No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ አማረ ገላው - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት በመዝገብ መጋቢት 8 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ብይንና የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 16 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት መጋቢት 23 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስላመለከተ ነው።
በዚህ መዝገብ ለሰበር ችልቱ የቀረበው ክርክር በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 164 ንኡስ አንቀጽ 1 እና ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ እውቅና እና ጥበቃ የተሰጣቸውን መብቶች ለማስከበር የሚቀርብ አቤቱታ ወይም ጥያቄ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበትን ሁኔታ የሚመለከት ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ለደሴ ወረዲ ፍርድ ቤት ኀዲር 21 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ/ አመልካች/ የደረጃ እድገት እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ክስ ነው። የአሁን አመልካች ተጠሪ ያቀረበው ክስ ከዚህ በፉት በፍርድ ያለቀ ነው። የከሳሽ /ተጠሪ/ ክስ በይርጋ ይቋረጣል የደረጃ እድገት በወድድር የሚሰጥ በመሆኑ ከሳሽ ይገባኛል በማለታቸው የሚሰጥ አይደም የሚል ክርክር ለወረዲው ፍርድ ቤት አቅርቧል።
የወረዲው ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ቀደም ብል በአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ የደረጃ እድገት እንዱሰጣቸው ክስ አቅርበው የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ውሣኔ ከሰጠላቸው በኋላ የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የላለው መሆኑን በመግለጽ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የቦርደን ውሣኔ የሻረ በመሆኑ ጉዲዩ የመጨረሻ ፍርድ አልተሰጠበትም። ክስ በይርጋ ይቋረጣል የሚለው የተከሳሽ/የአሁን አመልካች/ መቃወሚያ በተመለከተ የአሁን ተጠሪ ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 377/96 የተደነገገው የጊዜ ገደብ ሣያልፍ ክስ አቅርቦ የነበረና ክርክር ሑደት እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ደርሶ ቦርደ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን እንደላለው የተወሰነ በመሆኑ ተጠሪ ለቦርደ የቀረበው ክስና ክርክር የይርጋው ጊዜ የማያቋርጥ ነው በማለት የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ በመቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ተጠሪና አመልካች በዋናው ጭብጥ ላይ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ለተጠሪ የደረጃ እድገቱን ሉሰጣቸው ይገባል የሚል ውሳኔ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካችን ይግባኝ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
የአመልካች ነገረ ፈጅ መጋቢት 23 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ ሶስት ገጽ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን የአቤቱታቸውን ፍሬ ነገርም የወረዲው ፍርድ ቤት የተጠሪ ክስ በይርጋ ይቋረጣል በማለት ያቀረብነው የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያለፈብን አላግባብ ነው። የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ጉዲዩን አይቶ ውሣኔ የመስጠት የሥረ- ነገር ሥልጣን ለላለው አካል ማለትም ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ያቀረቡ በመሆኑ የይርጋው ጊዜ መቆጠሩን ያቋርጠዋል በማለት የሰጠው ብይን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162 