ክስ ማሻሻል አስፈላጊ ከሚሆንባቸዉ ምክንያቶች ዉስጥ አንደ የሆነው የክሱ ምክንያት ጠቃሚ አካል የሆነ ፍሬ ነገር ሳይጠቀስ የቀረ እንደሆነና ይህንኑ ፍሬ ነገር ማካተት አስፈላጊ ሆኖ ለክሱ መሰረታዊ የሆነዉ ነጥብ ግልጽ ካልሆነ፤ የክስ አቤቱታ እንዱሻሻል በማድረግ ክርክሩ በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋዉን ሥርዓት በተከተለ መንገድ ላመራና ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት በተከራካሪ ወገኖች ጠያቂነት ወይም በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ክሱ እንዱሻሻል መደረግ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 91/1
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ቡለላ ትሬዱንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር- ጠበቃ ብሩክ አሰፊ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- የሄጦሳ ወረዲ ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር - ነገረ ፈጅ ደዋኖ ሻሺ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከዉል የመነጨ ኪሳራ ነዉ የተባለዉን ለማስከፈል የተጠየቀ ዲኝነት መሰረት ያደረገ ነዉ። ክርክሩ በተጀመረበት በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ ግራ ቀኙ መካከል በቀን 04/12/2007ዓ/ም በተዋዋልነዉ ዉል አመልካች ከቻይና አገር ባለሙያዎችን፣ ኢንጂነሮችን እና ከዩሻን ግሩፔ ካምፒኒ ኤላክትሪሻኖችን ወደ አገር ዉስጥ በማስመጣት ለተጠሪ የደቄት ፊብሪካ ማሽን በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ ለመትከል ግዳታ የገባ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ለማሽን ተከላ 98,746.00 ድላር፣ የአገልግልት ክፍያ 400,000.00፣ ፊብሪካዉን ለመትከል ለሚያስፈልግ የሙያ ምክር አገልግልት 83,892፣ ለነዲጅ 103,500.00 እንዱሁም ለአልጋና ለምግብ ብር 293,000.00 ለመክፈል ግዳታ ገብቷል። አመልካች በዉለ መሰረት ባለሙያዎችን አስመጥቶ በቀን 06/12/2007ዓ/ም ሥራ ጀምሯል። ሆኖም የኤላክትሪክ ፣የዉሃ፣ የመብራት፣ የብረት፣ የኦክስጂን፣ የኬብል ትሪዮ፣ የስሚንቶ፣ የጠጠርና የመሳሰለት እጥረት በመኖሩ ተጠሪ ማቅረብ ባለመቻለ በ3 ወር ዉስጥ ሥራዉን መጨረስ አልተቻለም። እንዱሁም ተጠሪ የደቄት ፊብሪካዉን ወደ ምግብ ማቀነባበሪያ ለማሳደግ በመፈለጉና ይህንንም ለአመልካች በጽሁፍ በማሳወቁ በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ ስራዉን ማጠናቀቅ አልተቻለም። በተጨማሪም ለደቄት ፊብሪካ የተሰራዉ ግንባታ አመቺ እና አስፈላጊ ስላልሆነ ለሚፈጠረዉ ችግር ተጠሪ ኃላፉነት እንደሚወስድ በጽሁፍ ለአመልካች አሳዉቋል። ለግንባታ የሚያስፈልገዉ ኢልቬተር ካናስ የሚባለዉ እቃ አገር ዉስጥ ተፈልጎ ባለመገኘቱ የመጡት ባለሙያዎች ተመልሰዉ ሉሄደ ሲለ ተጠሪ ባለሙያዎቹ ያለሥራ ለቆዩበት ጊዜ ክፍያ እፈጽማለሁ በማለት ግዳታ በመግባቱ ባለሙያዎቹ ቆይተዉ የግንባታ ሥራዉ ተጠናቆ በቀን 14/03/2010ዓ/ም ተመርቋል።
