No summary available.
ሚያዚያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አብደራሂም አህመድ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍትሐብሕር ችልት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 481 ስር የተመለከተውን መሰረት በማድረግ ያስተላለፈውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አመልካቾች ጥር 22 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ስላመለከቱ የቀረበ ነው።
የአመልካቾች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ችልት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት በሰበር አቤቱታቸው ላይ ዘርዝረዋል። ይህ ችልትም የአመልካቾችን አቤቱታ ለአቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ ግልባጭ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሯል።
በዚህም መሰረት አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለት በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተያዘው የጉዱፈቻ ውል ይፅደቅልኝ ጥያቄ ሂደት ውስጥ ሐሰተኛ አቤቱታና አስተያየት በማቅረብና ፍርድ ቤቱን ለማሳሳት ሞክረዋል በሚል ምክንያት ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሕጻን ሂክማን ኢብራሂምን ተቀብል የሚያሳድጋት ብርሃን ሕይወት የሕጻናትና ቤተሰብ መርጃ ድርጅት አቶ አውግቸው እርገጤ ወኪል ለሆኑላቸው ጀርመናዊያን ባልና ሚስት በጉዱፈቻ ለመስጠት ያደረገውን ውል ፍርድ ቤት ለማስፀደቅ ጥቅምት 07 ቀን 2001 ዓ.ም ማመልከቻ ለፍርድ ቤቱ ቀርቦለት የሴቶች ጉዲይ ሚኒስቴር አስተያየት እንዱሰጥበት ችልቱ ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ.ም ትዕዛዝ መስጠቱን፣ ለሴቶች ጉዲይ ሚኒስቴር የተላከው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሕፃናት ቡድን መሪ ለሆኑት ላሁኑ ሁለተኛ አመልካች ቀርቦላቸው የጉዱፈቻ ማንነት ሲመረመር ሕጻናት ማሳደጊያው ተግባሩን እንዲይቀጥል በፍትሕ ሚኒስቴር እንደታገደ በመታወቁ ሕፃኗ በቅድሚያ ሕጋዊ ለሆነው የህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ባሁኑ ሦስተኛ አመልካች በሚተዲደረው የእናት ዓለም ሕፃናት ማሳደጊያ እንደተላለፈች፣ ከዚህም በኋላ ያሁኑ አንደኛ አመልካች ከአዱሱ የሕፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ጋር የጉዱፈቻ ውል ፈፅመው ሁለተኛ አመልካች አንደኛ አመልካች ሕፃኗን አዱስ ከተረከበው ድርጅት ጋር ያደረጉት የጉዱፈቻ ውል እንዱፀድቅ ታህሳስ 07 ቀን 2001 ዓ/ም አስተያየት መስጠታቸውን ሲሆን ፍርድ ቤቱ አመልካቾችን ጥፊተኛ ብል ቅጣት ሉያስተላልፍ የቻለው በተዘጋና እንደገና አስተያየት እንዱሰጥ ባልተጠየቀበት መዝገብ አስተያየት የተሰጠው ፍርድ ቤቱን ለማሳሳት ነው የሚለውን ምክንያት በመያዝ መሆኑን፣ አንደኛ አመልካች ብርሃነ ሕይወት የሕጻናት እና ቤተሰብ መርጃ ድርጅት መፍረሱን አያውቁም ነበር ተብል ታህሳስ 13 ቀን 2001 ዓ.ም በኋላ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በተሰጠበት መዝገብ ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 481 ይዘት ሲታይ በዲኝነት ስራ ላይ ወንጀል ሲፈፀም ፍርድ ቤቱ ጥፊቱ በተደረገበት ጊዜ በያዘው የፍትሐብሕር መዝገብ ወዱያውኑ ቀጥታ ቅጣት ሉያስተላልፍ የሚችል ስለመሆኑ ተመልክቷል። በዚህ መንገድ ቅጣት ሉያስከትል የሚችለው ድርጊት በአዱሱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 452(1) ስር የተመለከተው በተከራካሪ ወገን የሚሰጠው ሐሰተኛ ቃል ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ተጠያቂነት የሚመጣው ማንኛውም ተከራካሪ ወገን በፍርድ ቤት ወይም የዲኝነት ነክ ሥልጣን ባለው አካል ዘንድ ቀርቦ እውነት እናዱናገር ታዞ በፍርድ ቤቱ ወይም የዲኝነት ነክ ሥልጣን ባለው አካል በሚወሰን ጭብጥ ላይ አግባብነት ያላቸውን ፍሬ ነገሮችን በሚመለከት እያወቀ ሐሰተኛ ቃል የሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
