No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ተጠሪ፡-
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አመልካች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ነው። አመልካች በክሱ በወረዲ 23 ቀበላ 12 ክልል ውስጥ የሚገኘውን ቁጥር 1801/01 የሆነ ቤት ሰኔ 09 ቀን 1989 ዓ.ም በተፈረመ ውል በወር ብር 900(ዘጠኝ መቶ) ለአንደኛ ተጠሪ አከራይቶ የነበረ ቢሆንም አንደኛ ተጠሪ የውል ግዳታውን በመጣስ ሁለተኛ ተጠሪ እንዱኖሩበት በማድረጉ የኪራይ ውለ ተቋርጦ ቤቱን እንዱያስረክበውና ከመስከረም 23 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ድረስ ያለውን ውዝፍ ኪራይ እንዱከፍል እንዱሁም ሁለተኛ ተጠሪ የውል ግንኙነት ሳይኖራቸው በቤቱ እየተገለገለ በመሆኑ ያለአግባብ የበለፀጉበትን ኪራዩ ከቅጣቱ ጋር እንዱከፍለና ቤቱን እንዱያስረክቡ ጠይቋል።
አንደኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ከታዘዘ በኋላ አቤቱታ አቅርቦ መልስ እንዱያቀርብ የተፈቀደለት ቢሆንም በተደጋጋሚ ቀጠሮ መልስ ባለማቅረቡ መልስ የማቅረብ መብቱ ታልፎል። ሁለተኛ ተጠሪ ግን ቀርበው ከአመልካች ጋር ውል ስላላቸው ክሱ እንደማይመለከታቸው፣ ሁለት አመት ያለፈው ኪራይ ገንዘብ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2024(መ) መሰረት እንደተከፈለ እንደሚቆጠር፣ ውለ የተደረገው ለአንድ አመት ስለሆነና ስላልታደሰ ክስ ማቅረብ እንደማይችል፣ ቤቱን የያዙት በአደራ ጠባቂነት መሆኑን እንዱሁም ስምንት አመት ሙለ ያልታደሰ ውል መሰረት አድርጎ የቀረበው ክስ ተቀባይነት እንደላለው ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ሁለት አመት ያለፈው ክፍያ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2024(መ) መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል፣ ሁለት አመት ያላለፈውን ኪራይ ገንዘብ ከነቅጣቱ አንደኛ ተጠሪ ይክፈል፣ በዚሁ ጊዜ ሁለተኛ ተጠሪ በቤቱ መገልገላቸውን ስላልካደ ገንዘቡን ይክፈለ፣ ቤቱን ለአመልካች ያስረክቡ፣ ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን እስኪያስረክቡ በወር ብር 900.00(ዘጠኝ መቶ) ይክፈለ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። በቅሬታውም አንደኛ ተጠሪ ውዝፍ እዲ እንዲለበት ያመነ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2025(ሀ) መሰረት ውዝፍ እዲውን ሉከፍል ይገባል እንዱሁም ከ2ኛ ተጠሪ ጋራ የኪራይ ውል የላለውና ክሱ የቀረበው አለአግባብ በመበልፀጋቸው በመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2024(መ) በመጥቀስ የክፍያው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው።
ችልቱም ይህን የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪዎች እንዱቀርቡ መጥሪያ ቢላክም ሁለተኛ ተጠሪ ብቻ በመቅረባቸው አንደኛ ተጠሪ በላለበት ጉዲዩ ታይቷል። ችልቱም የቃል ክርክሩን ሰምቷል። መዝገቡንም እንደሚከተለው መርምረናል።
