ፍርድ ቤት ተከራካሪ ወገኖች በዝርዝር ባላቀረቡት ወይም በግልጽ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ መስጠት የማይችልና በተከራካሪ ወገን ያልተነሳን መከራከሪያ ፍርድ ቤት በራሱ አንስቶ ውሳኔ የሚሰጥ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2)
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ አሚን ሙመድ አሉ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ኢብሳ አህመድ ሙመድ - ጠበቃ ዱንቃ ደረጀ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በቀን 10/02/2014 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 25/01/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የጀመረው በስር የሀሮማያ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ባቀረቡት ክስ ነው።
ተጠሪ በቀን 22/04/2013 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ በሀሮማያ ወረዲ ኢፊ ኦሮሚያ አሉ ወዲይ ቀበላ ውስጥ የእርሻ መሬት ይዞታ የሆነ 26 ከተራ ጫት በላዩ ላይ የሚገኝ የጫትና የእህል መሬት የሆነ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰ 1 ጥማድ መሬቴን ተከሳሽ ዘመዳ ስለሆነ በቀን 21/10/2009 ዓ.ም በተደረገ ስምምነት በጫቱ ውስጥ እህል ዘርቶ የጫቴን ስርም ኮትኩቶልኝ ከጫቱ ላይ የሚገኘውን ምርት ለእኔ ገቢ እንዱያደርግልኝና እሱም እህል ዘርቶ ምርቱን እንዱወስድ ተባብለን እንደ አካባቢያችን ባህል በሰው ምስክሮች ዘንድ በቃል ውል ተዋውለን መሬቴን ሰጥቼዋለሁ። ነገር ግን ከተሰጠው ቀን ጀምሮ እንደ ውላችን በእምነት ከጫቱ የሚገባልኝን እኩል እስከ 2013 ዓ.ም ሉሰጠኝ አልቻለም፤ ለራሱ ጫቱን ሽጦ እየተጠቀመበት ይገኛል። ስለሆነም ድርሻየን በበጠቅላላው 48,000.00 (አርባ ስምንት ሺህ) ብር እንዱከፍለኝና መሬቱን እንዱለቅልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የስር ተከሳሽ በበኩላቸው በቀን 03/05/2013 ዓ.ም በሰጡት መልስ ክሱ የሀሰት ነው፤ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት ተከሳሽ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ 15 አመት ሙለ አርሼ የምጠቀምበት፣ ልጆቼን ምራዝ አውጥቼበት የሚገኝ ስለሆነ ከሳሽ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው። መሬቱን አስመልክቶ የእርቅ ሽማግላዎች ውጤት መልስ ባልሰጠሁበት ከእኔ ኋላ ተጽፍ የተሰጠ ስለሆነ በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 16(1) መሰረት ተቀባይነት የለውም፤ ስለሆነም የቀረበው የሀሰት ክስ ውድቅ ሆኖ ወጪና ኪሳራዬ ተከፍልኝ ልሰናበት በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና አማራጭ መልሳቸውን አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱ የመቃወሚያ ክርክራቸውንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ እንዱሁም ተጨማሪ ማስረጃዎችንም ከሰማ በኋላ ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ ከሳሽ በክሱ በጠቀሰው መልኩ በተደረገ ስምምነት መሬቱን ማስተላለፈና ካስተላለፈው 4 ዓመት ብቻ ስለመሆኑ በማስረጃዎቹ ሚዛን በሚደፊ መልኩ አላስረዲም፤
