No summary available.
ሐምል 19 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ገመቹ ቡቻላ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ በቀለ ኩማ(ቡቻላ) - በላለበት መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የውርስ ንብረት ክፍፍል የሚመለከት ነው። ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በማጽናቱ በውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል ሲል አመልካች አቤቱታ በማቅረቡ ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ሰበር ችልት እንዱመረመር የተያዘው ጭብጥ በተጠሪ በኩል ክስ የቀረበለት የወረዲ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም ያለውን የከፍተኛው ፍ/ቤት አጽንቶታል። ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ጉዲዩ የውርስ ክርክር ነውና የወረዲው ፍ/ቤት ሥልጣን አለው ካለ በኋላ በፍሬ ጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙ ወደ ወረዲው ፍ/ቤት ሳይመልስ መወሰኑ እና ቀደም ሲል በክልለ ሰበር ችልት የተወሰነ ነው ሲል የጠቀሰው መዝገብ ውሳኔ ይዘት አግባብነት ለመመርመር ሲባል ተጠሪ እንዱቀርብ ታዟል። ተጠሪ መጥሪያ ተቀብል መልስ አልሰጠም በዚሁ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
እኛም የቀረበውን አቤቱታ ከሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ አንፃር ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ከአመልካች አቤቱታ መረዲት የተቻለው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለው ክርክር የውርስ ንብረት የሚመለከት ነው። ቀደም ሲል አመልካች የአባቴን የውርስ ንብረት ድርሻ ያካፍለኝ ሲል ተጠሪ ያቀረበው ክስ በቀበላው በማህበራዊ ፍ/ቤት ታይቶ ከተወሰነለት በኋላ አመልካች እስከ ክልለ ሰበር ችልት አቤቱታ አቅርቦ የክልለ ሰበር ችልት በመ/ቁ. 4665 በሰጠው ትእዛዝ የአሁን አመልካች (ሥር ተከሳሽ) የመከላከያ ምስክር ሳይሰማ ውሳኔ መስጠቱን በመንቀፍ ይህው እንዱፈፀም ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለሱን፣ከዚያም ክርክር ተደርጏ ከተወሰነ በኋላ በይግባኝ በድጋሚ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲደርስ ተጠሪው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው የውርስ ንብረት መጠየቁ ተገቢ አይደለም ተብል መሻሩን ተጠቅሷል። እንግዱህ ለአሁኑ የሰበር ማመልከቻ መነሻ የሆነው ክርክር ከዚህ በኋላ በእደሳ መልክ የተጀመረ መሆኑን ተረድተናል። ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ ካገኘ በኋላ የውርስ ንብረት ክፍያ ጥያቄ ለወረዲው ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ወረዲው ፍ/ቤት የክልለን የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 110/99 በመጥቀስ የይዞታ ክርክር በቀበላ ማህበራዊ ፍ/ቤት መታየት አለበት ሲል መዝገቡን ዘግቷል። ከፍተኛው ፍ/ቤቱም ይህንኑ አጽንቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንን ውሳኔ ለመስጠት የጠቀሰው ምክንያት በግራ ቀኙ መካከል ያለው ክርክር የውርስ ንብረት የሚመለከት በመሆኑ የወረዲው ፍ/ቤት ሥልጣን አለው የሚል ነው። እንግዱህ የጉዲዩ አመጣጥ ይህንን የመሰለ መሆኑን ከተረዲን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፍሬ ነገሩ ላይ ውሳኔ መስጠቱ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን እንደሚከተለው መርምረናል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1/ በግልጽ እንደተመለከተው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሥር በመጀመሪያ መቃወሚያ ብቻ የወሰነውን ውሳኔ የለወጠ እንደሆነ የሥር ፍ/ቤት ወደ ክርክሩ ገብቶ እንደገና እንዱመለከተው መዝገቡን ሉመልስለት እንደሚችል ይደነግጋል። በርግጥ የዚህ ድንጋጌ የተቀመጠው መሪ ቃል አስገዲጅ ሆኖ አይታይም። ነገር ግን በግራ ቀኙ በኩል የሚቀርቡት የፍሬ ነገር ክርክሮች እና ማስረጃዎች በአግባቡ ለማጣራት ይቻል ዘንድ ለሥር ፍ/ቤት መመለሱ አስፈላጊ ይሆናል። በተለይም በዚህ ጉዲይ ላይ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን የፍሬ ነገር እና የማስረጃ ክርክር ከመመርመር እና ማጣራት አንፃር የመጨረሻው የሥልጣን እርከን በመሆኑ የግራ ቀኙን የይግባኝ እድል የሚያጣብብ መሆኑንም መገንዘብ ይቻላል። ከዚህም ላላ የመ/ደረጃው ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ስልጣን የለኝም ሲል መዝገቡን መዝጋቱ እንጂ አመልካች ያነሳው የይርጋ ክርክርም እልባት ያልተሰጠው ነጥብ መሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል።
ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሥር ፍ/ቤት በተገቢው ሥነ-ሥርአት ክርክር ያልተደረገበትን ፍሬ ነገር ጉዲይ በዚያው አጠቃል ውሳኔ መስጠቱ የሙግት አመራር እና የሥነ-ሥርአቱን የሥልጣን ክፍፍል መነሻ ሐሳቦች በአግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ ከሥነ-ሥርአት መርህ አንፃር ስሕተት ያለው ሆኖ አግኝተናል።
ከዚህም ላላ የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ውሳኔ በይዘቱም ሲታይ ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ማቅረቡ ተገቢ አልነበረም ሲል ከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ጉዲዩ ወደ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተመልሶ በአዱስ መልክ ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ ይዞ ክስ አቅርቦ በሥልጣን ጉዲይ ውሳኔ ተሰጥቶበት ከፍተኛው ፍ/ቤት ያፀናውን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሁለት የከፍተኛ ፍ/ቤት መዛግብት በማጣመር የሰጠው ውሳኔም ሥነ-ሥርአቱን ተከትል የቀረበ አይደለም። በመጨረሻም ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የጠቀሰው የሰበር መ/ቁ. 4665 ንብረት ይከፊፈለ የሚል ሳይሆን የአመልካች የመከላከያ ምስክር እንዱሰማ ወደ ሥር ፍ/ቤት የተመለሰ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ የግራ ቀኙ የፍሬ ነገር ክርክር በጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት በአግባቡ ያልተጣራ መሆኑን ያመለክታል። ስለሆነም የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 22866 የሰጠው ውሳኔ ከሙግት አመራር መርህ እና ሥነ-ሥርአት አንፃር መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል። የክልለ ሰበር ችልትም ይህንኑ ማረም ሲገባው ማለፈ ተገቢ አይደለም።
ስለሆነም ውሳኔው ሉታረም ይገባል ብለናል። ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22866 በ26/03/2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 24680 በ27/4/2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሻሽል ተከታዩ ተወስኗል።
የግራ ቀኙ ክርክር የውርስ ጉዲይ ነውና የወረዲው ፍ/ቤት የመዲኝት ሥልጣን አለው ሲል የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
በግራ ቀኙ በኩል የቀረበውን የፍሬ ነገር ክርክር የወረዲው ፍ/ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341/1/ መሰረት መልሰናል።
No topics extracted.