ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 345 መሰረት ተጨማሪ ማስረጃ የመቀበልና የመመዘን ሥልጣን ያለው በመሆኑ በዚህ አግባብ ማስረጃ ተቀብል በመመዘን የሚሰጠው ውሳኔ በሥር ፍ/ቤት ክርክር ያልቀረበ ማስረጃና ሥነ-ሥርዓታዊ አይደለም የማይባልና የክርክር አመራር ጉድለት ወይም የማስረጃ ምዘና መርሕ ስህተት ልባል የሚችል ኤፍ.ቲ.ሲ(FTC) ጠቅላላ የግንባታ ሥራዎች ኃ/የተ/የግል ማሕበር እና እነ አቶ ዲንኤል ዘውዳ (4 ሰዎች)
No summary available.
ቀን፡- ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ኤፍ.ቲ.ሲ(FTC) ጠቅላላ የግንባታ ሥራዎች ኃ/የተ/የግል ማሕበር ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
**
የሰበር መዝገቡ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የስር ከሳሽ ሲሆን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ተከሳሾች፤ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ጣልቃ ገቦች ነበሩ። አመልካች ያቀረበው ክስ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነ የሰላዲ ቁጥር 3- 60518 መኪና በሻሸመኔ ከተማ እየተሽከረከረ እያለ የ1ኛ ተጠሪ ንብረት የሆነ የሰላዲ ቁጥር 3-34249 ኢት የሆነ ተሽከርካሪ የትራፉክ ደንብ በመተላለፍ የራሱን የቀኝ አቅጣጫ መንገደን ሙለ በሙለ በመልቀቅ በአመልካች ተሽከርካሪ አቅጣጫ ውስጥ በመግባት ገጭቶ ጉዲት ያደረሰ በመሆኑ ለጥገና፣ ለትራንስፕርት የወጣውን ወጪና የ15 ቀናት ገቢ በመቋረጡ የደረሰውን ጉዲት በድምሩ ብር 549,975.00 የተሽከርካሪው ባለቤት 1ኛ ተጠሪና ሹፋሩ 2ኛ ተጠሪ እንዱከፍለ ዲኝነት ጠይቋል።
1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ ጥፊት የፈጸመው የአመልካች ተሽከርካሪ በመሆኑ ለጉዲቱ ኃላፉ አይደለሁም በማለት የተከራከሩ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ጉዲዩ በላለበት ታይቷል። በልላ በኩል 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተሽከርካሪያቸው በአመልካች ተሽከርካሪ ጥፊት ተገጭቶ ጉዲት የደረሰበት ስለሆነ የጥገና ወጪ ብር 367,070.38 እና 230 ቀናት የተቋረጠ ገቢ በቀን ብር 2,154.00 ሂሳብ ብር 495,461.40 በድምሩ ብር 867,181.78 አመልካች እንዱከፍላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ባቀረበው መልስ ጥፊቱ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ ስለሆነ ለጉዲቱ ኃላፉነት የለብኝም፤
በማስረጃነት የቀረበው የፍርድ ውሳኔ በይግባኝ ተሽሯል። 3ኛ እና 4ኛ ጣልቃ ገቦች ኃላፉነቴን እንዱጋሩ በክርክሩ ጣልቃ ገብተው ይከራከሩ በማለት ጠይቋል። በአመልካች ጥያቄ መሰረት 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ጣልቃ ገብተው እንዱከራከሩ የታዘዘ ሲሆን 3ኛ ተጠሪ ያቀረበው መልስ 1ኛ ተጠሪ አስገዲጅ የሆነው 3ኛ ወገን ኢንሹራንስ ሳይኖረው ነው ያሽከረከረ። በአመልካች ተሽከርካሪ ጥፊት ጉዲት መድረሱ ስላልተረጋገጠ በኃላፉነት አልጠየቀም ያለ ሲሆን 4ኛ ተጠሪ በበኩለ የኃላፉነት ወሰኑ እስከ ብር 100,000.00 ብቻ ነው መሆኑን በመጥቀስ ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደቡብ ምድብ ችልት የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማት የግጭት አደጋው ፔላን የተነሳው ከአራት ቀናት በኋላ ነው፣ፔላን የሰራው ባለሙያ በወንጀል ክርክሩ ቀርቦ ጥፊተኛው የአመልካች ሾፋር ስለመሆኑ አስረድቷል። የክልል ፕሉስ ኮሚሽን ባለሙያ ፔላኑ ግልጽነት የላለው፣ ማን ጥፊት እንዲለበት የማያሳይ ስለመሆኑ ቀርቦ ያስረዲ ቢሆንም ፔላን ያነሳው ባለሙያ የሰጠው ምስክርነት፣ ዓይን እማኞች ከሰጡት ቃል ተመዝኖ ሉወሰን የሚገባው ነው። የአመልካች የሰው ምስክሮች የዓይን ምስክር አይደለም፤ በልላ በኩል በ1ኛ ተጠሪ በኩል የቀረቡት ምስክሮች አደጋው ሲከሰት በቦታው የነበሩ ምስክሮች መሆናቸው ሲታይ ለአደጋው ጥፊት ያለበት የአመልካች ተሽከርካሪ ስለመሆኑ የቀረበው ማስረጃ ያስገንዝባል። ስለሆነም ጥፊቱ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ ባለመሆኑ አመልካች ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም። 