የድንጋጌው አይነተኛ ዓላማ የዲኝነትን ክብርን፣ የዲኝነት አስተዲደርን የሚነካ፣ ሕብረተሰቡ በፍርድ ቤቱ ላይ እምነት እንዲይኖረው የሚያደርግ ድርጊት መከላከልና እውነትን መሰረት ያደረገ ፍርድ እንዱሰጥ ማስቻል ነው ተብል ይታሰባል። ይህንን ለማሳካት ደግሞ ፍርድ ቤት ድንጋጌውን ሲያስፈጽም በድንጋጌው ስር የተመለከቱ የወንጀለ ማቋቋሚያ ነጥቦች መሟላታቸውንና በተገቢው ማስረጃ መደገፊቸውን ሉያረጋግጥ ይገባል። እንዱሁም ጉዲዩ የወንጀል ባሕርይ ያለው እንደመሆኑ መጠን በወንጀል ስነ-ሕግ ተቀባይነት ያላቸው መርሆዎችንና በሕገ መንግስቱ ውስጥ የተካተቱትን መሰረታዊ መብቶችን ግንዛቤ ውስጥ ሉያስገባ ይገባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አንደኛ ተጠሪ በጉዲዩ ባንድ መዝገብ ሁለት ጊዜ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን በመጀመሪያው ብይን ይኸው አመልካች በጉዲዩ ላይ የፈፀሙት ድርጊት እንደላለ ተገልፆ በነጻ ከተሰናበቱ በኋላ እንደገና እንዱቀጡ መደረጉ ተገቢውን ስርዓት በተከተለ ሁኔታ አይደለም። አንድ ሰው ባንድ የወንጀል ድርጊት ነጻ ተብል ከተወሰነ በኋላ በዚያው ጉዲይ እንደገና ላላ ማስረጃ እንዱቀርብ ተደርጎ የሚቀጣበት አግባብ የለምና። ሁለተኛ አመልካችን በተመለከተም አመልካች ሰጡ የተባለት አስተያየት በሕጉ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ለሕፃን ጥቅም ማስጠበቅ መሆኑ የሚገለፅ እስከ ሆነ እና ፍርድ ቤቱ አስተያየቱ ተቀባይነት ያለው መሆኑ ያለመሆኑን በመመርመር በጉዱፈቻ ውል መፅደቅ አለመጽደቅ ላይ ተገቢውን ውሳኔ የሚሰጥበት ከሚሆን በስተቀር ሐሰተኛ ነው ተብል የወንጀል ኃላፉነትን የሚያስከትል አይሆንም። ከሁለም በላይ ሁለተኛ ተጠሪ አስተያየት ሰጡ የተባለበት ድርጅት የፈረሰ መሆኑን እያወቁ አስተያየት መሰጠታቸው በእርግጠኝነት የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ አይደለም። እንዱህ ከሆነ ሁለተኛ አመልካች ሐሰተኛ ምስክርነት ቃል ሰጥተዋል ሉባለ የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም። ሦስተኛ አመልካችን በተመለከተም የተላለፈውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ስንመለከተው ይኸው አመልካች ተፈፀመ ለተባለው ድርጊት የነበራቸው የድርጊት ተሳትፍ ምን እንደሆነና ሐሰተኛ የምስክርነት ቃል የሚያሳይ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ የገለፀው ነገር የለም።
አንድ ሰው ደግሞ በወንጀለ ድርጊት የነበረው ተሳትፍ ባግባቡ ሳይረጋገጥ የሚቀጣበት ሕግ የለም። በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤቶች በአመልካቾች ያስተላለፈት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ሕጋዊ ስርዓቱን መሰረት ያላደረገ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 481 እና በአዱሱ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 452(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የማያሟላ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 20 እና 22 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 21 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናውን የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ሙለ በሙለ በመሻር አመልካቾችን በነፃ አሰናብተናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.