የከሳሽ ክስ በተከሳሽ የተካደ እንደሆነ በቅድሚያ ማስረጃዎችን አቅርቦ የማስረዲቱ ሸክም የሚወድቀዉ በመርህ ደረጃ በከሳሽ ላይ መሆኑ የማስረጃ አቀራረብ እና የማስረዲት ሸክም መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ በልዩ ሁኔታ በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም ከከሳሽ ወደ ተከሳሽ ላዞር የሚችለዉ ተከሳሽ በከሳሽ የተመለከተዉን ፍሬ ነገር አምኖ ኃላፉነት የለብኝም የሚልበትን አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር ካቀረበ ወይም ከሳሽ የህግ ወይም የፍሬ ነገር ግምት ተጠቃሚ ከሆነ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 258(1) እና 259(1)
No summary available.
ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ኩማ አስመጪና ላኪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር- ጠበቃ ዶ/ር ነዋይ ዘርጌ - ቀርበዋል ተጠሪዎች፡-
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አሰሪና ሰራተኛን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በተለያየ የቅጥር ዘመን በሳምንት በቁርጥ ከፍተኛው ብር 3,500.00፣ መካከለኛው ብር 2,000.00 እና ዝቅተኛዉ 1,500.00 እየተከፈለን ስንሰራ የቆየን ቢሆንም አመልካች የትርፍ ሰዓት ስራ አልሰራችሁም በማለት በህገ-ወጥ መንገድ የስራ ውላችንን ስላቋረጠዉ ከህገ-ወጥ ስንብት ጋር የተያያዙት የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የስራ ስንብት ክፍያ፣ ካሳ፣ ለዘገየ ክፍያ ቅጣት እና የዓመት እረፍት ክፍያ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍለን ይወሰንልን በማለት የጠየቁትን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
አመልካች በበኩለ በቀን 21/02/2013 ዓ.ም በተፃፈ መልሱ ተጠሪዎች የቀን ሰራተኞች ሆነው በሰሩት ልክ ይከፈላቸዋል እንጂ በመካከላችን የስራ ውል ግንኙነት የለም፤ ተጠሪዎች የስራ ግብር እና የጡረታ መዋጮ እንዲይቆረጥባቸው ከአመልካች ጋር የስራ ውል ግንኙነት የለንም ባለበት ክስ ማቅረባቸው ተገቢ ባለመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የስራ ውል ግንኙነት የለኝም ቢልም ይህንን በማስረጃ አስደግፍ አላስረዲም፤ ተጠሪዎች በሰሩት ልክ የሚከፈላቸው መሆኑ ብቻውን የስራ ውል ግንኙነት የለም የሚያስብል ባለመሆኑ በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል የስራ ውል ግንኙነት አለ ተብል የህግ ግምት ተወስዶል፤
አመልካች ተጠሪዎች ወደ ስራ ቦታ እንዲይገቡ በጥበቃ ሰራተኞች አማካኝነት የተከለከለ በመሆኑ አመልካች የስራ ውለን በህገ-ወጥ መንገድ ያቋረጠ መሆኑን ያሳያል፤ ደመወዝን በሚመለከት ተጠሪዎች በሰሩት ልክ የሚከፈላቸው እና ወጥነት ያለው ስለመሆኑ ከቀረበው ማስረጃ በመረጋገጡ ለክፍያ ስላት ዓላማ ብር 1,500.00 በመያዝ በዚሁ መጠን ተሰልቶ ለእያንዲንዲቸው የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የስራ ስንብት ክፍያ፣ ካሳ እና የዓመት እረፍት ክፍያ ይከፈላቸው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው አመልካች ይግባኙን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተሰርዟል።
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 29/07/2013 ዓ.ም በተፃፈ 11 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙለት ጠይቋል። የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ ተጠሪዎች የመጫን እና የማውረድ ስራ የሚሰሩ መሆናቸውን አምነው፣ ይህንንም ስራ በተለያዩ ድርጅቶች እየተዘዋወሩ የሚሰሩ እና ቋሚ ደመወዝ የላላቸው ሆነው እያለ፣ ከአመልካች ጋር ምንም ዓይነት የስራ ውል ግንኙነት ያላቸው ስለመሆኑም በማስረጃ ሳይረጋገጥ፣ እንዱሁም እንዱቀርብልን የጠየቅነው ማስረጃ ሳይቀርብ እና ምስክር የማሰማት መብታችን ያለአግባብ ታልፍ ህጉን በተሳሳተ መንገድ በመተርጎምና በመረዲት የስር ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር የስራ ውል ግንኙነት እንዲላቸው ግምት ተወስድ የጠየቁት ክፍያ በሙለ እንዱከፈላቸው መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪዎች ሰራተኞቼ አይደለም ብል በካደበት እና ፍርድ ቤቶች በኮቪድ ምክንያት በከፉል ዝግ በነበሩበት ወቅት ምስክር አላቀረበም በማለት ተጠሪዎች ያቀረቡትን ማስረጃ ሳይሰማ እና