የአመልካች የቅሬታ ነጥቦች ሁለት ናቸው። አንደኛው አንደኛ ተጠሪ ውዝፍ የኪራይ እዲ ያለበት ለመሆኑ ስላመነ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2024(መ) ስር የተመለከተው የህሉና ግምት ተጠቃሚ ላሆን አይገባም የሚል ነው። በፍ/ብ/ህ/ቁ 2024(መ) ስር ለቤቶች ኪራይና ለእርሻ ሃብት ለሆነ የሚከፈል እዲ እዲው እንዱከፈል መጠየቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት አመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ እንደሚቆጠር ተመልክቷል። የስር ፍ/ቤትም አመልካች ዲኝነት ከጠየቀባቸው ውዝፍ የቤት ኪራይ ገንዘብ ውስጥ ሳይጠየቁ ሁለት አመት ያለፈባቸው እንደተከፈለ የህግ ግምት የሚወሰድባቸው ናቸው በማለት ውድቅ አድርጓቸዋል። በልላ በኩል ግን አመልካች አንደኛ ተጠሪ ያልከፈለው ውዝፍ የቤት ኪራይ እዲ እንዲለበት አምኖ ለአመልካች የፃፈው ደብዲቤ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2025(ሀ) መሰረት ግምቱን ቀሪ ያደርገዋል በማለት ተከራክሯል።
በፍ/ብ/ህ/ቁ 2025(ሀ) ባለእዲው በጽሐፍ እዲውን ያመነ እንደሆነ እዲው እንደተከፈለ መቆጠሩ ቀሪ እንደሚሆን ያመለክታል። በመሆኑም አንደኛ ተጠሪ እዲውን ማመን አለማመኑ መረጋገጡ ሁለት አመት ያለፈው እዲ ሉከፈል ይገባል አይገባም? የሚለውን ጭብጥ ለመፍታት አስፈላጊ ነው። አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ ባቀረበበት ወቅት አንደኛ ተጠሪ መልስ ስላላቀረበ እዲውን በማመንም ሆነ በመካድ የሰጠው መልስ የለም። በልላ በኩል ግን አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ባቀረበበት ወቅት በስር ፍ/ቤት ክስ ከቀረበ በኋላ አንደኛ ተጠሪ ያልከፈለው ውዝፍ የቤት ኪራይ ገንዘብ እንዲለበት አምኖ ገንዘቡን እንደሚከፍል ደብዲቤ ስለፃፈ ይኸው ማስረጃ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱቀርብለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 327(3) እና 345(ለ) መሰረት ጥያቄውን ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ይግባኙን መልስ ሰጪን መጥራት ሳያስፈልግ ስለዘጋው ማስረጃዎቹንም አልተመለከተም።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
በመሰረቱ ከሳሽ ክሱን ሲያቀርብ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በሙለ አጠቃል ማቅረብ፣ ሉያቀርባቸው የማይችላቸውን ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 145 መሰረት በፍ/ቤቱ በኩል እንዱቀርቡለት መጠየቅ ይገባዋል። በመሆኑም ከሳሹ ሉያቀርባቸው ሲችል ሆነ ብል ወይም በቸልተኛነት ያላቀረባቸውን ማስረጃዎች በክርክር ሂደት ሁለ እያንጠባጠበ ሉያቀርብ አይችልም። የስነ-ስርዓት ህጉ አላማም ይህ አይደለም። ተጨማሪ ማስረጃዎች ሉቀርቡ የሚችለት ክሱ በተጀመረበት ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 256 እና በይግባኝ ደረጃ ደግሞ በቁጥር 345 ስር በተመለከቱት የተወሰኑ ሁኔታዎች ስለመሆኑ ከድንጋጌዎቹ ይዘት መረዲት ይቻላል። በይግባኝ ደረጃ ማስረጃ የሚቀርብባቸው ምክንያቶችን ስንመለከት የስር ፍ/ቤት ማስረጃውን ሉቀበል ሲገባ ያለበቂ ምክንያት ያልተቀበለው ከሆነ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት ወይም ተገቢ መስል ሲታየው ማናቸውም ምክንያት ተጨማሪ ማስረጃ እንዱቀርብ ሲያዝ ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 327 መሰረት ተጨማሪ ማስረጃ ወይም ምስክር እንዱቀርብ ማመልከቻ ከቀረበ ወይም በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አስተያየት ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው ከሆነ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች በይግባኝ ፍ/ቤት እንዱቀርብለት የጠየቃቸው ማስረጃዎች በስር ፍ/ቤት እንዱቀርቡ ተጠይቀው ፍ/ቤቱ አልቀበልም ያላቸው አይደለም። ነገር ግን አመልካች አንደኛ ተጠሪ ከክስ በኋላ እዲውን በማመን የፃፈው፣ ሁለተኛ ተጠሪም እንዱሁ እዲውን ለመክፈል የፃፈት ደብዲቤዎች ሲሆኑ እነዚህ ማስረጃዎች ክስ ሲቀርብ ያልነበሩ ናቸው። