመኖሩ ብቻ ሳይሆን በፍሬ ጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠ መሆኑ ሉረጋገጥ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5(1) ኪሳራ ለማስከፈል የሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን መሰል የዲኝነት ጥያቄን ተቀብል ዲኝነት ላሰጥ የሚችል ላላ የዲኝነት አካል በላለበትና የፍርድ ቤት ስልጣንም በቀጥታም ይሁን በግልጽ ባልታገደበት ሁኔታ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሚወስን ስላለመሆኑ
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ ፀጋነው መንበሩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አራዲ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፊዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ሓኖክ አበበ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 30/09/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 27/05/2013 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 09/09/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲጀመር የአሁን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው አመልካች ባቀረቡት ክስ ላይ ተጠሪ የመጀመሪያ መቃወሚያዎችን አቅርቦ ተከራክሯል። የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ከሳሽ ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ ለማየት ፍርድ ቤቱ ስልጣን አለው? ወይስ የለውም? ከሳሽ ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለ ጭብጦችን ይዞ ውሳኔ ሰጥቷል።
በሰጠው ውሳኔ በዚህ መዝገብ የተጠየቀው የዲኝነት ጥያቄ አላግባብ የተወሰነ ግብርን ተንተርሶ የደረሰ ኪሳራ በሚል ኪሳራውን ለማስከፈል የቀረበ ሲሆን ግብሩ አላግባብ ተወስኗል ወይስ አልተወሰነም የሚለውን ለማየት ፍ/ቤቱ ስልጣን የላለው በመሆኑ ይህን ተከትል የደረሰ ኪሳራ ለመወሰን ቀድሞ ጥፊት ባልተረጋገጠበት ሉወሰን ስለማይችል ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም። በልላም በኩል ከሳሽ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ ተከሳሽ አላግባብ ግብር የወሰነብኝ በመሆኑ ኪሳራ ይከፈለኝ በሚል ክስ አቅርበው ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም ብል መዝገቡን የዘጋው በመሆኑና ውሳኔውን በይግባኝ ሳያሽሩ የገንዘብ መጠን ከፍ በማድረግ ጉዲዩን ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይዘው መቅረባቸው አግባብ አይደለም። የተጠየቀው ዲኝነት አንድ አይነት ሲሆን ፍ/ቤቱ ወደ ፍሬ ነገር ገብቶ ያላከራከረ ቢሆንም በተሰጠው ብይን ይግባኝ ከማለት በቀር የገንዘብ መጠን ጨምሮ ክስ ማቅረብ አግባብ ባለመሆኑ የከሳሽ ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ይግባኙ በፍ/ብሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ የጉዲት ካሳ ይከፈለኝ በሚል ስልጣኑ ለሆነው ከፍተኛ ፍ/ቤት ዲኝነት ጠየቅኩ እንጂ ግብር ይነሳልኝ አላልኩም፤ ተጠሪ ለአመልካች የከለከለኝን የተሻሻለ ውሳኔ ግልባጭ ህግ እንዱሰጥ ስለሚያስገድደው እና በአስተዲደራዊ አሰራር እስከ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን እና አዱስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ሄጄ መፍትሄ ያልተገኘ ስለሆነ እንዱሁም በአስተዲደራዊ ችግር መፍትሄ የሚያፈላልገው የኢትዬጵያ ህዝብ እንባ ተቋም ሳይቀር ጠይቆ ፈቃደኛ አልሆነም፤
አመልካች ያቀረብኩት አቤቱታ ጭብጥና ይዘት ሳይመረምር አመልካች የተጠሪዎች ጥፊት የተሻሻለ ውሳኔ መከልከላቸው እና ይህም ወደ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እና ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቅሬታዬን እንዲላቀርብ ምክንያት በመሆናቸው ለጉዲቱ ሀላፉነት ይወስዲለ የሚል ሲሆን ፍ/ቤቱ አመልካች የግብር ይነሳልኝ እና የግብር ስላት ይታይልኝ ዲኝነት የጠየቅኩ በማስመሰል የግብር ጉዲይ የማየት ስልጣን የለኝም ሲል የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። በልላ በኩል አንድ የክስ ጉዲይ በልላ ፍ/ቤት ታይቷል የሚባለው ፍ/ቤቱ ስልጣኑ ሆኖ ከሳሽ እና ተከሳሽን አከራክሮ ብይን የሰጠበት ጉዲይ ብቻ ሲሆን የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የጉዲዩን ስረ ነገር ሳያይ ስልጣኔ አይደለም ሲል ብይን በመስጠቱ አመልካች ክሴን አሻሽዬ ስልጣኑ ለሚፈቅድለት ፍ/ቤት ከማቅረብ የሚያግደኝ ህግ የለም።
የፋ/ጠ/ፍ/ቤትም የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የስረ ነገር ጉዲዩን ያለማየቱን እና ስልጣኑ ያለመሆኑን ጠቅሶ መዝገቡን እንደዘጋው ከሰጠው ብይን ማየት እየቻለ የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱሻር በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሉየን) ኪሳራ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የለኝም በማለቱ የሰበር አመልካች ለቀጣይ ፍ/ቤት የጉዲት ኪሳራ ይከፈለኝ ጥያቄ ማቅረባቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5 ድንጋጌን የሚያሟላ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 25/06/2014 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ አመልካች በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና በከፍተኛው ፍ/ቤት ያቀረበው ክስና የጠየቀው ዲኝነት በግልጽ እንደተቀመጠው