No summary available.
ሰኔ 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት አድርጏ የተደረገ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካቾች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡ከየካቲት 27 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ከአንደኛ ተጠሪ ጋር የመሰረቱት የስራ ውል ከሕግ ውጪ ከመጋቢት 22 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ መቋረጡን ገልጸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ሁለተኛ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪን መቅጠሩን ሳይክድ ራሱ ያላሰናበታቸው መሆኑን ገልጾ ልጠየቅ አይገባም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን የተከራከረ ሲሆን አንደኛ አመልካች ደግሞ ተጠሪ የስራ ውልና ቅጥር የፈፀሙት ከሁለተኛ አመልካች ጋር በመሆኑ ክሱ እንደማይመለከተው በመጀመሪያ መቃወሚያነት ጠቅሶ የተከራከረ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃም ስንብቱ የተከናወነው ተጠሪ ከስራ ገበታቸው በመቅረታቸው፣የስራ ሰዓት ባለማክበራቸው እንዱሁም ያለፈቃድ በልላ ቦታ እያስተማሩ እንደሚገኙ ገልጾ ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት ተክራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ከሰማ በኋላ በአመልካቾች በኩል የቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ውድቅ አድርጏ በፍሬ ነገርም ማስረጃ ያለማቅረባቸውን ጠቅሶ አመልካቾችን ለክሱ ኃላፉ አድርጏ ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈለ ሲል ወስኗል። ከዚህም በኋላ አመልካቾች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች ነገረ ፈጅ ጥቅምት 09 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት ከስራ ከአምስት ተከትታይ የስራ ቀናት በላይ በመቅረታቸው ነው በሚል ገልፀንና ማስረጃም ቆጥረን እያለ ማስረጃዎቻችን ሳይታዩና ሳይሰሙ ማስረጃዎችን አላቀረቡም በሚል ምክንያት ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የአመልካቾች የመከላከያ ማስረጃዎች ሳይሰሙ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ ተጠሪ ቀርበው ጥር 26 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የአመልካቾችን የሰበር ቅሬታ ነጥቦች ተገቢ አለመሆን ያሳያለ ያሎቸውን ነጥቦችን በመዘርዘር የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። የአመልካቾች ነገረፈጅም የካቲት 17 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
ወኪል ይሁን አየነው - ቀረቡ የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ተጠሪ የስራ ውላቸው ያላግባብ የተቋረጠ መሆኑን ገልፀው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ላቀረቡት ክስ አመልካቾች ስንብቱ ሕጋዊ ነው የሚለበትን ምክንያት ጠቅሰው ለዚህም የሰነድና የሰው ምስክሮች ያሎቸው መሆኑን በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ማቅረባቸውን የስር ፍርድ ቤትን ዋና መዝገብ በማስቀረብ ተመልክተናል። የስር ፍርድ ቤት የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው አንደኛ አመልካች ተጠሪ ከስራ የቀሩ ስለመሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም በሚል ነው።
በመሰረቱ አንድ ሰው ክስ የመከላከል ሕጋዊ መብት ያለው ሲሆን ፍርድ ቤት ይህንኑ መብቱን ሉያልፍ የሚገባው ተከራካሪ ወገን የቆጠረው ማስረጃ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑን እርግጠኛ ሲሆን ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 223፣234፣137፣249 እና 256 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያሳያል። በመሆኑም ፍርድ ላሰጥ የሚገባው የማስረጃ አቀራረብ ሥርአት ምዘና ሥነ-ሥርአቱ በሚያስቀምጠው መንገድ ተከናውኖ መሆኑን እነዚህ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። ተከራካሪ ወገን ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ማስረጃ ቆጥሮ እያለ ማስረጃ ሳይሰማ ፍርድ መስጠት የመከራከር መብቱን የሚያጣብብ ነው፣ ውሳኔውም ሕጋዊ ሥርአቱን ተከትል ተሰጥቷል ልባል የሚችል አይደለም።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካቾች ከተጠሪ ጋር የተመሰረተው የስራ ውል የተቋረጠበትን ምክንያት በመከላከያ መልስ ማመልከቻው ላይ ከመግለፃቸውም በተጨማሪ ይህንኑ ፍሬ ነገር ለማስረዲት የሰነድና የሰው ማስረጃዎቻቸውን በመከላከያ ማስረጃው መግለጫ ዝርዝር ላይ ጠቅሰው እያለ እና የሰነድ ማስረጃዎችን አያይዘው ከማቅረባቸውም በላይ የቆጠሯቸውን የሰው ምስክሮችን ለማቅረብ ያልቻለ መሆኑ ሳይረጋገጥ የስር ፍርድ ቤት ማስረጃ በደፈናው ማስረጃ አላቀረቡም በሚል ምክንያት ማለፈ ስለማስረጃ አቀራረብ ሥርአት የተመለከቱትን የፍትሐብሕር ሥነሥርአት ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ ነው። አንድ አሰሪ የስራ ውልን ለማቋረጥ ምክንያት ነው ብል በስንብቱ ደብዲቤ ላይ የገለፀውን ምክንያት ለማስረዲት የቆጠረውና አግባብነት ያለው ማስረጃ ሉሰማለትና ሉመዘንለት ይገባል። የኸው ሥርአት ሳይከናወን የሚሰጥ ፍርድ የተሟላ አካሄድ ተከትል የተሰጠ ነው ልባል የማይችልና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው። በመሆኑም አመልካቾች በሥነ-ሥርአቱ መሰረት ማስረጃዎቻቸውን ዘርዝረው አቅርበው እያለ የቆጠሯቸው የሰነድና የሰው ምስክሮች ሳይታዩና ሳይሰሙ ማስረጃ አላቀረቡም በሚል የተሰጠው ውሳኔ የአመልካቾችን የመከላከል ሕጋዊ መብት ያጣበበ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 06 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ነሐሴ 19 ቀን 2001 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን ሰምቶ በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ በዚህ ችልት ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል።
No topics extracted.