አንቀጽ 164 እና አንቀጽ 147 ድንጋጌዎች ያላገናዘበ ነው የወረዲው ፍርድ ቤት ብይን ስለ ይርጋ መቋረጥ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1851/ለ/ የተደነገገውን ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ይኸም ቢታለፍ ያለ ውድድር ለተጠሪ የደረጃ እድገት እንድንሰጥ የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኛችንን በመሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር የሚጣራ ነጥብ ያለው በመሆኑ ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተጠሪ ግንቦት 1 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ ሶስት ገጽ መልስ አቅርበዋል። ተጠሪ ከአመልካች ጋር የሚያከራክራቸው ጉዲይ አመልካች ላወጣው የሥራ መደብ የትምህርት ማስረጃዬን ማለትም ለመወዲደር የሚያስችለኝን ዱፔልማ በማያያዝ ለውድድር ስቀርብ ዱፔልማውን ሥራ ስትቀጠር ያላስመዘገብከው ስለሆነ እንደማስረጃ አይያዝልህም ብል ስለከለከለኝ እየሰራሁ ተምሬ በዱፔልማ የተመረቅሁበት በፏርቸዚንግ የሥራ ሙያ ያወጣው የሥራ መደብ ብቸኛ ተወዲዲሪ ሆኜ ቀርቤ በእድገት ሉሰጠኝ ሲገባ አላግባብ ሲከለክለኝ በወቅቱ አቤቱታዬን ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ አቅርቤ ቦርደ የሥራ መደቡ ሉሰጠኝ እንደሚገባ ወስኗል። አመልካች በውሣኔው ቅር ተሰኝተው ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶት ነበር። አመልካች ውሣኔው የሕግ ስህተት አለበት በማለት ለዚህ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበው ችልቱ የግራ ቀኛችንን ክርክር ከሰማ በኋላ ጉዲዩ የግል የሥራ ክርክር በመሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን የለውም በሚል ምክንያት የቦርደንና የክልለን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሽሮታል። ከዚህ በኋላ የሰራተኛ ማህበሩና አመልካች ባደረጉት ውድርድር አመልካች የእኔንና የላልች ሰራተኞችን ዱፔልማ ተቀብል መድቦኛል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት ለወረዲው ፍርድ ቤት ያቀረብኩትን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም ለቦታው የቀረብኩ ብቸኛ ተወዲዲሪ በመሆኔ አመልካች ያቀረበው የይርጋ እና የፍሬ ጉዲይ ክርክር የሕግ መሰረት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል።
አመልካች በጽሐፍ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር አመልካችና ተጠሪ በጽሐፍ ያቀረቡት ክርክር ይዘት በእጭሩ ካላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠሪ ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎችና ይህ የሰበር ችልት በመዝገብ ከሰጠው የሕግ ትርጉም ጋር በማገናዘብ ውሣኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካችና ተጠሪ ካቀረቡት ክርክር ለመገንዘብ እንደቻልነው በመጀመሪያ ተጠሪ አመልካች ሥራ ከተቀጠርኩ በኋላ ያገኘሁትን የትምህርት ማስረጃ /ዱፔልማ/ በመቀበል ብቸኛ ተወዲዲሪ በሆንኩበት የሥራ መደብ የደረጃ እድገት ሰጥቶ ሉመድበኝ ይገባል የሚል ክስ ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ አቅርበው ቦርደ የአመልካችንና የተጠሪ ክርክር ከሰማ በኋላ ውሣኔ ሰጥቶ ነበር። አመልካች የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቦርደን ውሣኔ በማጽናቱ አመልካች ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበው የሰበር ችልቱ ጉዲዩ የውል የሥራ ክርክር ሣይሆን የግል የሥራ ክርክር በመሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ጉዲዩን የማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም በማለት በሰበር መዝገብ ኀዲር 10 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ ከዚህ በኋላ ለደሴ ወረዲ ፍርድ ቤት ኀዲር 24 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ አመልካች የደረጃ እድገት እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች የተጠሪ ክስ በይርጋ ይቋረጣል በማለት ያቀረበው መቃወሚያ ውድቅ በመደረጉ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል።
