ክስ ለማቅረብ በሕግ ችልታ የላለው ሰው በመሆኑ በሞግዚት ወይም በተሾመለት እንደራሴ አማካይነት ክስ ላቀርብ ሲገባ በዚህ አግባብ ሞግዚትና አሳዲሪ ሆኖ የተሾመ ስለመሆኑ የቀረበ የፍርድ ቤት ውሳኔ በላለበትና ክስ ለማቅረብ ችልታ ያለው መሆኑን ሳይረጋገጥ ወደ ክሱ ሥረ-ነገር በመግባት ውሳኔ የሚሰጥ ስላለመሆኑ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(1)፣ 34(1) እና የፍ/ሕ/ቁ. 210
No summary available.
ቀን፡- ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ አገልግልት ሶማላ ሪጅን ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ እና 2ኛ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ። 2ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ሟች አብደልአዚዝ አቦሽ የአመልካች ሰራተኛና የሉፍት መኪና ሾፋር ሲሆን በወር ብር 9,000.00 ደመወዝ ይከፈለው ነበር። ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓ/ም ሥራ ላይ እያለ አመልካች በቸልተኝነት የኤላክትሪክ ኃይለ ጠፍቷል በማለት የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ሟች በሚነዲው ተሽከርካሪ የኤላክትሪክ ትራንስፍርመር በሉፍት ለመጫን ሲሞክር በኤላክትሪክ አደጋ ሕይወቱ አልፎል። ሟች በሕይወት እያለ አባታቸው የሞተባቸው ስድስት ወንደሞች አሳዲጊ ነበር፤
በአደጋውም መተዲደሪያ ገቢያቸውን አጥተዋል። ስለሆነም የቀብር ወጪ ብር 25,000.00 እና ካሣ ብር 475,000.00 በድምሩ ብር 500,000.00 ለሟች ወንድሞች እንዱከፍል እንዱወሰን የሚል ነው።
አመልካች የሰጠው መልስ 2ኛ ተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት የለውም በማለት የተከራከረ ሲሆን ጣልቃ የገባው 1ኛ ተጠሪ በበኩለ በደንብ ቁጥር 303/2006 እና በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 382/2008 መሰረት ዓይነቱ 15 ኬቪ የሆነ የኤላክትሪክ ገመድ የአመልካች ንብረት የሆነና በፍ/ሕ/ቁ. 2069(2) መሰረት ኃላፉ ላሆን የሚገባው አመልካች እንጂ ጣልቃ ገብ አይደለም በማለት ተከራክሯል።
የፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ ከደቡብ ጅግጅጋ ወረዲ ፍርድ ቤት ሟች ልጅ ባይኖረውም ወንድሞቹ የሆኑት ወራሾች መሆናቸው የሚያረጋጥ ውሳኔ ስለቀረበ እና ሟች ታናናሽ ወንድሞች አሳዲጊ የነበረ በመሆኑ የቀረበ ክስ ነው። አመልካች የቀጠራቸውን ሰራተኞች ከአደጋ የመጠበቅ ኃላፉነት አለበት፤ የኤላክትሪክ ኃይለ ሳይጠፊ በቸልተኝነት ጠፍቷል በማለት የደረሰ አደጋ ነው። ስለሆነም አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋራ ብር 500,000.00 ለወራሾች እንዱከፍለ ወስኗል።
አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ይግባኝ አጣምሮ የተመለከተው የሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ 2ኛ ተጠሪ የሟች ወራሾች አሳዲጊ በመሆኑ፣ ሟች በሕይወት እያለ ይሰጣቸው የነበረው የመተዲደሪያ ገቢ ለመጠየቅ ክስ ማቅረቡ በፍ/ሕ/ቁ. 807፣ 808፣ 812፣ 845፣ እና 2216(1) እንዱሁም በክልለ ባሕላዊ ሕግ መሰረት ተገቢ ነው። 1ኛ ተጠሪ ሳይከሰስና በራሱ ፈቃድ ጣልቃ ከመግባት በፉት በግድ ጣልቃ እንዱገባ መደረጉ ተገቢ አይደለም። ሟች በአመልካች መስመር ላይ ሲሰራ አደጋ ስለደረሰበት ካሣ ብር 500,000.00 ሉከፍል የሚገባው አመልካች ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አሻሽሎል። 2ኛ ተጠሪ 1ኛ ተጠሪም ኃላፉነት አለበት ካለ ክስ ከመመስረት እንደማይግደው በውሳኔው ገልጿል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በፍ/ሕ/ቁ. 2095 ካሣ ለመጠየቅ ከሚችለ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ 2ኛ ተጠሪ የለም፤
(በቅጽ 5 የታተመ)፣ በ
(በቅጽ 22 የታተመ) መሰረት ተደርጎ የተወሰነ አይደለም። ጥገና ስንሰራ ኤላክትሪክ ኃይል ማከፊፈያ ጣቢያ ባለቤትና አስተዲዲሪ የሆነው 1ኛ ተጠሪ ኃይል ማቋረጫ ደብዲቤ በማስገባት እንዱቋረጥ የሚደረግበት የውልና የሥራ ግንኙነት አለን፤ ፉደር 2 ባለ 15 ኬቪ የሆነ መስመር ኤላክትሪክ ኃይል እንዱቋረጥ ጠይቀን መስመሩ የተቋረጠ/የጠፊ መሆኑን በማረጋገጡ የጥገና ሥራው በሆዮ የኤላክትሪክ ኢንስታላሽን ማሕበር እያሰራ እያለ የኤላክትሪክ ኃይል እንዱቋረጥ ከተጠየቀበት ሰዓት በፉት 9፡30 አካባቢ ኃይል በመልቀቁ የደረሰ አደጋ በመሆኑ ኃላፉነቱ የ1ኛ ተጠሪ ነው። 1ኛ ተጠሪ ንግድ ጣልቃ የገባ ነው በማለት ከክርክሩ ውጭ ማድረጉ ተገቢ አይደለም። ሟች ስንት ወራሾች እንዲለው፣ ሟች በሕይወት እያለ በመተዲደሪያ ረገድ ገንዘብ ይሰጣቸው የነበረ ስለመሆን አለመሆኑ፣ አደጋው እንዳት እንደደረሰ፣ ሟች ለማሽከርከር ፈቃድ ያለው ስለመሆን አለመሆኑ ማስረጃ ሳይሰማና ሳይመዘን የተሰጠው ውሳኔ ስህተት ያለበት ስለሆነ ውሳኔው ይሻርልን የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ 2ኛ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ መብትና ጥቅም የለውም በሚል የቀረበው ክርክር ውድቅ መደረጉ ከፍ/ሕ/ቁ. 2095 አኳያ ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ አዟል። 1ኛ ተጠሪ ያቀረበው መልስ ሟች ካሣ ከአሰሪው ዱዜድ ኮንስትራክሽን ነው መጠየቅ ያለበት፤
