No summary available.
ሀምላ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ገሰሰ - ጠበቃ አቶ መከተ ዲኘው - ቀረቡ ተጠሪ፡- በአራዲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 07/08 አስተዲደር ጽ/ቤት ነገረ ፈጅ አቶ ወንድሙ አድማሱ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሰበር ችልት ጥቅምት 2 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ችልት አመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን የቤት ኪራይና የቤት ባለቤትነት ክርክር ተጠሪ አመልካችን መጥሪያ ለማድረስ በአድራሻቸው አፈላልጎ ማግኘት ባለመቻለ መጥሪያው ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ እንዱለጠፍለት ባቀረበው ቃለመሀላ መሰረት መጥሪያው በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተለጥፍ አመልካች ባለመቅረባቸው ጉዲዩን አመልካች በላለበት አይቶ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ታህሳስ 4 ቀን 2000 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች ከተጠሪ ጋር የምትከራከረው በቤት ጉዲይ መሆኑና የመኖሪያ ቤቴ እየታወቀ በሀሰት ተፈልጋ አልተገኘችም ተብል ቃለመሃላ ቀርቦ ጉዲዩ በላለበት የተሰጠው ውሣኔ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 78 መሰረት ተነስቶ ክርክሩ እኔ ባለሁበት እንዱሰማ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ካከራከረ በኋላ አመልካች ያቀረቡት ምክንያት የህግ ድጋፍ የላለው በመሆኑ ታህሣሥ 4 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ የሚነሣበትና ክርክሩ እንደገና የሚታይበት ምክንያት ያለም በማለት የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት ብይን ሰጥቷል።
አመልካች መጥሪያ ለማድረስ ከመኖሪያ ቤቴ የመጣ ሰው የለም። ተጠሪ የመኖሪያ ቤቴንና አድራሻዬን በሚገባ ያውቀዋል። ተጠሪ መጥሪያ በአካል ለእኔ ማድረስ እየቻለ ያላደረሰ ሲሆን ይኸም ቢታለፍ መጥሪያው እኔ ላየው በምችለው ቦታ በመኖሪያ ቤቴ ላይ መለጠፍ ሲገባው እኔ ልደርስበት በማልችል ቦታ መጥሪያው እንዱለጠፍ በማድረግ የፍርድ ባለመብት የሆንኩበት ውሣኔ በላለሁበት የተሻረ መሆኑን በመረዲት ፍርደ ተሰርዞ ወደ ክርክሩ እንደገባ ያቀረብኩት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ ለአመልካች መጥሪያ ለማድረስ የሥነ ሥርዓት ሕጉ በሚደነግገው መሰረት ተገቢውን ጥረት አድርገናል ስለዚህ አመልካች በአግባቡ መጥሪያ ሳይደርሰኝ አላግባብ በላለሁበት ታይቶ ውሣኔ ተሰጥቶብኛል በማለት የሚያቀርቡት ክርክርክ የህግ ድጋፍ የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች በህጉ የተቀመጠው ቅደም ተከተል መሰረት መጥሪያ አልደረሰኝም በማለት የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች በላለበት የተሰጠው ውሳኔ የሚሰረዝበት ምክንያት የለም በማለት የተሰጠው ብይን ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን እንደመረመርነው አመልካች በህጉ በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሰረት በማድረግ መጥሪያ ደርሷቸዋል ወይስ አልደረሣቸውም የሚለው ነጥብ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን ጠቀሜታ አለው። አመልካች ተጠሪ እኔን ፈልጎ አላጣኝም በማለት ተከራክረዋል። ሆኖም ተጠሪ ፈልጌ አላገኘኋቸውም በማለት በቃለ መሀላ አረጋግጧል።
ተጠሪና አመልካች የሚከራከሩት በቤት ኪራይና በአመልካች ወጭ የተሰራ ቤት ባለሀብቱ ማን ነው በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ነው። ተጠሪ የአመልካች የቤት አከራይ ነው። ተጠሪ አመልካችን የመኖሪያ ቤት ቁጥር በሚገባ ያውቃል። ተጠሪ አመልካች የምትኖርበት ቤት ባለቤት ነው። መጥሪያ ለማድረስ በአማራጭ መጥሪያ ማድረሻ መንገድች መጠቀም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ መከሰሱንና ፍርድ ቤት ክርክር ያለበት መሆኑን ለማወቅ የሚያስችለውን የተሻለውን አማራጭ የመጠቀም ግዳታና ኃላፉነት አለበት።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤትም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በአካል ቀርበው ተከራክረዋል። በዚህ ጊዜ የአመልካች የመኖሪያ አድራሻ በተጠሪ በኩል የሚታወቅና የአመልካችና ተጠሪ የክርክር መንስኤ መሆኑ በመዝገቡ ተመልክቷል የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ተጠሪ አመልካችን በአድራሻቸው ፈልጌ አላገኘናቸውም በማለት ቃለመሀላ ሲያቀርብለት መጥሪያው በፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ እንዱለጠፍ ማድረጉ ስህተት ነው። ምክንያቱም አመልካች የመኖሪያ አድራሻ በግልፅ የሚታወቅ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 105 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት መጥሪያው በአመልካች የመኖሪያ ቤት ላይ እንዱለጠፍ ትዕዛዝ መሰጠት ነበረበት። ስለሆነም አመልካች በህጉ የተደነገገው ቅደም ተከተል መሰረት መጥሪያ በወቅቱ በአግባቡ እንዱደርሣቸው ሣይደረግ ክርክሩ ታይቶ መወሰኑ ስለተረጋገጠ የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አመልካች በላለበት በማየት ታህሣሥ 4 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 78 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት በመሰረዝ አመልካች በክርክሩ ገብተው የሚያቀርቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ ውሣኔ መሰጠት ሲገባው ታህሣሥ 4 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠሁትን ውሣኔ የማነሳበት ምክንያት የለም በማለት የሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጥቅምት 6 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ብይን ተሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አመልካች በላለበት አይቶ ታህሣሥ 4 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ ነክ የሰበር ችልት ጉዲዩን እንደገና አመልካች ባለበት አይቶ ውሣኔ ይሰጥ ዘንድ በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.