No summary available.
ሰኔ 16 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- 1ኛ ከድር ሐጂ ሁሴን 2ኛ ለሲ ኮላጅ አ.ማ ተጠሪ፡- 1ኛ አቶ አሚን ዐስማን 2ኛ ወ/ሮ ኑሪያ ጀማል መዝገቡን በአዲሪ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በተከራካሪ ወገኖች መካከል የነበረውን የፍርድ ቤት መሰረት በመተው እርቅ ተደርጎ ለፍርድ ቀርቦ ከተመዘገበ በኋላ ያለውን ሕጋዊ ውጤት የሚመለከት ነው።
የክርክሩ አመጣጥም በሚከተለው መልኩ የተመዘገበው ነው።
የአሁኖቹ ተጠሪዎች እና አመልካቾች ተጠሪዎች በለሲ ኮላጅ አ.ማ ውስጥ ያላቸውን የባለአክሲዮንነት መብት በተመለከተ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላይ የይግባኝ ክርክር የነበራቸው ሲሆን ክርክሩ በዚህ ደረጃ ላይ እያለ ግራ ቀኙ በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት ከፍርድ ቤት ውጪ ለመጨረስ ተስማምተዋል። በዚህም መሰረት የካቲት 30 ቀን 2000 ዓ.ም በተፈረመ የእርቅ ስምምነት አድርገው በስምምነቱ መሰረትም በፍርድ ቤት እንዱፀድቅ በመገለጹ ስምምነቱ ጉዲዩን በይግባኝ ይመለከተው ለነበረው ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ቤቱም የእርቅ ስምምነቱን ግራ ቀኙ ባለበት ተመልክቶና መርምሮ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አይደለም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 277(1)(2) መሰረት መዝግቦት በእርቁ መሰረት እንዱፈፀም ዘንድ ለስር የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልኮለታል። በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፀደቀውን ስምምነት እንዱያስፈጽም የታዘዘው ፍርድ ቤትም ከተመለከተ በኋላ ተጠሪዎች በአመልካቾች ላይ የተከፈተውን የወንጀል መዝገብ ያላዘጉ ስለሆነ በእርቁ መሰረት ሉፈጸም የሚችል አይደለም የሚል ምክንያት በመያዝ የእርቅ ይፈፀምልኝ ጥያቄን ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጓል። ከዚህም በኋላ ተጠሪዎች የሰበር አቤቱታቸውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታቸውን አቅርበው ችልቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ተጠሪዎች የወንጀል መዝገብ ለማዘጋት እርቅ አድርገዋል ለማለት እንደማይቻል ያሳያለ ያላቸውን ምክንያቶችን ዘርዝሮና እርቅ በተቻለ መጠን እንዱፈፀም መደረግ እንዲለበት በመተንተን የስር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር በእርቁ መሰረት እንዱያስፈፅም ጉዲዩን መልሶ ልኮለታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች የካቲት 10 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት የሰበር አቤቱታ በክልለ የሰበር ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝሮ አቅርቧል። ይዘቱም ባጭሩ እርቅ ውል እንደመሆኑ መጠን ስለውል አመሰራረትና አተረጓጎም የተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ተደርጎ መታየት እያለበት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ይህንኑ ተጠሪዎች የወንጀል መዝገብ ካለማዘጋታቸው ጋር ሳያገናዝብ የሚፈፀም ሕጋዊ እርቅ አለ በማለት መወሰኑ አልቀረቡም ጠበቃ ደረጀ ኢታቻ ቀረቡ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነ እርቅ ስምምነት ከአንደኛው ተጠሪ ግዳታ አንጻር ሉፈጸም የማይችል ለህግ ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ነው ከተባለ አመልካቾች እንደስምምነቱ ለመፈፀም ተነጻጻሪ ግዳታ ይኖርባቸዋል ወይስ አይኖርባቸውም?
