በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358 መሰረት የሚቀርብ አቤቱታ የክርክሩ ተሳታፉ ባልሆነበት በተደረገ ክርክር የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሦስተኛ ወገን የመቃወም አቤቱታዉን አቅርቦ የክርክሩ ተሳታፉ በመሆን ተከራክሮ መብቱን ማስከበር እንዱችል ታስቦ እንጂ ወኪል ሆኖ ሉከራከር የሚችልበት መብትና ጥቅም ክርክር በማድረግ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ጉዲዩ በሚመለከተዉ አካል ክርክር ቀርቦበት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ ዉሳኔዉን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358 መሰረት መቃወም የሚቻልበት ህጋዊ አግባብ ያለ ስላለመሆኑ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 33(3) እና 92 (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ መዝገብ ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጧል።)
No summary available.
ህዲር 29 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ ሰለሞን አረዲ ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- የካ ክ/ከተማ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ተጠሪዎች-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የሚቀርብ አቤቱታ የሚስተናገድበትን አግባብ የሚመለከት ነዉ። የጉዲዩም አመጣጥ ሲታይ ተጠሪዎች በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 01 አስተዲደር ጽ/ቤት ላይ ባቀረቡት ክስ ቤትና ንብረታቸዉን ያላግባብ አፍርሶ በመዉሰድ ጉዲት ያደረሰባቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ ካሳ እንዱከፈላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል። ጉዲዩን የተመለከተዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ በላለበት ጉዲዩን መርምሮ የተለያዩ ንብረቶች ዋጋ ብር 443,215.00 ንብረቱ ከተወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ተከሳሽ እንዱከፍል ዉሳኔ ሰጥቷል። ይህ ከሆነ በኋላ ተከሳሽ በነበረዉ በየካ ክ/ከተማ ወረዲ 01 አስተዲደር ጽ/ቤት ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ ሉሻር ይገባዋል በማለት አመልካች አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ የሚቀርበዉ ለአቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ ያረፈዉ የክርክሩ ምክንያት በሆነዉ ንብረት ላይ ሆኖ በክርክሩ ተካፊይ ያልሆነ ወገንን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ሲረጋገጥ ሲሆን፣ በተያዘዉ ጉዲይ ተከሳሽ መጥሪያ ደርሶት ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ክርክሩን ማሰማት ባለመፈለጉ ምክንያት በላለበት ዉሳኔ በተሰጠበት ሁኔታ አመልካች ተከሳሹ ክርክሩን አላሳወቀንም የሚል ምክንያት በመጥቀስ ዉሳኔዉ ይሻርልን በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉን አንቀጽ 358 ዓላማ ያገናዘበ አይደለም በማለት ዉድቅ አድርጎታል፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህንኑ በትዕዛዝ አጽንቶታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚሁ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች የካቲት 02 ቀን 2012 ዓ.