No summary available.
ሚያዝያ 5 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ይርጋአለም ከበደ - ጠ/ደሣለኝ ቀነኒ ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ፅጌ ሚካኤል - ጠ/ወጋየሁ ታደሰ (የ1ኛ,2ኛ,3ኛ,5ኛ ተጠሪዎች ጠበቃ) 4ኛ ተጠሪ አልቀረቡም
ተጠሪዎች የውርስ ንብረት እንዱጣራላቸው አመልክተው ውርስ ከተጣራ በኋላ ክፍፍለን አስመልክቶ በስምምነት ስለጨረሱ ይኸው እንዱፀድቅላቸው ለፍ/ቤት አመልክተው ፍ/ቤቱ ስምምነቱን ከመዘገበ በኋላ አመልካች ስምምነቱ ወንጀል መሰል ተግባር የተፈፀመበት በመሆኑ ዲኝነት እንደገና እንዱታይላቸው አመልክተው ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ በማድረጉ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6ን መሰረት በማድረግ ባቀረቡት አቤቱታ አራተኛ ተጠሪ የህፃን ማራናታ ወኪል ሳይሆኑ ወኪል ነኝ በማለት ስምምነቱን መፈረማቸው፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች የአቶ ባቻ ቱለ ወራሾች ሳይሆኑ ወራሾች ናቸው ተብል ስምምነቱ መደረጉ፣ የሚጣራው ንብረት የአቶ ባልቻ ቱለ ብቸኛ ሃብት ሆኖ እያለና ንብረቱ የወ/ሮ አስካለ የጋራ ንብረት ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ሳይኖር እንዱካፈለ የተደረገው ስምምነት በወንጀል መሰል ተግባር የተገኘ በመሆኑ ስምምነቱ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቀዋል። ተጠሪዎችም ቀርበው ክርክራቸውን አቅርበዋል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤትም የአመልካች ልጅ ማራናታ ተስፊዬ የመዝገቡ አካል ሆና በጠበቃም ተወክላ ጉዲዩን ስትከታተል የቆየች በመሆኑ አመልካች ወንጀል ነክ ተግባር መፈፀሙን ሰኔ 9 ቀን 2000 ዓ.ም ነው ያወኩት በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም፣ እንዱሁም አራተኛ ተጠሪ የልጃቸውን መብት በሚነካ መልኩ ስምምነት ስለማድረጋቸው በማስረጃ አላረጋገጡም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሲሆን አመልካች በቅሬታቸው ለአራተኛ ተጠሪ ውክልና የሰጡት ጠበቃ ወክለው እንዱከራከሩ እንጂ የእርቅ ስምምነት እንዱያደርጉ አለመሆኑ፣ ውክልናውንም የሰጡት እሳቸው እንጂ ልጃቸው ባለመሆናቸው ተጠሪው ልጅቷን ወክለው ስምምነት ማድረጋቸው፣ እንዱሁም አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች አቶ ባልቻ ቱለ ወራሽ ሳይሆኑ ወራሽ ነን ብለው ስምምነት ማድረጋቸው ሲታይ በሃሰት የተደረገ ስምምነት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ብይንና ውሳኔ እንዱሻርላቸው አመልክተዋል። ችልቱም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አግባብነት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 አኳያ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
አከራካሪው ጉዲይ የአመልካች ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 ስር የሚወድቅ ነው አይደለም የሚለው ስለሆነ ይህን ድንጋጌ ማየቱ ለጉዲዩ አወሳሰን ይጠቅማል። ይህ ድንጋጌ ይግባኝ ላቀርብበት የሚችል የመጨረሻ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ ውሳኔው ወይም ትዕዛዙ የተሰጠው በሃሰት ተዘጋጅቶ በቀረበ ሰነድን ሃሰተኛ የምስክርነት ቃልን፣ ወይም መደለያን ወይም ወንጀል ጠቅሶ የሆነ ተግባርን መሰረት አድርጎ መሆኑን አቤት ባዩ ሲረዲው ጉዲዩ በይግባኝ ከመታየቱ በፉት ውሳኔውን የሰጠው ፍ/ቤት ራሱ ዲኝነቱን በድጋሚ እንዱያይ ጥያቄ ለማቅረብ መብት የሚሰጠው ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካች የሚከራከሩት ፍ/ቤት የመዘገበው ስምምነት ወንጀል መሳይ ተግባር የተፈፀመበት ነው በማለት ነው።
እዚህ መደምደሚያ ላይ ያደረሳቸውም አንደኛው ምክንያት አራተኛ ተጠሪ ስምምነቱን የፈረሙት ከውክልና ስልጣናቸው በላይ ነው በማለት ነው። አራተኛ ተጠሪ ጠበቃ ወክለው እንዱከራከሩ ብቻ ከተሰጣቸው የውክልና ሥልጣን አልፈው ስምምነት አድርገው ከሆነ አመልካች ስምምነቱን ከመቃወም ወይም በይግባኝ ፍ/ቤቱ ስምምነቱን በመመዝገብ የሰጠው ትዕዛዝ ከሚያስለውጡ በቀር ድርጊቱ ወንጀል ተብል ዲግመኛ ዲኝነት ሉጠየቅበት የሚችል ጉዲይ አይደለም። ከክርክሩ ሂደትም የአመልካች ልጅ የክርክሩ አካል የነበረችና አመልካች ክርክሩን የሚያውቁ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም በወቅቱ ስምምነቱ እንዲይፀድቅ ወይም በይግባኝ እንዱሻር ጥያቄ ሉያቀርቡ ይችለ ነበር። በልላ በኩል ለአራተኛ ተጠሪ ውክልና የሰጡት እሳቸው እንጂ ልጃቸው ባለመሆኗ ተጠሪው የልጃቸው ወኪል በመምሰል ያደረጉ ስምምነት በተንኮል የተደረገ ነው የሚል ክርክር የቀረበ ቢሆንም አመልካች ለአራተኛ ተጠሪ ውክልና መስጠታቸው ያልተካደና አመልካችዋ የልጃቸው ሞግዚት እንደመሆናቸው ልጃቸውን ወክለው ህጋዊ ተግባራትን የሚፈፅሙ እሳቸው በመሆናቸው ከሳቸው በተሰጣቸው ውክልና መሰረት አራተኛ ተጠሪ ስምምነቱን ማድረጋቸው ወንጀል ነክ ተግባር ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም። በመጨረሻም አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪ የሟች አቶ ባልቻ ቱለ ወራሽ ነን በማለት ያልተከራከሩ መሆኑን አመልካች በሰበር ችልት በተደረገው ክርክር ወቅት ያመኑ በመሆኑ በውል ስምምነቱ ላይ ወራሽ ነን ብለው በመመዝገብ ፍ/ቤቱን አሳስተዋል በሚል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነው። በአጠቃላይ የስምምነት ሰነደ ወንጀል ጠቀስ ተግባር የተፈፀመበት ስለመሆኑ አመልካች ያላስረደ ስለሆነ ጥያቄአቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 ስር አይወድቅም ሲል የስር ፍ/ቤት የደረሰበት መደምደሚያ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል ለማለት አያስችልም።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።