ይልቁንም ተከሳሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት ይዞ መጠቀም የጀመረው ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን በቂና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ በማስረጃዎቹ እንዱሁም በተጨማሪ በቀረቡ ማስረጃዎች ተረጋግጧል። ተከሳሽ ለክርክር ምክንያት የሆነውን ይዞታ ይዞ መጠቀም ከጀመረ 15 አመት በላይ መሆኑን በከሳሽ ምስክሮችና በቀረቡ ተጨማሪ ምስክሮች ተረጋግጦ ስለሚገኝ በደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 32 መሰረት ከ12 አመት በኋላ ከሳሽ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ከሳሽ ይግባኝ ለሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ክርክር እና ማስረጃውን መርምሮ ተከሳሽ መሬቱን ይዞ ከ15 ዓመት በላይ እየተገለገለበት መሆኑ በማስረጃዎቹ ስለተረጋገጠ የስር ፍርድ ቤት ክሱን በይርጋ ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነው በማለት ውሳኔውን አፅንቷል። ከዚህ ቀጥል ይግባኙ የቀረበለት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ የስር ፍርድ ቤት ከግራ ቀኙ ምስክሮች በተጨማሪ የመሬቱን ጉዲይ በቅርበት የመሬቱ አዋሳኝ ባለይዞታዎችን በተጨማሪ ማስረጃነት ሰምቶ የሰጠው ውሳኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዟል።
ከሳሽ በመጨረሻ ቅሬታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዋል። የክልለ ሰበር ችልት በበኩለ ጉዲዩን መርምሮ መሬቱ ከከሳሽ እጅ ወጥቶ በተከሳሽ እጅ ሉገባ የቻለው ከሳሽ በመቸገሩ ምክንያት ተከሳሽ ገንዘብ ሰጥቶት ነው፤ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40(3) በይዞታ መሬት ላይ ግዥና ሽያጭ መዋዋል እንደማይቻል ተደንግጓል። በመሆኑም አንድ ሰው የእርሻ ይዞታ መሬት በህግ መሰረት ያገኘ እንደሆነ እንጂ ከህገ መንግስት ተቃራኒ በሆነ መንገድ ያገኘ እንደሆነ የይርጋ ጊዜ እንደ መጀመሪያ ተቃውሞ ቀርቦ ክሱ ውድቅ መሆን ስለማይችል የስር ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ ይዞታውን በህጋዊ መንገድ እንዲገኘ በመውሰድ ከሳሽ ያቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ሽሯል። አከራካሪውን መሬት ተከሳሽ ለከሳሽ እንዱለቅ በማለትም በዚያው ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ለክርክር ምክንያት የሆነውን መሬት ተጠሪ በራሱ ፍላጎት በ1995 ዓ.ም ሰጥቶኝ ያለምንም ተቃውሞ ከ15 አመት በላይ ስጠቀምበት የቆየሁት መሆኑን አረጋግጬ እያለ እንዱሁም የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ አንድ ሰው ለ3ኛ ወገን አሳልፍ ይዞታውን ከሰጠ መልሶ ለመቀበል እንደማይችል አስገዲጅ ውሳኔ ሰጥቶ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ ባላነሳው ክርክር ገንዘብ ወስድ መሬቱን ወሰደ በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው። አመልካች ለተጠሪ ብር የሰጠሁት በወንጀል ስለተከሰሰ ልረዲው እንጂ ከመሬቱ ጋር በተገናኘ አይደለም፤ ይህ ስለመሆኑም ምስክሮች ያረጋገጡት ጉዲይ ሲሆን ተጠሪም ብር ስለሰጠኝ መሬቱን ወሰደብኝ ብል አልተከራከረም፣ ክስም አላቀረበም። ይልቁንም ተጠሪ ይዞታውን ለእኔ መስጠቱን ራሱ አምኖ ተከራክሯል። በክሱ ላይ ጫቱን ለራሴ ገቢ እንዱያደርግ ፤ ጫቱ ስር የሚዘራው እህል ደግሞ ለራሱ እንዱጠቀም ተስማምተናል ብል ያቀረበውን ክስ በተመለከተ በጫት ስር ምንም አህል እንደማይዘራ የታወቀ ነው። በመሆኑም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ ያላነሳውን በራሱ ተነሳሽነት ጭብጥ በመያዝ የሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተሽሮ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት፣ የከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱሁም የወረዲ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱጸናልኝ በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርመሮ አከራካሪው መሬት በሽያጭ የተላለፈ ስለመሆኑ በስር ወረዲ ፍ/ቤት ሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የተደረገ ክርክር ሳይኖር የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሽያጭ ያገኘው መሆኑ ተረጋግጧል በማለት የወሰነበትን አግባብነት ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 25/06/2014 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ በስር ወረዲ ፍ/ቤት የቃል ክርክር ስናደርግ ተከሳሽ እንደሚለትም ቢሆን ህገ ወጥ ውል በመሆኑ በይርጋ አይታገድም በማለት አንስቼ ስለተከራከርኩ በስር ፍ/ቤቶች ያልተነሳ ክርክር አይደለም፤ ፍ/ቤቶችም ህገ መንግስቱ እንዲይጣስ የማረጋገጥ ሀላፉነት ስላለባቸው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም፤
የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በሰጠው አስገዲጅ ትርጉም አንድ ሰው የተወሰነ ገንዘብ ተቀብል የእርሻ መሬቱን ላልተወሰነ ግዜ ወይም በዘለቄታዊነት በውል ለላላ ሰው ቢያስተላልፍ የህገ መንግስቱን አንቀጽ 40(3) የሚጥስና ከአዋጅ ቁጥር 456/97 ጋር የሚቃረን በመሆኑ ውለ ህገ ወጥ ነው በማለት አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። የገጠር እርሻ መሬት መሸጥ ወይም መለወጥ ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ በይርጋ ሳይገደብ በማንኛውም ግዜ ሉፈርስና መሬቱ እንዱመለስ መጠየቅ እንደሚቻል የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም አመልካች ገንዘብ ሰጥቶ መሬቱን መውሰደ በልላ ቋንቋ መግዛቱ ስለሆነ ህገ ወጥ በመሆኑ የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የለውም ውሳኔው እንዱጸና በማለት ተከራክረዋል።
አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን ለሰበር ችልቱ ያያዘውን ጭብጥ መሰረት በማድረግ የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደሚታወቀው መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የመንግስትና የህዝብ ሀብት መሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 40(3) ስር ተደንግጓል። መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት ሆኖ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር የመሬት ባለይዞታ የመሆንና በመሬት የመጠቀም ከይዞታው ያለመፈናቀል መብት ያለው መሆኑም በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40(4) ስር በግልፅ ተደንግጓል። የአርሶ አደሮች የመሬት ባለይዞታ የመሆን፤
በመሬት የመጠቀምና ከይዞታቸው ያለመፈናቀል መብት ህጋዊና ተግባራዊ ለማድረግም የፋዳራል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 እና በኦሮሚያ ክልልም አዋጅ ቁጥር 130/99 እና ማስፈፀሚያ ደንቡ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
በአንፃሩ ክርክሩ የፍትሐ ብሄር በመሆኑ ሉመራ የሚገባውም በፍትሐብሄር ሥነ ስርዓት ህጉ አግባብ ነው። ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2) ግልጽ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለውም የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራከራዎቹ ወገኖች በዝርዝር ባላቀረቡት ወይም በግልጽ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ መስጠት አይችልም። ስለሆነም በተከራካሪ ወገን ያልተነሳን መከራከሪያ ፍርድ ቤቱ በራሱ አንስቶ እንዱወስን አይጠበቅም።