ም አዘጋጅቶ ያቀረበዉ አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአፈፃፀምና ማዘጋጃ አገልግልት አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 35/2004፣ አዋጅ ቁጥር 64/2011 ላይ በተመለከተዉ መሰረት አመልካች የከተማ አስተዲደሩ ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር በማናቸዉም ዲኝነት አካል ዘንድ የመቃወሚያ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለዉ፤ ተከሳሽ የነበረዉ ተቋም እና አመልካች በአንድ መንግስታዊ መዋቅር ስር መገኘታቸዉ ብቻ አከራካሪዉን ጉዲይ በተመለከተ ተመሳሳይ ጥቅምን የሚወክለ አካላት ናቸዉ ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ይህንኑ አረጋግጧል፤ ይህ ሆኖ እያለ አመልካች በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የጸናዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነዉ።
የሰበር አቤቱታዉ በአጣሪ ችልት ተመርምሮም አመልካች የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ የከተማ አስተዲደሩን መብትና ጥቅም ማስከበር እንደሚችል በህግ ስልጣን ተሰጥቶት እያለ አቤቱታዉን ዉድቅ በማድረግ የተሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዘጋጅተዉ በሰጡት መልስ አመልካች በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት ያቀረበዉን የመቃወም አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ በተሰጠ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለመኖሩን ጠቅሰዉ ጸንቶ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታዉን ለማስቀረብ የተያዘዉን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካች በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት ላቀረበዉ የመቃወም አቤቱታ መሰረት ያደረገዉ ተጠሪዎች በስር ተከሳሽ በነበረዉ የየካ ክ/ከተማ ወረዲ 01 አስተዲደር ጽ/ቤት ላይ ያቀረቡትን ክስ መሰረት በማድረግ ብር 443,215.00 ከወለድ ጋር ለተጠሪዎች እንዱከፈል ፍርድ ቤቱ የሰጠዉ ዉሳኔ የአስተዲደሩ ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም የሚነካ በመሆኑ እና አመልካች በፍርድ ቤት ክርክር አቅርቦ ይህን መብት ለማስከበር በህግ ስልጣን የተሰጠዉ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። በእርግጥ አመልካች በፍርድ ቤት ክርክር አቅርቦ የክፍለ ከተማ አስተዲደሩንና የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም የማስከበር ስልጣን በህግ የተሰጠዉ መሆኑ አላከራከረም። አከራካሪዉ እና የዚህን ችልት እልባት የሚያሻዉ ጭብጥ አመልካች በፍርድ ቤት ክርክር በማድረግ የከተማዉ ነዋሪዎችን/የህዝብና የመንግስትን መብትና ጥቅም ለማስከበር ያለዉ መብት/ስልጣን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣንና ኃላፉነት ባለዉ ላላ የከተማዉ አስተዲደር አካል ክርክር ተደርጎበት ዉሳኔ ያረፈበት ጉዲይ በድጋሚ እንዱታይ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ ያስችለዋል ወይ? የሚለዉ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸዉን የጽሐፍ ክርክር መርምረዉ፣ በቃል የሚቀርቡ ክርክሮችን አዲምጠዉ፣ ማስረጃዎችን መዝነዉ እና መሰረታዊ ህጎችን ተርጉመዉ ዉጤት ላይ መድረስ ይችለ ዘንድ ሥርዓት ያስፈልጋቸዋል። ክርክሮች የሚመሩባቸዉ ሥርዓት እና ደንቦች በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ተቀርጸዉ ስራ ላይ እንዱዉለ የሚደረግበት ምክንያትም ይሄዉ ነዉ። የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ የፍትሐ ብሓር ክርክሮችን አስመልክቶ የምንከተለዉ ስርዓት ሲሆን አጠቃላይ ዓላማዉም የፍትሐ ብሓር ጉዲዮችን ፍትሐዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ቀልጣፊ በሆነ ሁኔታ በመምራት ፍትሐዊ ዉሳኔ እንዱያገኙ ማስቻል ነዉ። ይህን ዓላማ ለማሳካት ይቻል ዘንድም የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ የተለያዩ ደንቦች እና መርሆዎችን ይደነግጋል። ክርክሮች በዘፈቀደ ሳይሆን ሥርዓት ባለዉ ሁኔታ እንዱመሩ በማድረግ የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት መብትን፣ ብልም ክርክሮች ባነሰ ወጪ እና ጊዜ መቋጫ እንዱያገኙ በማድረግ በፍርድ ቤት እና በተከራካሪ ወገኖች ላይ ያላግባብ የሚደርሰዉን የገንዘብ እና የጊዜ ብክነት በማስቀረት የክርክሩ ሂደትም ሆነ ዉጤቱ ፍትሐዊ እንዱሆን በማድረግ ረገድ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ የሚኖረዉ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በህጉ ላይ የተመለከቱትን ደንቦች እና መርሆዎች በአግባቡ ሥራ ላይ እንዱዉለ የማድረጉ አስፈላጊነትም የሚያጠያይቅ አይደለም።
በዚህ ረገድ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጋችን ዔዉቅና ከተሰጣቸዉ ደንቦች ዉስጥ አንደ በከሳሽነት እና በተከሳሽነት ከተሰየሙት ወገኖች ዉጪ ያለ ሦስተኛ ወገኖች የክርክር ተሳታፉ የሚሆኑበትን ሁኔታ የሚመለከተዉ ደንብ ነዉ። በከሳሽነት እና በተከሳሽነት ከተሰየሙት ተከራካሪዎች ዉጭ የሆነ ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ተሳታፉ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በጉዲዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት የማይችል ዓይነት (indispensable party) ከሆነ በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ወይም መብት ባለዉ ሰዉ አቤቱታ አቅራቢነት፣ እንዱሁም ዉጤቱ መብቴን ሉነካ ይችላል በሚል ወገን (interested party) አቤቱታ አቅራቢነት ሦስተኛ ወገን በተጀመረ ክርክር ተሳታፉ የሚሆንበትን ሥርዓት የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ ይዘረጋል (አንቀጽ 40 እና 41 ይመለከቷል)። ዓላማዉም የጉዲዩ አመራር ፍትሐዊ እንዱሆንና በሥርዓት እንዱከናወን ለማስቻል ሲባል ነዉ ተብል ይታመናል። ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ከላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ክርክሩ በሂደት ላይ እያለ በክርክሩ ተሳታፉ ሆኖ መብቱን ማስከበር ይችል የነበረ ሰዉ ተሳታፉ ባልሆነበት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ላሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ሉኖር ይችላል። ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም በህግ የዲኝነት ስልጣን ባለዉ አካል በተሰጠ ዉሳኔ መብቴ ተነክቷል የሚል ሦስተኛ ወገን አቤቱታዉን በማቅረብ ዉሳኔዉን በመቃወም መብቱን ሉያስከብር የሚችልበትን ሥርዓት በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ የድንጋጌዉ ሙለ ይዘትም፡በክርክሩ ዉስጥ ተካፊይ መሆን የሚገባዉ ወይም በክርክሩ ዉስጥ ለመግባት የሚችልና እንዱሁም ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠዉ ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማናቸዉም ሰዉ ራሱ ወይም ጠበቃዉ ወይም ነገረ ፈጁ ተካፊይ በልሆነበት ክርክር የተሰጠዉ ፍርድ ከመፈጸሙ በፉት መቃወሚያዉን ለማቅረብ ይችላል የሚል ሲሆን የዚህ ድንጋጌ የእንግሉዝኛዉ ቅጅም Any person who should or could or could have been a party to a suit and whose interests are affected by a judgment in the suit may, if he was not a party to such suit either in person or through a representative, file an opposition to such judgment at any time before such judgment is executed በማለት ይደነግጋል።
ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለዉም ክርክሩ መጀመሩን ሳይረዲና ሳያዉቅ በከሳሽነትና በተከሳሽነት በተሰየሙት ወገኖች መካከል የተደረገዉ ክርክር ተጠናቆ መወሰኑ እንኳ ቢታወቅ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ይረዲ ዘንድ በዉሳኔዉ መብቴ ተነክቷል የሚለዉ የክርክሩ ተካፊይ ያልነበረዉ ሰዉ ይህንኑ ዉሳኔ መቃወም የሚችል መሆኑን ነዉ። በተለይም በድንጋጌዉ ማናቸዉም ሰዉ ራሱ ወይም ጠበቃዉ ወይም ነገረ ፈጁ ተካፊይ ባልሆነበት ወይም በእንግሉዝኛዉ if he was not a party to such suit either in person or through a representative በሚል የተገለጸዉ የሚያሳየዉ ሦስተኛ ወገን የሚያቀርበዉ አቤቱታ ተቀባይነት የሚኖረዉ አቤቱታ አቅራቢዉ ለአቤቱታዉ በምክንያትነት የጠቀሰዉ ጉዲይ በቀደመዉ የክርክር ሂደት በመቃወም አመልካቹ በእራሱ ወይም በወኪለ ወይም ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ሰዉ ክርክር ያልቀረበበት ሲሆን ነዉ። በልላ አገላለጽ የመቃወም አመልካቹ ለአቤቱታዉ መሰረት ያደረገዉ ክርክሩ በሂደት ላይ በነበረበት ወቅት ጉዲዩ የሚያገባዉ ሰዉ የክርክሩ ተሳታፉ በሆነበት ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበት ጉዲይ ከሆነ እና የመቃወም አመልካቹ ዉሳኔዉ ‘ በግል’ መብቱን የሚነካ መሆኑን በአቤቱታዉ ካላሳየ በስተቀር አቤቱታዉ ተቀባይነት የሚኖረዉ አይደለም። የመቃወም አመልካች ለመቃወሚያዉ ምክንያት የሆኑትን ዝርዝር ምክንያቶች እና የሚጠይቀዉን ዲኝነት በአቤቱታዉ በዝርዝር መግለጽ እንዱሁም አቤቱታዉ ለላልች ተከራካሪ ወገኖች እንዱደርስ ተደርጎ ክርክሩም የሚሰማዉ የመጀመሪያዉ ክርክር በተሰማበት ሂደት ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 359 እና 360 ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎችም የሚያሳዩት ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ የመቃወም አመልካቹን መብትና ጥቅም በግል የሚነካ መሆን ያለመሆኑ ጉዲይ የመቃወም አመልካቹ እና በክርክሩ ተሳታፉ የሆኑ ላልች ተከራካሪ ወገኖች የሚያቀርቡትን ክርክር እና ማስረጃ መሰረት በማድረግ ታይቶ ዉሳኔ የሚሰጥበት መሆኑን ነዉ። ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠዉ የዲኝነት አካል የተሰጠን ዉሳኔን መቃወም የሚቻልበትን ሥርዓት አስመልክቶ በሥነ ሥርዓት ህጉ የተመለከተዉ ድንጋጌ በዉሳኔዉ መብቱ ‘በግል’ የተነካበት ሰዉ መቃወሚያዉን አቅርቦ መብቱን ለማስከበር እንዱችል እንጂ አንድን መብትና ጥቅም ለማስከበር የተለያዩ ሰዎች ተፈራርቀዉ የሚያቀርቡትን አቤቱታ ለማስተናገድ ያለመሆኑን መገንዘቡ ተገቢ ነዉ። ይልቁንም የመቃወም አቤቱታ የሚቀርብበትን ሁኔታ አስመልክቶ በድንጋጌዉ ላይ ከተመለከቱት መስፈርቶች አንፃር ሲታይ የድንጋጌዉ ዓይነተኛ ዓላማ በአንድ በኩል በከሳሽነት እና በተከሳሽነት በተሰየሙ ወገኖች መካከል በተደረገ ክርክር መነሻነት የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሰዉ ዉሳኔዉን በመቃወም ተከራክሮ መብቱን እንዱያስከብር በማድረግ ፍትሕ የማግኘት መብቱን በማረጋገጥ፣ በልላ በኩል በከሳሽነት እና በተከሳሽነት በተሰየሙት ወገኖች መካከል ክርክር ተደርጎበት እልባት ባገኘ ጉዲይ ላይ በድጋሚ ክርክር በማቅረብ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር በሚል በሦስተኛ ወገን የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት እንዲይኖረዉ በማድረግ በአንድ ጉዲይ ላይ ወይም ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር በሚል ክርክሮች በተደጋጋሚ ሉቀርቡ የሚችለበትን ሁኔታ በማስቀረት ክርክሮች በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጪ መቋጫ እንዱያገኙ ብልም የፍርድ ሂደቱም ሆነ ዉጤቱ ተገማች እንዱሆን ማድረግ ነዉ። ስለሆነም በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የቀረበ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን አስመልክቶ በፍርድ ቤቶች የሚሰጠዉ ትርጉም ይህንኑ ያገናዘበ ላሆን ይገባል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ በተጠሪዎች ከሳሽነት በስር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት የተሰየመዉ የየካ ክ/ከተማ ወረዲ አስተዲደር ጽ/ቤት ሲሆን ለቀረበዉ ክስ ምክንያት የሆነዉም የተጠሪዎችን ቤት አፍርሶ ንብረታቸዉንም ያላግባብ በመዉሰድ ጉዲት ያደረሰባቸዉ መሆኑ ነዉ። ተጠሪዎች ይህ ድርጊት በስር ተከሳሽ መስሪያ ቤት የተፈጸመ እና ለጉዲቱ ኃላፉነቱን የሚወስደዉም መስሪያ ቤቱ ስለመሆኑ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 33(3) እና 92 መሰረት አረጋግጠዉ ክስ ያቀረቡ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። ይህ በመሆኑም አመልካች በህጉ አንቀጽ 33(3) መሰረት በቀጥታ ተከሳሽ ሆኖ ላቀርብ የሚችልበት ሁኔታ አይኖርም። በተከሳሽነት የተሰየመዉ የወረዲዉ አስተዲደር ጽ/ቤት ቀርቦ ባለመከራከሩም ዉሳኔ በላለበት ተሰጥቷል። አመልካች የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ ተቋም በመሆኑ የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ የመንግስት ወይም የግል ተቋም እንደሚያደርገዉ ሁለ በቀጥታ ተቋሙን በሚመለከተዉ ጉዲይ ላይ በከሳሽነት፣ በተከሳሽነት፣ በጣልቃ ገብነት ወይም በመቃወሚያ አቤቱታ አቅራቢነት በፍርድ ቤት ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠዉ የዲኝነት አካል ቀርቦ የክርክሩ ተሳታፉ በመሆን እንደ ተቋም ያለዉን መብት የማስከበር መብትም ግዳታም አለዉ። ይሁንና በተያዘዉ ጉዲይ ላይ አመልካች በተጠሪዎች የቀረበዉ ክስ ይመለከተኛል ወይም በህጉ አንቀጽ 33(3) መሰረት በተከሳሽነት መጠራት የነበረብኝ እኔ ነኝ የሚል ክርክር የለዉም፤ ይልቁንም በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ያቀረብኩት የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት ሉኖረዉ ይገባል በማለት የሚከራከረዉ በስር ተከሳሽ የነበረዉ የየካ ክ/ከተማ ወረዲ 01 አስተዲደር እንዱከፍል የተወሰነበት ገንዘብ የክፍለ ከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑን እና የክፍለ ከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅምን በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መከራከር እንዱችል በህግ ስልጣን የተሰጠዉ መሆኑን ነዉ። በእርግጥም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 5 የዐቃቤ ሕግ ቢሮ የከተማዉ አስተዲደር መስሪያ ቤቶች የአስተዲደሩና የነዋሪዉ መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ እንደሚከራከር የተመለከተ ሲሆን፣ አመልካች የክፍለ ከተማ አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በመሆኑ ስለ ክፍለ ከተማ የሥልጣን አካላት ሥልጣንና ተግባር በሚደነግገዉ ክፍል አንቀጽ 78 መሰረት የክ/ከተማዉንና የክፍለ ከተማዉን ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ ወኪል ሆኖ ለፍርድ ቤት ወይም በህግ የዲኝነት ስልጣን በተሰጠዉ አካል ቀርቦ ክርክር የማቅረብ ስልጣን ይኖረዋል።