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ መሰረት አመልካችና 4ኛ ተጠሪ ለጉዲቱ ኃላፉ ናቸው። 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ኃላፉነት የለባቸውም። የጉዲት መጠኑ በቀረበውና ፍርድ ቤቱ ባጣራው ማስረጃ መሰረት የጥገና ወጪና የተቋረጠ ገቢ ብር 409,180.38 አመልካች ሉከፍል ይገባል። ከዚህ ወስጥ 4ኛ ተጠሪ ብር 100,000.00 ሉከፍል ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካች ያቀረበውን ይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራቀኙን አከራክሮ የአመልካች ተሽከርካሪ ጥፊት ስለመሆኑ ተመዝኖ የተወሰነ ነው፤ የአመልካች አንደ ምስክር ሾፋሩ ሆኖ እያለ የዓይን ምስክር አልቀረበም መባለ ተገቢ ባይሆንም አጠቃላይ የምዘና ውጤቱን የሚለውጥ አይደለም። የአመልካች ተሽከርካሪ ሾፋር የወንጀል ጥፊተኝነት በይግባኝ ተሽሮ የተመለሰ ቢሆንም የተመለሰለት ፍርድ ቤት ጥፊተኛ ያለው ስለመሆኑ በተጠሪዎች የቀረበውን ክርክር ላይ አመልካች የማስተባበያ ክርክር አላቀረበም። ስለሆነም ውሳኔው ላይ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም 3ኛ ተጠሪ እስከ ብር 100,000.00 ድረስ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ አምኖ ተከራክሮ እያለ መታለፈ ተገቢ አይደለም።
ጥፊቱ የ1ኛ ተጠሪ ነው። የወንጀል ጥፊተኝነት ፍርድ በሥር ሳይቀርብ ይግባኝ ሰሚ ችልቱ መቀበለ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ አይደለም። በአዋጅ ቁጥር 799/2005 መሰረት የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን የመድን ሽፊን ሳይኖረው ሲሽከረከር የነበረ በመሆኑና ይሕ ጥሰት በመሆኑ እንዱሁም ከቀረጥ ነጻ የገባውን ተሽከርካሪ ለላላ ዓላማ ሲያውል የደረሰ አደጋ ስለሆነ ጥፊቱ በፍ/ሕ/ቁ. 2035 መሰረት የ1ኛ ተጠሪ ነው። የጉዲት መጠን ገማች ፈቃድ የላለው ሰው ነው። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ይሻርልን የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ የ3ኛ ተጠሪ ኃላፉነት መታለፈና በሥር ያልቀረበ ማስረጃ በይግባኝ ቀርቦ መመዘኑ ተገቢነቱን ለማጣራት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ በማዘዙ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች የሰጡት መልስ የአመልካች ሾፋር በወንጀል ጥፊተኛ ተብሎል፤ በሥር ፍርድ ቤትም የወንጀል ጥፊተኝነት ማስረጃው ቀርቦ ነበር። ጥፊት ያለበት ስለመሆኑ ማስረጃ ቀርቦ ተመዝኖ የተረጋገጠ ነው። 3ኛ ወገን መድን ሽፊን ነበረው፣ በአደጋው ቀን ውለ ሳይታደስ በመቅረቱ ነው፤ በኋላም ታድሷል። ውለ ባለመታደሱ ላላ አካል ከሚጠይቅ በስተቀር 3ኛ ወገን የመድን ሽፊን የላለው ተሽከርካሪ ንብረት እንዱወድም ወይም እንዱገጭ የሚያደርግ አይደለም።
ከኃላፉነትም ነጻ አያደርግውም። ከቀረጥ ነጻ ለገባበት ዓላማ የዋለ ነው። ገማች ባለሙያው ፈቃድ ያለው ሰው ነው። ውሳኔው ሉጸና ይገባል ብለዋል። 3ኛ ተጠሪ በበኩለ ጥፊቱ የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ ነው።
የአመልካች ተሽከርካሪ ጥፊት አለ ከተባለ እስከ ብር 100,000.00 ድረስ ነው የኃላፉነት ወሰኔ ሲል ተከራክሯል። 4ኛ ተጠሪ እስከ ኃላፉነት ጣሪያ ድረስ እንድከፍል ተወስኖ ክፍያውን የፈጸምኩ በመሆኑ በዚህ ችልት ተከራካሪ ልሆን አይገባም ብሎል። አመልካች ለ1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች መልስ ላይ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር፣ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘውን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ያቀረበው ክስ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነ የሰላዲ ቁጥር 3-60518 መኪና በሻሸመኔ ከተማ እየተሽከረከረ እያለ የ1ኛ ተጠሪ ንብረት የሆነ የሰላዲ ቁጥር 3-34249 ኢት የሆነ ተሽከርካሪ የትራፉክ ደንብ በመተላለፍ የራሱን የቀኝ አቅጣጫ መንገደን ሙለ በሙለ በመልቀቅ በአመልካች