አመልካች በሥርና በሰበር የሚከራከረው ተጠሪ የመጀመሪያውን ክስ ያቀረበው ጉዲዩን አይቶ ውሣኔ ለመስጠት ሥልጣን ለላለው አካል መሆኑ ይህ የሰበር ችልት በሰጠው ውሣኔ ተረጋግጧል። ተጠሪ ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ለላለው አካል ያቀረበው ክስ የይርጋ ጊዜ መቆጠርን አያቋርጠውም በማለት ሲሆን ይህ የአመልካች ክርክርና ይህ የሰበር ችልት ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ለላለው ፍርድ ሰጭ አካል ክስ ማቅረብ ይርጋ አያቋርጥም በማለት በስር መዝገብ የሰጠውን የሕግ ትርጉም በአጠቃላይ በሕግ የይርጋ የጊዜ ገደብ መደንገግ ካስፈለገበት መሰረታዊ ምክንያትና ፍርድ ቤቶችና ላልች የዲኝነት ነክ ሥልጣን ያላቸው አካላት አንድ ጉዲይ ሲቀርብላቸው ላላኛውን ተከራካሪ ከመጥራታቸው በፉት ስላለባቸው ግዳታና ኃላፉነትና የይርጋ የሕግ ድንጋጌዎችና ይርጋ የሚቋረጥባቸውን ሁኔታዎች መሰረታዊ አተረጓጏም መርሆች በመመርመር ውሣኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩ አይቶ የመወሰን ሥልጣን ለላለው ፍርድ ቤት ወይም የዲኝነት ነክ ሥልጣን ላለው አካል ክስ መቅረቡና ክርክር መካሄደ ይርጋን አያቋርጥም በማለት አመልካች የሚያቀርበው ክርክር ሕግ አውጭው በተለያዩ የሕግ ማእቀፍች መብት አለኝ ወይም መብቴ ተጥሶብኛል የሚል ማናቸውም የተፈጥሮ ወይም የሕግ ሰውነት መብት ያለው አካል በማቅረብ መብቱን የሚጠይቅበትን የጊዜ ገደብ በሕግ ከሚደነግግበት መሰረታዊ ዓላማ አንፃር መታየት ያለበት ነው። ሕግ አውጭው ማናቸውም ሰው በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክሱን ለፍርድ ሰጭ አካላት ካላቀረበ ጥያቄው በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን በሕግ የሚደነግግበት አንደኛው ምክንያት መብት አለኝ ወይም መብቴ ተጥሶብኛል የሚል ሰው ተገቢውን ትጋት በማድረግ በሕግ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ መብቱን እንዱጠይቅ ለማድረግና መብቱን በሕግ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልጠየቅ ዲተኛ የሆነ ሰው ጊዜው ካለፈ በኋላ ክስ የማቅረብ መብቱን ለመገደብና መብቱን ቀሪ በማድረግ ሕግ ማእቀብ መጣልና መቅጣት ነው። አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ በተመለከተ የአሰሪና ሰራተኛ የሥራ ክርክር ችልትና የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 377/96 የተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፉነት ያለ መሆኑን ከአዋጁ አንቀጽ 138 እና ከአዋጅ አንቀጽ 147 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል። ተጠሪ መብቱን ለማስከበር ተገቢውን ጥረት ማድረግ የደረጃ እድገት አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ወሳኝ ቦርድ ነው በሚል እምነት ክሱን ለቦርድ ያቀረበ ሲሆን ቦርደም ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አለኝ በሚል እምነት ተከሳሹ አለኝ የሚለውን ክርክር እንዱያቀርብ መጥሪያ ልኮ የከሳሽና የተከሳሽ ክርክር በመስማት ውሣኔ ሰጥቷል። የቦርደን ውሣኔ በይግባኝ የተፈፀመ የሕግ ስህተት ካለ መርምሮ የማረም ሥልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቦርደ ውሣኔ የሰጠው በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረትና በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ድንጋጌዎች መሰረት መሆኑን በማረጋገጥ አጽንቶታል። የትኛው ጉዲይ የግል የሥራ ክርክር ነው?