No summary available.
የሰ/መ/ቁ2 41526 ግንቦት 2 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ትራንስ አፍሪካ ትራንስፕርት አ.ማ - ጠበቃ አቶ መከተ ዲኘው-ቀረቡ ተጠሪ፡- ሙለ ኤላክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግል ማሕበር - ጠበቃ እሸቴ ደምሴ - ቀረበ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የትራንስፕርት አገልግልት ክፍያ ገንዘብን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአመልካች የክስ ይዘት ባጭሩ ተጠሪና አመልካች ለስምንት ዓመታት ያህል የስራ ግንኙነት የነበራቸው መሆኑን አመልካች ለተጠሪ ጅቡቲ ወደብ ላይ በቃል በተደረገው ውል መነሻነት ለሰጠው የክሉሪንግና የትራንዚት አገልግልት ተገቢውን አገልግልት ከሰጠ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት በተጻፈለት የአገልግልት ሑሳብ ክፍያ መጠየቂያ ደብዲቤዎችና ኢንቮይሶች ብር 332,834.27(ሦስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከሃያ ሰባት ሳንቲም) የጠየቀ ቢሆንም ተጠሪ ፈቃደኛ አለመሆኑን አመልካች ለተጠሪ ከጅቡቲ አዱስ አበባ ድረስ የጭነት የማጓጓዝ የትራንስፕርት አገልግልት ሰጥቶ አመልካች ንብረቶችን ከተረከበ በኋላ ብር 39,600.00(ሰላሣ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ) እንዱከፍለው አመልካች ሲጠይቀው ተጠሪ ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልፆ ለክሱ መሰረት የሆነው ገንዘብ ብር 332,834.27(ሦስት መቶ ሰላሣ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከሃያ ሰባት ሣንቲም) ከተጠየቀበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድና ከተለያዩ ወጪና ኪሳራዎች ጋረ እንዱከፈለው ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስም አመልካች የክሉሪንግና የትራንዚት አገልግልት ሰጥቻለሁ በማለት እንዱከፈለው ያቀረበው ገንዘብ ሕጋዊና ታዓማኒ ሰነድ ወይም ደረሰኝ ያልቀረበበት መሆኑን አመልካች ለማስረጃነት የዘረዘራቸው ኢንቮይስ (የክፍያ ሰነድ) ሁለ ራሱ ባዘጋጀው ወረቀቶችና ጽሐፍች የተዘጋጀ መሆኑን የጭነት ማጓጓዣ ብር 39,600.00(ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ብር) በቼክ ቁጥር BB430772 በደረሰኝ ለአመልካች የከፈለው መሆኑን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ በግራ ቀኙ መካከል ውል መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ተጠሪ ለአመልካች ብር 38,808.00 (ሰላሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር) የከፈለው በመሆኑ ይኸው የገንዘብ መጠን ተቀንሶ ቀሪውን ብር 293,234.27(ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከሃያ ሰባት ሳንቲም) ግን ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ተከፍል አለቀ ድረስ ዘጠኝ ከመቶ ወለድና ከተለያዩ ወጪና ኪሳራዎች ጋር እንዱከፍል ሲል ወስኗል። አመልካች የስር ፍ/ቤት ብር 38,808.00(ሰላሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር) ለተጠሪ እንዱከፈል ሲል በሰጠው የውሳኔ ክፍል ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይኸው ፍርድ ቤት አመልካች አከራካሪው ብር ተከፍልበታል የተባለውን ሰነድ ሐሰተኛ መሆኑን የሚያስተባብል ማስረጃ አላቀረበም የሚል ምክንያት ይዞ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ አፅንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የውሳኔ ክፍል ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሕዲር 16 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ብር 38,808.00 (ሰላሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር) ተጠሪ ለአመልካች ስለመክፈለ ተረጋግጧል የተባለበት ሰነድ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው እና ሉታመን የማይችል በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሳኔ ሉታረም ይገባል ሲለ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም አከራካሪው የሆነው ገንዘብ ብር 38,808.00(ሰላሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት ብር) አመልካች አስቀድሞ ተከፍልታል የሚለው የስር ፍርድ ቤት መደምደሚያ አግባብነት ባለው ማስረጃ የተደገፈ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ የተጠሪ ጠበቃ ነሐሴ 21 ቀን 2001 ዓ.ም በተጻፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ የአመልካች ክርክር በማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን ገልፀው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች ጠበቃ መስከረም 21 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ አራት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ነጥብ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈፀመም? የሚለው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰርት አከራካሪውን ገንዘብ ለመጠየቅ መሰረት ያደረገው የተጠሪን ደረቅ ጭነት አጓጉዞ ያልተከፈለው የትራንስፕርት ገንዘብ ክፍያ መኖሩን ሲሆን ተጠሪን ገንዘቡን ለአመልካች መክፈለን ገልጾ ይህንኑ ክስ ለማስተባበል ደግሞ የገንዘብ መክፈያ ሰነድና ቼክ ለማስረጃነት ማቅረቡን ሲሆን አመልካች የተጠሪ ማስረጃዎች ሐሰተኛ ናቸው በማለት ተከራክሮም ይህንኑ ክርክር የሚደግፍለት ማስረጃ ያለማቅረቡን የበታች ፍርድ ቤቶች በውሳኔአቸው ላይ በግልፅ ያሰፈሩት ነጥብ መሆኑን ነው። አመልካች በሰበር ደረጃ የሚከራከረውም ክፍያው መፈፀሙን ያሳያል የተባለው ሰነድ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነበር በማለት ሲሆን ይህንኑ ለማስረዲት በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ማስረጃ ያቀረበው ግልጽ ማስረጃ ስለመኖሩ ግን ያረጋገጠው ሁኔታ አለመኖሩን ተመልክተናል። ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ የአመልካች የሰበር ክርክር በማስረጃው ምዘና ላይ የሚያተኩር መሆኑን ይህ ችልት ተገንዝቧል። ተጠሪ ክፍያውን ፈፅሟል? ወይስ አልፈጸመም? እና ክፍያው የተፈፀመው አመልካች ለተጠሪ ለሰጠው አገልግልትና ዲኝነት ለጠየቀበት ጉዲይ ወይስ ለላላ? የሚለው ጉዲይ የፍሬ ነገር ክርክር እንጂ የሕግ ክርክር የሚሆንበት አግባብ የለም። በዚህ ረገድ ደግሞ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችን በመመርመር ተገቢ ነው ያለትን የየራሳቸውን ምዘና አድርገዋል ተገቢ ነው ያለትንም ክብደት ሰጥተዋል።
የማስረጃ ምዘና ጉዲይ ደግሞ በዚህ ችልት የሚታረምበት የሕግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ ከኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ የማስረጃ ምዘናን የሚመለከት እንጂ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት ጥያቄ መመዘኛን የሚያሟላ ሆኖ ስላላገኘነው የአመልካችን ክርክርን አልተቀበልነውም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 04 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 2001 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.