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው አንደኛ ተጠሪ እዲውን ያመነ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2025(ሀ) መሰረት የህግ ግምቱ ተጠቃሚ ላሆን አይችልም በማለት በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አንደኛ ተጠሪ የህግ ግምቱ ተጠቃሚ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ በትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ተጠሪው እዲውን በማመን ፅፎል የተባለውን ደብዲቤ ሉያስቀርበው ይገባ ነበር። በተለይ ደብዲቤው ክስ ከቀረበ በኋላ ዘግይቶ የተፃፈ በመሆኑና አመልካች ክስ ሲያቀርብ በማስረጃነት ሉያቀርበው የሚችል ባለመሆኑና ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚረዲ ማስረጃ እንደመሆኑ ፍ/ቤቱ ተጨማሪ ማስረጃ እንዱቀርብ የቀረበውን ጥያቄ ሳይመረምር ይግባኙን መሰረዙ የተጠቀሰውን የስነ-ስርዓት ህግ በአግባቡ ያላገናዘበ መሆኑን ተረድተናል።
በልላ በኩልም ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን የያዙት ከአመልካች ጋር የውል ግንኙነት ሳይኖራቸው ከውል ውጪ ነው።
እሳቸውን በተመለከተም ተጠሪው በቤቱ ከመቼ ጀምሮ ይኖሩ እንደነበር እንዱሁም ውዝፍ ኪራዩን ለመክፈል ለአመልካች የፃፈት ደብዲቤ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱቀርብ ተጠይቋል። ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ከውል ውጪ የያዙ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2024(መ) ስር የተመለከተው የህግ ግምት ተጠቃሚ የሚሆኑበት የህግ አግባብ የለም። ተጠሪው ክስ የቀረበባቸው ቤቱን ያለ ውል ይዘው ያለአግባብ በልፅገዋል በሚል ነው። ነገር ግን የስር ፍ/ቤት ሁለት አመት ያለፈው የኪራይ ገንዘብ እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት ውድቅ ስላደረገው ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ከመቼ ጀምሮ እንደያዙት ያረጋገጠው ነገር የለም። ተጠሪው ቤቱን ከመቼ ጀምሮ የያዙት እንደነበር የሚያስረዲው ማስረጃ በስር ፍ/ቤት ክርክር ወቅት ሉገኝ ያልቻለ መሆኑና ኪራዩን ለመክፈል የፃፈት ደብዲቤም ቢሆን ክስ ከቀረበ በኋላ ዘግይቶ የተፃፈ በመሆኑ በስር ፍ/ቤት ላቀርብ አለመቻለን ተገንዝበናል። በመሆኑም ተጠሪው ያለአግባብ በልፅገዋል ልባል የሚችለው ከመቼ ጀምሮ ነው የሚለውንም ለመወሰን ተጨማሪ ማስረጃ መቅረቡ ጠቃሚ ይሆናል።
በአጠቃላይ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት በስር ፍ/ቤት ሉቀርቡ ያልቻለትንና በተጨማሪ ማስረጃ እንዱቀርቡ የተጠየቁትን ማስረጃዎች መርምሮ ሉወስን ሲገባ ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት መዝጋቱ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን የሥነ-ሥርዓት ህጉን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈፀሙን ተገንዝበናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱቀርቡ የጠየቃቸው ማስረጃዎች በመቀበል ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።