በተያዘውን ጉዲይ ተጠሪ በወረዲው ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በመቸገሬ ምክንያት አመልካች ገንዘብ ሰጥቶኝ በሽያጭ ውል መሬቱን አስተላልፋያለሁ፤ ስምምነታችን ህገ ወጥ ስለሆነ ቀሪ ተደርጎ መሬቴን ይመልስልኝ በማለት ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ የለም። በዚህ መልኩ ክርክር በቃልም ቢሆን ስለማቅረባቸው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አያሳይም። ይልቁንም ተጠሪ ያቀረቡት ክስና የጠየቁት ግልፅ ዲኝነት በተጠሪና አመልካች መካከል በቀን 21/10/2009 ዓ.ም በተደረገ ስምምነት አመልካች በጫት ውስጥ እህል ዘርቶ የጫቱን ስር እየኮተኮተ ከጫቱ ላይ የሚገኘውን ምርት ለእኔ ገቢ እንዱያደርግልኝና እሱም የእህል ምርቱን እንዱወስድ ስምምነት አድርገን ነበር እንደ ውላችን ከጫቱ የሚገባኝን እስከ 2013 ዓ.ም ሉሰጠኝ አልቻለም፤ ስለሆነም የድርሻዬን ግምት 48,000.00 (አርባ ስምንት ሺህ) ብር ከፍልይልቀቅልኝ የሚል ነው። አመልካች እንደዚህ አይነት ስምምነት አለመኖሩን ክደው ተከራክረዋል።
ተጠሪ ከፍ ሲል የተገለፀውን ፍሬ ነገር መሰረት አድርገው ክስ ቢመሰርቱም ፍሬ ነገር ለማጣራትና ማስረጃ ለመመዘን በህጉ ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ በክሱ በጠቀሰው መልኩ ከአመልካች ጋር በተደረገ ስምምነት መሬቱን ስለማስተላለፈቸው በማስረጃ አለማስረዲታቸውን፤ ከዚህ ይልቅ አመልካች ያለተቃውሞ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት ይዘው ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ እየተጠቀሙበት መሆኑ በማስረጃ መረጋገጡንና በደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 32 መሰረት ከ12 አመት በኋላ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ወስኗል። ይህ የፍሬ ነገር መደምደሚያ እና ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ችልቶችም ተቀባይነት አግኝቷል።
በዚህ መልኩ በስር ፍርድ ቤት መወሰኑ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ክርክሩ የሚመራበት የሥነ ሥርዓት ህግ ለመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት (ለወረዲው ፍርድ ቤት) የሰጠውን የዲኝነት ስልጣን እንዱሁም የክልለን የገጠር መሬት አዋጅና ደንብ የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ አልነበረም።
ይሁንና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በስር ያልተነሳ ክርክር እና ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ያልተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት በማድረግ መሬቱ ከተጠሪ እጅ ወጥቶ በአመልካች እጅ ሉገባ የቻለው በሽያጭ ነው፤ ከህገ መንግስት ተቃራኒ በሆነ መንገድ በሽያጭ ከተገኘ የይርጋ ጊዜ እንደ መጀመሪያ ተቃውሞ ላቀርብ አይችልም የሚለ ምክንያቶች ሰጥቶ ውሳኔውን መሻሩ የግራ ቀኙን ክርክር እና ጉዲዩ የሚመራበትን የሥነ ሥርዓት ህግ የተከተለ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም። በስር ፍርድ ቤቶች ክሱ በይርጋ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ከመደረጉ በቀር በፍሬ ነገር ላይ ውሳኔ አለመሰጠቱ እንኳ እየታወቀ የክልለ ሰበር ችልት በራሱ ወደ ፍሬ ጉዲዩ ገብቶ አከራካሪውን መሬት ተከሳሽ ለከሳሽ እንዱለቅ በማለት መወሰኑም ተቀባይነት የለውም።
በአጠቃላይ የክልለ ሰበር ችልት ያሳለፈው ውሳኔ የግራ ቀኙን ክርክር፤ የመሬት አዋጅና ደንቡን እንዱሁም የዲኝነት አሰጣጥ ስርዓትን የጠበቀ ባለመሆኑና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 25/01/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሀሮማያ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 13/07/2013 ዓ.ም፤ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 08/08/2013 ዓ.ም፤ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 10/09/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ስ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።