No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ የትምወርቅ ሰብስቤ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሸዋረጋ ደመቀ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የአመልካች የክስ ምክንያት ቀደም ሲል ውሳኔ የተሰጠበት ነው በማለት የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ፍርድ በአግባቡ ለመሆኑ ለመመርመር ነው።
የግራ ቀኙ ክርክር የእርሻ መሬት ይዞታን የሚመለከት ነው። ከሳሽ አመልካች ሆና ተጠሪ ተከሳሽ ነበር። ተጠሪ ያለአግባብ የያዘውን የእርሻ መሬት እንዱለቅልኝ ስትል አመልካች በሸርካ ወረዲ ፍ/ቤት ክስ ያቀረበች ሲሆን ተጠሪ በተመሳሳይ ጉዲይ በመ/ቁ. 345/97 በ14/6/2001 ዓ.ም ውሳኔ ተሰጥቷል ሲል መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን የወረዲው ፍ/ቤት ቀደም ሲል በፍሬ ጉዲዩ ላይ ውሳኔ ያልተሰጠ እና ይልቁንም ከሳሽ ማስረጃ አሟልታ ክስ እንድታቀርብ መብት ተጠብቆላት መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን ጠቅሶ መቃወሚያውን ውድቅ ማድረጉን መዝገቡ ያስረዲል። በፍሬ ጉዲዩ ላይ ማስረጃ ሰምቶ ተጠሪውን መሬት ለአመልካች እንዱለቅ ወስኗል። የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህንኑ አጽንቷል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ በጉዲዩ ላይ ቀደም ሲል ውሳኔ ተሰጥቶበታል ይህ ከሆነ ደግሞ በድጋሚ ላታይ አይገባም (res judicata) በሚል የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ሽሯል።
ለዚህ ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። ተጠሪም በሰጠው መልስ ቀድሞ ለአመልካች የተጠበቀ መብት የለም መዝገቡ በውሳኔ ተዘግቷል በማለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና አመልክቷል።
እኛም ከፍ ሲል ከተመለከተው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሥር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ የሻረው ጉዲዩ ቀድሞ ውሳኔ ያገኘ ነው በሚል ምክንያት መሆኑን ከውሳኔው ተረድተናል።
ከሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ይዘት መረዲት የቻልነው አመልካች ቀደም ሲል ያቀረበችው ክስ በፍርድ ቤቱ ከተሰማ በኋላ የአመልካች ክስ ግልጽነት የሚጏድለውና ማስረጃም ያልተሟላ በመሆኑ ማስረጃዋን አሟልታ ክስ እንድታቀርብ መብት ተጠብቆላት መዝገቡ የተዘጋ ስለመሆኑ ነው። ከዚህ መረዲት እንደሚቻለው በፍሬ ጉዲዩ ላይ የተሰጠ ውሳኔ አለ ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ ነው። ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ ሙለ በሙለ የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፍርድ አልሰጠም። ይልቁንም ማስረጃ አሟልተሽ ማቅረብ ትችያለሽ የሚል ውሳኔ ተሰጥቷል።
ይህ አካሄድ በመርህ ደረጃ አግባብነት ያለው ነው ባይሰኝም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ አንቀጽ 91/4/ በተደነገገው አግባብ ለጉዲዩ ፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ ይበጃል ብል ካመነ ፍ/ቤቱ ማሻሻያ እንዱደረግ ማዘዝ ይችላል። የሥር ፍ/ቤት ከዚህ ይልቅ አመልካች ማስረጃ አሟልታ ክስ እንድታቀርብ በማድረጉ ይህ ውሳኔው ሥነ-ሥርአታዊ አይደለም የሚለው ወገን በይግባኝ አስካላሻረ ጊዜ ድረስ ውሳኔውን መሰረት በማድረግ አዱስ ክስ መቅረቡ ተገቢ አይደለም ልባል አይገባም።
ከዚህ ላላ የቀድሞ መዝገብ ላይ በፍሬ ጉዲይ ረገድ የተሰጠ ውሳኔ ስለመኖሩ አልተጠቀሰም። እንግዱህ የጉዲዩ አጠቃላይ ይዘት ይህንን የመሰለ መሆኑን ከተገነዘብን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ መሰረት የሚሸፈን ነውን? የሚለውን እንመለከታለን።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ መሰረት በማድረግ ድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይቻለው በቀድሚው ክርክር የተያዘው ጭብጥና የፍሬ ነገር ክርክር ተመሳሳይ መሆኑ የተከራካሪ ወገኖች አንድነት ብቻ ሳይሆን በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠ መሆኑም መረጋገጥ አለበት። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ቀደም ሲል በተጠሪ ላይ ያቀረበችው ክስ በተመሳሳይ ፍሬ ነገር ላይ ቢሆንም በቀድሞ መዝገብ በፍሬ ነገር ረገድ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲልተሰጠበት ይልቁንም አመልካች ክሷን በማስረጃ አሟልታ እንድታቀርብ መብት የተጠበቀላት መሆኑን ከፍ ሲል ተመልክተናል። ይህ ከሆነ ደግሞ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ላይ በቀዲሚው መዝገብ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቷል ለማለት አይቻልም። ይህ መለያ እስካልተሟላ ድረስ ደግሞ አመልካች ያቀረበችው ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ ሥር የሚሸፈን አይሆንም። ስለዚህም የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ በድጋሚ የቀረበ ነው (res judicata) በሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 5/1/ ይሸፈናል ሲል የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል።
ስለሆነም ውሳኔው ሉታረም ይገባል ብለናል። በልላ በኩል አከራካሪው መሬት የማን ነው የሚለውን በተመለከተም ማስረጃ በማጣራት የወረዲው እና ከፍተኛው ፍ/ቤት የተሻለ ማስረጃ የአመልካች መሆኑን ስለማረጋገጣቸው ከመዝገቡ ተረድተናል።
ስለሆነም በፍሬ ነገር ረገድ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ማስረጃ መሰረት ያደረገ መሆኑን ስለተገነዘብን ባለበት ሉፀና የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።
በዚሁ መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 88224 በ17/05/2002 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የሸርካ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 06008 በ4/7/2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19080 በ24/11/2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.