ሥራዉ የተሰራዉ ከቻይና አገር በመጡ ባለሙያዎችና አስቀድሞ የራያ ዩኒዬን ፊብሪካ ለመትከል ወደ አገር ዉስጥ ገብተዉ የነበሩ ባለሙያዎችን በመጠቀም ሲሆን ከቻይና አገር ላስመጠናቸዉ ባለሙያዎች ደመወዝ፣ ምግብ እና የአልጋ ወጪ ለ323 ቀናት በተጠሪ ችግር ምክንያት አመልካች ተጨማሪ ወጪ ስላወጣሁ ተጠሪ ሉተካልኝ ይገባል። በዉላችን መሰረት በድላር የሚከፈለ ክፍያዎችን በተመለከተ ለአንድ ቀን 1,097.14 ድላር ስለሆነ የ323 ቀን ታስቦ 50,257.31 ድላር ከፍል 304,081.11 ድላር ስለሚቀር በዚያን ጊዜ ምንዛሬ 1 ድላር ብር 27.63 ስለሆነ ብር 8,401,761.06 እንዱከፍል እንዱወሰንልኝ። በዉለ መሰረት ተጠሪ በብር ለመክፈል የተስማማዉን በተመለከተ የ323 ቀን በቀን በብር 9781 ታስቦ መክፈል ካለበት ከብር 3,159,377.00 ዉስጥ ብር 138,484.00 ብቻ ክፍል ቀሪዉን ብር 3,020,893.09 እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ። ተጠሪ ከቻይና ለመጡ ባለሙያዎች ለምግብና ለሆቴል የወጣዉን ወጪ አልከፈለም። በዚህ ምክንያት አመልካች በቀን 700.00 ብር የሚያከራየዉ መኪና ለ69 ቀናት ተይዞ ስለቆየ ብር 48,300.00 ገቢ አጥቷል። በተጨማሪም ክፍያ ባለመፈጸሙ ለአየር መንገድ ቲኬት ቅጣት ብር 13,288.00 ወጪ አዉጥቷል። ስለሆነም ተጠሪ በአጠቃላይ ብር 11,435,942.06 ከወለድና ክሱ ካስከተለዉ ወጪዎች ጋር እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ለክሱ በሰጠዉ መልስ ለማሽን መትከያ ለመክፈል የተስማማሁበትን 98,746.00 ድላር በቀን 08/12/2008ዓ/ም በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ በኩል ብር 2,197,606.49 አመልካች ወስዶል። የአገልግልት ክፍያ ብር 400,000.00፣የምክር አገልግልት ክፍያ 83,892.00፣ የትራንስፕርትና የነዲጅ ክፍያ ብር 103,500.00 በአጠቃላይ 880,392.00 አመልካች ወስዶል።
የማሽን ተከላዉ ቀን ሲራዘም ክፍያ ይከፈላል የሚል ስምምነት የለንም። ስለሆነም ለ323 ቀናት ለማሽን ተከላ፣የምክርና የትራንስፕርት ክፍያ ተብል የተጠየቀዉ ተቀባይነት የለዉም። የ69 ቀናት የመኪና ኪራይ ክፍያ በሚል የጠየቀዉም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ያቀረበዉ በመሆኑ ዉድቅ ላሆን ይገባል። የአዉሮፔላን ቲኬት ቅጣት ብል የጠየቀዉም የማስረጃ ድጋፍ ያለዉ አይደለም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዱደረግለት በመጠየቅ ተከራክሯል። እንዱሁም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 01/04/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ያቀረበዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በማለት ዉድቅ አድርጓል። ዋናዉን ክስ በተመለከተ በግራ ቀኙ መካከል የደቄት ፊብሪካ ግንባታ ዉል በቀን 04/12/2007ዓ/ም መደረጉ አከራካሪ አይደለም። ከዚህ በኋላ ተጠሪ በቁጥር HFCU/116/68/17/08 በቀን 08/06/2008ዓ/ም በጻፈዉ ደብዲቤ የደቄት ፊብሪካ ግንባታዉ ወደ ምግብ ማቀነባበሪያ ፍብሪካ መቀየሩ በግራ ቀኙ የታመነ ነዉ። በዉለ ላይ ግንባታዉ በ90 ቀናት ዉስጥ እንዱጠናቀቅ ስምምነት ቢደረግም አመልካች ከቻይና አገር ሰራተኞችን አምጥቶ ሥራ ለመጀመር ዝግጁ ሆኖ የነበረ ቢሆንም ተጠሪ ለግንባታዉ የሚያስፈልጉትን ሥራዎች ማቅረብ ባለመቻለ ምክንያት ሥራዉ በ90 ቀናት ዉስጥ አለመጠናቀቁን ተጠሪ ካለመካደም በተጨማሪ የአመልካች ምስክሮችም ይህንኑ ስላስረደ ጊዜዉ በመራዘሙ ምክንያት በአመልካች ላይ የደረሰዉን ኪሳራ ተጠሪ የመተካት ኃላፉነት አለበት። አመልካች ሥራዉን በቀን 16/09/2008ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 16/02/2009ዓ/ም ድረስ ከራያ ዋካና የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበር ዩኒየን በመጡ ባለሙያዎች ለ198 ቀናት እንደሰራ ማስረጃዉ ስለሚያሳይ አመልካች በዉለ ከተመለከተዉ ጊዜ ዉጭ ለ102 ቀናት እንደሰራ ተረጋግጧል። አመልካች ባለሙያዎቹ ለ323 ቀናት መቆየታቸዉን በማስረጃ ስላላስረዲ ሉተካለት የሚገባዉ የ102 ቀናት ወጪ ነዉ።
እንዱሁም አመልካች በእነዚህ ቀናት 8 ባለሙያዎች በተጠሪ ሥራ ላይ እንደነበሩ አላስረዲም።
ይልቁንም ከራያ ዋከና ህብረት ሥራ ማኅበር ዩኒየን የተላከዉ ማስረጃ የሚያሳየዉ ከቻይና ከመጡ ባለሙያዎች ለተጠሪ የተላኩት 3 ሰራተኞች እንደሆኑ ስለተገለጸ ይህንን መነሻ በማድረግ ተጠሪ ለአመልካች የ2 ባለሙያዎች የ102 ቀናት ሉተካለት ይገባል። በዚህ መሰረት በዉለ የተመለከተዉ ለማሽን ተከላ የሚከፈል 98,146 ድላር፣ የአገልግልት ብር 400,000.00፣ የሙያ ምክር መክፈያ ብር 83,892.00፣ ለአገልግልት ክፍያ ብር 293,000.00 ተጠሪ መክፈለን አመልካች አልካደም። እነዚህ ክፍያዎች ከጊዜ መራዘም ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ክፍያዎች ስላልሆኑና አስቀድሞ የተከፈለ ክፍያዎች ስለሆኑ አመልካች እነዚህን ከፍያዎች ወደ ቀናት ቀይሮ እንዱከፈለዉ በድጋሚ መጠየቁ የሕግ መሰረት የለዉም። እንዱሁም ባለሙያዎቹ ከሥራ ዉጭ ሆነዉ ለቆዩበት ጊዜ የትራንስፕርት በማለት የጠየቀዉንም በዉለ መሰረት ከመቀበለም በተጨማሪ ለትራንስፕርት ወጪ ማዉጣቱን በማስረጃ ስላላረጋገጠ ዉድቅ ተደርጓል። መኪናዬ ስለተያዘብኝ የብር 48,300.00 ገቢ አጥቻለሁ በማለት እንዱተካለት የጠየቀዉም ከክርክሩ ጋር ተያያዥነት ስለላለዉ አልተቀበልንም። ከቻይና ለመጡ ባለሙያዎች የተቆረጠዉ ቲኬት ቀን በመቀየሩ ለቅጣት ከፈልኩኝ ያለዉን 13,288.00 በማስረጃ ባለማስረዲቱ አልተቀበልንም። የባለሙያዎቹ የቀን አበል 200 ድላር እንደሆነ ከራያ ዋከና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበር ዩኒየን ከመጣዉ ማስረጃ ተረጋግጧል በማለት የ2 ባለሙያዎችን በ102 ቀናት በማብዛት የአንድ የአሜሪካን ድላር በወቅቱ በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር የነበረዉ በብር 27.63 እንደሆነ በመግለጽ ተጠሪ ለአመልካች ብር 1,127,304.00 እንዱከፍል እንዱሁም ለሰራተኞቹ ለአልጋ ያወጣዉን ወጪ ብር 20,000.00 ተጨምሮ በድምሩ ብር 1,147,704.00 ከቀን 25/10/2010ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍል ወስኗል። በተጨማሪም አመልካች ለጠበቃ አበል ላወጣዉ ወጪ የዚህን ገንዘብ 10% እና የዲኝነት ክፍያ በተወሰነለት ልክ በታሪፈ መሰረት ብር 3571.55 እንዱሁም ለላልች ወጪዎች ብር 5000.00 ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍል ወስኗል።