በዚህም መሰረት በክፍለ ከተማዉ እና በስሩ የተደራጁት መስሪያ ቤቶች ከክፍለ ከተማዉ ነዋሪዎች መብትና ጥቅም ጋር በተያያዘ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ተሳታፉ በሆኑበት ጉዲይ ላይ አመልካች ወኪል ሆኖ መከራከር ይችላል። እንዱሁም እነዚህ መስሪያ ቤቶች የክርክሩ ተሳታፉ መሆን ሲገባቸዉ ተሳታፉ ባልሆኑበት የተሰጠ ዉሳኔ ሲኖር እና ዉሳኔዉም የክ/ከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም የሚጎዲ ከሆነ የሚመለከተዉን የክፍለ ከተማዉን መስሪያ ቤት በመወከል በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ ይችላል። ይህ እንዲለ ሆኖ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ወይም በጣልቃ ገብነት ወይም በመቃወም አመልካችነት የክርክር ተሳታፉ ሲሆን መስሪያ ቤቱ በእራሱ የህግ ባለሙያ ወይም ነገረ ፈጅ ክርክሩን ማቅረብ የሚችልበት ሁኔታ እንዲለ የሚታወቅ ነዉ። ይህም የሚያሳየዉ በፍርድ ቤት ክርክር አድርጎ አንድን መብትና ጥቅም በማስከበር ሂደት አመልካች (ዐቃቤ ህግ) እና ጉዲዩ የሚመለከተዉ መስሪያ ቤት ተሳታፉ ሉሆኑ የሚችለበት ዔድል መኖሩን ነዉ። ይህ ማለት ግን ሁለቱ ተቋማት አንድን መብትና ጥቅም ለማስከበር በጋራ ተከራካሪ በመሆን ይቀርባለ ወይም ከሁለቱ አንደኛዉ መስሪያ ቤቱን በመወከል ክርክር አድርጎ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ ላላኛዉ ወገን ተመሳሳይ መብትን የማስከበር በህግ ስልጣን/መብት ስላለዉ ብቻ ዉሳኔዉን ለመቃወም አቤቱታ ያቀርባል ማለት እንዲልሆነ መገንዘቡ ተገቢ ነዉ። ይልቁንም የከተማዉን/የክፍለከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም ከማስከበር ጋር በተያያዘ ክርክር ሲኖር የሚመለከተዉን መስሪያ ቤት ወክል ክርክሩን ማቅረብ የሚችል አካል ከአቃቤ ህግ እና ከመስሪያ ቤቱ የህግ ባለሙያ ማን መሆን እንዲለበት የአቃቤ ህግ መስሪያ ቤት እና መስሪያ ቤቱ ተነጋግረዉ የሚወስኑት ነዉ። በዚህ መልኩ ተነጋግረዉ ጉዲዩን አቃቤ ህግ እንዱይዝ ከተወሰነ ላላ የተለየ ዉክልና እንዱያቀርብ ማድረግ ሳያስፈልግ ጉዲዩን የሚመለከተዉ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ የሚያቀርበዉን ክርክር መቀበል እንዱችል የተመለከተ ድንጋጌ ነዉ። ከዚህ ዉጪ ዐቃቤ ህግ ጉዲዩ የከተማዉ ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም የሚመለከት በመሆኑ ብቻ የሚመለከተዉ መስሪያ ቤት የክርክሩ ተሳታፉ በመሆን በተደረገ ክርክር መሰረት ዉሳኔ ያገኘዉን መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን አለኝ በሚል ብቻ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ማስከበርን መሰረት ያደረገ አቤቱታ በፍትሐ ብሓር ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ አይችልም። ዐቃቤ ህግ ክርክር በማቅረብ የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም ማስከበር እንደሚችል ስልጣን የሚሰጠዉ ከላይ የተመለከተዉ የአዋጁ ድንጋጌ አተገባበርም ይህን እዉነታ ባገናዘበ መልኩ ላሆን ይገባል።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት ክሱ የቀረበበት የየካ ክፍለከተማ ወረዲ 1 አስተዲደር ጽ/ቤት ለፍርድ ቤት ቀርቦ ባለመከራከሩ በላለበት ጉዲዩ ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠ ሲሆን፣ ክርክር ሳይደረግ የተሰጠ ዉሳኔ የክፍለ ከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም የሚጎዲ ነዉ የሚል ከሆነ እና ተከሳሹ መስሪያ ቤት ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ክርክሩን ሉያቀርብ ያልቻለበት በቂ እና አሳማኝ ምክንያት አለዉ የሚል ከሆነ ከተከሳሽ መስሪያ ቤት ጋር በመነጋገር አቤቱታዉ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 78 መሰረት ማቅረብ ይችል ነበር። አመልካች ይህን ሳያደርግ እና በዚህም ምክንያት በተከሳሽነት የተሰየመዉ መስሪያ ቤት በላለበት ክርክሩ እንዱቀጥል ተደርጎ የተሰጠ ዉሳኔ ሥነ ሥርዓታዊ ነዉ ተብል በሚገመትበት ሁኔታ ዉሳኔዉን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።