ተሽከርካሪ አቅጣጫ ውስጥ በመግባት ገጭቶ ጉዲት ያደረሰ በመሆኑ ብር 549,975.00 የተሽከርካሪው ባለቤት 1ኛ ተጠሪና ሾፋሩ 2ኛ ተጠሪ እንዱከፍለ የሚል ሲሆን 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ጥፊት የፈጸመው የአመልካች ተሽከርካሪ በመሆኑ ለጉዲቱ ኃላፉ አይደለሁም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ባቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተሽከርካሪያቸው በአመልካች ተሽከርካሪ ጥፊት ተገጭቶ ጉዲት የደረሰበት ስለሆነ ብር 867,181.78 አመልካች እንዱከፍላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። ጉዲዩ ከውል ውጭ ኃላፉነት የጉዲት ካሣ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ሁለት ባለሞተር ተሽከርካሪዎች ሲጋጩ አንደ በአንደ ላይ አደጋ እንዲደረሰ እንደሚቆጠር በፍ/ሕ/ቁ. 2084(1) ላይ የተመለከተ ሲሆን በንዐስ ቁጥር ሦስት ላይ ደግሞ አደጋው የደረሰው በአንደኛው አሽከርካሪ ስህተት መሆኑ ከተረጋገጠ ጉዲቱን የመሸፈን ኃላፉነት ጥፊት የፈጸመው ተሽከርካሪ ስለመሆኑ ተመልክቷል።
በክርክር ሂደት ፍሬ ነገሮችን ማረጋገጥ የሚቻልባቸው ዘዳዎች ማስረጃ፣ በፍርድ ቤት በሚሰጥ የእምነት ቃል፣ ፍርድ ቤት በራሱ ግንዛቤ ሉወስድባቸው የሚችለ ጉዲዮች፣ የሕግ ግምት እና የመሒላ ቃል ናቸው። በፍትሐ ብሓር ክርክር የምንከተለው የማስረዲት ደረጃ ከሁለቱ ወገን የተሻለ ያስረዲው ማን ነው (preponderance of evidence) የሚለውን በመመርመር ነው። የማስረጃ ተገቢነት የማስረጃውና ተቀባይነትን ደንቦችን በመከተል የመወሰን ኃላፉነት ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን ኃላፉነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶች ዋና ተግባር ነው። የሥር ፍርድ ቤቶች የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማትና በመመዘን ለአደጋው ጥፊት ያለበት የአመልካች ተሽከርካሪ ስለመሆኑ የቀረበው አረጋግጠዋል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱሪ ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ሆነ የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሰበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ እንዱመለከት ሥልጣን አልተሰጠውም። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካች ተሽከርካሪ ሾፋር በወንጀል ጥፊተኛ ስለመባለ ማስረጃ ተቀብል መመዘኑ በሥር ያልቀረበ ማስረጃ ባለመሆኑ ሥነ-ሥርዓታዊ አይደለም በማለት የተከራከረ ሲሆን በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ለተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ባቀረበው መልስ በማስረጃነት የቀረበው የፍርድ ውሳኔ በይግባኝ ተሽሯል በማለት መግለጹ፣ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ፔላን የሰራው ባለሙያ በወንጀል ክርክሩ ቀርቦ ጥፊተኛው የአመልካች ሾፋር ስለመሆኑ አስረድቷል በማለት በውሳኔው መግለጹ የወንጀል ጥፊተኝነቱ በሥር ፍርድ ቤት የክርክርና የውሳኔ አካል የነበረ መሆኑን ከማሳየቱም ባለፈ ይግባኝ ሰሚ ችልትም በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 345 እንደተመለከተው ተጨማሪ ማስረጃ የመቀበልና የመመዘን ሥልጣን ያለው በመሆኑ የአመልካች ተሽከርካሪ ሾፋር ለክሱ ምክንያት በሆነው አደጋ ተከሶ ጥፊተኛ መባለን በመመዘን የሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ የክርክር አመራር ጉድለት የለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች የፈጸሙት የማስረጃ ምዘና መርሕ ስህተት የለም ብለናል።
በልላ በኩል አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 መሰረት የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ የ3ኛ ወገን የመድን ሽፊን ሳይኖረው ሲሽከረከር የነበረ በመሆኑና ይሕ ጥሰት በመሆኑ እንዱሁም ከቀረጥ ነጻ የገባውን ተሽከርካሪ ለላላ ዓላማ ሲያዉል የደረሰ አደጋ ስለሆነ ጥፊቱ በፍ/ሕ/ቁ.