አመልካች ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ በመ/ ላይ ቢያቀርብም ችልቱ በቀን 12/12/2012 ዓ/ም በተሰጠ ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞበታል። አመልካች በቀን 24/05/2013 ዓ/ም የተጻፈ የተሻሻለ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
በቀን 04/12/2007ዓ/ም በግራ ቀኙ መካከል በተደረገ ዉል መነሻ አመልካች የማሽን ተከላ የሚያከናዉኑ ባለሙያዎች በቦታዉ እንዱገኙ በማድረግ አመልካች የተከላ ሥራዉን በቀን 06/12/2007 ዓ/ም ስለጀመረ የ3 ወር ጊዜ ተጠናቆ ሥራዉ ሳይጠናቀቅ መዘግየት የጀመረዉ ከቀን 04/03/2008ዓ/ም ጀምሮ ነዉ። ተጠሪ በእሱ ችግር ሥራ መዘግየቱን አምኖ በቀን 05/03/2008ዓ/ም በቦርደ ዉሳኔ ባለሙያዎቹ እንዱቆዩ በማስወሰን በቀን 23/05/2008ዓ/ም ለኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዲይ ዋና መምሪያ በጻፈዉ እና በቀን 08/06/2008ዓ/ም ለአመልካች ተወካይ በጻፈዉ ደብዲቤ አሳዉቋል። በተጠሪ ጥያቄ መሰረት አመልካች ባለሙያዎቹን አገር ዉስጥ እንዱቆዩ አድርጓል። በዚህ መሰረት ሰራተኞቹ ለተጨማሪ 323 ቀናት ቆይተዋል።ተጠሪ በቀን 25/11/2009ዓ/ም በቁጥር hfcu/558/17/09 በተጻፈዉ ደብዲቤ ባለሙያዎቹ ከአንድ አመት በላይ እንደቆዩ አምኖ ወደ ሀገራቸዉ እንዲይመለሱ ለአመልካች እስካሳወቀበት ቀን ድረስ ሀገር ዉስጥ ለተጨማሪ ጊዜ እንዱቆዩ መደረጉን በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የ323 ቀናት ክፍያ የመፈጸም ግዳታ አለበት ብል አለመወሰኑ ስህተት ነዉ።
እንዱሁም በክሱ በተጠየቀዉና በዉለ ስምምነት በተደረገበት አግባብ ክፍያዎችን በድላር እና በብር እንዱከፈል አለመወሰኑ ስህተት ስለሆነ የ323 ቀናት በድላር የሚከፈለዉ ክፍያ 1097.17*323=354,385.91ድላር ነዉ፤ እንዱሁም በብር የሚከፈለዉ ክፍያ ደግሞ ብር 3,020,983.009 ስለሆነ ተጠሪ የከፈለዉ ብር 1,147,704 ተቀንሶ ብር 10,288,238.00 ለአመልካች ሉከፈል ይገባል ተብል የሥር ፍርድ ቤት ከሕግ፣ ከዉልና ከማስረጃ ዉጭ በሆነ አኳኋን የ102 ቀን የ2 ሰራተኞች ወጪ በቀን ዉል አበል በ200 ድላር ሂሳብ አስልቶ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ተብል ይታረምልኝ በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል። እንዱሁም አመልካች በተወሰነለት ገንዘብ ልክ እንኳ በታሪፈ መሰረት የከፈለዉ የዲኝነት ክፍያ ብር 17,000.00 ገደማ ሆኖ እያለ በታሪፈ መሰረት ብር 3571.55 እንዱተካለት ተብል የተሰጠዉ ዉሳኔም ከዲኝነት ታሪፍ ዉጭ ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች የተጠሪ ፊብሪካ ማሽን ተከላ አከናዉኖ ለመጨረስ በቀን 14/12/2007ዓ/ም ከተደረገዉ ስምምነት ዉጭ ላላ ተጨማሪ ሥራ እንዱሰራ በቀን 08/06/2008ዓ/ም በተጠሪ ጥያቄ የቀረበ ስለመሆኑና ከተለያዩ የአቅርቦት ችግር የተነሳ ያለሥራ የባከነ ጊዜን ጨምሮ ሥራዉ በቀን 25/11/2009 ዓ/ም እንደተጠናቀቀ ጠቅሶ ከዉጭ ሀገር የመጡ ባለሙያዎች እንዱሰናበቱ የሚል ማስረጃ ቀርቦ ባለበት ባለሙያዎቹ ሥራ ላይ የቆዩት ለ102 ቀናት ነዉ በሚል የወሰነበትን አግባብ ከመሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህ አተገባበር አንጻር ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 30/07/2013ዓ/ም የተጻፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርቧል።
አመልካች የተወሰነለትን ገንዘብ አስፈጽሞ ከተቀበለ በኋላ ያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም። የስር ፍርድ ቤት በሰጠዉ ትእዛዝ መሰረት የፋዳራል ኢሚግሬሽን በላከዉ ምላሽ ስምንት ባለሙያዎች ከ2000ዓ/ም እስከ 2002ዓ/ም ወደ ሀገር ዉስጥ እንደገቡ የገለጸበት ማስረጃ አመልካች ዉል ከፈረመበት ቀን 04/12/2007ዓ/ም ጀምሮ ዉለ እስከሚያበቃበት ቀን 30/02/2008ዓ/ም ድረስ በተጠሪ ስም ከቻይና አገር ወደ ሀገር ዉስጥ ሰራተኞችን እንዲላስገባ የሚያሳይ ነዉ። አመልካች ስምንት ባለሙያዎች በተጠሪ ስም ማስገባቱንና የቆዩበትን ጊዜ የማስረዲት ኃላፉነት የአመልካች ቢሆንም አላስረዲም።
አመልካች የተጠሪን ስራ ለመስራት የተጠቀመባቸዉን ሰራተኞች አስቀድሞ ከራያ ዋከና ዩኒየን ጋር በገባዉ ዉል መሰረት የራያ ዋከና ዩኒየንን ሥራ ለመስራት ያስገባቸዉ ሰራተኞች ናቸዉ። እነዚህን 8 ሰራተኞች ወደ ተጠሪ በማምጣት በዉለ በተቀመጠዉ ጊዜ ዉስጥ ሥራ ቢገልጽም የተጠሪን ሥራ የጀመረዉ በቀን 16/07/2008ዓ/ም እንደሆነ እና በተጠሪ ፊብሪካ የተሳተፈት 3 ባለሙያዎች እንደሆኑ ከራያ ዋከና ዩኒዬን ለፍርድ ቤቱ የተላከዉ የሰነድ ማስረጃ ያሳያል። በአጠቃላይ የራያ ዋከና ዩኒየን የላከዉ ማስረጃ እንደሚያሳየዉ ሰራተኞቹ ለ198 ቀናት ሥራ ላይ እንደቆዩና ከዚህ ላይ በዉለ የተመለከተዉ 90 ቀን ሲቀነስ ለ102 ቀናት ዉለ ጊዜ እንደተራዘመ ተረጋገጦ፣ ተጨማሪዉ ስራ ራሱን በቻለ ዉል የተፈጸመ መሆኑን፣ ውለ ላይ አመልካች ስንት ባለሙያዎችን አገር ዉስጥ አስገብቶ ስራዉን እንደሚሰራ በግልጽ ስምምነት ባለመደረጉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1738/1 መሰረት ዉለ መተርጎም ያለበት በዉለ ተገዲጅ የሆነዉን ተጠሪን በሚጠቅም መልኩ እንደሆነ የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ ሥራዉን 3 ባለሙያዎች እንደሰሩ ቢረጋገጥም ተጠሪ የሁለት ባለሙያዎችን በቀን የዉል አበል 200 ድላር አስልቶ የ102 ቀናት እንዱከፈለዉ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም በቀን 28/08/2013ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት ዉሳኔ ከመሰረታዊ የማስረጃ ምዘና አተገባበር አንጻር የያዘዉን ጭብጥ በመለወጥ ከክርክር አመራር አንጻር በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተዉ ከተጠሪ ጋር በቀን 04/12/2007ዓ/ም በተዋዋልነዉ ዉል አመልካች ከቻይና አገር ባለሙያዎችን፣ ኢንጂነሮችን እና ከዩሻን ግሩፔ ካምፒኒ ኤላክትሪሻኖችን ወደ አገር ዉስጥ በማስመጣት የተጠሪ የደቄት ፊብሪካ ማሽን በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ ለመትከል ግዳታ ገብቷል። ተጠሪ ደግሞ ለማሽን ተከላ 98,746.00 ድላር፣ የአገልግልት ክፍያ 400,000.00፣ ፊብሪካዉን ለመትከል ለሚያስፈልግ የሙያ ምክር አገልግልት 83,892፣ ለነዲጅ 103,500.00 እንዱሁም ለአልጋና ለምግብ ብር 293,000.00 ለመክፈል ግዳታ ገብቷል። ተጠሪ ለማሽን ተከላዉ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት ባለመቻለና የደቄት ፊብሪካዉን ወደ ምግብ ማቀነባበሪያ በመቀየር ለዚህ የሚያስፈልገዉን ምክንያት በዉለ በተመለከተዉ 3 ወር ጊዜ ዉስጥ የማሽን ተከላዉ ባለማለቁና ለተጨማሪ 323 ቀናት ጊዜዉ በመራዘሙ ምክንያት በድላር የሚከፈለዉ ክፍያ 1097.17*323=354,385.91ድላር እና በብር የሚከፈለዉ ክፍያ ደግሞ ብር 3,020,983.009 እንዱሁም የታጣ ገቢ ብር 48,300.00 እና ለአየር መንገድ ቲኬት ቅጣት የተከፈለ ብር 13,288.00 ጨምሮ ተጠሪ በአጠቃላይ ብር 11,435,942.06 እንዱከፍለዉ እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል። ተጠሪ ደግሞ የማሽን ተከላዉ ቀን ሲራዘም ክፍያ ይከፈላል የሚል ስምምነት የለንም። በዉለ በድላርና በብር ለመክፈል ስምምነት የተደረገበትን ክፍያዎች በሙለ ለአመልካች ተከፍልታል። ስለሆነም ለ323 ቀናት ለማሽን ተከላ፣ የምክርና የትራንስፕርት ክፍያ ተብል የተጠየቀዉ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክራል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን መርምሮ በሰጠዉ ዉሳኔ በተጠሪ ምክንያት በዉለ የተመለከተዉ ጊዜ ለ102 ቀናት በመራዘሙ የአመልካች 2 ሰራተኞች ለ102 ቀናት ያለሥራ በመቀመጣቸዉ በአመልካች ላይ ለደረሰዉ ኪሳራ ለአንድ ሰራተኛ በቀን 200 ድላር አበል ሂሳብ በማስላት ተጠሪ ለአመልካች ብር 1,127,304.00 እንዱከፍል እንዱሁም አመልካች ለሰራተኞቹ ለአልጋ ያወጣዉን ወጪ ብር 20,000.00 ተጨምሮ በድምሩ ብር 1,147,704.00 እንዱከፍል መወሰኑን የዉሳኔዉ ይዘት ያሳያል።
በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 182/2 ስር እንደተመለከተዉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ወገኖች በዝርዝር ባላቀረቡት ወይም በግልጽ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ ለመስጠት እንደማይችል ተደንግጓል። ከዚህ የምንረዲዉ የሚሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ በክሱ ላይ እና በመከላከያ መልስ ላይ ተዘርዝሮ በተገለጸ ፍሬ ነገር እና በተጠየቀ ዲኝነት ላይ የተመሰረተ መሆን እንዲለበት ነዉ።