የቀረበ ክስ በአንድ በኩል የውል አለመፈጸምንም መሰረት ያደረገ መሆኑን ሲያሳይ በልላ በኩል ውለ ከሚሸፍነው ጉዲት በላይ ስለደረሰ ጉዲቱን አጠቃል የቀረበ ከሆነ ከውል ውጭ ግንኙነትንም መሰረት ያደረገ የክስ አቀራረብ የተከተለና የውል ጉዲት ኪሣራ ማዔቀፍ ውስጥ የሚታይ እንጂ ግንኙነቱን ከውል ውጭ የሚያደርገውና ክስ አቀራረቡ የክሱን መሰረት ግልጽ ያላደረገ በመሆኑ በክስ አቤቱታው ላይ ትክክለኛ የሆነው የውል ግንኙነት በሚያሳይ መልኩ እንዱሻሽልና ተከሳሽም በተሻሻለው ክስ መሰረት ክርክር እንዱያቀርብ ተደርጎ ክርክሩ የሚመራ ስለመሆኑ የፍብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 91/1/
No summary available.
ቀን፡- ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ አማረ አምባዬ፡- ጠበቃ ትዔግስት ተስፊዬ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ። አመልካች ያቀረቡት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 06 የቤት ቁጥር 438 የሆነ ቤትና ቦታ ያለኝ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ አጎራባች ይዞታ ያላቸው በመሆኑ ተገቢውን ርቅት ጠብቀው ሕንጻቸውን መገንባት ሲገባቸው ከግድግዲዬ ጋር አጣብቀው የሰሩ በመሆኑ ቤቱ በመፍረሱ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ ውል የደረሰውን ጉዲት ሙለ በሙለ እተካለሁ በማለት ሥምምነት ያደረጉ ቢሆንም የበለጠ ጉዲት አድርሰው ውለ ከሚሸፍነው በላይ ተጨማሪ ጉዲት ደርሷል። 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ሰርተው እንዱያስረክቡ ብጠይቃቸውም ፈቃደኛ አይደለም። ስለዚህ ለደረሰው ጉደት ብር 726,417.91 እና የማከራየው ቤት ገቢ ስለተቋረጠ በየወሩ ብር 1,100.00 ካሣው ተከፍል እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዱከፍለ፣ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዱገነቡ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ 1ኛ ተጠሪ የገነቡትን ግንባታ አፍርሶ በሕግ የተቀመጠውን የቦታ ርቀት ያስጠብቅ ተብል ይወሰንልኝ የሚል ነው። 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ ጉዲዩ በሥምምነት ያለቀ ነው፤ ከአመልካች ጋር በሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ የውል ሥምምነት ደረሰ የተባለው ጉዲት በሽማግላዎች ተገምቶ ክፍያ እንዱከፈልና ግንባታው እንዱቀጥል ውል አድርገናል። ክሱ ውደቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የቃል ክርክር ሲደረግም አመልካች ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገው ውል ዔቃን እንጂ ቤትን የሚመለከት አይደለም፤ ውለም ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ ላላ ውል ተተክቷል። በውል ከተስማማነው በላይ ተጨማሪ ጉዲት አድርሷል ብለዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገው ሥምምነት ስለቤቱ ጉዲትም ሥምምነት አድርገዋል። አመልካችና 1ኛ ተጠሪ በእርቅ ወይም በሥምምነት የጨረሱትን ነገር ላይ ክስ መቅረቡ ተገቢነት የለውም፤ በሥምምነቱ መሰረት ካልተፈጸመ በሥምምነቱ መሰረት እንዱፈጸም ክስ ማቅረብ እንጂ ከዚህ ውጭ አዱስ ክስ መቅረቡ ተገቢነት የለውም በማለት የአመልችን ክስ ውደቅ አድርጓል። 2ኛ ተጠሪ ላይ የተጠየቀው ዲኝነት የማየት ሥልጣን ፍርድ ቤቱ የለውም በማለት ወስኗል። አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ባለመቀበል ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም እርቁ ወይም ውለ ተፈጸመ የሚባለው ክፍያ ሲፈጸም ወይም ንብረቱን ሲያድሱ ነው። ጉዲቱ አሁንም እየቀጠለ ባለበትና ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገው ውል ዔቃን ብቻ የሚመለከት ሆኖ እያለ ክሱ ውድቅ መደረጉ ተገቢነት የለውም። ፍርድ ቤቱ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገውን ሥምምነት መሰረት አድርጎ ውሳኔ አልሰጠበትም። 1ኛ ተጠሪ ተጨማሪ ጉዲት በማድረሳቸውና ውለ ከሚሸፍነው በላይ ጉዲት ስለደረሰ አጠቃልዬ ካሳ መጠየቄ ተገቢ ነው። በሥምምነቱ ባልተሸፈነው ጉዲት ላይ ውሳኔ ሳይሰጥበት ወይም ክስ የማቅረብ መብቴ አለመጠበቁ ስህተት ያለበት ነው። 