እንዱቀርቡ የተጠየቁ የሰነድና የሰው ማስረጃዎች በማለፍ ተጠሪዎች በህግ ግምት ሰራተኞች ናቸው፣ የስራ ውላቸውም በህገ-ወጥ መንገድ ነው የተቋረጠው በማለት የወሰነበት አግባብ ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች በተደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት በቀን 19/09/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ ተጠሪዎች በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከስድስት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ አገልግልት ያለን ሲሆን አመልካችም የስራ ግንኙነት ያለን ስለመሆኑ በግልጽ አልካደም፤ ማስረጃን በሚመለከት አመልካች በተደጋጋሚ ምስክሮቹን አቅርቦ እንዱያሰማ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጠውም ባለማቅረቡ ምስክር የማሰማት መብቱ ታልፍ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ከሚባል በስተቀር የሚነቀፍ ባለመሆኑ ሉፀና ይገባዋል በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደሚቻለዉ ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች ያላግባብ ከስራ ያሰናበታቸዉ መሆኑን የጠቀሱ ቢሆንም አመልካች በሰጠዉ መልስ ተጠሪዎች በቀን ሰራተኝነት በሰሩት ልክ የሚከፈላቸዉ እንጂ በመካላቸዉ የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት የላለ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሯል። አመልካች በዚህ ችልት ባቀረበዉ ቅሬታም ተጠሪዎች ሰሉጥ ወደ መጋዘን ሲገባ የማራገፍ ስራ የሚሰሩ ሲሆን የሚከፈላቸዉም ባራገፈት የኩንታል ልክ እየታሰበ መሆኑን በመጥቀስ ይከራከራል።
በአጠቃላይ የአመልካች ክርክር በአሰሪና ሰራተኛ ህጉ የሚሸፈን ዓይነት የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት በመካከላቸዉ የለም የሚል ነዉ። በመሆኑም አመልካች ተጠሪዎችን ያሰናበተዉ በህጋዊ መንገድ ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ነጥብ ከመታየቱ በፉት በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 246(1) መሰረት በጭብጥነት ተይዞ በግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ ተጣርቶ ዉሳኔ ላሰጥበት የሚገባ ትክክለኛ ጭብጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 4 ላይ በተመለከተዉ አግባብ በግራ ቀኝ መካከል የስራ ቅጥር ዉል አለ ወይስ የለም? የሚል ነዉ። ከላይ እንደተገለጸዉ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ በማድረግ የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት በመካከላቸዉ አለ በሚል ለሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ ምክንያት ይህን በቅድሚያ የማስረዲት ሸክሙ የአመልካች መሆኑንና አመልካች ምስክሮችን እንዱያቀርብ በተደጋጋሚ ታዞ ለማቅረብ አለመቻለን ነዉ።
በመሰረቱ የከሳሽ ክስ በተከሳሽ የተካደ እንደሆነ በቅድሚያ ማስረጃዎችን አቅርቦ የማስረዲቱ ሸክም የሚወድቀዉ በመርህ ደረጃ በከሳሽ ላይ መሆኑ ከማስረጃ አቀራረብ እና የማስረዲት ሸክም ጋር በተያያዘ ተቀባይነት ካገኙት መርሆዎች ዉስጥ አንደ ነዉ። ይህ መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ በልዩ ሁኔታ በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም ከከሳሽ ወደ ተከሳሽ ላዞር የሚችለዉ ተከሳሽ በከሳሽ የተመለከተዉን ፍሬ ነገር አምኖ ኃላፉነት የለብኝም የሚልበትን አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር ካቀረበ ወይም ከሳሽ የህግ ወይም የፍሬ ነገር ግምት ተጠቃሚ ከሆነ ስለመሆኑም መገንዘብ ያስፈልጋል። የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 258(1) እና 259(1) የተመለከቱት ድንጋጌዎችም ይህንኑ የሚያስገነዝቡ ናቸዉ። ከዚህ አንፃር የተያዘዉ ጉዲይ ሲታይ ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ የሚሸፈን የስራ ቅጥር ዉል ከአመልካች ጋር እንዲላቸዉ የጠቀሱ ቢሆንም አመልካች ይህን ፍሬ ነገር በግልጽ ክድ ተከራክሯል።