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 91/1 ስር እንደተደነገገዉ በአንድ ለፍርድ ቤት በቀረበ አቤቱታ(ክስ ወይም መከላከያ መልስ) ዉስጥ በተመለከተዉ ስህተት ወይም በግልጽ ካለመቅረብ የተነሳ ተከራካሪ ወገኖች ተገቢዉን ክርክር የማቅረብና ፍትህ የማግኘት መብቶች በጽኑ የሚነኩ መሆነቸዉን የተገነዘበ እንደሆነ የአቤቱታዉ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን ይበልጥ ያብራራል ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት ይረዲል የሚያስብል ሁኔታ በገጠመ ጊዜ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ወይም በተከራካሪ ወገኖች ጠያቂነት ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት አቤቱታዉ እንዱሻሻል ማድረግ ይችላል። በዚህ አግባብ ክስ ማሻሻል አስፈላጊ ከሚሆንባቸዉ ምክንያቶች ዉስጥ አንደ የክሱ ምክንያት ጠቃሚ አካል የሆኑ ፍሬ ነገር ሳይጠቀስ የቀረ እንደሆነና ይህንኑ ፍሬ ነገር ማካተት አስፈላጊ ሲሆን ነዉ። ለክሱ መሰረታዊ የሆነዉ ነጥብ ግልጽ ባልሆነበት የክስ አቤቱታ እንዱሻሻል ሳይደረግ ክርክሩ እንዱቀጥል በማድረግ የሚሰጠዉ ዉሳኔ የተከሳሹን የመከላከል መብት የሚያጠብ ከመሆኑም በተጨማሪ ለክርክሩ ትክክለኛ እልባት ወይም ትክክለኛ ፍትህ እንዲይሰጥ ስለሚያደርግ እንዱሁም ይህ ጉድለት እንዱስተካከል በየደረጃዉ ባለ ፍርድ ቤቶች በሚደረግ ምልልስ ሥነ ሥርዓት ሕጉ ክርክሮች በአነስተኛ ሀብት(የሰዉም ሆነ የገንዘብ) እንዱሁም በምክንያታዊ አጭር ጊዜ ጉዲዮች እልባት እንዱያገኙ ያለመዉ ዓላማ ከግብ ሳይደርስ እንዱቀር ስለሚያደርግ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 91/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት በተከራካሪ ወገኖች ጠያቂነት ወይም በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ክሱ እንዱሻሻል መደረግ ይኖርበታል።
በያዝነዉ ጉዲይ በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ እንደተገለጸዉ በዉለ ላይ ተጠሪ ለአመልካች በድላርና በብር ለመክፈል የተስማማቸዉን ክፍያዎች በሙለ ተጠሪ አስቀድሞ ለአመልካች እንደከፈለ አመልካች ካለመካደም በተጨማሪ የስር ፍርድ ቤት በማስረጃም ያረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ነዉ። እነዚህ ክፍያዎች ለማሽን ተከላ፣ ለአገልግልት ክፍያ ፣ ፊብሪካዉን ለመትከል ለሚያስፈልግ የሙያ ምክር አገልግልት ፣ ለነዲጅ ፣ ለአልጋና ለምግብ በድላርና በብር ለመክፈል ሥምምነት የተደረገባቸዉ ክፍያዎች እንደሆኑ ከግራ ቀኙ ክርክር ተረድተናል። በዚህ አግባብ ስምምነት የተደረገዉ የደቄት ፊብሪካ ተከላዉ በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ እንደሚጠናቀቅ ታሳቢ በማድረግ ጭምር ቢሆንም የክፍያዎቹ አይነት ሲታይ ለነዲጅ፣ ለአልጋና ለምግብ ለመክፈል ስምምነት ከተደረገበት ክፍያ ዉጭ ያለት ክፍያዎች በቀጥታ ከጊዜ መራዘም ጋር ግንኙነት ያላቸዉ እንዲልሆኑ ተገንዝበናል። አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተዉ በአመልካች በኩል በተፈጠረ ችግር(ምክንያት) በዉለ ከተመለከተዉ 3 ወር ዉጭ ለ323 ቀናት ጊዜዉ በመራዘሙ ለተጠሪ ሥራ ከቻይና አገር ያመጠኋቸዉ ባለሙያዎች ያለሥራ በመቀመጣቸዉ ምክንያት ኪሳራ ደረሰብኝ ወይም ለወጪ ተዲረኩኝ በሚል ምክንያት በመሆኑ የክስ አቤቱታዉን በግልጽ አብራርቶ ማቅረብ የሚጠበቅበት በዉለ በድላርና በብር ለመክፈል ስምምነት ከተደረገበት ተግባራት እና አገልግልቶች አንጻር ሳይሆን ለምን ያህል ሰራተኞች፣ ለምን ጉዲይ ምን ያህል ወጪ እንዲወጣ በማሳየት ላሆን ይገባል።