የአክሲዮን ማህበር አባላት የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎች ሳይከፍለ በመቅረታቸዉ ከማህበር አባልነታቸዉ እንዱወጡ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የወሰነዉ ዉሳኔ እንዱሰረዜላቸዉ ክስ አቅርበዉ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ሳለ፣ በፍ/ቤት ክርክር የማህበሩ አባላት ከአባልነት ይሰረዘ በማለት ማህበሩ የሚያቀርበዉ አቤቱታ ዲግመኛ የቀረበ ጉዲይና የክርክር አመራር ጉድለት ያለበት ነዉ የሚባል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 (1)
No summary available.
ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካቾች፡ ……1. አቶ ደለሳ ጅማ -- ቀረቡ 2. አቶ ጌቱ አበበ ቱጂ -- ቀረቡ 3. አቶ አዲነ ነጊያ ደንቦባ 4. አቶ ጌቱ ይመር ዋኬኔ አልቀረቡም 5. አቶ ሸምሱ ሲፊ ሁሴን 6. አቶ በድሩ ሃምዚ ቡሽራ -- ቀረቡ 7. አቶ ሃይለ ቤኛ ጉደታ -- አልቀረቡም 8. አቶ ተሾመ ደምሴ ምህረቱ -- ቀረቡ 9. አቶ ከማል ሽፊ እንቁ 10. አቶ ዘይኑ አሉ አማን አልቀረቡም 11. አቶ ተሻለ ፍቃደ ናድም -- ቀረቡ 12. አቶ ጸጋዬ ጉደታ አለጋ 13. ወ/ሮ ቦጋለች ደሴ አርጌ አልቀረቡም ተጠሪ፡- …ኮልፋ ቅደስ ራጉኤል አዱስ ሕይወት አክስዮን ማህበር-- ጠበቃ ሲሳይ መኮንን - ቀረቡ ይህ መዜገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የማህበር አባልነት ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሾች፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ፣ በዙህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑት እነ አቶ አምሳለ ባህሩ የሥር ጣልቃ ገቦች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዙህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካቾች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.269920 ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዚዜ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ ተከሳሾች የከሳሽ ማህበር አባላት ሁኖ የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎችን ባለመፈጸማቸዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ከማህበሩ እንዱሰናበቱ የወሰነ ሲሆን፣ ተከሳሾች ይህን ዉሳኔ ለማሰረዜ ክስ አቅርበዉ ዉድቅ የሆነባቸዉ ሲሆን፣ በዙህ ዉሳኔ መሰረት ለማስፈጸም ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ ክፍያ ያልከፈለ አባላት ክፍያዉንና ቅጣቱን በሁለት ወራት ዉስጥ እንዱከፍለ፣ ይህ ካልሆነ ሱቆቻቸዉ ወደ ማህበሩ በማስገባት ክፍያዉ ተሳስቦ እንዱከፈላቸዉ የተወሰነ በመሆኑ፣ ተከሳሾች ዉሳኔዉን ለማሰረዜ ክስ አቅርበዉ ዉድቅ የሆነባቸዉ ስለሆነ፣ ተከሳሾች አልከፈሎቸዉም ያለዉን ክፍያዎች በመዘርዘር፣ በጠቅላላ ጉባኤዉ ዉሳኔ መሰረት ከማህበሩ አባልነት እንዱወጡ ወይም እንዱሰረዘ እንዱወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተከሳሾች በዙህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም ተከሳሾች ከማህበሩ አባልነት እንዱሰረዘ በማለት የወሰነዉ ሥራ አልዋለም፤ ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም የተወሰነዉ ዉሳኔ የቀደመዉን ዉሳኔ የሚሽር ነዉ፤ ተከሳሽ በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔ እንጂ በማስታወቂያ ከማህበሩ ሉወጡ እንደማይገባ፤ ከሳሽ የጠቀሳቸዉ ክፍያዎች የተከፈለትን ክፍያዎችንና የተዋጡ መዋጮዎችን ታሳቢ ያላደረገ ነዉ፤ ከማህበሩ ጋር በነበረዉ ዉይይት የማህበሩ ሂሳብ በባለሙያ ተጣርቶ እዲ ያለባቸዉ እንዱከፍለ፣ ክፍያዎችን መክፈል ያልቻለትን ደግሞ ማህበሩ ትብብር አድርጎላቸዉ ከአበዲሪ ተቋማት ብድር ወስደዉ እንዱከፍለ ስለተባለ በዙህ አግባብ ትብብር እንዱደረግልን፤ ተከሳሾች ከማህበሩ ሉወጡ ይገባል የሚባል ከሆነ እንኳን የማህበሩ ሂሳብ ኦዱት ተደርጎ ድርሻችን ተከፍልን ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ከዙህ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር ባሳለፈዉ ዉሳኔ የከሳሽ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ የማህበሩ አባላት የሆኑት ተከሳሾች የግንባታና የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍለ በወሰነዉ መሰረት መክፈል ያለመቻላቸዉን ተከሳሾችም ያመኑ ጉዲይ ሲሆን፣ ተከሳሾች በዙህ አግባብ መክፈል ባለመቻላቸዉ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነ ቢሆንም በዙህ መሰረትም መክፈል ስላልቻለ፣ ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ በሁለት ወራት ጊዛ ዉስጥ እንዱከፍለ ካልሆነ ሱቆቻቸዉ ወደ ማህበሩ ገቢ ተደርገዉ ያላቸዉ ሂሳብ ተሰልቶ እንዱከፈላቸዉ የተወሰነ ሲሆን፣ ተከሳሽ በዙህ ዉሳኔ መሰረትም ግዳታቸዉን አልተወጡም። ተከሳሾች እነዙህን የጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔዎችን ለማሻር ክስ አቅርበዉ ዉድቅ የተደረገባቸዉ መሆኑን በግራ ቀኙ የታመነ እና በማስረጃም የተረጋገጠ ጉዲይ ነዉ፤ ተከሳሾች አሁን የጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔ ዉድቅ ነዉ በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለዉም፤ የጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔ ለማሻር የሚያስችል የሕግ መሰረት የለም፤ ተከሳሾች የሚጠበቅባቸዉን ግዳታቸዉን ሙለ በሙለ ያልተወጡ በመሆናቸዉ ከማህበሩ ሲወጡ ሉከፈላቸዉ ስለሚገባዉ ክፍያ ማጣራት ስለሚኖር በዙህ አግባብ መብታቸዉ የሚጠበቅ በመሆኑ በዙህ ደረጃ ሂሳብ ማጣራቱ ተገቢ አይደለም። በዙህ መሰረት ተከሳሾች በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔዎች መሰረት ግዳታቸዉን ሉወጡ ባለመቻላቸዉ ከማህበሩ አባልነት እንዱወጡ የተወሰኑ በመሆኑና ዉሳኔዉን የሚያሽር በቂ ምክንያት ባለመገኘቱ በዉሳኔዉ መሰረት ተከሳሾች ከማህበር አባልነታቸዉ እንዱወጡ በማለት ወስኗል።
ተከሳሾች በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን በትዕዚዜ በመሰረዜ የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዙህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካቾች በ10/1/2014 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የተጠሪ ማህበር አመልካቾች ክፍያ ስላልከፈለ ከማህበሩ አባልነታቸዉ እንዱወጡ በማለት ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም ባደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ የወሰነ ቢሆንም ይህን ለመወሰን ስልጣን የለዉም፤ ስልጣን አለዉ ቢባል እንኳን አሁን ለፍ/ቤት አመልካቾች ከአባልነት ይሰረዘ በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ ዲግመኛ የቀረበ ጉዲይና የክርክር አመራር ጉድለት ያለበት ነዉ፤ አመልካቾች የተለያዩ ክፍያዎችን ስንከፍል የቆየን ቢሆንም ይህን የተከፈለዉን ክፍያ በሂሳብ ባለሙያ እንዱጣራ ሳያደርግ የማህበሩን መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 3 (ለ) በመጣስ ከማህበር አባልነት እንድንሰናበት የሰጠዉ ዉሳኔን ፍ/ቤቱም በመቀበል ዲግመኛ ከማህበር አባልነት ተሰናብታችኋል በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። በመሆኑም አመልካቾች ከማህበሩ አባልነት የሚያስወጣን ምንም የህግ ምክንያት የለም ተብል እንዱወሰንልን፤ አመልካቾች ከማህበሩ ሉወጡ ይገባል የሚባል ከሆነ ለአመልካቾች ሉከፈለን የሚገባዉ የገንዘብ መጠን የማህበሩ ሀብት ተሰልቶ በከፈልነዉ የገንዘብ መጠን ሉከፈለን ይገባል በማለት በዜርዜር አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣የአሁን አመልካቾች ከማህበሩ አባልነት እንዱሰናበቱ የሥር ፍ/ቤት የወሰነበትን አግባብ ከመተዲደሪያ ደንብና አግባብነት ካላቸዉ የንግድ ህግ ድንጋጌዎች አንጻር ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዘዘዉ መሰረት መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት ባጭሩ፡ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካቾች የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎችን ባለመክፈላቸዉ የተጠሪ ማህበር ከአባልነት እንዱሰናበቱ የወሰነዉ ዉሳኔ ተገቢ ነዉ በማለት አመልካቾች ከማህበሩ አባልነት እንዱወጡ ያሳለፈት ዉሳኔ ከሕግ የሚቃረን ስላልሆነ፣ የአመልካቾች ቅሬታ ዉድቅ እንዱደረግልን በማለት በዜርዜር ተከራክሯል። አመልካቾች በ23/7/2014 ዓ.ም በተጻፈ የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸዉን በማጠናከር ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካቾች የተጠሪ ማህበር አባላት መሆናቸዉ፣ አመልካቾች የግንባታ እና የተለያዩ ክፍያዎችን መክፈል ባለመቻላቸዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም ባሳለፈዉ ዉሳኔ ከማህበሩ አባልነት እንዱሰናበቱ መወሰኑን፤ ይህን ዉሳኔ ለማስፈጸም ሲባል የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ባሳለፈዉ ዉሳኔ አመልካቾች የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎች በሁለት ወራት ጊዛ ዉስጥ እንዱከፍለ፣ ይህ ካልሆነ ሱቆቻቸዉ ወደ ማህበሩ ገቢ ተደርጎ ያላቸዉ ሂሳብ ታስቦ እንዱከፈላቸዉ በማለት መወሰኑን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። አመልካቾች በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔ መሰረት ግዳታቸዉን መወጣት ያለመቻላቸዉን በሥር ፍ/ቤት በማስረጃ ከመረጋገጡም በላይ አመልካቾችም ያመኑት ጉዲይ መሆኑን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያመለክታል።
በልላ በኩል አመልካቾች እነዙህ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔዎች ከሕግ ዉጭ የተወሰኑ መሆናቸዉን በመጥቀስ ዉሳኔዎቹ እንዱሰረዘላቸዉ ለፍ/ቤት ክስ አቅርበዉ ክሳቸዉም ዉድቅ የሆነባቸዉ መሆኑን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያስገነዜባል።በመሆኑም አመልካቾች የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎች ሳይከፍለ መቅረታቸዉን መነሻ በማድረግ ከማህበር አባልነታቸዉ እንዱወጡ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የወሰነዉ ዉሳኔ እንዱሰረዜላቸዉ ክስ አቅርበዉ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ሳለ፣ አሁን ጠቅላላ ጉባኤ ያሳለፈዉ ዉሳኔ ከመተዲደሪያ ደንብና ከሕግ ዉጭ ነዉ በማለት ያቀረቡት ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5 (1) መሰረት ተቀባይነት የለዉም። አመልካቾች ግዳታቸዉን ባለመወጣታቸዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ከማህበር አባልነት እንዱሰናበቱ ያሳለፈዉን ዉሳኔ የሥር ፍ/ቤቶች በመቀበል አመልካቾች ከማህበር አባልነት እንዱወጡ ወይም እንዱሰረዘ የወሰነዉ የሚነቀፍበት የህግ አግባብ የለም። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 (3፣ ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 (1) መሰረት ከተሰጠዉ ስልጣን አንጻር አመልካቾች ከማህበር አባልነት እንዱሰናበቱ የተወሰነዉን ዉሳኔ በተመለከተ ያቀረቡት ቅሬታ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን የሚያመለክት ባለመሆኑ ቅሬታቸዉ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ነገር ግን አመልካቾች ከማህበር አባልነት እንዱወጡ እስከተወሰነ ድረስ፣ ሉከፈላቸዉ የሚገባዉ የገንዘብ መጠን ምን ያህል ነዉ? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። የተጠሪ ማህበር ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ አመልካቾች መክፈል ያለባቸዉን ክፍያዎች በሁለት ወራት ጊዛ ዉስጥ ሉከፍለ እንደሚገባ ይህ ካልሆነ ሱቆቻቸዉ ወደ ማህበሩ ገቢ ተደርገዉ ያላቸዉ ሂሳብ ተሰልቶ ሉመለስላቸዉ እንደሚገባዉ መወሰኑን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። ከዙህ መረዲት እንደሚቻለዉ አመልካቾች ከማህበሩ ሲወጡ ያላቸዉ ሂሳብ ተጣርቶ ሉከፈላቸዉ የሚገባቸዉ ገንዘብ መኖሩ ከተረጋገጠ እንደሚመለስላቸዉ ነዉ። የሥር ፍ/ቤቶች አመልካቾች ከማህበሩ አባልነት እንዱወጡ ወስኖ ሲያበቃ ሉከፈላቸዉ የሚገባዉን ክፍያ በተመለከተ ከማህበሩ ሲወጡ ሂሳብ ማጣራቱ ስለማይቀር መብታቸዉ በዚ አግባብ የሚጠበቅ ይሆናል በማለት ያሳለፈዉ ዉሳኔ ከማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም። ይህንን ደግሞ የፍትሀብሓር ሥነሥርዓት ሕጉ በዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት አጣርቶ መወሰን ይገባል። የሥር ፍ/ቤት የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ያሳለፈዉ ዉሳኔ የሚሻርበት በቂ ምክንያት የለዉም ያለዉ ተገቢ ቢሆንም፣ ዉሳኔዉን በከፉል በመቀበል ከፉለን ደግሞ ባለመቀበል ለአመልካቾች የሚከፈለዉ ክፍያ ካለ አሁን ተሰልቶ ሉከፈላቸዉ እንደሚገባ መወሰን ሲገባዉ አጥጋቢ ያልሆነ ምክንያት በመጥቀስ የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካቾች የሚጠበቅባቸዉን ግዳታቸዉን ባለመወጣታቸዉ ከማህበር አባልነት ሉወጡ ወይም ሉሰረዘ ይገባል በማለት ያሳለፈት ዉሳኔ ተገቢ ቢሆንም ከማህበሩ አባልነት ሲወጡ ግን የሚከፈላቸዉ ክፍያ ካለ ተጣርቶ መወሰን ሲገባዉ ሳይወሰን መታለፈ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.276498 ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ያሳለፈዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.269920 ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዚዜ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት የተዘጋዉን መዜገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ ሐተታዉ በተመለከተዉ አግባብ አመልካቾች ከማህበሩ አባልነታቸዉ እንዱወጡ ወይም እንዱሰረዘ የተወሰነዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለአመልካቾች ሉከፈላቸዉ የሚገባቸዉ የገንዘብ መጠን በሂሳብ ባለሙያ ተጣርቶ እንዱቀርብ በማድረግ፣ ግራ ቀኙ ሪፖርቱ ላይ አስተያየታቸዉን እንዱሰጡ በማድረግ፣ እንዱሁም ጉዲዩን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ሁለ በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 (1) መሰረት ተመልሶለታል።
የሥር ፍ/ቤቶች አመልካቾች ከተጠሪ ማህበር አባልነት እንዱወጡ ወይም እንዱሰረዘ በማለት ያሳለፈት የዉሳኔ ክፍል አልተነካም ጸንቷል።
የዙህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዙህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዜገቡ ተዘግቷል።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.