2035 መሰረት የ1ኛ ተጠሪ ነው ልባል ይገባል በማለት የተከራከረ ሲሆን የፍ/ሕ/ቁ. 2035 ጥፊት ላይ የተመሰረተ ከውል ውጭ ኃላፉነትን የሚመለከት ድንጋጌ ይዘቱም ጉዲት ያደረሰው ድርጊት የተከሰተው ሕግን በመጣስ ወይም አድራጊው ሕግን በመተላለፍ ጥፊት ፈጽሞ ጉዲት ካደረሰ ለጉዲቱ ኃላፉ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። በተያዘው ጉዲይ ለጉዲቱ መንስኤ የሆነው ጥፊት የፈጸመው የአመልካች ተሽከርካሪ ስለመሆኑ ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል። አመልካች በሰበር አቤቱታው 1ኛ ተጠሪ ሕግ ተላልፎል በሚል የጠቀሳቸው ድርጊቶች ከደረሰው ግጭት/ጉዲት ጋር ተያያዥነት የላላቸው በመሆኑ አመልካች ለጉዲቱ ኃላፉ ነው በሚል የሥር ፍርድ ቤቶች የደረሱበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ተቀብለነዋል።
የካሣ መጠኑን በተመለከተ ካሣ በፍ/ሕ/ቁ. 2090(1) እንደተመለከተው ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመዛዛኝ ወይም ተመጣጣኝ መሆን እንዲለበት መርህ የተቀመጠ ሲሆን የ1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን ጉዲት በማስረጃ በማረጋገጥ የጥገና ወጪና የተቋረጠ ገቢ ብር 409,180.38 አመልካች ሉከፍል ይገባል፣ ከዚህ ወስጥ 4ኛ ተጠሪ ብር 100,000.00 ሉከፍል ይገባል በማለት መወሰኑ ተገቢ ነው። በልላ በኩል 3ኛ ተጠሪ ወደክርክሩ ጣልቃ የገባው የአመልካች ተሽከርካሪ ለሚያደርሰው ጉዲት የ3ኛ ወገን የመድን ኃላፉነት ሽፊን ሰጥቷል በሚል የአመልካችን ኃላፉነት ለመጋራት ሲሆን 3ኛ ተጠሪ የመድን ሽፊን የሰጠ መሆኑን ክድ አይከራከርም። የ3ኛ ተጠሪ ክርክር የአመልካች ተሽከርካሪ ጥፊት ያልፈጸመ በመሆኑ ለጉዲቱ ኃላፉነት የለበትም በማለት ነው። የአመልካች ተሽከርካሪ ጥፊትና ኃላፉነት ደግሞ በሥር ፍርድ ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ነው። ስለሆነም 3ኛ ተጠሪ በሰጠው የመድን ሽፊን መሰረት ብር 100,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍል መወሰን ሲገባው መታለፈ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች ብር 409,180.38 ለ1ኛ ተጠሪ ሉከፍል ይገባል፣ ከዚህ ወስጥ 4ኛ ተጠሪ ብር 100,000.00 ሉከፍል ይገባል ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ጸንቷል።
3ኛ ተጠሪ አመልካች ካለበት ኃላፉነት ውስጥ ብር 100,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍል ተወስኗል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱያስፈጽም አዘናል። ይጻፍ አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠ እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.