2ኛ ተጠሪ ላይ የቀረበውን ክስ ሳይሰማ ሥልጣን የለኝም ማለቱ ሕጋዊ አይደለም የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ በግራቀኙ መካከል ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገውን ሥምምነት ውሳኔ ሳይሰጥበት ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገው ሥምምነት መሰረት በማድረግ ብቻ ክሱን በብይን ውድቅ ያደረግበትን አግባብነት ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ አዟል። 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ይዘትም ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገው ውል አልተተካም። ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገ ሥምምነት ካለም ሥምምነቱን መሰረት በማድረግ መብታቸውን ይጠይቃለ እንጂ በራሳቸው በባለሙያ አስገምተው ካሣ መጠየቃቸው ተገቢነት የለውም። ስለሆነም የሰበር አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ 1ኛ ተጠሪ የግንባታ ፈቃድ የወሰደት ከ2ኛ ተጠሪ ጽ/ቤት ሳይሆን ከንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ጽ/ቤት በመሆኑና የአጎራባች ሥምምነት የሚፈጸመው በተጠሪ ጽ/ቤቱ በኩል ባለመሆኑ ክሱ አይመለከተኝም ብሎል።
አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘው ጭብጥ፣ በሥር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ያቀረቡት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 06 የቤት ቁጥር 438 የሆነ ቤትና ቦታ ያለኝ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ አጎራባች ይዞታ ያላቸው በመሆኑ ተገቢውን ርቅት ጠብቀው ሕንጻቸውን መገንባት ሲገባቸው ከግድግዲዬ ጋር አጣብቀው የሰሩ በመሆኑ ቤቱ በመፍረሱ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ ውል የደረሰውን ጉዲት ሙለ በሙለ እተካለሁ በማለት ሥምምነት ያደረጉ ቢሆንም ውለ ከሚሸፍነው በላይ ተጨማሪ ጉዲት ስለደረሰ ብር 726,417.91 እና የማከራየው ቤት ገቢ ስለተቋረጠ በየወሩ ብር 1,100.00 ካሣው ተከፍል እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዱከፍለ፣ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዱገነቡ እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ 1ኛ ተጠሪ የገነቡትን ግንባታ አፍርሶ በሕግ የተቀመጠውን የቦታ ርቀት ያስጠብቅ ተብል ይሰወንልኝ የሚል ነው።
የአመልካች ቤት ላይ ጉዲት ሲደርስ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ከውል ውጭ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ጉዲቱ መድረስ ከጀመረ በኋላ ግንኙነታቸው ውል መሰረት በማድረግ ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገው ሥምምነት ስለቤቱ ጉዲት ላይ መዋዋላቸውን የሥር ፍርድ ቤት አረጋግጧል። አመልካችም በክስ ማመልከቻው ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም ሥምምነት መደረጉንና ተጠሪ በውለ መሰረት ካለመፈጸማቸውም በላይ ተጨማሪ ጉዲት ማድረሳቸውን ገልጸዋል። ይሕም ለክሱ መሰረት የሆነው አለመግባባት ግራቀኙ ካደረጉት ውልና ካለባቸው ግዳታ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ የክሱ መሰረት የውል ግንኙነት መሆኑን ያስገነዝባል። በአመልካች የክስ አቤቱታ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ ውል የደረሰውን ጉዲት ሙለ በሙለ እተካለሁ በማለት 1ኛ ተጠሪ ሥምምነት ያደረጉ ቢሆንም የበለጠ ጉዲት አድርሰው ውለ ከሚሸፍነው በላይ ተጨማሪ ጉዲት ደርሷል፣ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ሰርተው እንዱያስረክቡ ብጠይቃቸውም ፈቃደኛ አይደለም በማለት ያካተቱት ፍሬ ነገር ክሱ በአንድ በኩል የውል አለመፈጸምንም መሰረት ያደረገ መሆኑን ሲያሳይ በልላ በኩል ውለ ከሚሸፍነው ጉዲት በላይ ስለደረሰ ጉዲቱን አጠቃልዬ ማቅረቤ ተገቢ ነው የሚለው የአመልካች መከራከሪያ ከውል ውጭ ግንኙነትንም መሰረት ያደረገ የክስ አቀራረብ የተከተለ መሆኑን ያሳያል። አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የውል ሥምምነት ካደረጉ በኋላ 1ኛ ተጠሪ የውል ሥምምነቱን በመፈጸም ሂደት ተጨማሪ ጉዲት ካደረሱ የውል ጉዲት ኪሣራ ማዔቀፍ ውስጥ የሚታይ እንጂ ግንኙነቱን ከውል ውጭ የሚያደርገው አይደለም።
