No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ፈትለወርቅ መንገሻ ፊንታ - ጠበቃ ገ/እግዚአብሓር ኪዲነ ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ በላይነሽ ወ/ኪዲን - ወኪል ተሾመ አባይ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቤት እና የቦታ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ከሣሽ የነበረችው የአሁንዋ ተጠሪ ናት። ተጠሪ ክስ የመሰረተችው እማሆይ ፀሃይነሽ በተባለች ሰው እና በአሁንዋ አመልካች ላይ ሆኖ አመልካች ባለመቅረብዋ ክርክሩ በላለችበት ተሰምቶ ውሳኔ ተሰጥቶአል። አከራካሪ ከነበሩት ጭብጦች አንደ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል በሚል በእማሆይ ፀሃይነሽ የተነሳው መቃወሚያ ስለሆነ የወረዲው ፍ/ቤት መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ በጉዲዩ ሥረ-ነገር ውሳኔ ሰጥቶአል። እማሆይ ፀሃይነሽ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ አቅርባ ተቀባይነት እንዲላገኘ እና እስከ ሰበር ድረስም አቤቱታ አቅርባ ውድቅ እንደሆነባት በመዝገቡ ተመልክቶአል። ይህ ሁለ ከሆነ በኋላ መዝገቡ(የወረዲው ፍ/ቤት) የተንቀሳቀሰው አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 78 መሰረት አቤቱታ በማቅረብዋ ነው።
የወረዲው ፍ/ቤትም የአመልካችን ተቀብል ግራ ቀኝ ወገኖችን አከራክሮአል። በመቀጠልም የአመልካችና የይርጋ መቃወሚያ በመቀበል የቀድሞው ውሳኔውን ለውጦአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ በየደረጃው ለበላይ ፍ/ቤቶች ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ በማቅረብዋ ጉዲዩ እንደገና ታይቶአል። ጉዲዩን በመጨረሻ የሰማው የትግራይ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ጉዲዩ ቀደም ሲል ታይቶ በውሳኔ እልባት ያገኘ በመሆኑ አመልካች ያቀረበችው የይርጋ መቃወሚያ በድጋሚ የሚታይበት አግባብ የለም በማለት በወረዲው ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ ሽሮአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ጥቅምት 17 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ በሥር የሰበር ችልት በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የምትልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታዋን አቅርባለች። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው አመልካች ያቀረበችው የይርጋ መቃወሚያ ቀደም ሲል አንደኛ ተከሣሽ የነበረችው የአመልካች እናት አንስታው ውድቅ ሆኖአል በማለት ተቀባይነት ማጣቱ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካች እና ተጠሪ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ከላይ እንዲመለከትነው አመልካች በዚህ ጉዲይ ተከራካሪ የሆነችው ተጠሪ ክስ ስላቀረበችበት ነው። በእርግጥ ክሱ በተሰማበት ጊዜ ልትቀርብ ባለመቻልዋ ጉዲዩ በላለችበት ተሰምቶ ውሳኔ ተሰጥቶ እንደነበረ ግልጽ ነው። በልላ በኩል ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 የተመለከተውን ድንጋጌ በመጠቀም ወደክርክሩ እንድትገባ ተፈቅድላታል። በዚህ የሥነሥርአት ሕግ ድንጋጌ እንደተመለከተው አቤቱታ አቅራቢው ወገን ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ የቀድሞው ውሳኔ ይነሳለታል። በዚህም ክርክሩ እንደና ይሰማል። ይህ ማለት ደግሞ ክርክሩ እንደገና ከተሰማ በኋላ የቀድሞው ውሳኔ ሉለወጥ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል ማለትም ነው።
በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው አመልካች ለቀረበባት ክስ በሰጠችው መልስ ያዋጣኛል ያለችውን ክርክር አቅርባለች የተከሰሰችው በስምዋ እንደመሆኑ መጠን መከራከር የምትችለው(መከራከር ያለባት) እሷን (በግልዋ) የሚመለከት የመከራከሪያ ነጥብ በማንሳት ነው። የክርክር አቀራረብ ስልትዋም ሆነ የማስረጃ አቀራረብዋም እንደዚሁ በግልዋ ባቀረበችው ክርክር የሚወሰን ነው። ይህም ማለት ከስዋ ጋር ተከሳ የነበረችው ሰው ያነሳችው ክርክር የስዋም የመከራከሪያ ነጥብ እንደሆነ ተደርጏ የሚወሰድበት አግባብ የለም። የወረዲው ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበችውን የይርጋ መቃወሚያ መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መታየት ያለበት ከዚህ አንፃር ነው። የሥር አንደኛ ተከሣሽ የነበረችው እማሆይ ፀሃይነሽ ያቀረበችውን የይርጋ መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ከተሰጠው ውሳኔ ጋር የሚያያዝበት አግባብ የለም።
ተደጋግሞ እንደተገለጸው አመልካች የክርክሩ ተካፊይ የሆነችው በግልዋ በቀረበባት ክስ ምክንያት በመሆኑ ክሱን መከላከል የምትችለው የግልዋ የመከራከሪያ ነጥብ እና የመከላከያ ማስረጃ በማቅረብ ነው። ከዚህ የተነሳም ጉዲዩ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ ከተመለከተው ድንጋጌ አንፃር የሚታይ አይደለም። የሥር ሰበር ችልት የአመልካች የይርጋ መቃወሚያ እማሆይ ፀሃይነሽ ባቀረበችው የይርጋ መቃወሚያ በተሰጠው ውሳኔ እልባት አግኝቶአል በማለት ያስቀመጠው ትችም ሆነ የደረሰበት መደምደሚያ ከሕጉ አተረጓጏም አንፃር ሲታይ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
የይርጋው መቃወሚያ በዚህ አግባብ ታይቶ ከመወሰኑ በፉት ወደ ጉዲዩ ሥረ-ነገር ገብቶ መወሰኑም ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
መስከረም 29 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
የሰበር ችልቱ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል አከራካሪ ሆኖ የቀረበው የይርጋ መቃወሚያ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖችን እንደገና ካከራከረ በኋላ ተገቢውን ይወስን ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ ብለናል።