No summary available.
ሰኔ 14 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ሙልሳ በየቻ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ደበላ በየቻ - በላለበት መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ ተከሳሽ በላለበት የተሰማ ክስ ላይ ማስረጃ ሳይሰማ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው።
ሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ ነበር። የተጠሪ ክስ የነበረው አመልካች በንብረት ላይ ጉዲት አድርሷል በሚል ግምት ብር ሦስት ሺህ አንድ መቶ አሥራ አምስት ብር እንዱከፍል እንዱወሰን የሚል ነበር።
አመልካች (ሥር ተከሳሽ) ቀርቦ ባለመከራከሩ የሥር ፍ/ቤት በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ እንዱከፍል ወስኗል።
የወረዲው ፍ/ቤት ውሳኔ በከፍተኛው ፍ/ቤት እና በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፀንቷል።
አመልካች በውሳኔው የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል በማለት ነሐሴ 28 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው አቤቱታ የቀረበው ክስ በከሳሽ ማስረጃ ሳይረጋገጥ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም ይታረምልኝ የሚል ነው።
ይህ ሰበር ችልትም ይህንኑ ለመመርመር ተጠሪ እንዱቀርብ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም መጥሪያ ተቀብል ባለመቅረቡ በላለበት ጉዲዩ ተሰምቷል። እኛም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል። ከመዝገቡ መረዲት የተቻለው አመልካች በተጠሪ ንብረት ላይ ጉዲት አድርሷል በሚል መነሻ ተጠሪ ይገባኛል ያለውን የካሣ መጠን ገምቶ ክስ ያቀረበ ስለመሆኑ ነው። አመልካች (ሥር ተከሳሽ) ቀርቦ ባለመከራከሩ ጉዲዩ በላለበት የተወሰነ ነው። የሥር ፍ/ቤት የካሣውን መጠን እንደከሳሽ ጥያቄ የወሰነው ተከሳሽ ቀርቦ አልካደም በሚል ነው። ይህ አካሄድ ከሥነ-ሥርዓት አንፃር በአግባቡ ስለመሆኑ እንደሚከተለው መርምረናል።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 235(2) የሚደነግገው በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ ይቆጠራል የሚል ሲሆን ይህ ተፈጻሚነቱ ተከሳሽ ቀርቦ ክርክሩን ባሰማ ጊዜ ነው። ከዚህም ላላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 83 እንደተመለከተው በመርህ ደረጃ በተከሳሽ በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ የሚቆጠር ቢሆንም የካሣ ጥያቄ ላይ ግን ይህ ግምት ተፈጻሚ ላሆን እንደማይችል ነው። ስለሆነም በተያዘው ጉዲይ አመልካች ቀርቦ ያልተከራከረ ቢሆንም የዲኝነት ጥያቄው የካሣ ጥያቄ እንደመሆኑ መጠን ቀርቦ እንኳ ቢከራከር ፍ/ቤቱ በማስረጃ ጉዲዩን ማጣራት እንዲለበት አመላካች ነው። ከዚህ አንፃር የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ እንደ ክሱ ያስረዲልኛል ያለውን ማስረጃ ሰምቶ መወሰን ሲገባው ተከሳሽ ቀርቦ አልተከራከረም ወይም አልካደም በሚል ብቻ ውሳኔ መስጠቱ ከተጠየቀው የዲኝነት ጥያቄ እና ከሥነ ሥርዓት ሕጉ የሙግት አመራር መርህ አኳያ ጉድለት ያለበት ሆኖ አግኝተናል።
ስለሆነም ይህ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል ብለናል።
ው ሣ ኔ
የሜታ ሮቢ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ የሰበር ውሳኔ እና የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የሰጠው ትዕዛዝ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሜታ ሮቢ ወረዲ ፍ/ቤት የሥር ከሳሽ (ተጠሪን) ማስረጃ ሰምቶ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ እንዱሰጥበት ብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መዝገቡን መልሰናል። ይፃፍ።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.