ይሕም ክስ አቀራረቡ የክሱን መሰረት ግልጽ ያላደረገ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በክስ በአቤቱታቸው ላይ የጠቀሱት ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገ ሥምምነት ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ደግሞ በመከላከያ ክርክራቸው ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገ ሥምምነት በመጥቀሳቸው የሥር ፍርድ ቤት በክሱ የተጠቀሰውን የግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም ሥምምነት በዝምታ በማለፍ ውሳኔውን ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገው ሥምምነት ላይ መስርቷል።
በክሱ የተጠቀሰውን የውል ሥምምነት መታለፈ የክርክር አመራር ግድፈት ያለበት መሆኑ እንደጠበቀ ሆኖ በሁለቱ የውል ሥምምነቶች መካከል ያለው ተዛምድ ምን እንደሆነ በክሱ ተብራርቶ አለመቅረቡ የክርክር አመራር ግድፈት ለመፈጸሙ እንደመነሻ ሉወሰድ የሚችል ነው።
ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰለትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል። በፍብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 91/1/ እንደተመለከተው ክርክርን ለመለወጥ፣ አቤቱታውን ለማብራራት ሆነ ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ አቤቱታን ማሻሻል ይቻላል። ክስ የሚሻሻለው የቀረበውን አቤቱታ ለማብራራት ወይም ለፍትሕ መሰናክል የሆነ ነገር ካለ አስተካክል በመምራት ውጤት ጋር እንዱደርስ ለማስቻል ነው። ፍርድ ቤቱ በጉዲዩ ላይ ፍትሐዊ ውሳኔ ለመስጠት የሚቸገር ከሆነ እንደሁኔታው ክስ ወይም መልስ ተሻሽል እንዱቀርብ በማድረግ የክርክር ሂደቱንም ሆነ የውጤቱን ፍትሐዊነት የማረጋገጥ ኃላፉነት ይኖርበታል። ስለሆነም አመልካች በክስ አቤቱታቸው የገለጹትን በማሻሻል ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ያላቸውን ትክክለኛ የሆነው የውል ግንኙነት በሚያሳይ መልኩ እንዱያሻሽለ ተደርጎ 1ኛ ተጠሪም በተሻሻለው ክስ መሰረት ክርክር እንዱያቀርቡ ተደርጎ ክርክሩ መመራት ሲገባው ይህ ሳይፈጸም ክርክሩ በቀረበው የክስ ጭብጥ መሰረት መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ግድፈት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል አመልካች ከውል አንጻር 1ኛ ተጠሪ ላይ ክስ ሲያቀርቡ በ2ኛ ተጠሪ ላይ ከዋናው ዲኝነት ጋር የተገናኘ ግን ደግሞ ከውል ውጭ ባለ ኃላፉነት 1ኛ ተጠሪ የገነቡትን ግንባታ አፍርሶ በሕግ የተቀመጠውን የቦታ ርቀት ያስጠብቅ ተብል ይወሰንልኝ ሲለ ክሱን አጣምረው አቅርበዋል። እንዱህ ዓይነት በአንድነት ተጣምረው መታየት የሚችለ ጉዲዮች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ተነጥል ከታየ ሥነሥርዓት ሕጉ ሉያሳካው የፈለገውን ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ክርክርን የመምራት ዓላማ እንዲይሳካ ያደርጋል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 17(2) ላይ በአንድ ክስ ውስጥ የተለያዩ ዲኝነቶች ሲቀርቡ ዋናውን ወይም ከፍተኛውን ዲኝነት የሚመለከተው ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን እንዲለው ተመልክቷል። አመልካች ያቀረቡት ዋናው የክስ መሰረት ንብረታቸው ላይ ጉዲት መድረስ ጋር ተያያዝ ዲኝነት በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ ላይ የተጠየቀው ዲኝነትም ተከታይና ተጨማሪ ዲኝነት በመሆኑ ዋናውን ዲኝነት ለመወሰን ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት አብሮ መወሰን ይኖርበታል። በዚህ ረገድ የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪ ላይ የቀረበውን ዲኝነት ለመመልከት ሥልጣን የለኝም ማለቱ መሰረታዊ የሆነ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በፍርድ በተመለከተው አግባብ የክሱን መሰረት ለይተውና አብራርተው ክሱን አሻሽለው እንዱያቀርቡ በማድረግ፣ የተጠሪዎችን መልሰ በመቀበል ግራቀኙን አከራክሮ የመሰለውን እንዱወሰን ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም አዘናል። ይጸፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.