፣ የትኛው የደግሞ የወል የሥራ ክርክር ባህሪ ይኖረዋል? የሚለውን በመተርጏም ይህ ሰበር ችልት በመዝገብ ቦርደ ሥልጣን የለውም በማለት መወሰኑ ተጠሪ ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ክስ አቅርቦ እስከ ሰበር ድረስ በተከራከረበት ጊዜ ውስጥ ይርጋ ሉቋረጥለትና ጉዲዩ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 182 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ይርጋው እንደ አዱስ ሉቆጠር አይገባውም በማለት ተጠሪ የሚያቀርበው ክርክር በሕግ የይርጋ የጊዜ ገደብ መደንገግ ያስፈለገበትን አጠቃላይ መሰረታዊ ዓላማ ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በሁለተኛ ደረጃ አመልካች ተጠሪ የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ጉዲዩን አይቶ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን የላለው በመሆኑ ለቦርደ ያቀረበው ክስ ይርጋው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 164 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት አይቋርጥም በማለት ያቀረቡት ክርክር ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት ወይም የዲኝነት ሥልጣን በሕግ የሰጠው ላላ አካል የከሳሽ ክስ ከተቀበለ በኋላ ለተከሳሹ መጥሪያ ከመላኩ በፉት በሕግ እንዱያደርግ ከተጣለበት ግዳታና ኃላፉነት አንፃር መታየት አለበት። አንድ ጉዲይ ዲኝነት አይቶ ውሣኔ እንዱሰጥ የክስ አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት ወይም በሕግ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን የተሰጠው አካል ለተከሳሹ ክስ አቤቱታውን ከመጥሪያ ጋር በመላክ ከማከራከሩ በፉት የክስ ማመልከቻውን መመርመርና ጉዲዩን አይቶ የመወሰን የስረ-ነገር ወይም የግዛት ክልል ስልጣን የላለው መሆኑን ከተረዲ የቀረበለት የክስ አቤቱታ አይቶ የመወሰን ሥልጣን የላለው መሆኑን በመግለጽ ውሣኔ ላሰጥ እንደሚገባው ከፍትሐብሕር ሥነ- ሥርአት ሕግ ቁጥር 9 እና 23 ንኡስ አንቀጽ 1/ለ/ ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ወይም ከሕግ የዲኝነት ነክ ሥልጣን የተሰጠው አካል የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ ጉዲዩን አከራክሮ ለመወሰን የሚችል መሆኑን በማመን ከሳሽ ከተከሳሹ መጥሪያ እንዱያደርስ ትእዛዝ ከሰጠና ተከሳሽም የፍርድ ቤቱን መጥሪያ ወጭ በማድረግ ለተከሳሹ በማድረስ አሳውቆ ከሆነ ይርጋው የሚቋረጥ መሆኑ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1851/ለ/ የተደነገገው ድንጋጌ ከሳሽ ክሱን ሰምቶ ለመወሰን ለሚችል አካል የማቅረብ ኃላፉነት ያለበት ቢሆንም ዋንኛው ኃላፉነት የክስ አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤት ለተከሳሹ መጥሪያ ከመላኩና ክርክር መስማት ከመጀመሩ በፉት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን ያለው መሆኑን ወይም አለመሆኑን መመርመርና መወሰን እንዲለበት የሚያመለክት ነው።
በያዝነው ጉዲይ ክርክሩ ይህንን ያሕል ጊዜ የፈጀው ተጠሪ ክሱን ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ በማቅረቡ ምክንያት ብቻ አይደለም። የተጠሪን ክስ የተቀበለው ቦርድ ጉዲዩን ከማየቱ በፉት ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው መሆኑን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 231 ንኡስ አንቀጽ 1/ለ/ መሰረት በመመርመር ጉዲዩን አይቶ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን የለኝም በማለት ተወስኖ ጉዲዩን ባለመዝጋቱ ምክንያት ነው። ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የዲኝነት ነክ ስልጣን የተሰጣቸው አካላት በሕግ የተጣለባቸውን ግዳታና ኃላፉነት በአግባቡ ባለመወጣታቸው ወይም ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያላቸው ወይም የላላቸው ስለመሆኑ የሕጉ ድንጋጌ አሻሚ፣በጠቅላላ አነጋገር የተገለፀና ክፍተት ያለበት በመሆኑ ምክንያት አከራካሪና የሕግ ትርጉም መስጠት የሚያሰፈልገው በመሆኑ ምክንያት ጉዲዩን መወሰን ሥልጣን እንዲላቸው በመተርጏም ክርክሩን ሲሰሙ ለቆዩበት ጊዜ ይርጋው አይቋረጥም በሚለት ከሳሽ ክስ የማቅረብ መብቱ ይርጋ እንዱታገድ የሚደረግበት ምክንያት የለም። በእነዚህ አይነት ሁኔታ የይርጋ ጊዜ መቆጠሩ መቋረጥና ከሳሽ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1852 ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሰረት ሥልጣን ላለው አካል ክሱን ሲያቀርብ እንደአዱስ ይጋው ሉቆጠርለት የሚገባ በመሆኑ አመልካች ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