ከዚህ አንጻር የስር ፍርድ ቤት አመልካች በዉለ በድላርና በብር ለመክፈል ስምምነት ከተደረገበት ክፍያዎች አንጻር ወደ ቀን ቀይሮ በጠየቀዉ መሰረት ሉከፈለዉ አይገባም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ የሚነቀፍ ባይሆንም ዉሳኔ የሰጠዉ አመልካች በክሱ ላይ ለተጠሪ ሥራ ከቻይና አገር ያስመጣቸዉና ከላላ ድርጅት ጋር በገባዉ የዉል ስምምነት መነሻ አስቀድሞ ያስገባቸዉ ሰራተኞች እና በዉለ ከተመለከተዉ የ3 ወር ጊዜ ዉጭ ለሆነዉ ጊዜ ለተጠሪ ሥራ የተሰማሩ ሰራተኞች ምን ያህል እንደሆኑና ለእነዚሁ ሰራተኞች ያወጣዉ ወጪ አይነትና መጠን በግልጽ የሚያሳይ ክስ ባልቀረበበትና ተጠሪም በዚህ አግባብ በግልጽ የተዘጋጀ ክስ ደርሶት የራሱን መከላከያ መልስ አቅርቦ ባልተከራከረበት ከተጠየቀዉ አግባብ ዉጭ በሆነ አኳኋን ዉሳኔ መስጠቱን ተገንዝበናል። የተራዘመዉ ጊዜ 102 ቀናት ነዉ ወደሚል እና የሰራተኞቹን ቁጥር 2 ናቸዉ የሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰበት አግባብም ግልጽ ካለመሆኑም በተጨማሪ በግራ ቀኙ ክርክር ላይ የተመሰረተ አይደለም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ በሚረዲ አኳኋን የክስ አቤቱታዉ እንዱሻሻል በማድረግ ክርክሩ መምራት ሲገባዉ በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋዉን ሥርዓት ባልተከተለ መንገድ እና በክሱ ተዘርዝሮ ከተመለከተዉ ዉጭ በሆነ አኳኋን ክርክሩን በመምራት ዉሳኔ መስጠቱ ስለተረጋገጠ በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የክርክር አመራር ጉድለት ተፈጽሟል ብለናል። እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የይግባኝ ሰሚ ችልትም በዚህ ረገድ የሚታየዉን ስህተት ሳያርም ይግባኙን በትእዛዝ መሰረዙ ሉታረም የሚገባዉ ስህተት በመሆኑ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 01/04/2012ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 12/12/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ አመልካች የክስ አቤቱታዉን ከላይ በፍርድ ክፍል ላይ በተገለጸዉ መሰረት በዉለ ከተመለከተዉ 3 ወር ዉጭ በተጠሪ ምክንያት የተራዘመዉን ጊዜ ብዛት፣ ለተጠሪ ሥራ ከቻይና አገር መጥተዉ በተራዘመዉ ጊዜ ሥራ ፈተዉ የተቀመጡ ሰራተኞች(ባለሙያዎች) ብዛት፣ ለሰራተኞቹ ያወጣቸዉን ወጪዎች አይነትና የወጪዉን መጠን በግልጽ ዘርዝሮ የክስ አቤቱታዉን አሻሽል እንዱያቀርብና በተሻሻለዉ ክስ ላይ ተጠሪ መከላከያ መልሱን እንዱያቀርብ አድርጎ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ ክርክሩን በመምራት ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት መልሰንለታል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.