ተጠሪዎች ባወረደት ኩንታል ልክ ታስቦ ገንዘብ የሚከፈላቸዉ ስለመሆኑ ገልፆ መከራከሩ በአሰሪና ሰራተኛ ህጉ የሚሸፈን በመካከላቸዉ የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት መኖሩን ማመኑን የሚያሳይ አይደለም። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጠቀሰዉ የአዋጁ አንቀጽ 4 ድንጋጌም የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት የለም የሚል ክርክር ያቀረበ ተከሳሽ ይህን አስቀድሞ የማስረዲት ሸክም እንዲለበት እና የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት እንዲለ ግምት ይወሰዲል የሚል ይዘት የለዉም። ይልቁንም አመልካች ክሱን በግልጽ ክድ የተከራከረ በመሆኑ ከአመልካች ጋር በአዋጁ አንቀጽ 4 ላይ በተመለከተዉ አግባብ የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት ያላቸዉ ስለመሆኑ በቅድሚያ የማስረዲት ሸክሙ የተጠሪዎች እንጂ የአመልካች ላሆን የሚችልበት የህግ ምክንያት የለም። በመሆኑም የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት በመካከላቸዉ አለመኖሩን አመልካች በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም አለበት በሚል የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ተቀባይነት ያገኘዉን የማስረጃ አቀራረብ እና የማስረዲት ሽክም መርህን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረባቸዉን ምስክሮች ያልሰማበት ምክንያት አመልካች ምስክሮችን እንዱያቀርብ በተደጋጋሚ ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶት ማቅረብ ያለመቻለን ሲሆን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ አመልካች የሚያቀርበዉ ክርክር ወቅቱ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች በከፉል ዝግ በሆኑበት ሐምል ወር 2012 መሆኑን ነዉ። ተጠሪዎች ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረቡት መልስ ምስክሮቹ እንዱያቀርቡ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የተሰጠዉ አመልካች በአቤቱታዉ በጠቀሰዉ ጊዜ ስለመሆኑ ክደዉ አልተከራከሩም።
ሐምል ወር 2012 ዓ.ም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች በከፉል ዝግ ሆነዉ የቆዩ ስለመሆኑ ይህ ፍርድ ቤትም ግንዛቤ የሚወስድበት ፍሬ ነገር ነዉ። ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ምስክሮቹ እንዱቀርቡ ትዕዛዝ ሲሰጥም ሆነ ባለመቅረባቸዉ ምክንያት የሚወስደዉ እርምጃም ይህንኑ እዉነታ ከግምት ዉስጥ ያስገባ ላሆን እንደሚገባ ይታመናል። ይሁንና ፍርድ ቤቱ ይህን ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ከመሆኑም በላይ ምስክሮቹን የማሰማት መብት በትዕዛዝ ከታለፈ በኋላ አመልካች ይህንኑ እዉነታ በመጥቀስ ምስክሮቹ እንዱሰሙለት ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ ማድረጉንም ከግራ ቀኝ ክርክር ለመገንዘብ ተችሎል።
በአጠቃላይ በመካከላቸዉ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 የሚሸፈን የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት የላለ መሆኑን ጠቅሶ አመልካች ግልጽ ክርክር አቅርቦ እያለ እና የስራ ቅጥር ውል በመካከላቸዉ መኖሩን በቅድሚያ የማስረዲት ሸክሙ የተጠሪዎች ሆኖ እያለ፣ ምስክሮች ቀርበዉ እንዱሰሙ ጊዜዉን ያላገናዘበ ትዕዛዝ በመስጠት የአመልካች ምስክሮችን ሳይሰማ በግራ ቀኛቸዉ የስራ ቅጥር ዉል እንዲለ ግምት በመዉሰድ ስንብቱም ህገ ወጥ ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 05/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 20/07/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ በግራ ቀኝ መካከል በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 የሚሸፈን የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት መኖር ያለመኖሩን አስመልክቶ በቅድሚያ የተጠሪዎችን ምስክር እና ማስረጃ በመስማት በመቀጠል እንደአግባብነቱ የአመልካችን የሰዉ ምስክር እና ማስረጃ በመስማት እና አስፈላጊ ከሆነም ተጨማሪ ማስረጃዎችን በማስቀረብ እና በመመርመር አግባብ ነዉ የሚለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 343(1) መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
የሰበር አጣሪ ችልት በቀን 12/08/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ማ/አ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት