No summary available.
ሰኔ 17 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ደጀኔ በላቸው - ከጠበቃ ዲኜ አዱሴ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ነስሩ አወል- አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶታል።
ጉዲዩ የውል ይፈፀምልኝ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፤ተጠሪ በብር 149,000.00(አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ብር) የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪና ሸጠውላቸው በእለቱ ብር 145,000.00(አንድ መቶ አርባ አምስት ሺህ ብር) ተቀብለው ሉብሬውንና መኪናውን ያስረከቡ መሆኑን፣ቀሪውን ገንዘብ ስም ሃብቱን ሲያዛውሩላቸው አመልካች ለተጠሪ ለመክፈል እንደተስማሙ፣ተጠሪም መኪናውን ከእዲና እገዲ ነፃ በማድረግ ስመ ሃብቱን ለማዛወር በውለ ላይ በግልጽ ግዳታ መግባታቸውን፣ሆኖም ተጠሪ በገቡት ግዳታ መሰረት መኪናውን ከእዲና እገዲ ነፃ ለማድረግ እና ስመ ሃብቱንም ለማዛወር ፈቃደኛ ሉሆኑ አለመቻላቸውን ገልጸው በውለ መሰረት መኪናውን ከእዲና እገዲ ነፃ አድርገው ስመ ሃብቱን እንዱያዛውሩላቸው እንዱሁም የገደብ ገንዘብ ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር) እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪም ለክሱ በሰጡት መልስ በመካከላቸው የመኪና ሽያጭ ውል መደረጉንና በክሱ ላይ የተገለጸውን ገንዘብ በመቀበል መኪናውንና ሉብሬውን ለአመልካች ማስረከባቸውን እንዱሁም በውለ ላይ መኪናውን ከእዲና እገዲ ነፃ ለማድረግ እና ስመ ሐብቱንም ለማዛወር ግዳታ መግባታቸውን ሳይክደ መኪናውን ከእዲና እገዲ ነፃ ሉያደርጉት ያልቻለት በወንጀል ጉዲይ ዋስ የሆኑላቸው ግለሰብ በመሰወራቸው መሆኑን፣ስመ ሃብቱንም የማዛወር ስልጣን የላላ አካል እንጂ የተጠሪ አለመሆኑን፣እንዱሁም ውለ ፈራሽ ነው ያልተባለ በመሆኑም የገደብ መቀጫ የሚጠየቁበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ውለ መኖሩን ከአረጋገጠ በኋላ ተጠሪን አመልካች ሉጠየቁ የሚገባው ውለ እንዱፈርስ እንጂ እዲና እገዲውን ነፃ እንዱያደርጉ አይደለም፣ስመ ሃብቱን የማዛወር ስልጣንም የተጠሪ ሳይሆን በሕጉ አግባብ ስልጣን የተሰጠው አካል ነው የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ ክሱ የክስ ምክንያት የለውም ሲል ውድቅ አድርጏታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸው ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሚያዝያ 16 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪ ጥሪ ተደርጏላቸው ቀርበው የጽሐፍ መልስ እንዱሰጡ በችልት ተነግሯቸው የፁሐፍ መልሳቸውን ባለማቅረባቸው የጹሐፍ መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም ለስመ ንብረት ዝውውር ሲባል በተሸጠው መኪና ላይ አስቀድሞ የተሰጠውን የእግድ ትእዛዝ ሻጩ እገዲ እንደሚያስነሳ በውለ ግዳታ መግባቱ ከተረጋገጠ፣ይኸው ግዳታ እንዱፈጸም ክስ ማቅረብ በጉዲዩ ላይ የክስ ምክንያት የለውም ለማለት ይቻላል? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሲሆን ላልች ነጥቦች በዚሁ ነጥብ ስር የሚሸፈኑ ሆነው አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአመልካችና የተጠሪ ግንኙነት የመነጨው ከመኪና ሽያጭ ውል መሆኑን፣ውለ ስለመኖሩና በይዘቱ ላይ ግራ ቀኙ ያልተካካደ መሆኑን፣ለክርክሩ መነሻ የሆነው መኪና በገዢው ስም ሉዛወር ያልቻለው ተጠሪው ለላላ ግለሰብ በወንጀል ጉዲይ በብር 10,000.00(አስር ሺህ) በፍርድ ቤት ዋስ ስለሆኑ እግድ በመሰጠቱ መሆኑን፣ እግደም ለመንገድ ትራንስፕርት ባለስልጣን ተላልፍ ከመኪናው ማህደር ጋር ስለመያያዙ ተጠሪ ያልካደት ፍሬ ነገር መሆኑ ነው።