ሲጠቃለል በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የሚቀርብ አቤቱታ የክርክሩ ተሳታፉ ባልሆነበት በተደረገ ክርክር የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሦስተኛ ወገን የመቃወም አቤቱታዉን አቅርቦ የክርክሩ ተሳታፉ በመሆን ተከራክሮ መብቱን ማስከበር እንዱችል ታስቦ የተዘረጋ ነዉ። በመሆኑም አቃቤ ህግ ወኪል ሆኖ ሉከራከር የሚችልበት መብትና ጥቅም ክርክር በማድረግ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ጉዲዩ በሚመለከተዉ መስሪያ ቤት ክርክር ቀርቦበት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ አቃቤ ህግ ዉሳኔዉን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት ሉቃወም የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም። በዚህ አግባብ ለመወሰን ለክርክሩ ምክንያት ከሆነዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ ሁለቱም (ዐቃቤ ህግ እና ጉዲዩ የሚመለከተዉ መስሪያ ቤት) የሚያስከብሩት መብትና ጥቅም አንድ እስከሆነ ድረስ የአቃቤ ህግ መስሪያ ቤት እና በክርክሩ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት የተሰየመ መስሪያ ቤት የየራሳቸዉ ስልጣንና ኃላፉነት ያላቸዉ መሆን ያለመሆኑ ጉዲይ በጭብጥነት ሉያዝ የሚገባዉ ጉዲይም አይደለም። ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘ አመልካች የሚያቀርበዉ ክርክር ተገቢነት የለዉም። በእርግጥ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በቅጽ 8 ላይ በታተመዉ ዉሳኔ ሁለት ራሳቸዉን የቻለና የህግ ሰዉነት ያላቸዉ ተቋሞች በአንድ የመንግስት መዋቅር ሥር የሚገኙ በመሆናቸዉ ብቻ ተመሳሳይ ጥቅምን የሚወክለ አካላት ናቸዉ ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አለመሆኑን በመጥቀስ ከከተማ አስተዲደሩ አንደ አካል የክርክሩ ተሳታፉ በሆነበት ክርክር ተደርጎ ዉሳኔ መሰጠቱ የአመልካች መስሪያ ቤት በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ እንዲያቀርብ የሚከለክል አይደለም የሚል ይዘት ያለዉ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። ይሁንና ይህ የህግ ትርጉም በሦስተኛ ወገን አቤቱታ የሚቀርብበትን ሁኔታ አስመልክቶ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ ዓላማ ያገናዘበ ባለመሆኑ ሉለወጥ የሚገባዉ የህግ ትርጉም ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህ ሁለ ምክንያት ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ሐምል 02 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ ታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንተዋል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ (ቅጽ 8 ላይ እንደታተመዉ) የሰጠዉ የህግ ትርጉም ተለዉጧል።
የአዱስ አበባ ከተማ ዐቃቤ ህግ ቢሮ (በየደረጃዉ ያለ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤቶችን ይጨምራል) ወኪል ሆኖ ክርክር በማቅረብ የነዋሪዉን መብትና ጥቅም እንዱያስከብር በአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጁ ስልጣን የተሰጠዉ ቢሆንም፣ ይህ ስልጣኑ ብቻዉን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣን ያለዉ የሚመለከተዉ የከተማዉ አስተዲደር አካል የክርክሩ ተሳታፉ በሆነበት ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበትን ጉዲይ መሰረት አድርጎ እንደገና ክርክር ለማድረግ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ እንዱያቀርብ ምክንያት አይሆንም።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
የሰበር አጣሪ ችልት የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
ማ/አ የማይነበብ የሰባት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.