2ኛ ተጠሪ የሟች አጎት ነው፣ ሞግዚት ስለመሆኑም ማስረጃ ያልቀረበ በመሆኑ ካሣ ለመጠየቅ መብት የለውም። ሟች ወራሾቹን ይረዲ የነበረ ስለመሆኑ በክሱ አልተጠቀሰም፣ ማስረጃም አልቀረበም፤
ውሳኔው ሉታረም ይገባል ብሎል። 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ጉዲዩ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እንጂ ለሰበር ችልቱ ላቀርብ አይገባም። ሟች በሕይወት እያለ ስድስቱን ሕጻናት ወንድሞቹን ሲያስተዲድር ነበር፤ ሞግዚትነቴ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ ነው። ውሳኔው ማስረጃው ተመዝኖ የተሰጠ ስለሆነ ሉጸና ይገባል ብለዋል። አመልካች የመልስ መልሰ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙ ክርክር፣ የሰበር አጣሪ ችልት የያዘውን ጭብጥ፤ በሥር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው 2ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ሟች አብደልአዚዝ አቦሽ ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓ/ም ሥራ ላይ እያለ አመልካች በቸልተኝነት የኤላክትሪክ ኃይለ ጠፍቷል በማለት የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ሟች በሚነዲው ተሽከርካሪ የኤላክትሪክ ትራንስፍርመር በሉፍት ለመጫን ሲሞክር በኤላክትሪክ አደጋ ሕይወቱ አልፎል፤ ሟች በሕይወት እያለ አባታቸው የሞተባቸው ስድስት ወንደሞች አሳዲጊ ነበር፤
በአደጋውም መተዲደሪያ ገቢያቸውን አጥተዋል። ስለሆነም የቀብር ወጪ ብር 25,000.00 እና ካሣ ብር 475,000.00 በድምሩ ብር 500,000.00 ለሟች ወንድሞች እንዱከፍል እንዱወሰን የሚል ሲሆን አመልካች በበኩለ ለአደጋው ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል። በክርክሩ ሂደትም 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብቶ ተከራክሯል።
2ኛ ተጠሪ ክሱን ያቀረቡት ስለሟች ወንድሞች ስለመሆኑ በክሱ የገለጹ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ የሟች ወንድሞችን ወክለው ክስ ለማቅረብ ችልታ ያላቸው ስለመሆን አለመሆኑ መርምረናል።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(1) መሰረት ክስ ለማቅረብ በሕግ ችልታ ያለው ሰው መሆን ይገባዋል።
የተፈጥሮ ሰው ከሆነ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ወይም መብቱ በፍርድ የተከለከለ ሰው በራሱ ክስ ለማቅረብ ችልታ የለውም፤ ክስ ለማቅረብ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 34(1) እንደተመለከተው በሞግዚት ወይም በተሾመለት እንደራሴ አማካይነት ክስ ላቀርብ ይችላል። ድርጅት፣ ማሕበር ወይም ላላ አካል ከሆነ ደግሞ ክስ ለማቅረብ በሕግ ሰውነት ያገኘ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል። ከክርክሩ ሂደት የተገነዘብነው 2ኛ ተጠሪ የሟች አብደልአዚዝ አቦሽ ሆነ የሟች ወንድሞች አጎት ናቸው። በፍ/ሕ/ቁ.
210 መሰረት የሕጻናቱ አባትና እናት በሕይወት ከላለ አጎትም የሕጻናቱ ሞግዚት ሆኖ ሉሾም ይችላል። 2ኛ ተጠሪ በዚህ አግባብ ሞግዚትና አሳዲሪ ሆነው የተሾሙ ስለመሆኑ የቀረበ የፍርድ ቤት ውሳኔ የለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች 2ኛ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ ችልታ ያላቸው መሆኑን ሳያረጋግጡ ወደ ክሱ ሥረ-ነገር በመግባት ካሣ መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የሶማላ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁጥር 05-1-26/13 ታህሳስ 06 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 052-65/2012 ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
2ኛ ተጠሪ የሟች አብደልአዚዝ አቦሽ ወንድሞችን ወክለው ክስ ለማቅረብ ችልታ የላቸውም ተብል ተወስኗል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን እንዱችለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.