በመሰረቱ አንድ በፍርድ ቤት የቀረበ ጉዲይ የክስ ምክንያት አለው ብል ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዲኝነት ለማግኘት ሕግ ይፈቅድለታል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ፍርድ ቤቱ አዎንታዊ ምላሽ ለመስጠት የሚችል የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ በዚህ ረገድ የተፃፈት የማብራሪያ ፁሐፍች ያሳያለ።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም በግራ ቀኙ መካከል የመኪና ሽያጭ ውል መኖሩና ተጠሪ መኪናውን ከእዲና እገዲ ነፃ በማድረግ ስመ ሐብቱን ለአመልካች ለማዛወር ግዳታ የገቡ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች በክሳቸው የገለፁትም ይህንኑ ፍሬ ነገርና ተጠሪ በገቡት ግዳታ መሰረት ውለን ያልፈፀሙ መሆኑን ነው። ይህ ፍሬ ነገር ደግሞ በተጠሪ በኩል ማስተባበያ ያልቀረበበት የታመነ ጉዲይ ነው። አመልካች ተጠሪ መኪናው ላይ የተላለፈውን የእግድ ትእዛዝ እንዱያስነሱ ጥያቄ ማቅረባቸው ደግሞ በሕግ የተፈቀደ ነው። ማንም ሰው በገባው ዋስትና መሰረት በንብረቱ ላይ እግድ ተሰጥቶ ከሆነ ንብረቱን ለላላ ሰው በሽያጭ ሲያስተላልፍ ገዢው በንብረቱ ላይ የሚያገኘውን የባለቤትነት መብት ሙለ በሙለ ተግባራዊ ለማድረግ እንዱችል እግድን የማስነሳት ግዳታ አለበት። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካች ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም በማለት የደረሱበት ድምዲሜ ስለክስ ምክንያት አጠቃላይ መንፈስ እና ይዘት በሕጉ ላይ የተመለተውን መመዘኛን ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል።
ክሱ የክስ ምክንያት አለው ከተባለ አመልካች ያላቸውን መፍትሓ ይህ ችልት በዚሁ የክርክር ደረጃ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።
ተጠሪ በመኪናው ላይ ያሰጡትን እግድ የማያስነሱበት ሕጋዊ ምክንያት ያላቸው ስለመሆኑ አላስረደም። ተጠሪ መኪናቸውን ከሸጡ ደግሞ የመኪናውን ባለሃብትነት ለገዠው ለማዛወር ሕጋዊ ግዳታ የአለባቸው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2273/2/ ድንጋጌ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። የመኪናው ስመ ሃብት ሉዛወር የሚችለው ተጠሪ በመኪናው ላይ ያሰጡትን እግድ ሲያስነሱ ነው። ተጠሪ ስመ ሃብቱን ለማዛወር ስልጣን የላቸውም ቢባል እንኳ በአዋጅ ቁጥር 465/97 አንቀጽ 3/2/ ድንጋጌ መሰረት ሥልጣን ያለው አካል ተግባርን ሉወጣ የሚችለው በፍርድ ቤት የተሰጠው እግድ መነሳቱ ሲረጋገጥ ነው። ስለሆነም በሕጉ አግባብ ስልጣን የተሰጠው አካል ስመ ሃብቱን ለማዛወር እንዱችል ተጠሪ የፍርድ ቤቱ የእግድ ትእዛዝ እንዱነሳ የበኩላቸውን ግዳታ ሉወጡ የማይገደደበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ ስለውል አፈፃፀም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1740 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የተመለከቱትን ደንቦችንም ሆነ የግራ ቀኙን የውል ይዘት ባግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚሁም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች ክስ የክስ ምክንያት አለው ብለናል።
ተጠሪ በገቡት ውል መሰረት በአካራካሪው መኪና ላይ የተላለፈውን እግድ በማስነሳት የሚመለከተው አካል ስመ ሃብቱን ለአመልካች እንዱያዛውር እንዱያደርጉ ብለናል።
በዚህ ችልት ውሳኔ እንዱያስፈጽምም የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍለት ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.