የሚለውን ነጥብ ለማየት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር እንዱቀርብ ተብል በመታዘዙ ተጠሪዎች እንዱቀርቡ ተደርጎአል።
የተጠሪ ጠበቃ ግንቦት 26 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት ማመልከቻ የክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው ውሳኔው ሉፀና ይገባል ሲለ መልሳቸውን ሰጥተዋል። አመልካቾችም ሰኔ 09 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
እንግዱህ የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ ግልባጭ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ጉዲይ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለ ለማለት ይቻላል ወይስ አይቻልም? የሚለው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ግራ ቀኙ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ይታይ የነበረውን ክርክር በመተው ጉዲዩን በእርቅ ጨርሰው የእርቅ ስምምነቱ ሰነድ ለፍርድ ቤቱ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ሰነደን ተቀብል ከመረመረ በኋላ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አይደለም በሚል ምክንያት መመዝገቡንና በእርቁ መሰረት እንዱፈጸምም ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን የላከለት መሆኑን በእርቁ ሰነድ በአንቀፅ 4 ስር ደግሞ የተጠሪዎች ግዳታ በፍርድ ቤቶች ያስከፈቷቸውንና የከፈቷቸውን የፍትሐብሕር እና የላልች ክርክሮችን ማዘጋት ተብል መቀመጡን አመልካቾች ተጠሪዎች በዚህ የእርቅ ሰነደ አንቀፅ መሰረት ያለባቸው ግዳታ የፍትሐብሕርና የወንጀል መዛግብትን ማዘጋት መሆኑን ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን፣ የወንጀል መዝገብ በተጠሪዎች አቤቱታ ባይሆንም ጉዲዩን ሲመለከቱ በነበሩት ፍርድ ቤቶች የሚያስከስስ አይደለም ተብል መዘጋቱ በአሁኑ የክርክር ደረጃ መረጋገጡን ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ በፍርድ ቤት ጉዲዩ እየታየ ባለበት ሁኔታ ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸውን በእርቅ ጨርሰው ሲመጡና ፍርድ ቤቱ ይህንኑ እንዱመዘገብላቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ ፍርድ ቤት የእርቅ ስምምነቱን ሕጋዊነትና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆን መርምሮ ተገቢውን ትዕዛዝ ላሰጥ የሚችልበት ጉዲይ መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 277 ስር በግልጽ ተመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ተቀብል ከመዘገበው እርቁ እንደፍርድ ቤት ውሳኔ ላታይ የሚችል ስለመሆኑንም ከተጠቀሰው ድንጋጌ መንፈስ እና ይዘት ያስገነዝባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካቾች የእርቅ ስምምነቱን ማድረጋቸውንና በፍርድ ቤት መፅደቁን እንዱሁም ይኸው በፍርድ ቤት የፀደቀው የእርቅ ስምምነት ቅሬታ ያሳደረበት ወገን ኖሮ ቅሬታውን ለበላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ እርቁን አለማስለወጡን ሳይክደ አጥብቀው የሚከራከሩት የእርቅ ስምምነቱ በፍርድ ቤት ያለትን የፍትሐብሕር ክርክሮችን ማዘጋት ብቻ ሳይሆን የወንጀል መዛግብትን ጭምር ለማዘጋት በመሆኑ እና የወንጀል መዛግብትን ደግሞ ተጠሪዎች ያላዘጉ በመሆኑ እርቁ የአመልካቾች ፍላጎትና ሐሳብ መሰረት ባደረገ መልኩ ተፈጽሟል ለማለት አይቻልም በሚል ነው። ይሁን እንጂ የእርቁ ሰነድ ስለወንጀል መዛግብት መዘጋት እንደቅድመ ሁኔታ የማያስቀምጥ መሆኑን የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያረጋገጠው ከመሆኑም በላይ ተደርጓል የሚል ድምዲሜ ቢኖር እንኳ ወንጀልቹ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚዘጉ ባለመሆኑ ተቀባይነት የላለው ነው። ከሁለም በላይ ደግሞ የወንጀል መዛግብት የተባለት ባሁኑ ጊዜ ጉዲዩ አያስከስስም በሚል ምክንያት በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት የተዘጉ መሆኑ ተረጋግጧል። በመሆኑም የወንጀል መዛግብት አለመዘጋት ለእርቁ ሕጋዊ አለመሆን ምክንያት ላሆን ይገባል በሚል የቀረበው የአመልካቾች ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። በአጠቃላይ የእርቅ ስምምነቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 277 አግባብ የፀደቀ በመሆኑ የማይፈፀምበት ሕጋዊ ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም፤ ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 24 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት መጋቢት 08 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።