የብር መጠን ከማበላለጥ ውጭ ግብር አላግባብ መወሰኑ ጋር ተያይዞ ለደረሰባቸው ካሳና ኪሳራ ይከፈለኝ የሚል በመሆኑ የሁለቱም ክርክሮች ሥረ ነገርና የተያዘው ጭብጥ ተመሳሳይ በመሆኑ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ጉዲዩ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ነው በማለት ክሱን ውድቅ ማድረጉ አግባብ ነው። አመልካች የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ብይን ፍ/ቤቱ የቀረበውን የ1,000,000 (አንድ ሚሉየን) ብር ካሳና ኪሳራ ጥያቄ ፍ/ቤቱ ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ የማየት ስልጣን የለኝም ብል ብይን የሰጠ አስመስል ፍ/ቤቱን ለማሳሳት አቀረቡ እንጂ በዚህ አግባብ ውሳኔ አልተሰጠም። አመልካች በስር ፍ/ቤቶች ያቀረቡት ዲኝነትና ጭብጥ ተጠሪ ግብር አላግባብ በመወሰን የንግድ ስራ እንዲቆም በማድረጉ ይህን ተከትል ለደረሰብኝ ኪሳራና ካሳ ሉከፈለኝ ይገባል ሲለ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሉየን) እና ለከፍተኛ ፍ/ቤት የብር 4,497,685.00 (አራት ሚሉየን አራት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት) የካሳ መጠኑን ጨምሮ ተመሳሳይ ዲኝነት በመጠየቅ ያቀረቡት ክስ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉነቀፍ አይገባም ተብል እንዱጸና በማለት ተከራክሯል። አመልካችም ክርክራቸውን አጠናክረው የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን በበኩላችን ለሰበር ችልቱ የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 231(1) ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለው ፍርድ ቤቱ በክሱ አቤቱታ ላይ የተገለፀው ነገር የማያስከስስ ሆኖ ሲያገኘው፤ እንዱሁም በክሱ ላይ የተገለፀው ጉዲይ ከፍርድ ቤቱ ሥልጣን ውጪ መሆኑን ሲረዲው የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብል በመወሰን ሉመልስ ይችላል። ነገር ግን በዚህ መልኩ መወሰኑ ከሳሽ ክሱን አሻሽልና አስተካክል እንዲያቀርብ የሚከለክል አይደለም። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 232(2) በግልጽ እንደተመለከተው በቁጥር 231 በተመለከተው መሰረት ክሱ ተቀባይነት የለውም መባለ ወይም መሰረዙ ከሳሽ ክሱን አሻሽል እና የጎደለውን አሟልቶ በዚያው ነገር እንደገና ክስ ከማቅረብ የሚያግደው አይሆንም።
በልላም በኩል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5(1) በግልጽ እንደተመለከተው በድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይቻለው በቀደመው ክርክር የተያዘው ጭብጥ እና የፍሬ ነገር ክርክር ተመሳሳይ መሆኑና የተከራካሪ ወገኖች አንድነት በመኖሩ ብቻ ሳይሆን በፍሬ ጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠ መሆኑ ሉረጋገጥ ይገባል።
በተያዘው ጉዲይ የፋደራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን ከመዝጋቱ በቀር በፍሬ ጉዲይ ላይ የተሰጠ ውሳኔ አለመኖሩ ግራ ቀኙን አላከራከረም።
ይህ ሆኖ እያለ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠየቀው ዲኝነት አስቀድሞ ከቀረበው ጋር አንድ አይነት ነው፤ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ወደ ፍሬ ነገር ገብቶ ያላከራከረና በፍሬ ጉዲዩ ውሳኔ ያልሰጠ ቢሆንም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው በማለት ክሱን ውድቅ ማድረጉ ከፍ ሲል የተገለፀውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5(1) ትክክለኛ ይዘት መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ውሳኔው ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ይህን ሳያርም ማለፈ የሚነቀፍ ነው።
በልላም በኩል የስር ፍርድ ቤት የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ አላግባብ የተወሰነ ግብርን ተንተርሶ የደረሰ ኪሳራ ለማስከፈል የቀረበ ቢሆንም ኪሳራውን ለማስከፈል ግብሩ አላግባብ ተወስኗል ወይስ አልተወሰነም የሚለውን ለማየት ፍ/ቤቱ ስልጣን የላለው በመሆኑ ይህን ተከትል የደረሰ ኪሳራ ለመወሰን ቀድሞ ጥፊት ባልተረጋገጠበት ሉወሰን ስለማይችል ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለትም ወስኗል። ይሁንና ለጉዲቱ ተጠሪ ሀላፉነት አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ጭብጥ የግራቀኙ ዝርዝር ክርክርና ማስረጃ ከቀረበ በኋላ የሚወሰን ከመሆኑም በላይ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ የግብር ስላትን መሰረት አድርጎ እንዱያርም የቀረበ አይደለም። ኪሳራ ለማስከፈል የሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን መሰል የዲኝነት ጥያቄን ተቀብል ዲኝነት ላሰጥ የሚችል ላላ የዲኝነት አካል በላለበትና የፍርድ ቤቱ ስልጣንም በቀጥታም ይሁን በግልጽ ባልታገደበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት መወሰኑ የሚነቀፍ ነው።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤቶች ክሱን ውድቅ በማድረግ ያሳለፈት ውሳኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 27/05/2013 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 09/09/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ቀሪውን ክርክር መርምሮ ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 341/1/ መሰረት መልሰናል። የውሳኔው ግልባጭ ይተላለፍ።
በዚህ ችልት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.