3.አመልካች ያቀረበው ክርክር ማንኛውም ሰው በፍርድ ሉያልቁ የሚችለ ጉዲዮችን ለፍርድ ቤት ወይም በሕግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብ መብት ያለው መሆኑ በሕገ-መንግቱ አንቀጽ 37 ከደነገጋቸው ጋር ማገናዘብ ያስፈልጋል። የይርጋ የሕግ ድንጋጌዎች መብታቸውን ለመጠየቅ ተገቢውን ትጋት ያደረጉና ዲተኛ ያልሆነ ሰዎች ፍትህ የማግኘት መብት በማያሣጣ ሁኔታ በጠባቡ ሉተረጏሙና ፍትህ የማግኘት መብትን በሚያረጋግጥ መንገድ ተግባራዊ ሉሆኑ ይገባቸዋል። መብታቸውን ለፍርድ ቤት ወይም በሕግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው ላላ አካል የሕጉ የጊዜ ገደብ ከማለፈ በፉት ለማቅረብ ተገቢውን ትጋት ያደረጉ ሰዎች ላይ የይርጋ ጊዜ መቆጠሩ እንዱያቋረጥ የሚያደርግ የሕግ አተረጓጏም በመጠቀም የይርጋ ጊዜ አላግባብ እንዱቆጠር በማድረግ የዜጏች ፍትህ የማግኘት መብት እንዲይሸራረፍና በዚህ ምክንያት የፍትህ መዛባት እንዲይደርስ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ውስጥ የውል የሥራ ክርክር አይቶ የመወሰን ሥልጣን ባለው የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ክሱን አቅርቦ ክሱ በቦርደና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በአግባቡ ያቀረበ መሆኑን አረጋግጠው ውሣኔ ሰጥተውበታል። ጉዲዩ የወል የሥራ ክርክር ነው? ወይስ የግል የሥራ ክርክር? የሚለው እስከ ሰበር ድረስ ያከራከረ ጭብጥ ሲሆን ጭብጡ ይህ በሰበር ችልት የወሰነው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በመስጠት ነው። በዚህ ሁኔታ ተጠሪ በመጀመሪያ ክሱን ያቀረበው ሥልጣን ለላለው አካል ስለሆነ ይርጋው ሉቋረጥ አይገባም በማለት አመልካች የሚያቀርበው ክርክር መብቱን ለማስከበር ተገቢውን ትጋት በማድረግ በሕግ የዲኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ክስ ያቀረበውን የተጠሪን ሕገ-መንግስታዊ ፍትሕ የማግኘት መብት በሚያጣብብ ሁኔታ ችልቱ የሕግ ትርጉም እንዱሰጥ የሚጠይቅ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 በዘረዘርናቸው መሰረታዊ ምክንያቶች ከዚህ በፉት አምስት ዳኞች ተሰይመው በመገብ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠርና ስለ ይርጋ መቋረጥ የሰጡትን የሕግ ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 4 በሚደነግገው መሰረት በመለወጥና የሕግ ትርጉም በመስጠት ወስነናል።
አመልካች ተጠሪ ያለ ውድድር እድገት ሉሰጠው አይገባም በማለት ያቀረበውን ክርክር በተመለከተ አመልካች ያቀረበውን ክርክር ለማስረዲት አለመቻለንና በአንፃሩ ተጠሪ ክርክሩን ያስረዲ መሆኑን በማረጋገጥ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ሰጥተውበታል። አመልካች ለቦታው ብቁ የሆኑ ሰራተኞች እንዱወዲደሩ ማስታወቂያ ያወጣና ተጠሪ መስፈርቱን አሟልቶ ያቀረበ ብቸኛ ተወዲዲሪ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የደሴ ወረዲ ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ የሰጡበት በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 80 ንኡስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ለሰበር ችልት ከተሰጠው ሥልጣን ውጭ የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና ክርክር በመሆኑ አልተቀበልነውም። ስለሆነም የወረዲውና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት አጽንተነዋል።
የአማራ ክልል የደሴ ወረዲ ፍርድ ቤትና የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
ሥልጣን ለላለው ፍርድ ቤት ወይም በሕግ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል ክስ ቀርቦ ክርክር ሲደረግ መቆየቱ የይርጋ ጊዜ መቆጠሩን ያቋርጠዋል ብለናል።
የተጠሪ ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት
No topics extracted.